Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.8K subscribers
2.01K photos
76 videos
4 files
537 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የማኔጅመንት አባላት ሐበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካን ጎበኙ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር እመቤት መለሰ ከባንኩ የማኔጅመንት አባላት ጋር በመሆን ዛሬ ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ/ም ፋብሪካው ያለበትን ሁኔታ ተዛዋውረው የተመለከቱ ሲሆን ከጥሬ እቃ ጀምሮ ምርቱ እስኪወጣ ያለውን ሂደት ጎብኝተዋል።

ዶ/ር እመቤት መለሰ በጉብኝቱ ወቅት ፋብሪካው ያለውን ጠንካራ ጎን የገለጹ ሲሆን በቀጣይ ሊስተካከሉ ስለሚገባቸው ጉዳዮች አንሰተው ፋብሪካው የሚያስፈልገውን ማስፋፊያ መመልከታቸውን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የማኔጅመንት አባላትና የሀበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ ከፍተኛ አመራሮች ባደረጉት ውይይት ከደንበኞች ምን እንደሚጠበቅና ባንኩ ሊያደርግ ስለሚችላቸው ጉዳዮች ተወያይተዋል።

ሐበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ እንደ ሀገር ያለውን ከፍተኛ የሆነ የሲሚንቶ ፍላጎት ከመሸፈን ባሻገር ከፋብሪካው ሰራተኞች ጀምሮ እስከ አከፋፋዮች ድረስ ከፍተኛ የሆነ የስራ ዕድል በመፍጠር ለሀገር ኢኮኖሚ ድጋፍ እንደሚያደርግም በውይይቱ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሐበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ በቀን 3,000 ቶን ማምረት የሚያስችል አቅም እንዲኖረው የፋይናንስ ድጋፍ በአውሮፓውያኑ 2013 ያደረገለት ሲሆን በተለያዩ ጊዜያት ተጨማሪ ብድር እና የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል።
12
ኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዕለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን

Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Monday, November 3, 2025

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://x.com/dbeethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/com.../development-bank-of-ethiopia
ዩቱብ:- https://www.youtube.com/@developmentbankofethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#ExchangeRate #የኢትዮጵያልማትባንክ
#developmentbankofethiopia
5
ኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዕለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን

Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Tuesday, November 4, 2025

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://x.com/dbeethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/com.../development-bank-of-ethiopia
ዩቱብ:- https://www.youtube.com/@developmentbankofethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#ExchangeRate #የኢትዮጵያልማትባንክ
#developmentbankofethiopia
7
የ‎አምራች ድርጅቶች ችግር እንዲፈታ ተገቢውን ክትትል እንደሚያደርግ ቋሚ ኮሚቴው ገለፀ፡፡
‎የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ዲስትሪክት ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የብድር ድጋፍ ያገኙ አምራቾችን ተመልክቷል።
‌‎ኮሚቴው በዲላ ከተማ የቤት እና የቢሮ እቃዎች ማምረቻ፣ የዱቄት የፋብሪካ እንዲሁም በይርጋዓለም ከተማ ላይ የሳሙና እና ዲተርጀንት ፋብሪካ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
‎ከባንኩ ደንበኞች ጋር በነበረው ቆይታም ከአነስተኛ ሥራዎች ተነስተው በባንኩ እገዛ የተለያዩ ማሽኖችን በማስገባት ሥራቸውን ማስፋፋት እንደቻሉ እና አሁን ላይ ጥራቱን የጠበቀ ተኪ ምርት በማምረት ላይ እንደሚገኙ ደንበኞች ለቋሚ ኮሚቴው ገልጸዋል።
‌‎በተጨማሪም ብዙ ወጣቶችን በማሰልጠን የሥራ ዕድል መፍጠር መቻላቸውን ገለጸው በዚህም ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በቅርበት በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እድሉን እንደፈጠረላቸው ገልፀዋል።
‌‌‎የቋሚ ኮሚቴው አባል እና የምልከታ ቡድኑ መሪ የተከበሩ ዘውዱ ታደሰ (ፒ.ኤች.ዲ.)፣ ባዩት ነገር መደሰታቸውን አመላክተው፣ አምራቾቹ ያቀረቧቸውን ችግሮች በየደረጃው ካሉ የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ችግሮች እንዲፈቱ ተገቢውን ክትትል እንደሚያደርጉ በዚሁ ወቅት ገልፀዋል።
5