Don Bosco School G12(2015)
455 subscribers
223 photos
3 videos
184 files
12 links
Download Telegram
2015/2023 Grade 12 Entrance Exam High Scorer
#ማስታወቂያ

በ 2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ)  ለመማር ያለፋችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርትቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፡

 በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ ምርጫችሁ ውስጥ በማካተት መመደብ የምትችሉ መሆኑ እናሳውቃለን።
የትምህርት ሚኒስቴር

ውድ ተማሪዎቻችን ከትምህርት ምንስቴር  በተገለፀው መሰረት ነገ ዓርብ ጥቅምት 09/2016ዓ.ም ከ3 : 00 ሰዓት ጀምሮ ትምህርት ቤት በመምጣት የዩኒቨርስቲ ምርጫችሁን እንድታስተካክሉ እናሳስባለን ።
ት/ቤቱ
students (5).xlsx
53.5 KB
University choice(Edited)
ከተፈጥሮ ሳይንስ ወደ ማህበራዊ ሳይንስ መቀየር የምትፈልጉ ተማሪዎች ነገ ት/ቤት መጥታችሁ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
#የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆኗል

በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለምትከታተሉ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

Website: https://result.ethernet.edu.et/
Telegram bot: @moestudentbot
የሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።

የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ500) የተቆረጠ መሆኑ ተመላክቷል።

ከላይ በተራ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የRemedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች 255 ከ700 ያመጡ

የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች 234 ከ700 ያመጡ

የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች 218 ከ600 ያመጡ

የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች 200 ከ600 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 224 ከ700 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 210 ከ700 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 192 ከ600 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 180 ከ600 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 210 ከ700 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 210 ከ700 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 180 ከ600 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 180 ከ600 ያመጡ

ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 150 ከ500 ያመጡ

ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 150 ከ500 ያመጡ መሆን አለባቸው ተብሏል።

መረጃውን ትምህርት ሚኒስቴርን ዋቢ በማድረግ ያሰራጨው ኤፍ ቢ ሲ ነው።

@tikvahethiopia
ማስታወቂያ
(ህዳር 5/2016 ዓ.ም) የRemedial ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ምርጫን በተመለከተ
በ 2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ህዳር 12/2016 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፡ -
ከታች የተዘረዘሩ ዩኒቨርሲቲዎች የ Remedial ፕሮግራም የማያስተናግዱ መሆኑን እንገልጻለን።

1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

2. አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

3. አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

4. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

5. አርሲ ዩኒቨርሲቲ

6. ኮተቤ የትምህርት ዪኒቨርሲቲ

ትምህርት ሚኒስቴር
የፕሮግራም ለውጥ
በ2015ዓ.ም የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና(Entrance Exam) ከ600 በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በከንቲባ ጽ/ቤት እውቅና ለመስጠት ለሰኞ ህዳር 10/2016ዓ.ም ፕሮግራም ተይዞ የነበረና በዚህም መሰረት ጥሪ ለተማሪዎች እና ለወላጅ ተላልፎ እንደነበረ ይታወሳል። ሆኖም ዛሬ ማምሻ ላይ ከክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ተደውሎ የእውቅና የፕሮግራም ቀን ለማክሰኞ ህዳር 11/2016ዓ.ም 2 : 00 ሰዓት ላይ የተለወጠ መሆኑን የተገለፀለን ስለሆነ ውድ ተማሪዎቻችን እና ወላጆች ይህንን አውቃችሁ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ከንቲባ ጽ/ቤት እንድትገኙ እናሳስባለን።

የሰዓት ማስተካከያ ተደርጓል
ጠዋት 2 : 00 ሰዓት የነበረው ከሰዓት 7 : 00 ሰዓት ላይ ሆኗል።
ት/ቤቱ