ውድ ተማሪዎቻችን እና የተከበራችሁ ወላጆች ነገ ሰኞ(ህዳር 27/03/2014ዓ.ም) የተማሪዎች የት/ቤት ቆይታ እስከ 6:30 መሆኑን እያሳወቅን ነገ የሳምንቱን የዘመቻ ኘሮግራም እና የተማሪዎች የት/ቤት ቆይታ በተመለከተ በዝርዝር በደብዳቤ የምናሳውቃችሁ መሆኑን እንገልፃለን።
ውድ ተማሪዎቻችን እንደምን አመሻችሁ!የግሪን ክበብ አባላት የሆናችሁ ተማሪዎች ነገ 1:00 ሰዓት ላይ ጋርመንት አደባባይ ላይ ችግኝ የመንከባከብና ውሃ የማጠጣት ዘመቻ ስለሚካሄድ በተጠቀሰው ሰዓት ት/ቤት እንድትገኙልን እያሳወቅን የተሰጠን ኮታ ትንሽ ስለሆነ ቀድሞ ለመጣ ቅድሚያ የምንሰጥ መሆኑን እንገልፃለን።