Dark truth
520 subscribers
177 photos
12 videos
እንኳን ለሞት ቀርቶ ዝምታ ለዋጠው ለኑሮም አልሰጋን አፈር ለሚያስጌጠው!!
Download Telegram
የፈላስፋው ፍሬድሪክ ኒቼን ደብዳቤዎች ያነበበ ሰው በብቸኝነት ስሜት ብዙ እንደተሰቃየ ይገነዘባል። በ1887 ዓ.ም ለጓደኛው ኮቭሪክ እንዲህ ሲል ደብዳቤ ጻፈለት፦

“ልጅ እያለሁ ብቻዬን ነበርኩ ዛሬ ላይ አርባ አራት አመት ሞልቶኝም ብቻዬን ነኝ። የሰው ልጅ ሁሌም እንደናፈቀኝና እንደፈለኩት ነው። እኔ ግን ይሄ ፍለጋ ሁሌም እራሴን ያስገኝልኛል ምንም እንኳን እራሴን ባልናፍቅም። ከእንግዲህ ወዲህ ማንም ወደ እኔ የሚመጣ የለም፤ እኔማ ወደ ሁሉም ሄጄ ነበር ቢሆንም አንድም አላገኘሁም!።”
@darktrut
💔18😢51👍1
ድንገት በቻት ነበር የተዋወቅነው ብቻዬን በነበርኩበት ሰአት ...እሷ ሁሉን ሆነችልኝ በአካል አብሬ ከማሳልፈው ጊዜ በላይ እሷ ጋር የምናወራው ይበልጥ ነበር በቃ አብራኝ ነበር የምትውለው ከምላችሁ በላይ የምትገርም ሴት ናት የሚያውቀኝ የልብ ጓደኛዬ እንኳ የሷን ያህል የሚጨነቅልኝ አይመስለኝም ነበር ከፋኝ ስላት ትዘፍንልኛለች.. ድምጿ ያምራል... አይተውት የማያውቁትን አካል መልኩን ያላዩትን ማፍቀር እንደሚቻል ያወኩት ያኔ ነበር(አጠር አድርጌ ልንገራችሁ ብዬ ነው).....ከዛ እንዳፈቀርኳት ነገርኳት አይሆንም አለችኝ ጓደኝነቱ ይበልጥብናል አለችኝ እኔም ይሄን ግጥም ፃፍኩላት .....አንብቡልኝማ(ደሞ ርዕስም አልሰጠሁትም በቃ ዝምብላችሁ አንብቡት)


በሳቅሽ ጥልቅ ሀዘኔን ረሳሁት፣
ድብርት ስሙን ዘነጋሁት፣
ቀልድ ሳይኖርሽ እየፈጠርሽ የሌለሽን አጫወትሽኝ፣
መከፋቴን ነጠቅሽና ድርብ ደስታን አቀበልሽኝ።
እንዲያ ሲሆን ሞኙ ልቤን መውደድ ጎኑን ጎሻሸመው፣
ንፁህነት የለበሰ ፍቅር ሚባል ያልነካካው ፣
ብትፈልጊም ጓደኝነት አፈቀረሽ ምን ላድርገው?
እና.. ጥፋቴ ምንድነው ላልሽኝ ምን እንደሆን ቆይ ልንገርሽ፣
ለማታውቂው አንድ ተራ ሰው ይሄን ሁሉ ያደረግሽው አንቺ ማነሽ?

ማን ብትሆኚ ምን ብትሆኚ....
ድንገት በ chat ላወቅሽኝ ሰው...
እንዳይከፋኝ ተጠንቅቀሽ፣
እንዳላዝን አስተውለሽ ፣
ምታወሪኝ በድምፅሽ ሳይ ሳቅ ጨምረሽ፣
ከእለታት በሆነ ቀን ቢደብረኝ ፣
ሀዘን ቢጤ ቢጫጫነኝ፣
አትከፋ እኔን ይክፋኝ፣
ብለሽ ዘፍነሽ ያፅናናሽኝ፣
እምባን በሳቅ የለወጥሽኝ፣
እኮ ለምን የረሳሁትን ሳቅ ዘመዴን ያስታወስሽኝ?
ይሁን ተይው መልሱ ይቅር፣
ግን ይሄነትሽን ይቻላል ወይ አለማፍቀር?
ቢቻል ኑሮ ምን በወጣኝ፣
እንዲህ አጥቼሽ ብቸኝነት የሚቀጣኝ።
ቢቻልማ ሁሉን ትቼ፣
ማፍቀር ሚባል ረስቼ፣
እንኳን ጓድሽ ባሪያሽ መሆን መች ጠልቼ።

#እውነተኛ_ታሪክ
@darktrut
😢8💔71👍1🤝1
ኤሊ ምንም ብትዘገይ ቤቷን አዝላ ነው ፡፡!!!

@darktrut
👍10
`` ነፍሴን ከጭንቀት ብቸኝነቴን ከአንበሶች አድናት..``
@darktrut
👍112
ሁሌም አውቀክም ቢሆን ለቀልድም እንኳን ቢሆን በራስክ ላይ መጥፎ ንግግሮችን አትናገር ሳታስበው እራስክ ያልከው ነገር ተብትቦክ ታገኘዋለክ።

ሁሌም መልካምን ቃል ዝራ።
@darktrut
18👍1
ክረምት ሆኖ የሚያስተክዝ ብርድና ዝናብ ሲመጣ ፣ ሰው በየቤቱ ገብቶ እሳት ሲሞቅ ፣ ቡና ሲጠጣ ፣ ቆሎ ሲቆረጥም ፣ አሹቅ ሲቅም ብቻዬን እከተማ እወጣለሁ። ጭር ይላል። ሁሉ በየቤቱ ነበር። በስክርክር የቦይ አበላ ስጫወት እቆይና . . . ተዳክሜ ወንዝ ዳር እየተንዘፈዘፍኩ እቆማለሁ። ብርዱ ውስጤ ነበር። እውነቴን ነው ውስጤ ነበር። እንደኳስ ተድበልብሎ የተቀመጠ ብርድ ነው። ታድያ ወደሞላው ወንዝ ጉሮሮዬ እስኪበጠስ እጮሃለሁ . . .ምንአልባት የውስጤ ቅዝቃዜ እንደ  ትውከት ተወርውሮ ቢወጣ ብዬ። ተጣብቆ ይቀመጣል። ብርዱ አንጀቴ ላይ እንደኖረ ፣ ጎጆውንም በሲምንቶ እንደቀለሰ ኮሶ ተጣብቆ ይቀመጣል. . ከዚያ የቀን ሕልሜን እጀምራለሁ . . .


             ፦ ግራጫ- ቃጭሎች 📖


                @darktrut
👍169
ሁለት ዓይነት ሴቶች አሉ..👱🏼‍♀

¹ብልህነቷን የምትጠቀም

   ²ብልቷን የምትጠቀም
😁166👍4👎3🤝3😱1
"መሃል ሰፋሪ" ይባል ነበር በደርግ ጊዜ። "እስቲ ይህን ነገር ቅድሚያ ላጣራ" ብለህ ነጠል ብትል የሁሉም ጎራ ጠላት ሆነህ ትመታለህ። እውነት ቢኖርህም ዋጥ አድርገህ የመንጋው የስሜት ማእበል ውስጥ ገብተህ መንቦጫረቅ ነው።
👍8🔥43👏2
ወንዶች በተፈጥሮ ውሸታም ሲሆኑ ሴቶች ደግሞ ይሄንን ውሸት ያምኑበት ዘንድ ተፈጠሩ !

Art ; 'The Flirtation' by Eugene von Blaas
😁17👍54
ችግር መልክ ቢኖረው
💔18😢7👍31
....አዳም የበሰበሰ በለስ ውጦ ከዚህች ኤደን ነው ያወጣን? ወደ ሞት ወደ ጦርነት ወደ ደም ወደ አርበኝነት ወደ ባንዳነት? 😕😕……. ያቺ ሴት ያቺ ቂልና ቀልቃላ ሴት፡፡ ያቺ ሄዋን የምትባል ሀጠራው!......

ህማማትና በገና

/Book Excerpt


#አዳም_ረታ
👎147👍4🤬4😁2
በዘመናችን ዳቦ እና ውሃ ይዘ ካንተ ጋር መኖርን የሚመርጥ ዶሮ ብቻ ነው
👍4🤔42😁2😭1
“ሴት በጣም አስቀያሚ እና የማትስብ በሆነች ቁጥር ጩኸቷ እና ቅናቷ ይበልጥ እየጨመረ ይመጣል..”


                ―ፍሬድሪክ ኒቼ
👍9👎8😁7
#What_is_Feminist ?

    "እንደወንድ ለመሆን የምትጥር ሴት"።
👍18😁6👎41
"ድሀ የፍቅር ሀብታም ነው" 😌
👎86🔥3👍2🤝2👏1
“ልብህን ስለሰበርኩት አዝናለሁ”

፦ልቤ
😁8👏3😢3🤝1
ትላንትና ነፃነትን ናፍቀናታል : ዛሬ ፍቅርን እንናፍቃለን : ነገ ላይ ሰብአዊነትን እንዳንናፍቀው እፈራለሁ!


መሀሙድ ዳርዊሽ
7👍7🤝1
የምትወደውን ፈልግ ከዛም እንዲገድልህ ፍቀድለት !

ቻርለስ ቡኮቩስኪ
💔7👍3
ይህቺ አይጥ በወጥመዱ ትያዛለች፤ ምክንያቱም ምግቡ ለምን በነፃ እንዳገኘችው አልገባትም..
👏5🤔4👍32
Dark truth
#What_is_Feminist ?     "እንደወንድ ለመሆን የምትጥር ሴት"።
#What_is_Atheist ?

"ግድ የለሽ ቸልተኛ ተስፍ የቆረጠ" ።
😁8😢4👍2💔2
Forwarded from ጥበብ ፍልስፍና (.)
????????

መቼ ነው እንዲ የሆንኩት? ክሳቴ ግርጣቴ መቼ ነው የጀመረው ??

መቼ ነው እንዲ ልብሴ መነተብ ሲጀምር ችላ ያልኩት ?? መቼ ነው ለልብሴ ግድ የለሽ መሆን የጀመርኩበት ቀን ??


መቼ ነው ሰው ይንቀኛል ብዬ ማሰብ የጀመርኩት እና የተቀበልኩት??

መቼ ነው ህልሜ የታመመው?
     መቼ ነበር የቀበርኩት??

የቱ ቦታ ጋ ነው መሞቻዮን ያስተናገድኩት??
     ተስፋዬን ከየት እወልደዋለው???


አብሮ አደጎቼ መቼ ነበር እንዲ መራቅ  የጀመሩበት ወደፊት እርምጃ የተራመዱበት።
እኔ ወደ ኋላ የጎተተኝን እርምጃ መቼ ነበር  ሀ  ያልኩት::


መንገዴ ላይ የሆነ አይነት ፍላጎት ነበረኝ የምጥለው፣ የማነሳው ፣ የምሟገተው . . . . . . .
      
         ( አሁን )
መፈለግ ራሱ ምንድነው ??
    መንገድ ሲያደክም እንዲ ነው? . . . . . .

ከስቃይ ላላመልጥ ተረግሜ ይሆን??  ያያት፣ የቅም አያት ሃጥ በወጣት ገላ ተከናንቤ?


ወይስ እንደ ድመት ስንት ነፍስ ቢኖረኝ??
           እንዲህ ማረፍን ለምኜ
          አለም  ልትለቀኝ  የማትሻ .......


                      ያማል ! !

     ሞትም ፥ ህይወትም ሲገፋኝ....

@ethiosecret
6😢4💔1