❤12🔥3
የፈላስፋው ፍሬድሪክ ኒቼን ደብዳቤዎች ያነበበ ሰው በብቸኝነት ስሜት ብዙ እንደተሰቃየ ይገነዘባል። በ1887 ዓ.ም ለጓደኛው ኮቭሪክ እንዲህ ሲል ደብዳቤ ጻፈለት፦
“ልጅ እያለሁ ብቻዬን ነበርኩ ዛሬ ላይ አርባ አራት አመት ሞልቶኝም ብቻዬን ነኝ። የሰው ልጅ ሁሌም እንደናፈቀኝና እንደፈለኩት ነው። እኔ ግን ይሄ ፍለጋ ሁሌም እራሴን ያስገኝልኛል ምንም እንኳን እራሴን ባልናፍቅም። ከእንግዲህ ወዲህ ማንም ወደ እኔ የሚመጣ የለም፤ እኔማ ወደ ሁሉም ሄጄ ነበር ቢሆንም አንድም አላገኘሁም!።”@darktrut
💔18😢5❤1👍1
ድንገት በቻት ነበር የተዋወቅነው ብቻዬን በነበርኩበት ሰአት ...እሷ ሁሉን ሆነችልኝ በአካል አብሬ ከማሳልፈው ጊዜ በላይ እሷ ጋር የምናወራው ይበልጥ ነበር በቃ አብራኝ ነበር የምትውለው ከምላችሁ በላይ የምትገርም ሴት ናት የሚያውቀኝ የልብ ጓደኛዬ እንኳ የሷን ያህል የሚጨነቅልኝ አይመስለኝም ነበር ከፋኝ ስላት ትዘፍንልኛለች.. ድምጿ ያምራል... አይተውት የማያውቁትን አካል መልኩን ያላዩትን ማፍቀር እንደሚቻል ያወኩት ያኔ ነበር(አጠር አድርጌ ልንገራችሁ ብዬ ነው).....ከዛ እንዳፈቀርኳት ነገርኳት አይሆንም አለችኝ ጓደኝነቱ ይበልጥብናል አለችኝ እኔም ይሄን ግጥም ፃፍኩላት .....አንብቡልኝማ(ደሞ ርዕስም አልሰጠሁትም በቃ ዝምብላችሁ አንብቡት)
በሳቅሽ ጥልቅ ሀዘኔን ረሳሁት፣
ድብርት ስሙን ዘነጋሁት፣
ቀልድ ሳይኖርሽ እየፈጠርሽ የሌለሽን አጫወትሽኝ፣
መከፋቴን ነጠቅሽና ድርብ ደስታን አቀበልሽኝ።
እንዲያ ሲሆን ሞኙ ልቤን መውደድ ጎኑን ጎሻሸመው፣
ንፁህነት የለበሰ ፍቅር ሚባል ያልነካካው ፣
ብትፈልጊም ጓደኝነት አፈቀረሽ ምን ላድርገው?
እና.. ጥፋቴ ምንድነው ላልሽኝ ምን እንደሆን ቆይ ልንገርሽ፣
ለማታውቂው አንድ ተራ ሰው ይሄን ሁሉ ያደረግሽው አንቺ ማነሽ?
ማን ብትሆኚ ምን ብትሆኚ....
ድንገት በ chat ላወቅሽኝ ሰው...
እንዳይከፋኝ ተጠንቅቀሽ፣
እንዳላዝን አስተውለሽ ፣
ምታወሪኝ በድምፅሽ ሳይ ሳቅ ጨምረሽ፣
ከእለታት በሆነ ቀን ቢደብረኝ ፣
ሀዘን ቢጤ ቢጫጫነኝ፣
አትከፋ እኔን ይክፋኝ፣
ብለሽ ዘፍነሽ ያፅናናሽኝ፣
እምባን በሳቅ የለወጥሽኝ፣
እኮ ለምን የረሳሁትን ሳቅ ዘመዴን ያስታወስሽኝ?
ይሁን ተይው መልሱ ይቅር፣
ግን ይሄነትሽን ይቻላል ወይ አለማፍቀር?
ቢቻል ኑሮ ምን በወጣኝ፣
እንዲህ አጥቼሽ ብቸኝነት የሚቀጣኝ።
ቢቻልማ ሁሉን ትቼ፣
ማፍቀር ሚባል ረስቼ፣
እንኳን ጓድሽ ባሪያሽ መሆን መች ጠልቼ።
#እውነተኛ_ታሪክ
@darktrut
በሳቅሽ ጥልቅ ሀዘኔን ረሳሁት፣
ድብርት ስሙን ዘነጋሁት፣
ቀልድ ሳይኖርሽ እየፈጠርሽ የሌለሽን አጫወትሽኝ፣
መከፋቴን ነጠቅሽና ድርብ ደስታን አቀበልሽኝ።
እንዲያ ሲሆን ሞኙ ልቤን መውደድ ጎኑን ጎሻሸመው፣
ንፁህነት የለበሰ ፍቅር ሚባል ያልነካካው ፣
ብትፈልጊም ጓደኝነት አፈቀረሽ ምን ላድርገው?
እና.. ጥፋቴ ምንድነው ላልሽኝ ምን እንደሆን ቆይ ልንገርሽ፣
ለማታውቂው አንድ ተራ ሰው ይሄን ሁሉ ያደረግሽው አንቺ ማነሽ?
ማን ብትሆኚ ምን ብትሆኚ....
ድንገት በ chat ላወቅሽኝ ሰው...
እንዳይከፋኝ ተጠንቅቀሽ፣
እንዳላዝን አስተውለሽ ፣
ምታወሪኝ በድምፅሽ ሳይ ሳቅ ጨምረሽ፣
ከእለታት በሆነ ቀን ቢደብረኝ ፣
ሀዘን ቢጤ ቢጫጫነኝ፣
አትከፋ እኔን ይክፋኝ፣
ብለሽ ዘፍነሽ ያፅናናሽኝ፣
እምባን በሳቅ የለወጥሽኝ፣
እኮ ለምን የረሳሁትን ሳቅ ዘመዴን ያስታወስሽኝ?
ይሁን ተይው መልሱ ይቅር፣
ግን ይሄነትሽን ይቻላል ወይ አለማፍቀር?
ቢቻል ኑሮ ምን በወጣኝ፣
እንዲህ አጥቼሽ ብቸኝነት የሚቀጣኝ።
ቢቻልማ ሁሉን ትቼ፣
ማፍቀር ሚባል ረስቼ፣
እንኳን ጓድሽ ባሪያሽ መሆን መች ጠልቼ።
#እውነተኛ_ታሪክ
@darktrut
😢8💔7❤1👍1🤝1
ሁሌም አውቀክም ቢሆን ለቀልድም እንኳን ቢሆን በራስክ ላይ መጥፎ ንግግሮችን አትናገር ሳታስበው እራስክ ያልከው ነገር ተብትቦክ ታገኘዋለክ።
ሁሌም መልካምን ቃል ዝራ።
@darktrut
❤18👍1
ክረምት ሆኖ የሚያስተክዝ ብርድና ዝናብ ሲመጣ ፣ ሰው በየቤቱ ገብቶ እሳት ሲሞቅ ፣ ቡና ሲጠጣ ፣ ቆሎ ሲቆረጥም ፣ አሹቅ ሲቅም ብቻዬን እከተማ እወጣለሁ። ጭር ይላል። ሁሉ በየቤቱ ነበር። በስክርክር የቦይ አበላ ስጫወት እቆይና . . . ተዳክሜ ወንዝ ዳር እየተንዘፈዘፍኩ እቆማለሁ። ብርዱ ውስጤ ነበር። እውነቴን ነው ውስጤ ነበር። እንደኳስ ተድበልብሎ የተቀመጠ ብርድ ነው። ታድያ ወደሞላው ወንዝ ጉሮሮዬ እስኪበጠስ እጮሃለሁ . . .ምንአልባት የውስጤ ቅዝቃዜ እንደ ትውከት ተወርውሮ ቢወጣ ብዬ። ተጣብቆ ይቀመጣል። ብርዱ አንጀቴ ላይ እንደኖረ ፣ ጎጆውንም በሲምንቶ እንደቀለሰ ኮሶ ተጣብቆ ይቀመጣል. . ከዚያ የቀን ሕልሜን እጀምራለሁ . . .፦ ግራጫ- ቃጭሎች 📖
@darktrut
👍16❤9
....አዳም የበሰበሰ በለስ ውጦ ከዚህች ኤደን ነው ያወጣን? ወደ ሞት ወደ ጦርነት ወደ ደም ወደ አርበኝነት ወደ ባንዳነት? 😕😕……. ያቺ ሴት ያቺ ቂልና ቀልቃላ ሴት፡፡ ያቺ ሄዋን የምትባል ሀጠራው!......
/Book Excerpt
#አዳም_ረታ
ህማማትና በገና
/Book Excerpt
#አዳም_ረታ
👎14❤7👍4🤬4😁2
“ሴት በጣም አስቀያሚ እና የማትስብ በሆነች ቁጥር ጩኸቷ እና ቅናቷ ይበልጥ እየጨመረ ይመጣል..”―ፍሬድሪክ ኒቼ
👍9👎8😁7