Dark truth
520 subscribers
177 photos
12 videos
እንኳን ለሞት ቀርቶ ዝምታ ለዋጠው ለኑሮም አልሰጋን አፈር ለሚያስጌጠው!!
Download Telegram
ድብብቆሽ እንጫወት?!እኔ ልብ ውስጥ ከተደበቅሽ አንቺን ማግኘት አይከብድም። ከራስሽ ቅርፊት ጀርባ ከተደበቅሽ ግን ማንም አንቺን በመፈለግ አይጠቀምም።
#ጂብራን_Khalil
@darktrut
👍51
እብድ ነህ " ለሚሉኝ አዎ ሆኖ መልሴ
ግራ ቢገባቸው ለእብደት መኮፈሴ
ከንፈር መጠው ሄዱ ከንፈር ስላቅ ከንፈር
ያሳፍራል እንዲህ በእበደት አለማፈር ?

     አዎ እኔ እብድ ነኝ
      ገደብ ያልከለለኝ
      ድንበር ያልወሰነኝ
መንገድ ዳር የጣሉት የፌስታል ጌጠኛ
አዎ እኔ እብድ ነኝ...
ከረሳኝ የሰው ዘር  የማይከዳን ውሻ አቅፌ ምተኛ።

p h o t o :  Diogenes 📷
@darktrut
7🔥1
‹‹ያየን ሁሉ ተሰናክለን የማናውቅ ይመስለው ዘንድ የተረጋጋን ዝም ብሎ የሚሄድ ሰው መሆን ምን ማለት እንደሆነ አያውቁም። ማንም ምን ያህል እንደደከመን አያውቁም። በዝምታ ፈገግ በማለታችን እና የተስተካከለ ቁመናችንን አይተው ምን ያህል የድካም ዝርዝሮችን እንደተሸከምን ለማንም ጉዳዩ አይደለም።

በቃ አይረዱሃችሁም.. ሺህ ማይል እያሰብን የተራመድንበትን ነገር ብናወራው እነሱ አንድ እርምጃ ስላልተራመዱ አይሰማቸውም። በልባችን ውስጥ ያለውን የለሊት ሃሳቦች ሚሊዮን ጊዜ ብናስረዳ ልባቸውን አንዷን ሌሊት እንኳን አያንኳኳም። ግን ይህ ጥፋታቸው አይደለም በልምድና በቃላት መካከል ያለው ሰፊ እርቀት ነው።››

     
―አህመድ ካልድ ታውፊቅ
@darktrut
👍61
"Illusion of life"
ባዶህን ሊሞላህ ማንም አይመጣም።ነገርግን ሙላትህን ለመካፈል የሚመጡ ብዙዎች ናቸው። ይህ በህይወቴ የተማርኩት አስገራሚ ሃቅ ነው። የወዳጅነት እና የህይወት ከንቱነትን አጉልቶ ያሳያል።
     

      @darktrut
👍102🤝1
“ከእንቅልፋችን ስንነሳ መጀመሪያ ማድረግ ያለብን በራሳችን ማፈር ነው” 🤞🏽😑

           ―ኤሚሊ ሲዮራን
@darktrut
👍9🤔4
በነገራችን ላይ በአሁን ጊዜ ፈጣሪ በሰው አምሳል ወደምድር ወርዶ "እኔ ፈጣሪ ነኝ" ብሎ ቢናገር፤ በኀብረትና በጭካኔ የሚገድሉት ሃይማኖተኛ ነን የሚሉ ማኀበረሰቦች ነበሩ 🪓


    መልካም በዓል ሃይማኖተኞች
@darktrut
👏6👍52
የመጀመሪያዋ ወይም የመጨረሻዋ አልያም የእሷ ብቻ ላትሆን ትችላለህ። ካንተ በፊት አፍቅራለች እና እንደገና በፍቅር ወድቃለች። ግን አሁን ከወደደችህ ሌላ ምን ዋጋ አለው? እርሷ ፍጹም አይደለችም አንተም አይደለህም። ሁለታችሁም ፍጹም አትሆኑም። ግን አንድ ጊዜ እንኳ ልታስቅህ ከቻለች ሁለቴ እንዳታስብ። ሰው መሆንህን እና መሳሳትህን የምታምን ከሆነ ያዛት እና የምትችለውን ሁሉ ስጣትቅኔ አትቀኝልህም በእያንዳንዱ ቅጽበት አታስብልህም ነገር ግን ልትሰብረው እንደምትችል የሚያሳይ ድርሻ ትሰጥሃለች እሱም ልቧን ነው። አትጉዳት፣ አትቀይራት፣ እናም ከምትሰጠው በላይ አትጠብቅ። ትንታኔ ውስጥ አትግባ ስታስቅህ ሳቅ ስታስደስትህ በዝምታ ናፍቃት። ፍቅሯን ስትቀበል በሙሉ ልብህ ውደድ ምክንያቱም ፍፁም የምትባል ሴት ስለሌለች።
ፍጹም የምትባል ሴት አትፈልግ፤ ነገር ግን አልሰማም በማለት ፍጹም የምትባል ሴት አገኘው ብለህ ስትመጻደቅ ፍጻሜህን ታቀርበዋለች 🙌🏽🙃

;-ቦብ ማርሌይ
@darktrut
👍9👏1
ይሄ ሰው በየቀኑ በሟች ታሪክ ላይ የተመሰረተ Death story ጋዜጣ ላይ ያነባል። ም/ት ‹‹እኔና አንተ ብንለያይ እሞታለሁ›› ያለችውን ሴት ስም ፍለጋ..

        እስካሁን አላገኛትም 🤗
@darktrut
👍6😁5😢1
ጌታ ሆይ !<<ከዝሙት አድነኝ ነገር  ግን  አሁን  አይደለም >>


   [ቅዱሥ አውጊስቲን ]

@dartrut
😁7🔥3🤔3
እውነትህን የሚገነዘቡልህ በጠፉም ጊዜ ጭምር ለኔ ትገባኝ ነበር!!...

@darktrut
👍41
ጥምቀት ሃይማኖታዊ በአል ነው concrete or festival እደልም!!!
6
‘‘መከራ ውስጥ ነህ ማለት የስኬት መንገድ አይደለም፤ ልትሰቃይ እና ልትሞትም ትችላለህ እንደማለት ነው!።’’


-ቶልስቶይ
4👍2
Desire detachment, and attachment The more you let go of your desire, the more you get linked to your presence

በመፈለግ ውስጥ ካለ ምኞት በተነጠልክ ቁጥር መሆን ውስጥ ወዳለ ምኞት ታድጋለህ፡፡ በመሆን ውስጥ ያለ ምኞት መሆን እንጂ ምኞት አይደለም።
@darktrut
👍21
በዙሪያችን ያሉ ነገሮች መዓዛቸውን እየቀየሩ እየደረቁና እየሞቱ፣ ትርጉም አልባ ብሎም ውበት የለሽ መስሎ ከተሰማን። ይህ ማመን አለብን እየጠወልግን ያለነው እኛ ነን!።
@darktrut
👍6
ለብቸኝነቴ ጓደኛ ያስፈልገዋል፤ ለዛ ነው ሁሌም አብሬው የምሆነው..

🃏
@darktrut
13
ጠዋት ጠዋት ምንድነው ምትፈልገው

     ቡና ወይስ ሻይ?


      ‹‹..እንቅልፍ..››
@darktrut
👍152
“ከእንግዲህ ምንም ስሜት እንዳይኖራቸው የወሰኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አሉ። በቆዳቸው ውስጥ ወፍራም ሽፋን አደገ፤ ያም ሌሎች እንዳይበድሏቸው ተከላከለ። ቢሆንም ይህ ሁሉ አስከፊ ዋጋን አመጣ። በእርግጥ ማንም ሊጎዳቸው አይችልም፤ ግን ደግሞ ማንም ሊያስደስታቸው አልቻለም..!”

               ―ባግዋን ኦሾ
@darktrut
👍4
ብዙዎቻችን ከ20ዎችሁ በላይ በ19፣ 20፣21 እድሜያችን ላይ እንቀራለን..

@darktrut
5👍2
ባይሆንም ይሆናል ቢሆንም አይሆንም፤
በቃ ልክ ናቸው እግ'ዜርም ሰይጣንም!

ግራ
@darktrut
🤔10👍2
ያ የብቸኝነት ስሜት የመገለል፣ ሰው የመናፈቅ ስሜት፤ ከፈጠሪ እርቆ ማንነትን እየወቀሱ አዕምሮን በጸጸት ማድከም፤ ከራስ መጉደል ጉድለቱም ሀዘን የሞላው ባዶነት መሸከም፤ ብቸኛ ሆይ እግሮችህን ወደ ደረትህ አጣብቀ ስጋ የራቀው አካልህን በደንብ አድረገህ እቀፈው፤ በጸጥታ በዝምታ መታገልህን አቁምና ተኛ!።
@darktrut
👍43
አልረሳውሽም...አለመኖርሽን ነው.. የለመድኩት።

@darktrut
😢8💔6