Dark truth
521 subscribers
177 photos
11 videos
እንኳን ለሞት ቀርቶ ዝምታ ለዋጠው ለኑሮም አልሰጋን አፈር ለሚያስጌጠው!!
Download Telegram
#100% true
👍10🔥3
#ያልተፈታ_እንቆቅልሽ

በአንድ ወቅት አንድ በጣም የሚናገርና ፈጣሪ የለም ብሎ የሚያምን ጸጉር አስተካካይ ነበር...አንድ ቀን አንድ ትሁት ቄስ ጸጉራቸውን ሊስተካከሉ ወደዚህ ጸጉር ቤት ገቡ። አስተካካዩ ሥራውን እየሰራ፣ እንደ ልማዱ አንድ ሁለት ወሬ ጀመረ...

_ "አባቴ እኔ እኮ ፈጣሪ አለ የሚለውን ነገር አላምነውም!" አላቸው፡፡

_ ቄሱም በመገረም "ለምን ልጄ?" ብለው ጠየቁት...

_ አስተካካዩም በኩራት እንዲህ አለ፦ "ወደ ውጭ ወጥተው መንገዱን ይመልከቱ! ፈጣሪ ቢኖር ኖሮ ይሄ ሁሉ በሽተኛ ይኖር ነበር... ይሄ ሁሉ የታረዘና የተራበ ሕፃን ይታይ ነበር? ይሄ ሁሉ ግፍና መከራ በምድር ላይ ይፈጸም ነበር? አፍቃሪ የሆነ አምላክ ቢኖር ኖሮ ይሄን ሁሉ መከራ አይፈቅድም ነበር... ስለዚህ ፈጣሪ የለም!" ብሎ በድፍረት ተናገረ።

ቄሱም በዚያ ሰዓት ክርክር ውስጥ ሳይገቡ ጸጉራቸውን ተስተካክለው፣ ክፍያቸውን ከፍለው ወጡ... ልክ ከጸጉር ቤቱ በር ላይ እንደወጡ፣ ቄሱ አንድ ሰው አዩ፡፡ ያ ሰው ጸጉሩ በጣም አድጎና ተንጨባርሮ፣ ጺሙም ተዘበራርቆ ፊቱ ሁሉ ተሸፍኖ ነበር... ቄሱ ወዲያውኑ ወደ ጸጉር ቤቱ ተመልሰው ገቡ፡፡

_ ቄሱም አስተካካዩን ጠርተው፦ "ልጄ ሆይ፣ አሁን አንድ እውነት ገባኝ፤ በዚህ
#ሰፈር ላይ ጸጉር አስተካካይ የሚባል ሰው የለም" አሉት።

_ አስተካካዩ እየሳቀ "ምን ማለትዎ ነው አባቴ... እኔ እኮ እዚህ ቆሜ ጸጉርዎን አሁን አስተካከልኩልዎት። እንዴት የለም ይላሉ?" አላቸው...

ቄሱም ወደ ውጪ ጠቁመው፦ "አየህ፣ ጸጉር አስተካካይ ቢኖር ኖሮ ያ ሰውዬ ጸጉሩ እንደዛ ተንጨባርሮ በመንገድ ላይ ይሄድ ነበር? ጸጉር አስተካካይ ቢኖር ኖሮ እኮ ሁሉም ሰው ጸጉሩ የተስተካከለ ይሆን ነበር" አሉት።

_ አስተካካዩም "ኧረ አባቴ! እኔ እኮ አለሁ። ችግሩ ያ ሰውዬ ወደ እኔ መጥቶ አስተካክለኝ ስላላለን እንጂ፣ እኔ እኮ ዝግጁ ነኝ" አለ።

ቄሱም ፈገግ አሉና "በትክክል! ፈጣሪም አለ! ችግሩ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መጥተው እርዳን፣ ማረን ስለማይሉት እንጂ፣ ፈጣሪ ሁልጊዜም ዝግጁ ነው! አሉት..."

_ አስተካካዩም ዝም ብሎ ማሰብ ጀመረ፤ "እና ሰው ምን ነካው፣ ይሄንን ሂዎት መርጦ የሚኖረው አለ?"

_ ቄሱም "እሱ ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው ልጄ፣ በዓለማችን ላይ ላለው መከራ ሁሉ ተጠያቂው ፈጣሪ አይደለም..." ብለውት ሄዱ።

ጠቅለል ስናደርገው ለስንፍና፣ ለውድቀት ምክንያታችን ፈጣሪ የሰጠን እድላችን አይደለም! የምንደበቅበት፣ የአለመቻል መደበቂያ ያደረግነው እኛ ነን! ከሰበበኝነት ወጠን መንገዳችንን እናስተካክል! አላማችንን እንወጥን፤ ግፉበት! ይሄ እራስን ማታለል (self-deception) ነው!! ነቃ በል ወንድሜ /እህቴ🤝

<እውቀትና እብደት>
6🔥5👏1😁1🤔1
Dark truth
አንድ ብር አለህ እንበል...         - የለኝም ግድ የለም አለህ እንበል?      - የሌለኝን! እሺ ይኖረሃል እንበል .. - አንድ ብር ብቻ? እሺ ነበረህ እንበል - እኮ አንድ ብር ብቻ? ኦፋ ጫወታ አታውቅም ልበል?   - መጫወቻ አታድርገኛ እሺ ለምሳሌ....    - ምሳሌ ስጠኝ እንጂ ምሳሌ አታድርገኝ ገደል ግባ   - ሜዳ ሜዳውን እያየሁ እሄዳለሁ
- የሆነስ ሆነና፣ ስምህ ማን ነው?
- ላገር አይመች

- ማን አወጣልህ?
- ጎረቤቶች

- የናትህ ስሟ ማን ነው?
- ሳልወለድ ሞተች

- የሆነስ ሆነና፣ እግዚሀርን አይተኸዋል አላየኸውም?
- አዎን አይቸዋለሁ

- ቀይ ነው ጥቁር?
- ተከናንቦ ነበር

- ረዥም ነው አጭር?
- ቁጭ ብሎ ነበር

📚አምስት - ስድስት -ሰባት..
ጋሽ ስብሃት ገብረ-እግዚኣብሄር
😁102
አንደኛው ሰው ሌላኛውን ሰው በቤቱ አሳደረው፤ ሌላኛው ሰው ግን የአንደኛው ሰውዬ ቤት ዘረፈው!።

በእኛ ማኀበረሰብ ብልጠት እንደ እንደሁለተኛው ሰው ይወከላል። ኢግኖራንስ ፒፕል ሆይ that high criminal እንጂ not a business idea🙂
11
አንድ ነገር በጣም ከተወደደብህ በመተው አርክሰው። Who cares...😎
👏12🔥74🤔2🤝1
Dark truth pinned «አንድ ሰው ያለ ምክንያት ከዘጋህ ምክንያት ስጠው!! who cares.»
Dark truth
#What_is_Globalization? "የተዋበ ከተማ ላይ የተራበ ሕዝብ" ።
#What_is_Love?
"ለውዶቻችን ቤዛ ለመሆን ሞራልን ፣ ስሜትን ፣ ህሊናን ገብያ ልናወጣ እንችላለን። ምክንያታዊነት ሳይገድበን ለራሳችን እየሱሳዊ ባህሪን አላብሰን ፤ ለሌሎች መስዕዋት መሆን መልካምነት እና ግዴታ እስከመሆን ጭምር ለራሳችን ተናግረን ራሳችንን እናሳምናለን!!።"
🔥32
በዚህ እብደቱ ውስጥ በልቡ ስቃይን አብልጦ ወደደ ምን አልባትም ሰላሜን በዚያ ውስጥ ካገኘሁ!' በማለት

ሊዮ ቶልስቶይ
💔3🔥2😢2👍1
የሚቀዘቅዙ ክረምቶች በሚሞቅ ገላ ይረሳሉ፤ የቀዘቀዙ ገላዎች የሞቀ ኑሮን ያበርዳሉ!
5🔥2👏2
`` ሁልጊዜ ህይወቴን እያባከንኩ ነው በሚል ኣሳብ ከራሴ ጋር እጣላለሁ..! ``

                     -ቻክ ቡላኔክ
8🔥5
ተጣልተው የሚያሳልፉት የመጀመሪያ ፋሲካ ነው፡፡ text አደረገላት " እንኳን አደረሰሽ " ብሎ። እንኳን አብሮ አደረሰን አንተ ግን ደህና ነህ ብላ መለሰችለት፡፡ አይደለሁም!ገድለሽኝ ሄደሻል! ክርስቶስን አይደለሁ አልነሳ ነገር። ብሎ ፃፈላት፡፡ የሴት ራስ ወንድ ነው። ከሞትህ ተነሳ እና እኔም ሁለት ፋሲካ ላክብር እባክህ፡፡ ብላ ፃፈችለት፡፡ታ.ረ.ቁ.
እኛም እንታረቅ?!!!
💔75🔥5👍4😁1
እውነተኛው ጥያቄ ከሞት በኋላ ህይወት አለ ወይ የሚለው አይደለም ፤ ትክክለኛው ጥያቄ ከመሞትህ በፊት በህይወት አለህ ወይ! የሚለው ነው።           

¹ በሕይወት መኖር ምን ማለት ነው???
                   ² የመኖር መለኪያውስ????
🤔7🔥6👍3🤝2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"በመጮህ ሳይሆን  ቃላቶችህን አሳድግ! አበቦች የሚያድጉት በዝናብ እንጂ በነጎድጓድ አይደለም"

:- ሩሚ
10👍4👎2🔥2🤣2
Dark truth
single ብንሆንም ከገሃነም እሳት አምልጠናል😭
ከቆሎ መሀል ፈልጌ ያገኘሁሽ ለውዜ ነሽ 😍


ላክላት አትፋራ ወንድ ልጅ ታሞ እንጂ ፈርቶ አይሞትም
😁123🔥2
Burger ትልቅ ነገር ከሚመስለው ሰው ራቁ 🙌😌
🤣17🤝5🔥4
አንዳንዴ መፍትሄ ከሚሰነዝሩልን አፎች በላይ የሚያዳምጡን ጆሮዎች ያስፈልጉናል። በጥልቀት በመፍትሔ ሳይሆን በመደመጥ ብቻ የሚድኑ ህመሞች ብዙ ናቸው። ማቀፍ ደረጃ ያልደረሱ በመዳበስ ላይ የሚገኙ መነካካቶች ብቻ የብቸኝነትን ቆፈን ይገፋሉ።
11🤝4👍2🔥2
ለድሆች ምግብ ስሰጥ ቅዱስ ይሉኝል ፤ ለምን ደሆች ምግብ
የላቸውም? ብዬ ሥጠይቅ ኮምኒስት ይሉኛል።

፡– ኦስካር ሮሜሮ
😁5👍43🔥1👏1
"አማርፓሊ ሆይ! የሴት ልጅ አይምሮ በቀላሉ የሚሳሳትና የሚረበሽ ነው። ሴት ከፍላጎቷ ጋር ተጣብቃ፣ለቅናቷ ምርኮኛ የሆነች ፍጡርም ናት። ስለዚህም የተቀደሰውን መንገድ ትከተል ዘንድ ለሴት ልጅ እጅግ አስቸጋሪ ነው። ይህ ደግሞ በተለይ ለወጣትና ቆንጆ ሴት እውነትነቱ የጎላ በመሆኑ ፍላጎትና ፈተናን ድል አድርገሽ ወደፊት ትሄጂ ዘንድ የግድ ነው።

፡· ቡድሀ
5👍3🔥1👏1🤬1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#True_Love_Means :- በነገራችን ላይ ፍቅር ስርዓት እና ሕግ አይደለችም። በሕግ በስርዓት እና በድንበር ውስጥ ፍቅርን አትፈልጓት፡፡ የለችም፡፡ ፍቅር ማለት በመከራ ውስጥ ሆኖ ፊት ለፊት መተያየት ነው።

እውነተኛ ፍቅርን የገለፀ ድንቅ ፊልም! ካገኛቹት እንድታዩት recommend አረጋቹሀለው


#Movie #Edward_Scissorhands
7😢4💔3