"ያልተመረመረ ሕይወት ዋጋ የለውም"
ሶቅራጥስ በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፦ "ያልተመረመረ ሕይወት ለሰው ልጅ መኖር አይገባውም።" ብዙዎቻችን በየቀኑ እንሮጣለን፤ ግን ወዴት? ለምን? መድረሻችንስ የት ነው? ብዙ ጊዜ የምንኖረው ማህበረሰቡ በሰጠን "ካርታ" ላይ እንጂ የራሳችንን መንገድ ቀደን አይደለም። ጥያቄው፦ ዛሬ የምታደርጋቸው ነገሮች የራስህ ምርጫዎች ናቸው ወይስ ልማዶች? መልእክቱ፦ ቆም ብለህ ማንነትህን ካልጠየቅክ፣ የሌላ ሰው ታሪክ ተዋናይ ሆነህ ትቀራለህ።
👏7❤6👍3🤔2
Dark truth
ያ የብቸኝነት ስሜት የመገለል፣ ሰው የመናፈቅ ስሜት፤ ከፈጠሪ እርቆ ማንነትን እየወቀሱ አዕምሮን በጸጸት ማድከም፤ ከራስ መጉደል ጉድለቱም ሀዘን የሞላው ባዶነት መሸከም፤ ብቸኛ ሆይ እግሮችህን ወደ ደረትህ አጣብቀ ስጋ የራቀው አካልህን በደንብ አድረገህ እቀፈው፤ በጸጥታ በዝምታ መታገልህን አቁምና ተኛ!። @darktrut
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሁሌም የሞቴን ክብረ በዓል እያከበርኩ ነው። ቀን በቀን ቀስ በቀስ እየሞትኩ ነው። አሞኛል አዎ ታምሚያለሁ። ቁስሌን መልሼ መላልሼ እልጣለሁ። እንደማልድን አውቃለሁ፤ ነገር ግን አንድ ቀን አልጋዬ ላይ ደርቄ እንደምገኝ በቁም እያለው እመሰክራለሁ።
የማወርሰው ንብረት የለኝም፤ የምጠብቀው ገነት የለም!። እንዲህ ያለህ ህመም ከሚገድለኝ ሞት በላይ ያማል። ለነፍስም ለሥጋም አለመሆን ከአፈር የተጣላ ከሰማይ ተባሮ በዓየር እንደተበተነ የእሳት ብናኝ ነው።
አንባቢዬ ሆይ እያመመኝ ነው የምጽፈው ስታነብ ከዳንክ የሌለኝን ፈውስ ነው የሰጠውህ። እኔው በገዛ እጄ ባመጣውት የውስጥ ደዌ ተመትቻለሁ። ያነበብከው የሚያስቅ ከሆነም ይህንን እወቅ፤ እጅግ በጣም በሃዘን ተውጫለሁ!።
👍3💔3👎1
Dark truth
‹‹እሺ›› እና ‹‹እምቢ›› ማለት የማይችሉ ሰዎች ሌላው መለያቸው ችግራቸውን አይናገሩም፡፡ እንደ ህጻን ልጅ በኩርፊያ ነው ችግር ላይ መሆናቸውን የሚያሳውቁት፡፡ የመናገር ድፍረት የላቸውም፡፡ ‹‹ምን ሆነህ ነው?›› ስትለው ምንም አይመልስልህም፡፡ ወደ ውስጡ ነው የሚያሰርገው፡፡ አንተ ከውጪ እየጠየቅከው እሱ ወደ ውስጡ ነው የሚመልሰው፡፡ 📚ምን ሆኛለዉ @darktrut
“ታውቃለህ.. በሕይወቴ አንድም ግዜ የምፈልገውን ነገር አግኝቼ አላውቅም። ታምናለህ ላንዴ እንኳን!። እንዲህ መኖር ምን እንደሆነ መገንዘብ አትችልም፤ ሰው የሚፈልገውን ከማያገኝበት ህይወት ጋር ሲላመድ በመጨረሻም ለምንም ነገር ፍላጎት የለሽ ይሆናል!።”— ሀሩኪ ሙራካሚ
😢11
Dark truth
አሁንም ስላንተ ምታስብ ነዋ ሚመስልህ ቱ🙊
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
single ብንሆንም ከገሃነም እሳት አምልጠናል😭
😁6🤣5😭3🔥2
አንድ ብር አለህ እንበል...
- የለኝም
ግድ የለም አለህ እንበል?
- የሌለኝን!
እሺ ይኖረሃል እንበል ..
- አንድ ብር ብቻ?
እሺ ነበረህ እንበል
- እኮ አንድ ብር ብቻ?
ኦፋ ጫወታ አታውቅም ልበል?
- መጫወቻ አታድርገኛ
እሺ ለምሳሌ....
- ምሳሌ ስጠኝ እንጂ ምሳሌ አታድርገኝ
ገደል ግባ
- ሜዳ ሜዳውን እያየሁ እሄዳለሁ
- የለኝም
ግድ የለም አለህ እንበል?
- የሌለኝን!
እሺ ይኖረሃል እንበል ..
- አንድ ብር ብቻ?
እሺ ነበረህ እንበል
- እኮ አንድ ብር ብቻ?
ኦፋ ጫወታ አታውቅም ልበል?
- መጫወቻ አታድርገኛ
እሺ ለምሳሌ....
- ምሳሌ ስጠኝ እንጂ ምሳሌ አታድርገኝ
ገደል ግባ
- ሜዳ ሜዳውን እያየሁ እሄዳለሁ
😁12😭9❤1