እመለስ ይሆናል ምናልባት እራሴን ፈልጌ ማግኘት ከቻልኩ ...ካልቻልኩ ግን እዚሁ በስደት መቅረቱን እመርጣለሁ፡፡ የምመለሰው ያጠፋውትን እኔነቴን ካገኘሁ ብቻ ነው፡፡ ወዜን ትዕግስቴን አደቤን ስነ ስርዓቴን ህልሜን ተስፋዬን እንደ ነበር ማግኘቱ ቀላል አይመስለኝም፡፡ ግን እሞክራለሁ... እኔነቴን ካገኘሁ እመለሳለሁ፡፡ እመጣለሁ ምናልባት ያጡትን መመለስ ቢከብድም ምናልባት እመጣለሁ..
❤10💔6
Dark truth pinned «እመለስ ይሆናል ምናልባት እራሴን ፈልጌ ማግኘት ከቻልኩ ...ካልቻልኩ ግን እዚሁ በስደት መቅረቱን እመርጣለሁ፡፡ የምመለሰው ያጠፋውትን እኔነቴን ካገኘሁ ብቻ ነው፡፡ ወዜን ትዕግስቴን አደቤን ስነ ስርዓቴን ህልሜን ተስፋዬን እንደ ነበር ማግኘቱ ቀላል አይመስለኝም፡፡ ግን እሞክራለሁ... እኔነቴን ካገኘሁ እመለሳለሁ፡፡ እመጣለሁ ምናልባት ያጡትን መመለስ ቢከብድም ምናልባት እመጣለሁ..»
ለ አንደበታችን ብቻ ሳይሆን ለ ልባችንም ፣ ለ ጆሯችንም ፣ ለ አይናችንም ልክ እናበጅለት ፤ "ልካችንን እንወቅ ጆሮም አይንም ልብም ለባለቤቱ ባዳ ነው"🥲
❤11
ከመንገድ ላይ ወድቆ ነው ያገኘውት በጣም ደስ ስላለኝ አጋራዋቹህ ...ሁላቹም ለእህቶቻቹ ማጋራት ትችላላችሁ መልካም ቀን ☺️
❤10
“ሌሎች እናንተ ሳትኖሩ በፊት ብቻቸውን ኖረዋል፤ ወደፊትም ያለእናንተም ይኖራሉ። የሆነ ሰው የሚፈልግን ይመስላችኋል? ዳቦ አይደላችሁም፤ ውሃ አይደላችሁም ማንም አይፈልጋችሁም” 🫤
―ማክሲም ጎርኪ❤4👎3🤔3
ለምን ግን የወደድነውን ለመኖር፣ለመናገር ፈራን?
የምንወዳቸው ሰዎች የወደድነው እንደማይወዱልን ማነው የነገረን?
አይምሮአችን በምንወዳቸው ሰዎች ስም የደገመብን ድግምት ሊኖር አይችልም? #Soul ፊልም ላይ እናቱን መከራከር ትቶ ስለ ሒወቱ ደስተኛ አለመሆን በፍቅር ሲያወራት እሺ ብላ አትሒድ ብላ የምትከለክለው ኮንሰርት ላይ ተመልካች ሆና ትገኛለች።
አንድ ጓደኛዬ የእናቱን ስም በግብዳው ክንዱ ላይ ተነቅሷል። ለእናቴ ነው ምኖረው ብሎ ምሏል። ለእናቱ እንደሚገድል ሲናገር አይኖቹ አይርገበገብም። እንጀራ አባቱ እንኳ ቢሆን።
የሆነ ቀን ግን ምን ትላለች እናት..
"በመሀከላችን አትግባ"

ደነገጠ። ሊመታት ሁሉ አማረው። ለምን እንደሚኖር ጠፋው!
Soul የራስህ ናት 🧡
❤10😢1