DaniApps™
1.01K subscribers
611 photos
34 videos
537 files
219 links
✅The Best Android Apps And Games Are Here.📱
✅For Any Questions ➡️ @DaniappsBot Or Group ➡️ @daniappsgroup
✅ Apps Or Games ➡️ @daniappsstore
✅Ask Any Apps ➡️ @Daniapps2bot
✅ Website https://daniapps.epizy.com/

https://g.page/r/CYhVwdbaF335EA0/review
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🧨Netflix ለትክክለኛው SQUID GAME ቀረጻ ከፍቷል።

በአለም ላይ ከየትኛውም ቦታ ሆነው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ያላቸው 456 ተሳታፊዎችን ይፈልጋሉ። የሽልማት ጣሪያው 4.56 ሚሊዮን ዶላር ድረስ ነው።

መሞከር ከፈልጋላችሁ፡ SquidGameCasting.com
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔅የ #IOS 16 አንዳንድ Features ማየት ከፈለጋችሁ እቺን ቪድዮ ተመልከቱ😊

©️Ethiocyber
©️DaniApps
✅ " ቴሌግራም ፕሪሚየም "

ቴሌግራም በነፃ ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ በክፍያ አገልግሎት የሚሰጥበትን " ቴሌግራም ፕሪሚየም " ትላንት ለሊት ይፋ አድርጓል።

የቴሌግራም ፕሪሚየም ወራዊ ክፍያ 5.99 የአሜሪካ ዶላር መሆኑም ታውቋል።

አሁን ላይ የIOS (አይፎን) ተጠቃሚዎች መተግበሪያቸውን Update ማድረግ የሚችሉ ሲሆን ፤ ዛሬ አልያም በቀጣይ ቀናት ለአንድሮይድ ተጠቃሚዎች ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

" ቴሌግራም ፕሪሚየም " ሌላ ተጨማሪ መተግበሪያ ሳይሆን እዚሁ አሁን የምንጠቀመውን መተግበሪያ Update ስናደርገው በውስጡ የምናገኘው አገልግሎት ነው።

" ቴሌግራም ፕሪሚየም " ከሚሰጠው አገልግሎት መካከል በጥቂቱ ፦
- እስከ 4 GB ድረስ ፋይል መላክ / ማስቀመጥ
- ፈጣን ዳውንሎድ
- መቀላቀል የሚቻለው ግሩፕ እና ቻናል እስከ 1000 ድረስ
- የፎቶ እና ቪድዮ Caption እስከ 2048 ድረስ
- በአንድ መተግበሪያ ማገናኛት የምንችለው አካውንት 4 ድረስ
- ድምፅን ወደ ፅሁፍ የመቀየር አገልግሎት
- የፕሮፋይል ባጅ (የፕሪሚየም ተጠቃሚዎች መለያ)

ከጊዜ ወደ ጊዜ አገልግሎቱን እያዘመነ የመጣው ቴሌግራም በአሁን ሰዓት ወርሃዊ ተጠቃሚዎቹ 700 ሚሊዮን መድረሳቸውን አብስሯል።

©️
Ethiocyber
©️DaniApps
Update Android

ከአንድ ቀን በፊት ቴሌግራም ለIOS (አይፎን ስልክ) ተጠቃሚዎች ' ቴሌግራም ፕሪሚየም ' የተካተተበትን መተግበሪያ Update ማድረጉ ይተወሳል።

ትላንት ለሊት የአንድሮይድ ተጠቃሚዎች አገልግሎቱ እንዲደርሳቸው ሆኗል።

ዋናውን በድርጅቱ በኩል የሚቀርበው የቴሌግራም መተግበሪያ (ባለ ሰማያዊ ምልክቱ) ይጠቀሙ። Update ለማድረግ ሊንክ ይኸው
https://play.google.com/store/search?q=telegram&c=apps

" ቴሌግራም ፕሪሚያም " አሁን በነፃ እየተሰጠ ካለው አገልግሎት በተጨማሪ አዳዲስ አገልግሎቶች የተካተቱበት ሲሆን በወር 5.99 ዶላር ያስከፍላል።

በአዲሱ Update በነፃ በሚሰጠው አገልግሎት ላይ ከዚህ በፊት ከነበረው ማሻሻያ እና የነበሩትን ችግሮች የመቅረፍ ስራ መሰራቱ ድርጅቱ አሳውቋል።
👍1
✅ ውሃ ውስጥ የገባን የሞባይል ስልክ
ማከሚያ መንገዶች

📍 በአጋጣሚ የሚጠቀሙበት ተንቀሳቃሽ ስልክ ውሃ ውስጥ ሊወድቅ እና ሊበላሽ ይችላል።
📍 አንዳንድ ስልኮች ውሃን በቀላሉ እንዳያሰርጉ ተደርገው የተዘጋጁ ቢሆንም፥ ውሃ ወደ ውስጠኛ ክፍላቸው የሚገባባቸው ሁኔታዎችን ግን ሙሉ በሙሉ የዘጉ አይደሉም።

⚠️በየትኛውም አጋጣሚ የሞባይል ስልክዎ
ውሃ ውስጥ ቢወድቅብዎ

👉 ፈጥኖ ከውሃው ውስጥ ማውጣት፦ ስልኩ በውሃ ውስጥ በቆየ ቁጥር የሚደርስበት ጉዳት እየከፋ ይመጣል።
👉 ስልኩን ፈጥኖ መዝጋት
👉 ከስልኩ መለየት የሚችሉ ለምሳሌ
ባትሪውን እና ሲም ካርዱን ፈጥኖ ማውጣት በሞባይል ስልኩ ውስጥ እርጥበት ስለሚኖር ይህ ካልተወገደ ስልኩ መስራት አይችልምና፥ እርጥበቱን ለማጥፋት፦
👉 በደረቅ እና ነፋስ ሊያገኝ በሚችል ስፍራ
ማስቀመጥ፣
👉 ከ100 እስከ 110 ዲግሪ ፋራናይት ሙቀት እንዲያገኝ በሚችል ስፍራ ማስቀመጥ።
ስልኩ የአፕል ምርት ከሆነ ደግሞ፥
ኩባንያው እስከ 115 ዲግሪ ፋራናይት
ሙቀት ሰጥቶ እርጥበቱን ማስወገድ
እንደሚቻል ይመክራል።
👉የሞባይል ስልኩ እስከሚደርቅ ድረስ
ጥቂት ቀናት ማቆየት፣ ስልኩን በሩዝ
ማከምም ሌላኛው አማራጭ ነው።
ለዚህም ውሃ ውስጥ የወደቀውን የሞባይል ስልክ በጥሬ ሩዝ ውስጥ በመክተት ማቆየት።
ይህ ደግሞ ሩዝ በተፈጥሮው እርጥበት
የመሳብ ባህሪ ስላለው በስልኩ ውስጥ
ያለውን እርጥበት በመምጠጥ
እንዲደርቅ ያደርገዋል።

©️EthioCyber
©️DaniApps
✅ DaniApps On TikTok Soon.
👍2
🖐 Hello Guys

👉 DaniApps Is Now On TikTok

👍 Show Us Your Support By Like & Sharing Our Video
🚨Elon Musk #ትዊተርን ለመግዛት የነበረውን ስምምነት አፈረሰ።

📌ይህም የሆነበትን ምክንያት ሲጠየቅ ትዊተር ያሉትን Spam Users (ፌክ አካውንቶችን) ብዛት በትክክል ባለማሳወቁና በሌሎችም ምክንያቶች ነው ብሏል።

📌ትዊተርም በበኩሉ ይህን ጉዳይ በህግ እንደሚያየው አሳውቋል።

©️Ethio_techs
©️DaniApps
👍1
የኮምፒውተርዎ ፓስዋርድ ከነአካቴው ቢጠፋብዎት ብዙም አይጭነቅዎ መፍትሄ አለው ። ከብዙ መፍትሔዎች ሀለቱን መንገዶች እንመልከት።

የሚያስፈልገው ሶፍትዌር “Spotmou Bootsuite.iso” ወይም "isee password Windows password Recovery pro"

ሲሆኑ ሁለትም ከ internet ላይ ማውረድ ትችላላችሁ ነገር ግን isee password windows password recovery pro የሚለውን ገዝታችሁ የምታገኙት

🔒በ "Spotmou Bootsuit.iso ሶፍትዌር ፓስዎርዳችሁን መክፈት ለምትፈልጉ:-

🔘ቀጣዮቹን 10 ስቴፖች ተከትለው ኮምፒውተርዎን መክፈትና መጠቀም ይችላሉ፡፡

👉1 መጀመረያ ሶፍትዌሩን በፍላሽ ወይም CD ላይ እንጭናላን

👉2 ኮምፒዩተራችንን Turn OFF ማድረግ፡፡

👉3 ፍላሹን /ሲዲውን/ ኮመፒዩተሩን ጋር አገናኝተን Turn ON ማድረግ፣ ከዛF12 (Boot key) (ለHp ላፕቶፕ F9) መንካት፡፡

👉4 “Boot Sequence” የሚል ሲመጣልን “USB” የሚለውን መርጠን “Enter”ን መንካት ከዛ ትዕዛዙን መከተል፡፡

👉5 ኮምፒዩተሩ ከተከፈተ በኃላ “Spotmou Bootsuite 2012 Application” ይከፈትልናል፡፡

👉6 ከአፕልኬሽኑ ላይ “Password and Key Finder” የሚለውን “Menu” እንመርጣለን፡፡

👉7 “Admin Password Resetter” የሚል መንካት፡፡

👉8 “Please select the target widows” ከሚለው ሥር የኮምፒዩተሩን “Window Version (XP/7/8/8.1/10)” ይመርጣሉ፡፡ ቀጥሎ “please select the target user” ከሚለዉ ሥር ደግሞ መክፈት የሚፈልጉትን “User Account” መርጠዉ “Reset” የሚለውን መጫን፣ ከዛ “OK” ከዛ “YES” የሚለውን እንጫናለን፡፡

👉9 መጨረሻ ላይ “Password is reset successfully” የሚል መልዕክት ይደርሶታል፡፡

👉10 ኮምፒዩተሩን ዘግተው ይክፈቱት (Reboot). በትክክል 100% ይሰራል።

©️EthioCyber
©️DaniApps
👍4😱1
⏭ በቀጣይ...
✳️ በ ጉግል ፎቶስ (Google Photos) - የእድሜ ልክ፣ ገደብ የለሽ፣ የፎቶ እና የቪዲዮ ማከማቻ!

🚩 በካሜራዎ ላይ አንዳንድ ወሳኝ የሆኑ አፍታዎችን ለመያዝ ሞክረዉ ዝቅተኛ ማከማቻ ስላልዎት ማንሳት አይችሉም የሚል ችግር አልገጠምዎትም? ጉግል ፎቶስ፣ ለዚህ ችግር ሁነኛ መፍትሄ የሚሆን ያልተገደበ፣ የእድሜ ልክ፣ የፎቶ እና የቪዲዮ ማከማቻ አገልግሎት ይዞ ብቅ ብሏል፡፡

🚩 ጉግል ለፎቶ(እስከ 16 ሜጋፒክስል) እና ቪድዮ(እስከ 1080ፒ ባለ Full HD ድረስ) ያለገደብ ለእድሜ ልክ መጫን እና ማስቀመጥ እንደሚቻል አስታዉቋል። የ ጉግል ፎቶስ መተግበሪያ በ Android, iOS, Mac እና Windows ጨምሮ በሌሎቸም ፕላትፎርሞች ይገኛል።

🚩 ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክዎ ላይ ይህን መተግበሪያ በሚከፍቱበት ጊዜ, ለመጠባበቂያዎቹ (backup) የሚጠቀሙበትን የጉግል መለያዎን (account/email) ይጠይቅዎታል። አንዴ ከተዋቀረ እና ከተስተካከለ በኋላ ስልክዎ ከ WiFi ጋር ሲገናኝ ሁሉንም ፎቶዎች እና ቪድዮዎች መጠባበቂያ ላይ ያስቀምጣል። መጠባበቂያዉ ላይ አስቀምጦ ከጨረሰ በኋላ ከስልክዎት ላይ ማጥፋት እና የስልክዎን ማከማቻ መጠን ማሳደግ ይችላሉ።

በተጨማሪም፦
🚩 ሁሉንም ፎቶዎችዎን እና ቪድዮዎችዎን ለመጠባበቂያ በሰጣችሁት መለያዎ ሲገቡ ከማንኛውም ኮምፒተር፣ ተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ ወይም ብሮውሰር (
photos.google.com በመክፈት) ማግኘት እና ማየት ይችላሉ።

🚩 ፎቶዎትን መከርከም (cut)፣ ማሽከርከር (rotate) ወይም ቀለሙን (color setting) ማስተካከል ካስፈለገዎት መሰረታዊ የፎቶ አርትዖት በመተግበሪያው ውስጥ ራሱ ቀርቧል።

🚩 በኮምፒተርዎ ላይ የ Mac ወይም Windows መተግበሪያን ማውረድ እና በጉግል ፎቶስ ላይ በጠቅላላ አለኝ የሚሏቸውን ፎቶዎች ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡ በሚፈልጓቸው ጊዜም ከጉግል ፎቶስ ድህረ ገጽ (
photos.google.com) ላይ በቀላሉ ሊያገኟቸው ይችላሉ።

🚩 ይህን ከማድረግዎ አስቀድመዉ ግን ለመለያዎ በቀላሉ ሊገመት የማይችል አስተማማኝ የይለፍ ቃል መስጠት እንዳለብዎት እንመክራለን፡፡ እናም ይሄንን መንገድ በመጠቀም ስለስልክዎ ማከማቻ መጠን እና ስልክዎ ሲጠፋ አብረዉ ስለሚጠፉት ማስታወሻ ፎቶዎች መጨነቅ ያቁሙ።


©️ElaTech
©️DaniApps
👍4
⏭ በቀጣይ...
✅ TRUE CALLER እንዴት ነው ሚሰራው ብላችሁ ራሳችሁን ጠይቃችሁ ታቃላችሁ🤔?

🔆TRUE CALLER Application ሀከር፣መረጃ የሚሰርቅ አፕልኬሽን ሆኖ አይደለም

🔆ነገሩ እንዲህ ነው......

🔅ለምሳሌ አንድ ሰው ስልኩ ላይ #Truecaller Application ቢጭን ልክ እንደጫነው ስልኩ ላይ ያሉትን ኮንታክት እስከ ቁጥሩ ወደ True caller ሰርቨር ወዲያውኑ ያስተላልፈዋል ።

እንበልና የወንድሜን👱‍♂ ስም "ኢትዮጵያ" ብዬ ብመዘግበው True caller ለሁሉም ሰው ኢትዮጵያ ብሎ ያሳያል ማለት ነው። ወንድሜ Truecaller Application ላይ ስሙን እስካልቀረ ድረስ ኢትዮጵያ ብሎ ለሁሉም ያሳያል ማለት ነዉ።

✅ስለዚህ Truecaller ሁል ጊዜ ትክክለኛ #ስም ያሳያል ብሎ መናገር አይቻልም።

🔅በተጨማሪም አንድ ሰው አዲሰ ሲም ካርድ ገዝቶ ስልኩ ላይ Truecaller ካልጫነ ስሙን አያሳየንም ማለት ነው። ነገር ግን Truecaller ዳታ ቤዙ ላይ ሰርች አድርጎ ቁጥሩ ካለ ስሙን ያሳየናል።

አሁን ላይ Truecaller እንዴት እንደሚሰራ እንደገባችሁ ተስፋ አደርጋለሁ😊

🔅ለመጨመር ያህል ስልካችሁ Truecaller ላይ ገብቶ ከሆነ እና ለዘላለም እንዲወጣ ከፈለጋችሁ

http://www.truecaller.com/unlisting

በዚህ ሊንክ በመግባት ማስወገድ ትችላላችሁ 😊

©️Ethio_Techs
©️DaniApps
👍1
✅ ፍላሽ ከኮምፒውተራችን 🖥️ ስንነቅል Ctrl Key ነው መጫን ያለብን ይህን ለማወቅ #Task manager ጋር ገብታችሁ performance ሚለውን በመንካት #Ctrl በመንካት ምን እንደሚፈጠር ራሳችሁ ማየት ትችላላችሁ ሁሉም ነገር Process ሚያደርገው ይቆማል🙅‍♂።ያኔ ፍላሻችንን መንቀል እንችላለን።

©️ethio_techs
©️DaniApps
ቤት ውስጥ ሆነን የተለያዩ ሰራዎችን በRemotely የምንሰራባቸው ዌብሳይቶች

1. UpWork
https://www.upwork.com/
2. TopTal
https://www.toptal.com/
3. Fiverr
https://www.fiverr.com/
4. Hired
https://hired.com/
5. PeoplePerHour
https://www.gettyimages.com/

©️adamatech
©️DaniApps
👍1
🖐 Visit DaniAppsStore For The Best Apps & Games

✅Link 👉 @DaniAppsStore
👍2
📍Server(ሰርቨር) ምንድን ነው?

ሰርቨር ማለት በሁለት ይከፈላል እነሱም Hardware Server and Software Server በማለት።

ሰርቨር ማለት ከስሙ እንደምንረዳው አገልጋይ ማለት ሲሆን ለ Client Devices አገልግሎት የሚሰጥ ማለት ነው። በዚህም የሶፍትዌር ሰርቨር የምንላቸው ዌብ ሰርቨር፣ ዶሜን ኔም ሰርቨር፣ ሜይል ሰርቨር በጥቂቱ መጥቀስ እንችላለን። ከዚህ በተጨማሪም ስርቨር የሆኑ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን መጥቀስ ይቻላል ለምሳሌ ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ሰርቨር፣ ኡቡንቱ ጥቂቶች ናቸው።

Hardware Server የምንለው የኮምፒውተር አይነት ሲሆን መረጃን ለመያዝ የሚያገለግልና በክሊያንት ኮምፒውተሮች መረጃውን እንዲደርስና ዋና መረጃው የሚቀመጥበት ማለት ነው። ሰርቨር ኮምፒውተር በጣም በጣም ከፍተኛ የሆነ መረጃን የመያዝ አቅም ያለው፣ መረጃን ፕሮሰስ የማድረግ አቅሙ በጣም ከፍተኛ የሆነ የመስራት አቅሙ በጣም ከፍተኛ የሆነ በዋጋ፣ በአካላዊ ከመደበኛው ኮምፒውተር የሚተልቅ እቃ ነው።

በአንድ ሰርቨር ኮምፒውተር ለብዙ ክሊያንት ኮምፒውቲንግ እቃዎች(ሞባይል፣ ላፕቶፕ፣ ደስክቶፕ፣ ካሜራ፣ ፕሪንተር ወዘተ...) በአንድ ላይ ኔትወርክ በመጠቀም እርስ በራሳቸው እንዲተዋወቁ፣ መረጃ እንዲለዋወጡ፣ መረጃውን እንዲጋሩ ያደርጋል።

Client Devices የምንለው ማንኛውም የኮምፒውቲንግ እቃዎች ከሰርቨሩ ጋር በመግናኘት መረጃዎችን አሳሾችን(Browsers) በመጠቀም መረጃን የምንጠቀምበት እቃዎችን ያካትታል ለምሳሌ አሁን የምንጠቀምበት ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ፣ ሞባይል ስልክ ስልካችን ክሊያንት ዲቫይስ የሆነበት ምክንያት ለምሳሌ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ዩቱቭ ስንጠቀም መረጃውን ከሰርቨር ኮምፒውተር ላይ ኔትወርክ በመጠቀም የሚያመጣልንና ስለምንጠቀም ነው። በአጠቃላይ ሰርቨር ኮምፒውተር ማለት በጣም ብዙ መረጃዎችን አምቆ የያዘ ለተጠቃሚዎች በክሊያንት ኮምፒውተር አማካኝነት በመጠቀም መረጃን ከሰርቨር ኮምፒውተር በማምጣት ለተጠቃሚዎች የሚያደርስ ነው።

ክሊያንትና ሰርቨር ኮምፒውተር የሚገናኙበት ፕሮቶኮል TCP/IP ይባላል። TCP/IP በዋናነት መልእክቶች ከሰርቨር ኮምፒውተር ወደ ክሊያንት ኮምፒውተር እንዲለዋወጡ የሚያደርግ ሲሆን በLAN Local Area Network ወይም በWAN Wide Area Network ክሊያንት ኮምፒውተሮችን ከሰርቨር ኮምፒውተሮች ጋር በማስተሳሰር መረጃን መለዋወጥ ያስችላል።

©️ethio_techs
©️DaniApps
👍1
ሰላም! ዛሬ ስለ computer አፃፃፍ ትንሽ እንማማር ።
ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ እንዴት እንደሚፃፍ ያውቃሉ?ሲጽፉስ ምን ያህል ይፈጥናሉ?
=========================
❖መጀመሪያ Ge'ez 10 Software ያወረዱ እና install ያድርጉት ከዛም አማርኛ መፃፍ ስትፈልጉ power ge'ez status phonetic Unicode Mode (ፎ) ላይ ያድርጉት በ English መፃፍ ስትፈልጉ ደግሞ power ge'ez status English Mode (ኢ) ላይ አድርጉት ከዛም የሚከተሉትን ኣጭር መግላጫ በትክክል ይመልከቱ።
◕ሀ➭H_ሁ➭Hu_ሂ➭Hi_ሃ➭Ha_ሄ➭Hy_ህ➭He_ሆ➭Ho
◕ለ➭L_ሉ➭Lu_ሊ➭Li_ላ➭La_ሌ➭Ly_ል➭Le_ሎ➭Lo
❖ሐ➭Shift+h_ሑ➭Shift+hu_ሒ➭Shift+hi_ሓ➭Shift+ha_ሔ➭Shift+hy_ሕ➭Shift+he_ሖ➭Shift+ho
መ➭M_ሙ➭Mu_ሚ➭Mi_ማ➭Ma_ሜ➭My_ም➭Me_ሞ➭Mo
❖ሠ➭Shift+s_ሡ➭Shift+su_ሢ➭Shift+si_ሣ➭Shift+sa_ሤ
➭Shift+sy_ሥ➭Shift+se_ሦ➭Shift+so
◕ረ➭R_ሩ➭Ru_ሪ➭Ri_ራ➭Ra_ሬ➭Ry_ር➭Re_ሮ➭Ro
◕ሰ➭S_ሱ➭Su_ሲ➭Si_ሳ➭Sa_ሴ➭Sy_ስ➭Se_ሶ➭So
❖ሸ➭Shift+s_ሹ➭Shift+su_ሺ➭Shift+si_ሻ➭Shift+sa_ሼ
➭Shift+sy_ሽ➭Shift+se ሾ➭Shift+so
◕ቀ፡➭Q ቁ፡➭Qu ቂ፡➭Qi ቃ፡➭Qa ቄ፡➭Qy ቅ፡➭Qe ቆ፡➭Qo
◕በ፡➭B ቡ፡➭Bu ቢ፡➭Bi ባ፡➭Ba ቤ፡➭By ብ፡➭Be ቦ፡➭Bo
◕ተ፡➭T ቱ፡➭Tu ቲ፡➭Ti ታ፡➭Ta ቴ፡➭Ty ት፡➭Te ቶ፡➭To
◕ ቸ፡➭C ቹ፡➭Cu ቺ፡➭Ci ቻ፡➭Ca ቼ፡➭Cy ች፡➭Ce ቾ፡➭Co
◕ነ፡➭N ኑ፡➭Nu ኒ፡➭Ni ና፡➭Na ኔ፡➭Ny ን፡➭Ne ኖ፡➭No
❏ኘ፡➭Shift +n ኙ፡➭Shift +nu ኚ➭Shift+ni ኛ፡➭Shift +na ኜ፡➭Shift +ny ኝ፡➭Shift + ne ኞ፡➭Shift +no
◕ከ፡➭Ka ኩ፡➭Ku ኪ፡➭Ki ካ፡➭Ka ኬ፡➭Ky ክ፡➭Ke ኮ፡➭Ko
❖ ኸ ☛capslock + Shift + h
ኹ ☛capslock + Shift + hu
ኺ ☛capslock + Shift + hi
ኻ ☛Capslock + Shift + ha
ኼ ☛Capslock + Shift + hy
ኽ ☛Capslock + Shift + he
ኾ ☛Capslock + Shift + ho
❏ኀ፡➭ Capslock + H ኁ፡➭ Capslock + HU ኂ፡➭Capslock + HI ኃ፡➭Capslock + HA ኄ፡➭Capslock + HY ኅ፡➭Capslock + HE ኆ፡➭Capslock + HO
❏አ፡➭Capslock X ኡ፡➭Xu ኢ፡➭Xi ኣ፡➭Xa ኤ፡➭Xy እ፡➭Xe ኦ፡➭XoDe
❖ዐ፡➭Shift +x ዑ፡➭Shift +xu ዒ➭Shift +xi ዓ፡➭Shift +xa ዔ➭Shift +xy ዕ፡➭Shift +xe ዖ➭Shift +xo
✪ወ፡➭W ዉ፡➭Wu ዊ፡➭Wi ዋ፡➭Wa ዌ፡➭Wy ው፡➭We ዎ፡➭wo
✪ዘ፡➭Z ዙ፡➭Zu ዚ፡➭Zi ዛ፡➭Za ዜ፡➭Zy ዝ፡➭Ze ዞ፡➭Zo
❏ዠ፡➭Shift + Z ዡ፡➭Shift + Zu ዢ፡➭Shift + Zi ዣ፡➭Shift +Zaዤ፡➭Shift + Zy ዥ፡➭Shift +Ze ዦ፡➭Shift + Zo
✪ፈ፡➭F ፉ➭Fu ፊ፡➭Fi ፋ፡➭Fa ፌ፡➭Fy ፍ፡➭Fe ፎ፡➭Fo
✪ ፐ፡➭P ፑ፡➭Pu ፒ፡➭Pi ፓ፡➭Pa ፔ፡➭Py ፕ፡➭Pe ፖ፡➭Po
✪ገ፡➭G ጉ፡➭Gu ጊ፡➭Gi ጋ፡➭Ga ጌ፡➭Gy ግ፡➭Ge ጎ፡➭Go
✪ደ፡➭D ዱ፡➭Du ዲ፡➭Di ዳ፡➭Da ዴ፡➭Dy ድ፡➭ዶ፡Do
❏ጠ፡➭Shift + t ጡ፡➭Shift + tu ጢ፡➭Shift + ti ጣ፡➭Shift+ta ጤ፡➭Shift + ty ጥ፡➭Shift + te ጦ፡➭Shift + to
❏ጨ፡➭Shift +c ጩ፡➭Shift +cu ጪ፡➭Shift +ci ጫ፡➭Shift+caጬ፡➭Shift +cy ጭ፡➭Shift +ce ጮ: ➭Shift +co
❏ጸ፡➭Capslock + t ጹ፡➭Capslock + tu ጺ፡➭Capslock + ti ጻ፡➭Capslock + ta ጼ፡➭Capslock + ty ጽ፡➭Capslock + t ጾ፡➭Capslock + to
❖ ፀ➭☞Capslock+Shift+t
ፁ➭☞Capslock+Shift+tu
ፂ➭☞Capslock + Shift + ti
ፃ➭☞Capslock + Shift + t
ፄ➭☞Capslock + Shift + ty
ፅ➭☞Capslock + Shift + te
ፆ➭☞Capslock + Shift + to
✪ጀ፡➭J ጁ፡➭Gu ጂ፡➭Ji ጃ፡➭Ga ጄ፡➭Gy ጅ፡➭Ge ጆ፡➭Jo
✪ቨ፡➭V ቩ፡➭Vu ቪ፡➭Vi ቫ፡➭Va ቬ፡➭Vy ቭ፡➭Ve ቮ፡➭Vo
ቋ➭Capslock+qwa ቧ➭Capslock+bwa
ቷ➭Capslock+twa
ኟ➭Capslock +Shift+nwa
ቿ➭Capslock+cwa
ሟ➭Capslock+mwa
ቷ➭Capslock+twa
ጓ➭Capslock gwa
ፏ➭Capslock+fwa
ሯ➭Capslock +rwa
ዷ➭Capslock+dwa
ቯ➭Capslock+vwa
ኋ➭Capslock+hwa
ዟ➭Capslock+zwa
ዧ➭Capslock+Shif+zwa
ኗ➭Capslock+nwa
ሏ➭Capslock+lwa
ኳ➭Capslock+kwa
ሷ➭Capslock+swa
ጇ➭Capslock+jwa
ጧ➭Capslock+twa

©️EthioCyber
©️DaniApps
👍2