DaniApps™
1.01K subscribers
611 photos
34 videos
537 files
219 links
✅The Best Android Apps And Games Are Here.📱
✅For Any Questions ➡️ @DaniappsBot Or Group ➡️ @daniappsgroup
✅ Apps Or Games ➡️ @daniappsstore
✅Ask Any Apps ➡️ @Daniapps2bot
✅ Website https://daniapps.epizy.com/

https://g.page/r/CYhVwdbaF335EA0/review
Download Telegram
🌐 የGoogle አስገራሚ እውነታዎች፡

✅ Googleን ከቀኝ ወደ ግራ ገልብጠን ብንፅፍ elgooG ይሆናል፡፡
elgooG.im ብለን የገፀ ድር አድራሻ ላይ ብንፅፍ የተገለበጠ የጎግል መፈለጊያን ማየት እንችላለን፡፡

✅ Zerg rush ብለን ጎግል ላይ ሰርች ብናደርግ አስገራሚ ነገር እናያለን፡፡

✅ አሁን የሚጠራበት ጎግል የሚለው ስያሜ በስህተት የቀረበ መሆኑን ያውቃሉ ካልሆነ ይህ መጠሪያው ትክክለኛው ሳይሆን በአጋጣሚ የመጣ መጠሪያው ነው። ይህ የሆነው መስራቾቹ Googol ብለው ለመጻፍ በማሰብ በስህተት Google ብለው ከሰየሙት በኋላ ነው፤ ይህ መጠሪያ ደግሞ በሂሳብ ከኋላው 1 መቶ ዜሮዎችን የሚያስከትል 1 ቁጥርን ይወክላል።

✅ የጎግል ሰራተኞች Googlers የሚል መጠሪያ ሲኖራቸው አዲስ ተቀጣሪዎች ደግሞ Nooglers ይባላሉ።

✅ የጎግል የመጀመሪያው ትክክለኛ መጠሪያ Backrub ይባል ነበር፤ ይህ የሆነው ደግሞ በማፈላለጊያ ገጹ ላይ ለሚፈለጉ አድራሻዎች በሚሰጠው አድራሻ እና ደረጃ አማካኝነት ነው።

✅ ወደ ገጹ ገብተው ምናልባት “ራሴን ማጥፋት እፈልጋለሁ" I want to commit suicide የሚል ቃልን ቢጽፉ ይህን እንዳያደርጉ እና እርዳታ
የሚያገኙባቸውን በሚገኙበት አካባቢ እርዳታን እንዲያገኙ የሚያስችሉ ቁጥሮችንና መርጃ መንገዶች ያቀርብልዎታል።

✅ ዘና ማለት ካሰኘዎት ደግሞ በጎግል ምስል መፈለጊያ ላይ ገብተው Atari breakout ብለው ይፈልጉና በሚመጣልዎት ጨዋታ ዘና ማለት ይችላሉ።

✅ በመፈለጊያ አድራሻው ላይ የፈለጉትን ያክል ቁጥር እስከቻሉት ድረስ ይጻፉ ጎግል በፊደል እያስደገፈ ያቀርብልዎታል።

✅ ጎግል ለፈለጉት ነገር ትክክለኝነት ማረጋገጫ 28 የተለያዩ ማረጋገጫ እና አምስት ማስጠንቀቂያ መንገዶችን ይከተላል።

✅ አይበለውና አንድ የድርጅቱ ሰራተኛ ከዚህ አለም በሞት ቢለይ የሟቹ የፍቅር ወይም የትዳር አጋር፥ በየወሩ ከደሞዙ 50 በመቶውን ለ10 አመት ያክል መውሰድ ይችላል። ምናልባት ሟቹ ልጅ ካለው ደግሞ ልጁ 19 አመት እስከሚሞላው/ላት ድረስ በየወሩ 1 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ይከፈላቸዋል።

✅ ከሚኖሩበት ምድር ወደ ላይ አልያም ወደ ላይ ከፍ ብለው ሰማየ ሰማያት ላይ ምን እንዳለ ማወቅ ከፈለጉ ደግሞ
www.google.com/sky . ከፍተው ይመልከቱ እና ጨረቃ፣ ከዋክብት አልያም የከዋክብት ስብስቦችን ይመልከቱ።

✅ Google Maps ደግሞ የሚኖሩባትን ምድር የተለየ ገጽታ ማየት ያስችልዎታል።

✅ ማወቅ አይከፋምና ወደ Google Mars ገብተው ስለ ቀይዋ ፕላኔት የፈለጉትን መረጃ ከየትኛውም ቦታ በተሻለ መልኩ ማግኘትም ይችላሉ።

✅ እንዴት ነው የሚከፈላቸው የሚለው እንዳለ ሆኖ ግን፥ ይህ ኩባንያ ጎግል ማፕን ተጠቅሞ የበረሃን እይታ ለደንበኞቹ ለማድረስ ለዚህ ስራ ብቻ የሚያገለግል ግመልም ቀጥሯል። እናም ለተጠቃሚዎቹ እርካታ ጎግልም የበረሃዋን ግመል ቀጥሮ ያሰራል፤ እርሷም ደሞዝ ተከፋይ የጎግል ሰራተኛ ናት።

©️Ethio Cyber
©️Dani_Apps
👍2
✅ ዳታዎቻችንን የክላውድ ማከማቻ አገልግሎት (cloud storage service) ላይ የማስቀመጥ በርካታ ጥቅም!

🌐 የስልክ፣ የላፕቶፕ፣ የታብሌት እንዲሁም የሌሎች ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መሰረቅ እና መጥፋት በማህበራዊ ሚዲያ በየዕለቱ ከምንሰማቸው ጉዳዮች መካከል ይገኙበታል። ብዙ ግዜ እቃዎቹን የተሰረቁ ግለሰቦች የስልኩ ወይንም የላፕቶፑ መጥፋት ሳይሆን በውስጡ የተከማቹ ዳታዎች በሌላ ሰው ዕጅ መግባታቸው በተለይ እንደሚያሳስባቸውም ሲናገሩ ይደመጣል።

🌐 በእርግጥ ለብዙ ዓመታት ያከማቸናቸው ፎቶዎች፣ የስልክ አድራሻዎች፣ ጽሁፎች፣ እና ሌሎች ዳታዎች ከዕጅ ሲወጡ በግልና በስራ ህይዎታችን ላይ ብዙ ነገር ያመሰቃቅላሉ።

🌐 በስርቆትም ይሁን በመጥፋት አልያም በብልሽት ምክንያት በስልክዎት ወይንም በላፕቶፕዎ ያከማቿቸው ዳታዎች ከእጅዎ ወጥተው እንዳይቀሩ የክላውድ ማከማቻ አገልግሎት (cloud storage service) መጠቀም ይመከራል።

🌐 የክላውድ አገልግሎት ፎቶዎች፣ የስልክ አድራሻዎች፣ ፋይሎችና ሌሎች ዳታዎችን በማከማቸት በስልክዎ ወይንም በላፕቶፕዎ እንዳይቀመጡ ያስችልዎታል። ጎግል፣ አፕል፣ ድሮፕቦክስ፣ ማይክሮሶፍት እና ሌሎች ድርጅቶች የክላውድ አገልግሎት የሚያቀርቡ ሲሆን ዋን ድራይቭ (One Drive)፣ ጎግል ድራይቭ (Google Drive)፣ ድሮፕቦክስ (Dropbox) እና አይክላዎድ (iCloud) ከተለመዱ መተግበሪያዎች መካከል ይጠቀሳሉ።

🌐 ብዙዎቹ የክላውድ አከማች መተግበሪያዎች አዲስ ስልክ ወይንም ላፕቶፕ ሲገዙ አብረው ተጭነው የሚመጡ ሲሆን ከሌሉ በቀላሉ አውርደው መጫን ይችላሉ። ለምሳሌ አንድሮይድ ስልክ ካለዎት የጎግል ድራይቭ መተግበሪያን በቀላሉ በመጠቀም ፋይልዎችዎን ማከማቸት የሚችሉ ሲሆን የሚያስፈልግዎ የጂሜይል አካውንት መክፈት ብቻ ይሆናል። ጎግል ድራይቭ 15 ጂጋ ባይት ነጻ ማከማቻ ይሰጥዎታል።

🌐 ፋይልዎችዎን በክላውድ ማከማቸት ከጀመሩ በኃላ ስልክዎ አልያም ላፕቶፕዎ ቢሰረቅ፣ ቢጠፋ አልያም ቢበላሽ ሌላ ስልክ ወይንም ላፕቶፕ በመጠቀም እንደገና ማግኘት ይችላሉ። የክላውድ ማከማቻ አገልግሎት የፋይሎችን ደህንነት ከመጠበቅ በተጨማሪ በስልክዎና በላፕቶፕዎ የሚያከማቿቸውን ዳታዎች እንዲቀንሱ ያስችልዎታል።

🌐 ከፕራይቬሲና ከሌሎች የዳታ ደህንነት ጉዳዮች አንጻር ፋይሎችን በክላውድ መተግበሪያዎች ማስቀመጥን በተመለከት የሚነሱ ጥያቄዎች ያሉ ሲሆን ብዙዎቹ አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች ባለስ ሶስት ደርዝ ስወራን (three levels of encryption) በመጠቀም የዳታዎችን ደህንነት ይጠብቃሉ።

🌐 በክላውድ ማከማቻ የሚቀመጡ ፋይልዎችዎን ደህንነት ይበልጥ ለመጠበቅ ጠንካራ የማለፊያ ቃል (password) መጠቀም፣ የማለፊያ ቃል በየጊዜ መቀየር እና ለተለያዩ አካውንቶች ልዩ የሆኑ የማለፊያ ቃሎችን መጠቀም ይመከራል። የይለፍ ቃል የሚያስተናብሩ (password manager) መገልገያዎች እንዲሁም ባለሁለት ደርዝ ማረጋገጫ (two-step verification) መጠቀምም ጥሩ ነው። አጠራጣሪ ኢሜሎችን አለመክፈትም እንዲሁ ይመከራል።

ŠEla tech
©️Ethio Cyber
©️Dani_Apps
👍1
⚠️ ከግማሽ በላይ አሜሪካውያን ራሳቸውን ከኢንተርኔት ማጥፋት ይፈልጋሉ
55 በመቶ አሜሪካውያን ቢችሉ ራሳቸውን ከኢንተርኔት ማጥፋት ይፈልጋሉ፡፡

✅ NordVPN በሰራው አዲስ ጥናት መሰረት 18 በመቶ አሜሪካውያን ደግሞ ጭራሽ ኢንተርኔት ባይኖር ተመኝተዋል፡፡

✅ 60 በመቶው የግል መረጃዎችን ማስወገድ ይፈለጋሉ፣ ሩብ ያህሉ ደግሞ የሚያፍሩባቸውን ፎቶ፣ ቪዲዮና ሌሎች ሁነቶች ከኢንተርኔት ማስወገድ ይፈልጋሉ፡

✅ 3 በመቶዎቹ ደግሞ ኦንላይን ላለመታወቅ ሲሉ 1 ሺህ ዶላር ሊከፍሉ እንደሚችሉ ተገልጿል።

©️Ethio Cyber
©️Dani_Apps
🌐 ሳፋሪኮም ኩባንያ የቴሌኮም አገልግሎት የሚጀምርበት ቀነ ገደብ ተራዘመ !

✅ የኢትዮጵያ ኮምንኬሽን ባለሥልጣን ሳፋሪኮም ኩባንያ የቴሌኮም አገልግሎት የሚጀምርበትን ቀነ ገደብ ከሚያዚያ ወደ ሐምሌ እንዳራዘመ ካፒታል የኢትዮ ቴሌኮምን ምንጮች ጠቅሶ ዘግቧል።

✅ ቀነ ገደቡ የተራዘመው፣ ኩባንያው እና ኢትዮ ቴሌኮም የቴሌኮም መሠረተ ልማቶችን በጋራ ለመጠቀም የሚያስችላቸውን ስምምነት ገና በይፋ ባለመፈራረማቸው እና ባንዳንድ ዓለማቀፋዊ ሁኔታዎች የተነሳ እንደሆነ ዘገባው ገልጧል።

✅ ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላም፣ ወደ ተግባር ለመግባት ሦስት ወይም አራት ወር እንደሚፈጅ የኢትዮ ቴሌኮም ምንጮች ተናግረዋል።

©️bbc_amharic1
©️DaniApps
💻 ለስራዎ ምቹ የሆነ ላፕቶፕ እንዴት ይገዛሉ?

✅ በአሁኑ ወቅት ላፕቶፕ ለመግዛት ሲታሰብ ብዙ አማራጮች አሉ፡፡ ያሉት ላፕቶፖች በሙሉ የራሳቸው የሆነ ጥሩና መጥፎ መገለጫ ቢኖራቸውም ላፕቶፕ ሲገዙ ቢንስ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መገለጫዎችመመልከት በጣም አስፈላጊ ነው

1ኛ. የስክሪን ስፋት እና የላፕቶፕ ክብደት (Screen size and weight)

✅የላፕቶፕ ስክሪን በአብዛኛው ከ9-17 ኢንች (ከ23-43 ሳንቲ ሜትር) ድረስ ይሆናል፡፡ የስክሪን ስፋቱ እየጨመረ በሄደ ቁጥር የላፕቶፑም ክብደት ይጨምራል፡፡ እዚህ ላይ ላፕቶፑን ለምን እንደሚፈልጉት ማሰብ አስፈላጊ ነው፡፡ የላፕቶፑ መጠን እየጨመረ በሔደ ቁጥር ለማንቀሳቀስ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ከባድ ላፕቶፖችን አዘውትሮ መሸከም በሰውነታችን ቅርጽ ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ ልዩ ልዩ ጥናቶች አመልክተዋል፡፡ ስለዚህ ስራችን ብዙ እንቅስቃሴ ያለበት ከሆነ ክብደታቸው አነስተኛ የሆኑና በቀላሉ ልናንቀሳቅሳቸው የምንችላቸውን መርጦ መግዛት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሰፊ ስክሪን ያላቸው ላፕቶፖች የባትሪ ቆይታ ጊዜያቸው አነስተኛ ነው፡፡

2ኛ. CPU (የላፕቶፑ አእምሮ)

✅ በአለማችን ሁለት የታወቁ የCPU አምራች ኩባንያዎች አሉ፡፡ እነዚህም Intel እና AMD ናቸው፡፡ Intel ገበያውን የተለያዩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በጨመር ሲቆጣጠረው፤ AMD ደግሞ ተወዳዳሪ የሆኑ ሞዴሎችን በአነስተኛ ዋጋ ያቀርባል፡፡ እዚህም ላይ ኮምፒውተሩን ለምን ስራ እንደሚፈልጉት ማሰብ አስፈላጊ ነው፡፡ ለምሳሌ የግራፊክስ ባለሙያ ከሆኑ ኤዲተር ከሆኑ ጥንድ ኮር (Dual-core CPU) ቢጠቀሙ የተሸለ የመፈጸም ብቃት አለው፡፡ ከዚህ ውጭ ለመሰረታዊ የኮምፒውተር አገልግሎት የሚፈልጉት ከሆነ ነጠላ ኮር (single-core CPU) ያለውን ላፕቶፕ ቢገዙ ከዋጋም አንጻር ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

3ኛ. RAM

✅ ኮምፒውተርን ለመደበኛ አገልግሎት ማለትም ለቤትከሆነ ውስጥ እና ለቢሮ ወይም ለጉዞ የሚጠቀሙት ከሆነ ከ 2-4 GB ያላቸውን መጦ መግዛት የተሻለ ነው፡፡ የግራፊክ አርቲስት ከሆኑ ወይም ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ቪዲዮዎች የሚያዘጋጁ ከ4 GB እስከ 8 GB RAM ያላቸውን ላፕቶፖች መርጦ መግዛት ውጤታማ ያደርጋል፡፡

✅ ተማሪዎች የቤት ስራቸውን ለመስራት፣ ለኢሜይል ወይም የጠለያዩ ድረ ገፆችን መጎብኘት የመሳሰሉ ተግባራትን ለመከወን ግን 1 GB RAM ያላቸውን ላፕቶፖች መግዛትም ይቻላል።

©️Ethio Cyber
©️Dani_Apps
👍1
✅ ሶስት ዓይነት ማልዌሮችን በተመለከተ መረጃ ላቀብላችሁ፦

1ኛ:- ቫይስ(Virus)

⚠️ ቫይስ(Virus) ማለት ከማልዌር ዓይነቶች አንዱ ሲሆን ኮምፒውተር ወይም ሞባይል ስልክ ላይ ያሉ ፋይሎች ውስጥ እራሱን አመመሳስሎና ተሸሽጎ ይቀመጥና ፋይሎችን ስትከፍቱ በኮምፒውተሩ ወይም በሞባይሉ ሲስተም ይሰራጫል። ቫይስ(Virus) እራሱን በራሱ ማብዛት(Replicate ማድረግ ) ይችላል።
የተሸሸገበበትን ፋይል እንደ ትራንስፖርት ይጠቀምበታል። በሌላ አነጋገር ለምሳሌ ቫይረሱ የሙዚቃ ፣ፎቶ ወይም ሙዚቃ ፋይሎች ውስጥ ከተሸሸገ ሰዎች በፍላሽ ዲስክ ወይም በሌላ እነዚህን ፋይሎች ሲለዋወጡ ቫይረሱ ከአንዱ ኮምፒውተር ወደ ሌላው ኮምፒውተር በቀላሉ ይዛመታል ማለት ነዉ ።

⚠️ምን_ዓይነት_ጥቃት_ይፈፅማል?

✅ ቫይስ(Virus) ፋይሎችን የማጥፋትና የፋይሎችን ባህርይ ይቀይራል።በ#ቫይስ(Virus) የተጠቃ ኮምፒውተር ወይም ሞባይል ስልክ ጥሩ በሚባል አንታይ ቫይረስ ብናፀዳውም እንኳ ቫይረሱ ከነጭራሹ ማጥፋት አስቸጋሪ ነው።

2ኛ:- ዎርም(Worm)

✅ ሌላኛው የማልዌር ዓይነት ነው። ዎርም(Worm) ከኤሜል ወይም ቴክስት ጋር እራሱን አጣብቆ ይመጣል(as Attachement)።ከኢሜሉ ጋር ተጣብቆ የመጣውን Attachment ስትከፍቱት ዎርሙ ኮምፒውተራችን ላይ Installed ይሆነናል ወይም ይጫናል።

⚠️ምን_ዓይነት_ጥቃት_ይፈፅማል?

✅ ዎርም(Worm) የኮምፒውተራችን ሃርድ ዲስክ ትርፍ ቦታ(space) በማጨናነቅ ቀውስ ይፈጥራል።በተጨማሪም ዎርም(Worm) ፋይል ይሰርቃል።ከጀርባ ሆኖ ለሀከሮች በር በመክፈት ሀከሮች የፈለጉትን ማለትም ፋይል_መስረቅ ወይም ፋይል_ማጥፋት ወይም ፋይል_መቀየር የመሳሰሉ ጎጂ ድርጊቶች እንዲፈፅሙ ይረዳል።

3ኛ:- ትሮጃን_ሆርስ(Trojan horse)

✅ ማለት ሌላው ማልዌር ሲሆን ይህ ማልዌር እራሱን እንደጠቃሚ ፕሮግራም በማስተዋወቅ ለምሳሌ የዲስክ ስፔስ አፀዳለሁ ወይም የኮምፒውተር ፍጥነት እጨምራለሁ ብሎ በማስተዋወቅ ሰዎች ፕሮግራሞቹን ዳውንሎድ እንዲያደርጉ ያማልላል።
ሰዎች እነዚህን ፕሮግራሞች ሲጭኑ ትሮጃኑ ሰተት ብሎ ወደ ሲስተማችን በመግባት ይጫናል።

✅ ትሮጃኑ የኮምፒውተሩ ሲስተም ውስጥ ከተጫነ በኋላ የጀርባ በር ለሀከሮች ይከፍታል።

⚠️ምን_ዓይነት_ጥቃት_ይፈፅማል?

✅ ሀከሮች በተከፈተላቸው በር (Back door ) ሰተት ብለው ወደ ኮምፒውተሩ ሲስተም በመግባት:-

Ⓐ ዳታ ያጠፋሉ(Deleting Data)
Ⓑ ዳታ ብሎክ ያደርጋሉ
Ⓒ ዳታ ኮፒ ያደርጋሉ
Ⓓ ዳታ ይለውጣሉ።

©️Ethio Cyber
©️Dani_Apps
👍1
Vanger pro🔥🔥🔥
VAGNER PRO.apk
28.7 MB
👌 DSTV FOR FREE 😍

CRACKED NO ADS
ብዙ Channel አለው
connection ግን ትንሽ ፈጠን ያለ ይፈልጋል

✅ Login ላይ Code ሲጠይቅ ዝምብላቹ login ንኩት Crack ስለሆነ

©️AdamaTech
©️DaniApps
📱ስማርት ፎን ምንድነው ?

✅ ስማርት ፎን ማለት ተንቀሳቃሽ ሞባይል ስልክ ሆኖ እንደምናውቃቸው ትንንሽ ስልኮች ከመደወል እና አጭር የጽሁፍ መልእክት ከመላላካ ባለፈ እንደ ኮምፒውተር የተለያዩ ግልጋሎቶችን የሚሰጡ ተንቀሳቃሽ የስልክ ቀፈፎዎች ናቸው፡፡ ለስማርት ፎን ቀጥታ ወይንም ስታንዳርድ የሆነ ትረጉም አልተሰጣቸውም ግን በተለያዩ መመዘኛዎች መለየት ይቻላል መመዘኛዎች 

📍 የራሳቸው የሆነ የተደራጀ ኦፐሬቲንግ ሲስተም አላቸው በኦፐሬቲንግ ሲስተማቸው ላይ በመመርኮዝም የተለያዩ አፕሊኮሽኖችን ለቀፎዎቹ መገንባትም መጠቀመ ይቻላል•
ምሳሌ ፡ እንደ ኮመፒውተር ጽሁፍ የሚዘጋጅ አፕሊኬሽ በመጫነን የተለያዩ ጽሁፎችን እናዘጋጅባቸዋለን ፤ፎተዎችን እናቀናብርባቸዋለን ከፍተኛ የምስል ጥራት ያላቸውን ጨዋታዎች እንጫወትባቸዋለን 

📍ስማርት ፎኖች እንደ ኮምፒውተር የ Q W E R T Y ኪይቦርድ ነው ያላቸው ይህም ማለት የቀፎዎቹ ኪይቦርድ ከ ኮምውተራችን ኪይቦርድ ቁጥር መተየቢያው ውጪ ተመሳሳይ ነው ማት ነው

📍  ስማርት ፎኖች በተለያያ መልኩ ከ ቀላል የመረጃ ፍለጋ ጀምሮ አስከ ኢነተርኔት ቤስድ አፕሊከሽኖች ድረስ የመረጃ መረብን መጠቀም ያስችሉናል

📍 ስማርት ፎኖች ዘመናዊ የሆኑ የ 3ኛ (3G) እና 4ኛ (4G) ትውልድ የሚባሉትን የኔትዎርክ መሰረተ ልማት እንድንጠቀም ያስችሉናል

📍 በተጨማሪም የተሻለ ጥራት ያለው ካሜራ አላቻው 

📍 ዋየርለስ አገልግሎቶችን ማስተናገድ ይችላሉ፤ 

📍 á‹¨áŠŤáˆ­á‰ł እና አቅታጫ አገልሎት ይሰጣሉ 

📍ዳታ የማከማቸት አቅማቸው እና ተጨማሪ የዳታ ማከማቻ ካርዶችን የመቀበል አቅማቸው የላቀ ነው 

📍አብዛኛውን ጊዜ ሰፊ ስክሪን ይኖራቸዋል እና ተች ስክሪን ናቸው

©️Ethio Cyber
©️Dani_Apps
📶 ዋይ ፋይ ምንድነው? እንዴትስ ይሰራል?

✅ ይህ ቃል ለአብዛኛው ተጠቃሚ፤ ሞያተኛውንም ሲጨምር አጋጥሞናል ከ ኢንተርኔት ጋር እየተለዋወጠ ሲገባ እናየዋለን፡፡ በሞያችንም ለሰዎች ለማስረዳት ስንሞክር አለመግባባት ይከሰታሉ፡፡ እርግጥ ነው ዋይ ፋይ ኢንተርኔት ለማገኘት ይራዳል ነገርግን በራሱ ኢንተርኔት አይደለም፡፡
✅ምንም እንኳን በአይናችን ባናያቸውም የራዲዮ ሞገዶች ሁሌም መረጃዎችን ተሸክመው በዙሪያችን እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ከእነዚህ የሬዲዮ ሞገዶች ጥቂቶቹ የWi-Fi ሲግናሎች ናቸው፡፡ Wi-Fi በሚለው ስም ውስጥ የሚገኙ ሆሄያት እንደ አህጽሮተ ቃል የትኛውንም ነገር የማይወክሉ ሲሆን በመነሻነት አንድ ከፍተኛ መጠን ያለውን መረጃ በአጭር ርቀት ውስጥ የራዲዮ ሞገዶችን በመጠቀም ማስተላለፍ የሚችልን ቁስ በቀላሉ ማስታዎስ እንዲቻል ተብሎ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡

✅ እንደ ብሮድካስት ራዲዮና ተንቀሳቃሽ ስልክ ሲግናሎች ሁሉ የWi-Fi ሲግናልም በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ አካባቢ የተገኘ ሳይንሳዊ ፈጠራ ነው፡፡ ኤሌክትሮኖች በሽቦ ውስጥ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ በየተወሰኑ ጊዜያት አቅጣጫዎችን ይቀይራሉ፡፡ በሌላ ሽቦ ላይ የሚገኙ ኤሌክትሮኖች ከእነዚህ አቅጣጫ ከሚቀያይሩ ኤልክትሮኖች ጋር ቴሌፋቲክ በሆነ መንገድ የተያያዙ ስለሆኑ መንቀሳቀስ ይጀምራሉ፡፡ ይህ ግኝት መጀመሪያ የታወቀው በ1887 በሄንሪክ ሄርትዝ ነው፡፡

✅ የሚታይ ብርሃንን የያዙ ኤሌክትሮመግነጢሳዊ ህብሮች ከራዲዮ ሞገዶች የተሻለ ከፍተኛ ፍሪኩየንሲን ያመነጫሉ፡፡ የተለመዱት የኤ ኤም ወይም ኤፍ ኤም ራዲዮ እና የቴሌቪዥን ስርጭቶች መረጃን በተከታታይ ሲግናሎች ወይም በአናሎግ ያደርሳሉ፡፡ Wi-Fi መረጃን የሚያሰራጨው እንደ ያልተያያዙ ዋጋዎች የባይናሪ መረጃ ዜሮዎችና አንዶች በዲጂታል መንገድ ነው፡፡ ይህም የሞባይል ቁሶች ከፍተኛ መጠን ያላቸውን እንደ ቪዲዮ፣ ምስል፣ ድምጽ እና የጽሁፍ መልዕክቶችን በቀላሉ እንዲልኩ ያስችላቸዋል፡፡

✅ አንድን መረጃ በዋይ ፋይ ኦንላይን ላይ ስንፈልግ የዋይ ፋይ ቁሳችን የሬዲዮ ሞገዶችን አልፎ ከዋይ ፋዩ መገኛ ነጥብ ጋር ይናበባል፡፡ ይህም በኢንተርኔት ራውተራችን አንቴና አማካኝነት ነው፡፡ ከዚያም በአካባቢው ባሉ የኢንተርኔት ገመዶች አማካኝነት ጥያቄያችን ወደምንፈልገው የመረጃ ቋት ይተላለፋል፡፡ ሂደቱ ሲያልቅም በመጣበት መንገድ ተመልሶ ይመጣል፡፡

✅ በተለያዩ ኩባንዎች የተሰሩ የዋይ ፋይ ቁሶች 802.11 የተሰኘ ተመሳሳይ ስታንዳርድን ስለሚከተሉ እርስ በርሳቸው መናበብ ይችላሉ፡፡ ይህ ስታንዳርድ ዜሮዎችና አንዶች ራዲዮ ሞገድን በመጠቀም እንዴት እንደተወከሉና ቁሶቹ ራሳቸውን እንዴት እንደሚለዩ የሚወስን ነው፡፡ እነዲሁም ደግሞ ኬሪየር ሴንስ መልቲፕል አክሰስ (CSMA) የተሰኘ እንዴትና መቼ መግባባት እንዳለባቸው የሚወስን አሊጎሪዝም ይከተላሉ፡፡ ይህ አሊጎሪዝም የዋይ ፋይ ቁሶችን ስማርት ያደርጋቸዋል፡፡

✅ አንዳንድ ጊዜ ከዋይ ፋይ ጋር በተያያዘ ችግሮች ይገጥሙናል፡፡ ወይም ከዋይ ፋዩ መገኛ ነጥብ ጋር ለመገናኘት እንቸገራለን ይህም የሚሆነው የራዲዮ ሲግናሎች በርቀት ምክንያ ሲደክሙ ነው፡፡ ለምሳሌ ወፍራም ግድግዳ፣ የብረት መከለያዎች አንዲሁም አኳሪየም የራዲዮ ሞገዶችን ሊያደክማቸው ይችላል፡፡

✅ ዋይ ፋይ ይህ ቃል ለአብዛኛው ተጠቃሚ፤ ሞያተኛውንም ሲጨምር አጋጥሞናል ከ
ኢንተርኔት ጋር እየተለዋወጠ ሲገባ እናየዋለን፡፡ በሞያችንም ለሰዎች ለማስረዳት ስንሞክር አለመግባባት ይከሰታሉ፡፡ እርግጥ ነው ዋይ ፋይ ኢንተርኔት ለማገኘት ይራዳል ነገርግን በራሱ ኢንተርኔት አይደለም፡፡

✅ ዋይ ፋይ ገመድ አልባ የኮምፒውተር ግንኙነት መፍጠሪያ ዘዴ ሲሆን ኢንተርኔትን ጨምሮ የተለያዩ መረጃዎችን፣ ፋይሎችን፣ እንዲሁም እቃዎችን (ፕሪንተር፣ እስካነር) በጋራ እንድንጠቀም ይረዳናል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የባለገመድ ግንኙነት (cable Network) ምትክ መሆኑን ያሳያል፡፡

©️Ethio Cyber
©️Dani_Apps
👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መርከብ በሰማይ

ኤለን መስክ በህዋ ምርምር ተቋሙ በኩል ይፋ ያደረገው ሮኬት ወደ ህዋ ለመጓጓዝ በምድርም ላይ የትኛውም ስፍራ እስከ አምስት መቶ ሺህ ቶን እቃ በደቂቃዎች ለማጓጓዝ የሚያስችል ነው፡፡

©️EIIA
©️DaniApps
⚠️📱 በሞባይል ስልክዎ በሚላክልዎ አጭር የፅሁፍ መልዕክት መረጃ
ከስልክዎ መመዝበር እንደሚቻል ያዉቃሉ?


📍በሞባይል ስልኮቻችን ወይም በተለያዩ ኤሌክትሮኒክ መገልገያዎቻችን ላይ በኤስ ኤም ኤስ # SMS መልዕክት አማካኝነት የሚፈጸሙ የመረጃ ጥቃትን ለመከላከል፤

❌ ከማናውቀው ሰው መልዕክቶች ከሊንኮች ጋር በሚላኩልን ጊዜ በፍጥነት ከመክፈት መቆጠብ፡፡ በተለይ የተላከው የሊንክ አድራሻ
ትክክለኛነት ማረጋገጥ መቻል አለበት፤ ለምሳሌ ዶሜን ኔም(domain name)፣ ሆስትና አጠቃላይ ዩ አር ኤል( URL) ደህንነቱን ማዎቅ ያስፈልጋል፤

❌ ለማንኛውም ዓይነት ግላዊ የፋይናንስ መረጃዎቻችንን ለሚጠይቁን
መልዕክቶች ምላሽ ከመስጠት መቆጠብ ያስፈልጋል፤

❌ ስለምንሰራቸው የቢዝነስ እሴቶቻችን እንዲሁም አብረውን በሽርክናና በተለያዩ ዘዴዎች ስለምናከናውናቸው መረጃዎች ለሚጠይቁ አጭር የጽሁፍ አጭር የፅሁፍ መልዕክቶች ከመመለሳችን
በፊት ወደ አጋሮቻችንን በመደወል ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ ያሥፈልጋል፤

❌ የሚላኩልን መልዕክቶች ከማናውቃቸው ቁጥሮች ከመሆናቸውም በተጨማሪ አስቸኳይ የሆነ ምላሽን የሚጠይቁን ከሆኑ መመለስ የለብንም፤

❌ ከማናውቃቸው የኤስ ኤም ኤስ ቁጥሮች በብዛት መልዕክቶች የሚላኩልን ከሆነ የቁጥሮቹን ህጋዊነት ወደ ቴሌ በመደውል ማረጋገጥና ካልፈለግናቸው እንዲቋረጡ ማድረግ ያስፈልጋል፤

❌ እንኳን ደስ ያላህ/ያለሽ፤ አሸናፊ ሆነሃል/ሆነሻል በማለት ወደ ማናውቀው ስልክ እንድንደውል ከሚሞክሩ አጭበባሪዎች ራሳችንን መከላከል ያስፈልጋል፤

❌ የሚላኩልን መልዕክቶች የተላኩበትን ጊዜ መቼና ስንት ሰዓት የሚሉትን ጉዳዮች በመመልከት የተላከው መልዕክት ባልተለመደ
ሰዓት ከሆነ ከመመለስ መቆጠብ ያስፈልጋል፤

❌ በኤስ ኤም ኤስ የባንክ አካውንታችንን በተመለከተ ለምንጠየቀው ማንኛውም መረጃ መልስ ከመስጠታችን በፊት በባንክ አካውንታችን
ላይ ለተጠቃሚዎቹ የተቀመጡትን ህግና ስርዓቶች መመልከትና ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡
ይህን በማድረግዎ ራስዎን ከአጭበርባሪዎች መጠበቅ ይችላሉ፡፡

©️EthioCyber
©️DaniApps
👍1
⚠️ ከመተኛቶ በፊት ከስልክዎ ጋር ለረጅም ሰዓት ያሳልፋሉ?

📍 እንግዲያውስ እንዲያቆሙ እንመክሮታለን፡፡
ከመኝታ በፊት ከስልክዎ ጋር ረጅም ሰዓትን ማሳለፍ 3 ከፍተኛ ጉዳትን በጤናዎ ላይ ያመጣል ይጠነቀቁ ዘንድ እንንገሮዎ

1. አይኖን ይጎዳል
ስማርት ስልኮች ስክሪን (blue light) ናቸው፡፡ bluelight ማለት የተለያዩ የብርሃን ቀለሞች ጥርቅም ሲሆን አይኖቻችን ውስጥ ሬቲና(retina) and Macular degeneration የሚባሉ የአይኖቻችንን ክፍል ይጎዱታል ይሄ ማለት የማየት አቅማችን ይቀንሳል ከፊት ለፊታችን ያለውን ማየት አንችልም ማለት ነው ፡፡ በቀላሉ የ blue light ን ጉዳት ለማወቅ በየቀኑ ወደ ፀሃይ አተኩሮ ከማየት ጋር እኩል ነው ይሉታል እንደ ሳይንቲስቶቹ ጥናት ስለዚህም ስማርት ስልኮች ፤ ታብሌቶች ፤ ላፕቶፖች blue light ስላላቸው በተለይ ከመኝታ በፊት ለረጅም ሰዓታትን መጠቀሞን ይተዉ፡፡

2. የእንቅልፍ ማጣት ቅድም በመጀመሪያው ላይ እንደገለፅነው ስልኮቻችን blue light አላቸው ብለናል ይሄው blue light
በሰውነታችን ያለውን melatonin production
የሚባለውን ሆርሞን ያዛባል melatonin production የተስተካከለ እንቅልፍ እንዲኖረን የሚያደርግ ነው ፤ስለዚህ በቂ እንቅልፍ ማግኘት አንችችም ማለት ነው ይሄ ደግሞ ለብዙ የጤና ችግር ይዳርገናል
ለምሳሌ፡- ለልብ በሽታ ፤ ለማስታውስ ችግር ፤ ለጭንቀት፤ ክብደት መቀነስና የቆዳ ማርጀትን ያመጣል፡፡

3. ከፍተኛ የካንሰር ተጋላጭነት በምሽት የስልኮቻችንን መጠቀም ስናበዛ ለእንቅልፍ ችግር እንዳረጋለን ይሄ ደግሞ ለካንሰር ተጋላጭ ያደርገናል በተለይ ለጡት ካንሰር በወንድ መራቢያ አካል (prostate cancer) ካንሰር ያጋልጣል melatonin የሚባለው
ሆርሞን ስራውን ይዛባል፡፡ በነገራችን ላይ melatonin ካንሰርን ለመዋጋት የሚረዳ ተፈጥሮ የሰጠችን ሆረሞን ነው፡፡
ይሄ ተጎዳ ማለት የሚጣውን አስቡት፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች የሚፈጠሩት በብዛት በመኝታ ሰዓታችን ስልኮችቻን ፤ ታብሌት ወይም ኮምፒተራችን ስንጠቀም ነው፡፡

©️EthioCyber
©️DaniApps
🌐 የ3ጂ/ 4ጂ የሞባይል📱 ኢንተርኔት አገልግሎት ፍጆታን ለመቆጣጠር ወይንም ለመቀነስ 12 ጠቃሚ ምክሮች! በተለይ ቁጥር 3. በጣም ጠቃሚ ነው..

የኢንተርኔት አጠቃቀምን መመጠን
የተለያዩ መተግበሪያዎች/
Applications/ ሙሉ በሙሉ ስራላይ በሚሆኑበት ጊዜ የተለያየ መጠን ያለው ኢንተርኔት ይጠቀማሉ..
ለምሳሌ:-
ቪዲዮ የሚያጫውቱ እንደ ዩቲዩብ/youtube/ እና ፌስ ቡክ/facebook/ ያሉ መተግበሪያዎች ከሌሎች መተግበሪያዎች ይልቅ ከፍተኛ መጠን ያለው ኢንተርኔት ይጠቀማሉ፡፡

በመሆኑም ስልክዎ ላይ ጭነው የሚጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች የሚጠቀሙትን የኢንተርኔት መጠን ለመቆጣጠር የሚከተለውን ቅደም ተከተል መተግበር ይችላሉ፡
ከተቻለ ሁልጊዜም ለወይፋይ ቅድሚያ ይስጡ ካልሆነ ግን የሚከተሉትን መላዎች ይጠቀሙ

1.ሴቲንግ /Setting/ ውስጥ Data usageን ይመርጣሉ > mobile data ውስጥ > data usage cycle የሚለው ላይ > ቀስቶቹን በማንቀሳቀስ ምን ያህል መጠን ያለው ኢንተርኔት በምን ያህል ጊዜ ውስጥ መጠቀም እንደሚፈልጉ መመጠን ይችላሉ፡፡

2. በራስ መር ማዘመንን /Update/ ማጥፋት ስልክዎ ላይ የተጫኑ ሶፍትዌሮች ወይም መተግበሪያዎች እንዲዘምኑ /Update/ ካልፈቀዱ በስተቀር በራሳቸው ጊዜ ያለርስዎ ፈቃድ እንዳይዘምኑ በማድረግ ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡

3. ቪዲዮ ሙዚቃ እና ጌም በቀጥታ ከኢንተርኔት ላይ መመልከት/መጫወት ከፍተኛ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ ቪዲዮዎች እና ሙዚቃዎችን በቀጥታ ሲመለከቱ ወይም ሲያወርዱ በተለይ ደግሞ ጥራታቸው ከፍ ያሉ ቪዲዮዎች እናሙዚቃዎች ከሆኑ ከፍተኛ የኢንተርኔት ፍጆታ ይጠቀማሉ፡፡በአንዳንድ አጋጣሚዎች ከፍተኛ ጥራት ያለው ቪዲዮ እና ሙዚቃን መምረጥ በጥራት ዝቅተኛ ከሆነ ተመሳሳይ ይዘትካለው ቪዲዮ እና ሙዚቃ በሁለት እጥፍ የሚልቅ የኢንተርኔት ፍጆታ ይጠቀማሉ፡፡ለምሳሌ:-በሞባይልዎ ከዩቲዩብ (youtube)ቪዲዮ እና ሙዚቃን እየተመለከቱ ከሆነ ጥራቱን ዝቅ በማድረግየኢንተርኔት አጠቃቀምዎን መመጠን ይችላሉ፡፡ ይህንንለማድረግ
3.1. ስልክዎ ላይ የዩቲዩብ/youtube/ መተግበሪያን ይክፈቱ
3.2.ሜኑ የሚለው ውስጥ ጄነራል/General/ን ይምረጡ
3.3.High Quality on Mobile የሚለውን ያልተመረጠ /Un-tick/ በማድረግ የቪዲዮውን ጥራት ዝቅ ማድረግ ይችላሉ
ያስተውሉ
* ከፍተኛ ጥራት ያለው ሙዚቃ(ምስል የሌለው) በ(256kbps) የጥራት መጠን ሲጠቀሙ በሰዓት እስከ 100 ሜጋባይት የኢንተርኔት ፍጆታ ይጠቀማሉ በተመሳሳይ ሁኔታ ቪዲዮ በHD ጥራት ሲመለከቱ በሰዓት እስከ 1ጂቢ የኢንተርኔት ፍጆታ ይጠቀማሉ፡፡

ጌሞችን ከኢንተርኔት በቀጥታ እየተጠቀሙ ከሆነ በሰዓት ከ10 እስከ 80 ሜ.ባ ድረስ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ፡፡

4. መተግበሪያዎች ማሳወቂያ/
Notification/ እንዳይልኩ ማድረግ እና ከጀርባ በኩል/Background/ ኢንተርኔት እንዳይጠቀሙ ማገድ

★ አንዳንድ መተግበሪያዎች እየተጠቀሙባቸው ባይሆንም በውስጥ በኩል እርስዎ ሳያውቁ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ
ለምሳሌ:- የተሻለ የመተግበሪያው/Application/ ስሪት ሲኖር ራሳቸውን ያዘምናሉ። ስለዚህ መተግበሪያዎችን ስልክዎ ላይ ሲጭኑ ስለመተግበሪያው የተለያዩ ማሳወቂያዎች/
notifications/ እንዲደርስዎ ይፈልጉ እንደሆነ ሲጠየቁ መከልከል እንዲሁም አካባቢዎን ፈልጎ እንዲያገኝ ፈቃድ ሲጠየቁ ባለመፍቀድ የኢንተርኔት አጠቃቀምዎን መመጠን ይችላሉ፡፡
የጫኗቸውን መተግበሪያዎች ማዘመን /አፕዴት ማድረግም ሆነ መጠቀም ሲፈልጉ ብቻ ራስዎ ገብተው እንዲፈቅዱ አድርገው መጫን ይችላሉ

©️EthioCyber
©️DaniApps
👍2🔥1
የዩኒቨርሲቲዎችን ትክክለኛ ገፅ ብቻ በመከተል ከሀሰተኛ የዩኒቨርሲቲ ጥሪዎች እራሳችሁን ጠብቁ ፦

👉 ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://m.facebook.com/DDUniv/

👉 ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://m.facebook.com/Hawassa.University/

👉 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://m.facebook.com/Addis-Ababa-University-496255483792611/

👉 ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፦
https://m.facebook.com/TheUniversityofGondar/

👉 ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፦
https://m.facebook.com/bduethiopia/?ref=page_internal&mt_nav=0

👉 አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://m.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/?_se_imp=0ueaW0ZojpEObV9zR

👉 ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://m.facebook.com/HRMUNIV/

👉 ጅማ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://m.facebook.com/JimmaUniv/

👉 አርሲ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=357578986410375&id=100064748293256

👉 ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://m.facebook.com/pages/category/Education-website/Wolaita-Sodo-University-246568056057804/

👉 ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://m.facebook.com/WachemoUniversity2008/

👉 ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://www.facebook.com/265529850297666/posts/1845133279003974/?app=fbl

👉 መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://www.facebook.com/141864125910414/posts/4794315817331865/?app=fbl

👉 ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://m.facebook.com/pages/category/Education-website/Wollega-University-Corporate-Communications-2319182621440303/

👉 አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://www.facebook.com/234983083247967/posts/5141798579233035/?app=fbl

👉 ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://www.facebook.com/2181225212102194/posts/3109977289226977/?app=fbl

👉 ቦረና ዩኒቨርሲቲ ፦
https://m.facebook.com/BoranaUniversityBRU/

👉 ቀብሪድሃር ዩኒቨርሲቲ ፦
https://m.facebook.com/pages/category/Education/Kebri-Dehar-University-306587496533329/

👉 ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://m.facebook.com/pages/category/Education/Jinka-University-178538809733160/

👉 ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፦
https://www.facebook.com/547073878695780/posts/5065885566814566/?app=fbl

👉 ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://www.facebook.com/1879460055640998/posts/3057857987801193/?app=fbl

👉 ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://m.facebook.com/WoldiaUniversity/

👉 ወሎ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://m.facebook.com/WolloUniversity111/

👉 ደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://www.facebook.com/1301588393256101/posts/5145148712233364/?app=fbl

👉 ኦዳቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ፦
https://m.facebook.com/OBUEthiopia/

👉 አምቦ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://m.facebook.com/AmboUniversityofficial/

👉 ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://m.facebook.com/Mizan-Tepi-University-MTU-362390684253048/

👉 ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://www.facebook.com/614590095253065/posts/5432186613493365/?app=fbl

👉 ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://www.facebook.com/979926502053136/posts/5129611493751262/?app=fbl

👉 ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://www.facebook.com/336146983089022/posts/5029908297046177/?app=fbl

👉 ኮተቤ ፦
https://www.facebook.com/792405150779154/posts/5397052686981021/?app=fbl

👉 ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://www.facebook.com/100064618752509/posts/386404006856888/?app=fbl

👉 መቱ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://www.facebook.com/330316734055129/posts/1468350973585027/?app=fbl

👉 መቅደላአምባ ዩኒቨርሲቲ ፦
https://m.facebook.com/Mekdela.Amba.University/

ŠTikvahethiopia
©️EthioCyber
©️DaniApps
👍1
⚠️ 5 አስፈሪ ወይም አስጊ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን አጠር አርገን እናያለን።

5. internet Surveillance

◽️ ኢንተርኔትን በመጠቀም በስልኮቻችን ፣ በታብሌቶቻችን ፣ በላፕቶፖቻችን ልንሰለል እና የግል Privacy ልናጣ እንችላለን። አብዛኞቹ የሞባይል አምራቾች የራሳቸውን Privacy Policy ይዘው እንደሚንቀሳቀሱ ይታወቃል ነገር ግን እነዚህ ድርጅቶች የኛን ሚስጥራዊ መረጃዎች በመንግስታት ተገደው ሊሰጡ ይችላሉ።

ለምሳሌ፡ ስንቶቻችን የስማርት ስልኮች ተጠቃሚ ነን። ስማርት ስልኮች ቢያንስ 2 ካሜራ (የፊትና የኋላ) የGPS መሳሪያ አላቸው። እነዚህን መሳሪያዎች በመጠቀም ብቻ የት እንዳለን ማን እንደሆንን የእለት ተእለት ኑሮአችን ጭምር ሊታይ ይችላል። ማን ያውቃል ይህንን ፖስት በምታነቡበት ሰአት እራሱ የሆነ ሰው ሰልፊ ካሜራችሁን በመጠቀም እያያችሁ ይሆናል።

4. Robotic Solders

◽️ ሰውሰራሽ ወታደሮች ያላቸውን ሀይል ለማወቅ Terminator ማየት በቂ ነው። በእርግጥ Terminator Science Fiction የሆነ ፊልም ነው። ነገር ግን በአሁኑ ሰአት በጣም ብዙ ነገር ማድረግ የሚችሉ ሮቦቶች እየተሰሩ ነው። ማን ያውቃል በቀጣይ እራሱን Terminatorን ቢሰሩትስ።

◽️ ሮቦቶች አይርባቸውም ፣ አይጠማቸውም ፣ አይደክማቸውም በፍጥነት በጥንካሬ እና በብዙ ነገር ከሰዎች ይበልጣሉ ነገርግን የሰው ልጅ ያለው ፈቃድ የሚባል ነገር የላቸውም ስለዚህ እንዲጨፈጭፉ ከታዘዙ ያለምንም ርህራሄ ያደርጉታል። ሰው ሰራሽ ወታደሮች የሰሯቸውን ሰዎች የማጥፋት አቅም አላቸው።

3. DNA Editing

◽️ ሳይንቲስቶች የሰው ልጆችን ዘረመል ወይም DNA ካገኙ ጀምሮ የተለያዩ ምርምሮች እየተደረጉ ይገኛሉ። ነገርግን ይህ ዘረመል በሰው ልጆች ለይ ብቻ የሚገኝ አይደለም በሁሉም ህይወት ያላቸው ነገሮች ለይ አለ። እናም ይህንን DNA በማስተካከል ድክመት የሌለው ፍጥረት ለመስራት እየተሞከረ ይገኛል።

◽️ ሳይንቲስቶች የሰዎችን ዘረመል ማረም ወይም ማስተካከል ይቻላል ብለው ያምናሉ። በአሁኑ ሰአት አለምን ያስጨነቀው ኮሮና እራሱ በጂኔቲክ ኤዲቲንግ የተፈበረከ ባዮሎጂካል መሳሪያ እንደሆነ ጥርጣሬያቸውን የሚሰጡ አሉ።

2. Micro Chips

◽️ በአሁን ጊዜ የተለያዩ መረጃዎቻችንን ወይም ሰነዶቻችንን የምንይዘው በወረቀች ወይም በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ነው። ነገር ግን አሁን እየተመረተ ያለ ቴክኖሎጂ መታወቂያችንን ፣ የልደት ሰርተፊኬታችንን ፣ የባንክ ቡካችንን ወዘተ መረጃዎቻችንን በአንዲት ቺፕ ለይ በመጫን ይህቺን መሳሪያ በሰውነታችን ውስጥ ትቀበራለች።

◽️ ነገር ግን ይህች በሰውነታችን ውስጥ የምትቀበር መሳሪያ የኛን መረጃዎች ከመያዝ ባለፈ የእኛን እንቅስቃሴዎች እና አኳኋን ከመከታተል እስከ መቆጣጠር ድረስ አገልግሎት ለይ ልትውል ትችላለች።

1. Nuclear Bombs

◽️ የኒኩሌር ቦምቦች የሚያደርሱትን ጥፋት ለመረዳት የጃፓኖቹን ሂሮሺማ እና ናጋሳኪ ማየት በቂ ነው። ሳይንቲስቶች እንደሚሉት አያርገውና በአሁኑ ሰአት የኒኩሌሬ ጦርነት ቢነሳ አለማችን ትጠፋለች። በሀያላን ሀገራት ዘንድ ብቻ የሚገኘው ይህ መሳሪያ ሂሮሺማ እና ናጋሳኪ ለይ ሲጣል ከነበረው በላይ ዘምኖና ተሻሽሎ ተሰርቷል።

◽️ አሁን ያለው የኒኩሌር ቦምብ ቢፈነዳ በትንሹ የጨረራ ራዲየስ 7.49 ኪ.ሜ ወይም 176 ካሬ ኪ.ሜ. ይሸፍናል ፣ የአየር ፍንዳታ ራዲየስ 12.51 ኪ.ሜ ወይም 491 ስኩዌር ኪ.ሜ ይሸፍናል ፣ የሙቀት ጨረር ራዲየስ 77.06 ኪ.ሜ ወይም 18626 ካሬ ኪ.ሜ ይሸፍናል ፡፡ አሜሪካ በ2ኛው የአለም ጦርነት ጃፓን ለይ ከጣለችው ቦምብ በ3,333 እጥፍ ያህል የበለጠ ኃይል አለው፡፡

©️EthioCyber
©️DaniApps
👍3
✅ ኢትዮ-ቴሌኮም ሁለት አዳዲስ አገልግሎቶችን ይፋ አደረገ

📍ኢትዮ-ቴሌኮም 'አሻም ቴሌ' እና 'ቴሌ ገበያ' የተሰኙ አዳዲስ አገልግሎቶችን ይፋ ማድረጉን አስታወቀ።የተቋሙ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በተገኙበት አገልግሎቶቹን ይፋ ማድረጊያ መርሃ-ግብር ተከናውኗል።

📍 የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ አዳዲስ አገልግሎቶቹ ደንበኞች ከኩባንያው ጋር ያላቸውን ትስስር የሚያጠናክሩ ናቸው ብለዋል።አገልግሎቶቹም ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሆኑ ገልጸዋል።

📍 ከአገልግሎቶቹ አንዱ የሆነው 'አሻም ቴሌ' ደንበኞች የኢትዮ-ቴሌኮም አገልግሎትን ሲያገኙ በሚሰበሰብላቸው ነጥብ መልሶ የሚከፍል የአገልግሎት አይነት ነው ብለዋል።ደንበኞች የቴሌኮም አገልግሎት ሲጠቀሙ እንዲሁም ክፍያቸውን በቴሌ ብር ሲፈጽሙ በሚሰበስቧቸው ነጥቦች አማካኝነት ሽልማት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው።

📍 ይህ ማለት ደንበኞች አገልግሎት ለማግኘት በሚፈጽሙት የአገልግሎት ግዢ ብዛትና በቴሌ ብር በተፈጸመ ክፍያ ብዛት የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረጊያ ስልት መሆኑንም አክለዋል።በዚህም መሰረት በ'አሻም ቴሌ' የሚመዘገቡ ደንበኞች በሚያስመዘግቡት ነጥብ መጠን ማበረታቻ እንዲያገኙ ይረዳል ብለዋል።

📍 ሌላው ይፋ የሆነው አገልግሎት 'ቴሌ ገበያ' ሲሆን ይህ ደግሞ የቴሌኮም አገልግሎት 'ኦን ላይን' ሽያጭ አማካኝነት ደንበኞችን ተጠቃሚ ማድረጊያ ነው ብለዋል።በዚህም ካሉት ከ600 በላይ የሽያጭ ማዕከላት በተጨማሪ ደንበኞች ካሉበት ሆነው የኢትዮ-ቴሌኮም ምርቶችን በቴሌ ብር አማካኝነት መግዛት እንዲችሉ ዕድል ይፈጥራል ነው ያሉት።

📍 ደንበኞች የሞባይል ቀፎዎችን፣የኢንተርኔት መጠቀሚያ ሞደሞችን፣ መደበኛ ብሮድ ባንድ ኢንተርኔት እና ሌሎች የቴሌኮም አገልግሎቶችን ማግኘት የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።ደንበኞች 'ቴሌ ገበያ' የኢትዮ-ቴሌኮም ድረ-ገጽን በመጠቀም የሽያጭ ማዕከላትን ማግኘት እንደሚችሉም አክለዋል።

©️EthioCyber
©️DaniApps
👍5
✅ ዳሽን ባንክ ደንበኞች ማንኛውንም እቃ በዱቤ ለመሸመት የሚችሉበትን “ዱቤ ፔይ” የተሰኘ አገልግሎት አስጀመረ!!

📍 ባንኩ ሰዎች የሚፈልጉትን እቃ ለመግዛት ገንዘብ ቢያጥራቸው እንኳን፤በዱቤ መግዛት የሚችሉበትን አገልግሎት በዛሬዉ እለት በይፋ ማስጀመሩን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

📍 አገልግሎቱ “ዱቤ ፔይ” የሚባል ሲሆን፤ የነጋዴውን ምርት ለሸማቾች በዱቤ መልክ የሚያቀርብ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ይህም በገንዘብ እጥረት ምክንያት ፤ ሰዎች የሚፈልጉትን ነግር ከመግዛት እንዳያግዳቸው እና በቀላሉ የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ተብሏል፡፡

📍 የዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን ደንበኞች የዳሽን ባንክ የዱቤ የሂሳብ ደብተር በማውጣት እና የዱቤ ፔይ መተግበሪያን በማውረድ መመዝገብ እንደሚችሉ፤የባንኩ ዲጂታል ባንኪንግ ዋና ኦፊሰር አቶ ዮሃንስ ሚሊዮን ተናግረዋል፡፡

📍 ታዲያ በማንኛው ሰዓት መግዛት የሚፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ያለምንም ችግር በዱቤ መልክ መግዛት እንደሚችሉ ኦፊሰሩ ተናግረው፤ እንደ ገንዘቦቹ ልክ የአንድ ዓመት፤የ6 ወር እና የ3 ወር ዱቤን የመመለሻ ሲስተሞች መዘርጋታቸውን ተናግረዋል፡፡

📍 ዳሽን ባንክ እና የመተግበሪያው አበልጻጊ ድርጅት ኤግልላይን በዛሬው እላት ይህን ሲስተም ማስኬድ የሚቻልበትን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

📍 የዱቤ አገልግሎት ማግኘት የሚፈልጉ ደንበኞች ከሚያወጡት የዱቤ የሂሳብ ደብተር እና ከሚያወርዱት መተግበሪያ በተጨማሪ ከሚሰሩበት ቦታ ደሞዛቸውን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት፤ካልሆነም ንብረት ማስያዝ እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል፡፡
መተግበሪያው በሃገራችን 4 ቋንዎች ማለትም በአማርኛ፣ትግረኛ፣አፋን ኦሮሞ እና ሶማሊኛ እንዲሁም በእንግሊዝኛ ቋንቋ አማራጭ መቅረቡ ተነግሯል፡፡

©️EthioCyber
©️DaniApps
🌐 ፌስቡክ የተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ገጽ በሶስት ወራት ውስጥ ከ27 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቱ ተነገረ፡፡

📍 ፌስቡክ ከአስር ዓመታት ወዲህ በጣም አዝጋሚ የሆነው የገቢ ዕድገት እያስመዘገበ ቢሆንም በ2022 ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት የዕለት ተዕለት ንቁ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ቁጥር ወደ 1 ነጥብ 96 ቢሊዮን ማደጉን ኩባንያው ገልጿል።

📍 በገቢ ረገድም በ2022 ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት የተገኘው ገቢ ከ2021 ጋር ሲነጻጸር 7 በመቶ ብቻ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ገቢዉም 27.9 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ተብሏል።

📍 ኩባንያዉ በሚቀጥለው ሩብ ዓመት ደግሞ ከ28 እስከ 30 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ያገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ የምጣኔ ሃብት ተንታኞች ግምታቸዉን አስቀምጠዋል፡፡

📍 የባለፈዉ አመት ሪፖርት እንደሚያሳየዉ ማህበራዊ መድረኩ የተጠቃሚዎቹ ቁጥር በተለያዬ ምክንያት በመቀነሱ ኩባንያዉ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዋጋ እንዲቀንስ አድርጎታል ከርሟል፡፡

📍 እ.ኤ.አ. በ2004 ፌስቡክን የመሰረተው የሜታ አለቃ ማርክ ዙከርበርግ “ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ብዙ ሰዎች አገልግሎቶቻችንን ይጠቀማሉ።

📍 ምርቶቻችን በዓለም ዙሪያ ሰዎችን እንዴት እንደሚያገለግሉ ሳይ ኩራት ይሰማኛል” ሲሉ ስለመናገራቸው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

©️EthioCyber
©️DaniApps
👍1
✅ ቻይና ለአሽከርካሪ አልባ የታክሲ አገልግሎት ፍቃድ ሰጠች

📍 በቻይና የአሽከርካሪ አልባ የታክሲ አገልግሎት እንዲሰጡ ባይዱ እና ፖኒ.ኤ.አይ የተባሉ ኩባንያዎች ፍቃድ ማግኘታቸው ተገለፀ፡፡

📍 የአሽከርካሪ አልባ የታክሲ ፍቃዱ ከዚህ ቀደም ለመሰል አገልግሎቶች የሚጠየቀውን በተሽከርካሪ ውስጥ የተጠባባቂ ሾፌር መኖርን የሚያስቀር መሆኑ ተመላክቷል፡፡ አዲሱ ፍቃድ በተሽከርካሪው የፊተኛው የተሳፋሪ መቀመጫ የደህንነት ተቆጣጣሪ ብቻ እንዲኖር የሚያስገድድ መሆኑን ኤ.ቢ.ሲ ኒውስ አስነብቧል፡፡

📍 ቻይና በአውሮፓውያኑ 2020 ባስቀመጠችው ግብ በ2030 በሀገሪቱ የሚሸጡ ተሽከርካሪዎች ደረጃ ሁለት እና ሦስት የተባሉ የአሽከርካሪ አልባ የቴክኖሎጂ ደረጃዎች እንዲኖራቸው አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

📍 በደረጃ ሁለት ተሽከርካሪው ግማሽ የኦቶሜሽን አቅም እንዲኖረው ይጠበቃል፡፡ በዚህም ተሽከርካሪው የመሪ እንቅስቃሴ እና ፍጥነትን በራሱ እንዲቆጣጠር የሚያስችል መሆኑ መረጃው አመላክቷል፡፡

📍 በቀጣዩ ደረጃ ተሽከርካሪው አካባቢውን ሙሉ በሙሉ የሚረዳ እና እራሱን ማሽከርከር የሚችል መሆን እንደሚኖርበት ተገልጿል፡፡


©️EthioCyber
©️DaniApps
ŠEAII