DaniApps
1.08K subscribers
610 photos
34 videos
537 files
219 links
The Best Android Apps And Games Are Here.📱
For Any Questions ➡️ @DaniappsBot Or Group ➡️ @daniappsgroup
Apps Or Games ➡️ @daniappsstore
Ask Any Apps ➡️ @Daniapps2bot
Website https://daniapps.epizy.com/

https://g.page/r/CYhVwdbaF335EA0/review
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌐 የድህረ ገጽ ጥቆማ :- CleanUp

👉 እንበልና ከሆነ ሰዉ ጋር ፎቶ ተነስታቹ የራሳቹን ፎቶ ብቻ ለማውጣት ብትፈልጉ ግዴታ የሆነ ቦታ ቆርጣቹ ማውጣታቹ አይቀርም ያኔ ግን ብዙም ደስ አይልም (background ብቻ ሁሉ ነገሩ) ወይም በአጭሩ አላስፈላጊ ነገሮችን ከፎቶ ላይ ለማውጣት የሚጠቅም ድህረ ገጽ ነው።

©
Ethiology
©️Ethio_Cyber
©️Dani_Apps
🌐 SafaricomEthiopia

⚡️ሳፋሪኮም - ኢትዮጵያ በሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ ሥራ እንደሚጀምር አሳውቋል።

⚡️የድርጅቱ የቁጥጥር እና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ማቲው ሃሪሰን ሃርቬይ ከመንግስት ጋር ያላቸው ስምምነት እንደሚያሳየው ፍቃድ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በዘጠኝ ወር ወደ ስራ መግባት እንደሚኖርባቸው ገልፀው ከመጪው ሚያዝያ ወር ጀምሮ በይፋ የንግድ ሥራ ለመጀመር እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

⚡️ኃላፊው ይህን የገለፁት ለካፒታል ጋዜጣ ነው።

⚡️እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 9፣ 2021 ጀምሮ የሚቆጠር የመሥሪያ ፍቃድ ያገኘው ሳፋሪኮም ቴሌኮሙኒኬሽን ኢትዮጵያ በሀገሪቱ የቴሌኮም ማስፋፊያ ስራዎችን ጀምሯል።

⚡️ባለፈው ወር የኩባንያው የመጀመሪያ የመረጃ ማዕከል ስራ የጀመረ ሲሆን ኩባንያው የኔትወርክ ዝርጋታውን እየሰራ ነው።

⚡️ማቲው ሃሪሰን ሃርቬይ ሳፋሪኮም ከ2 የኔትወርክ አቅራቢዎች ኖኪያ እና ሂዋዌ ጋር እየሰራ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በአዲስ አበባ እና አካባቢው ያለውን የኮር ኔትወርክ መሠረተ ልማት በኖኪያ ኩባንያ እንደሚሰራ ሁዋዌ ቀሪውን የአገሪቱን ክፍል እንደሚሸፍን አስረድተዋል።

⚡️" የመሰረተ ልማት መጋራት በተመለከተም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር እስካሁን በድርድር ደረጃ ላይ ነን " ሲሉም አክለዋል።

⚡️ከመሰረተ ልማት ጎን ለጎን የሳፋሪኮም ደንበኞች እና የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች እንዲገናኙ ለማድረግ ስራዎች እየተሠሩ መሆኑን ገልፀዋል።

©️Ela_Tech
©️Dani_Apps
🖥 የኮምፒዩተር ኮድ በመጻፍ ከሰዎች ጋር የሚፎካከረው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት

አልፋኮድ የተባለ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት የኮምፒዩተር ኮዶችን በመጻፍ በተደረገ ውድድር አበረታች ውጤት ማስመዝገቡ ተገለፀ፡፡

ሥርዓቱ ኮድፎርስ ተብሎ በሚታወቀው የኮምፒዩተር ፕሮግራሚንግ የውድድር መድረክ ላይ ከሰዎች ጋር በመፎካከር ጥሩ ውጤት ካስመዘገቡት ሃምሳ አራት በመቶ ቀዳሚ ተፎካካሪዎች ውስጥ መካተት መቻሉን የዲፕ ማይንድ ድረ-ገፅ አስነብቧል፡፡

በመድረኩ በተመረጡ አስር ፉክክሮች ላይ የተሳተፈው አልፋኮድ በመካከለኛ ሁኔታ በሚመደብ የተፎካካሪነት ደረጃ መገኘት መቻሉ ተገልጿል፡፡ ይህም ለፉክክር የበቃ የመጀመሪያው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮድ አመንጪ ሥርዓት እንደሚያደርገው ዘገባው ያስረዳል፡፡

ይህ ሥርዓት የኮምፒዩተር ኮዶቹን ለማመንጨት ትራንስፎርመር ቤዝድ ላንጉዬጅ የተባለውን ስልት እንደሚጠቀም መረጃው ጠቁሟል፡፡

ሥርዓቱ የበለፀገው በጉግል ባለቤትነት በሚተዳደረው ዲፕማይንድ ኩባንያ ነው፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉበት ይህ መድረክ በጥልቀት ማገናዘብን፣ አመክንዮን፣ ስልተቀመሮችን፣ ኮድ እና ተፈጥሯዊ ቋንቋን አዋህዶ መረዳትን ይጠይቅ እንደነበር ተመላክቷል፡፡

©️EAII
©️Dani_Apps
እግራቸው ለማይንቀሳቀስ ሰዎች እንዲራመዱ የረዳው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት

📍የሥርዓተ ነርቭ አለመታዘዝ እክል ገጥሟቸው መራመድ የማይችሉ ሰዎች እጅግ ዘመናዊ በተባለ ሕብለ ሰረሰር ላይ በሚገጠም አነስተኛ መሣሪያ አማካኝነት መራመድ፣ መዋኘት እና ሳይክል መንዳት መቻላቸው ተገለፀ፡፡

📍ግለሰቦቹ ሆድ ውስጥ በሚቀበር ተጨማሪ አጋዥ መሣሪያ ላይ የተጫነው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት ሕብለ ሰረሰር ላይ የሚገጠመውን አነስተኛ መሣሪያ ይቆጣጠራል፡፡

📍በዚህም የእግር ጡንቻዎችን የሚያዘው የሕብለ ሰረሰር አካባቢን የነርቭ ሕዋሶች በማነቃቃት እና ወደስራ እንዲገቡ በማስቻል የእግር ጡንቻዎች መታዘዝ እንዲችሉ አድርጓል ሲል ዴይሊ ሜይል አስነብቧል፡፡

📍በሞተር ሳይክል አደጋ ምክንያት ከአራት ዓመታት በላይ በተሽከርካሪ ወንበር እንዲያሳልፍ ተገዶ ለነበረ ግለሰብ ቴክኖሎጂው ዳግም የመራመድ እድልን አጎናፅፎታል፡፡

📍 የስዊዘርላንዱ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ውጤት የሆነው ይህ ቴክኖሎጂ ለታማሚዎቹ ከተገጠመ ከአንድ ቀን በኋላ ግለሰቦቹ መቆም፣ መራመድ፣ ሳይክል መንዳት፣ መዋኘት እና አካላቸውን መቆጣጠር መቻላቸው ተመላክቷል፡፡

©️EAII
©️Dani_Apps
ለተሻለ ውጤት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን የምትጠቀመው አነስተኛ ካሜራ

📍 የዘመኑ ካሜራዎች ከሚያነሱት የተሻለ ምስልን ማስቀረት የምትችል የጨው ቅንጣት መጠን ያላት ካሜራ በፕሪንስተን እና ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች እውን መሆኗ ተነገረ፡፡

📍 ሌሎች የካሜራዋ ቴክኖሎጂዎች ከብርሃን ጋር በሚኖራቸው መስተጋብር የሚፈጠረውን ሂደት በመጠቀም የማሽን ለርኒንግ ስልተቀመሮች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ምስሎችን ለመፍጠር ጥቅም ላይ መዋላቸው ተመላክቷል፡፡

📍 ባለ ሙሉ ቀለም ምስሎችን ማስቀረት የምትችለው ካሜራ ለሕክምና ከሚውሉ ሮቦቶች ጋር በመጣመር ለአገልግሎቱ ተጨማሪ ግብዓት እንደምትሆን ዘኢንዲፔንደንት ዘግቧል፡፡

📍መደበኛ ካሜራዎች ከሚሰሩበት በተለየ መልኩ የኮምፒዩተር ቺፕ የሚዘጋጅበት የቴክኖሎጂ ሂደት ካሜራዋን ለመስራት ውሏል፡፡

📍 ፈጠራው በስማርት ስልኮች ላይ የሚታየውን ከአንድ በላይ ካሜራ የማካተት ፍላጎት ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ምስሎችን መቅረጽ በሚችል አንድ ካሜራ የመተካት ተጨማሪ ዓላማ አካቷል፡፡

©EIIA
©️Dani_Apps
[Napoleon-Hill]-Think-And-Grow-Rich(z-lib.org).pdf
1003.8 KB
📍ዛሬ አንድ በአለማችን ላይ የብዙ ሰዎችን ህይወት ላይ ትልቅ አሻራ ያሳረፈ መፅሃፍ ልንጠቁማችሁ ወደናል።

📍 ቦብ ፕሮክተር(Bob proctor) የተባለው ታዋቂ ሚሊየነር፣ ደራሲና የአደባባይ ተናጋሪ ከ 55 ጊዜ በላይ መፅሀፉን እንዳነበበውና ህይወቱን የቀየረለት ይሄ መፅሀፍ እንደሆነ ደጋግሞ ይናገራል። ለዚህ መፅሀፍ በርካታ ዘጋቢ ፊልሞች የተሰሩለት ሲሆን ብዙዎች ደግሞ የስኬት መፅሀፍ ቅዱስ ነው ይሉታል።

📍 መፅሀፉ Think and grow rich ይባላል። ፀሀፊው ናፖሊዮን ሂል ሲሆን መፅሀፉን ለመፃፍ በአለማችን የስኬትና የሀብት ቁንጮ ከነበሩት ቶማስ ኤዲሰን፣ ኤድዊን ባርንስ፣ ሄንሪ ፎርድ፣ አንድሪው ካርኒጌ እና ሌሎች ግዙፍ ስብዕና ያላቸው ሰዎች ጋር በፊት ለፊት በመገናኘትና አብሮ በማሳለፍ ብዙ ጥናት አድርጎ የስኬታቸውን ምስጢር የፃፈ ታላቅ ደራሲ ነው።

©️Tech21
©️Dani_Apps
#Sumuni (ስሙኒ)

📍 ስራ ፈጣሪዎችን ከባለሀብቶች ጋር የሚያገናኝ መተግበሪያ " ስሙኒ " ምንድነው ? እንዴትስ ላግኘው ?

📍 ትላንት " ስሙኒ " የተሰኘ ኩባንያ ከኮካ ኮላ ቢቭሬጅስ አፍሪካ-ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ስራ ፈጣሪዎችን ከባለሀብቶች ጋር የሚያገናኝ በመተግበሪያ እንዲሁም በድህረገጽ በይፋ አስጀምረዋል።

📍 ስሙኒ የሥራ ፈጠራ ባለቤቶችንና ባለሃብቶች ማገናኛ በስራ ፈጠራ ስነምህዳር ውስጥ ያሉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚገናኙበት እና የሚተሳሰሩበት የኦንላይን መድረክ ነው።

📍 መድረኩ የውጭ ኢንቨስተሮች በሀገር ቤት ስታርታአፖች ላይ መዋለ ንዋይ እንዲያፈሱ በማስቻል ምንዛሪ በማስገኘት እንዲሁም የውጭ ኢንቨስትመንት በመሳብ ለኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት እድገት ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሎ ታምኗል።

📍 በተጨማሪም በባለድርሻ አካላት መካከል የኢኮኖሚ ትስስርና ለወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር ለሀገሪቱ ዕድገት አስተዋፅዖ ያደርጋል።

📍 ኮካ ኮላ ቤቭሬጅስ በስሙኒ መገናኛ መተግበሪያ በኩል በዚህ ዓመት ለ10 ስታርታፖች ለእያንዳንዳቸው 100,000 ብር ስራ ማስጀመሪያ ይሰጣል፡፡

📍 በተጨማሪም 10,000 የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን፣ ወጣት ስራ ፈጣሪዎችን እና አነስተኛ የንግድ ባለቤቶችን አቅም ለመገንባት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የክህሎትና የዕውቀት ድጋፍ በማድረግ ከሌሎች ኢንቨስተሮችን የማገናኘት ስራ ይሰራል፡፡

መተግበሪያውን እና ድረገፁን እንዴት ላግኘው ?

http://139.59.95.164/sumuni.net/index.php


መተግበሪያው : https://play.google.com/store/apps/details?id=com.sumuni.sumuni_new

©tikvahethiopa
©️Ethio_Cyber
©️Dani_Apps
“በዋልታ የፌስቡክ ገጽ ላይ የደረሰዉ ጥቃት ከአድሚኖች እና ኤዲተሮች ጋር የተያያዘ ነው።“ :- የኢ.መ.ደ.ኤ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው

📍በዋልታ የፌስቡክ ገጽ ላይ የደረሰዉ ጥቃት ከአድሚኖች እና ኤዲተሮች ጋር የተያያዘ ጥቃት መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ገለጹ።

📍 በዋናነት ለጥቃቱ ሁለት ምክንያቶችን ያስቀመጡት ዋና ዳይሬክተሩ፤ አንዱ የዋልታ የፌስቡክ ገጽ ዋና አድሚን አገር ዉስጥ ካለመሆኑ ጋር የተያያዘ እንደሆነ እና ሁለተኛዉ ምክንያት ደግሞ የሚዲያዉን የፌስቡክ አካዉንት እንዲያንቀሳቅሱ ሃላፊነት በወሰዱ አካላት ስህተት መሆኑን ገልፀዋል።

📍 በተለይም አንዱ የፌስቡክ ኤዲተር የተላከለትን አጥፊ ተልዕኮ ያለዉን ሊንክ ያለ ጥንቃቄ በመክፈት ለመረጃ ጥቃቱ መፈጸም ሚና እንደነበረዉ ዶ/ር ሹመቴ ተናግረዋል።

©️bbc_amharic1
©️Dani_Apps
#የዌብሳይት_ጥቆማ

📍ለስልክ እንዲሁም ለPC አፖች እንዲሁም ጌሞችን ማዉረጃ ዌብሳይት ለምትፈልጉ ⬇️

ለስልክ 📲

1. rexdl.com (mods, apk, obb)
2. apkpure.com (original, full apk)
3. apkreal.com (mods, apk, obb)
4. oceanofapk.com

ለ Computer 💻
G
1. fougamers.com (crack, mods, DLCs)
2. dzrepackteam.com (crack, mods, DLCs)
3. Oceanofgames.com
4. softonic.com

©️EtCyberTech
©️Dani_Apps
🖐 ሰላም ሰላም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች በመጀመሪያ ሳይኮሎጂ ማለት የሰው ልጅን አእምሮ እና ባህሪ የሚያጠና ሳይንስ ነው።👌

የምትወዱት❤️ ሳይኮሎጂ Trick👇

ሚዛን ለማይደፋ ምክንያት የምታዝኑ ከሆነ አንድ ሰው ናፍቃችኋል ወይም ደግሞ አንድን ሰው ናፍቃቹታል።

አንድን ሰው ብዙ ጊዜ ስትገናኙት አይን አይችሁን የሚያያችሁ ከሆነ ያ ሰው ተመችታቹታል እንዲሁም ከእናንተ ጋር ሲሆን ደስተኛ ይሆናል ማለት ነው።

( Crush ) የአይን ፍቅር የሆናቹበት ሰው እናንተን በ20% የበለጠ ቆንጆ እንደሆናችሁ ነው የሚመለከታችሁ።

10000% በሳይኮሎጂ ሳይንቲስቶች የተረጋገጠ ነው።

©️Yofantech
©️Dani_Apps
👆ፌስቡክ ሜታ ቨርስ

Facebook Meta verse
👆 በ GOOGLE ላይ "241543903" ይህን ቁጥር ፅፋችሁ ምስሎችን ስትፈልጉ የምታገኙት የተለያዮ ሰዎች ጭንቅላታቸውን ፍሪጅ ውስጥ ከተው የሚያሳዩ ምስሎችን ነው።😁


©️Ethio_Cyber
©️Dan_Apps
ቶማስ ኤዲሰን ብዙ ተሳስቶ አምፖልን ፈጠረ።

📝 ስለስህተቶቹ ሲያወራ ግን እንዲህ ይላል
" እኔ ብዙ ስለሞከርኩ ደስተኛ ነኝ ምክንያቱም ሁሌም ስሞክር ወይ ልክ ነኝ ወይ ደግሞ ተምሬበታለው" ይለናል። ያለፉ ስህተቶቻችንን ለከፍታችን መጠቀም አለብን፤ ሰሞኑን ካጋጠመኝ ችግር ምን ተማርኩበት እንበል። ሁለቴ መውደቅ የሚፈልግ የለም መቼም...አሸናፊ ማለት የማይወድቅ አይደለም፤ ቢወድቅም መልሶ የሚነሳ ነው። የሆነ ነገር አልሳካ ሲለን እስኪ ምንድነው ያጎደልኩት ብለን ጊዜ ወስደን ማሰብ አለብን። ከስህተት በላይ ምን አስተማሪ ነገር አለ? እንደውም ምርጥ አርጌ ደግሜ እንድሰራው እድል ተሰቶኛል ማለት አለብን።

©️TechEthioOfficial
©️Dani_Apps
😉 እንዳያመልጣችሁ!
1 BNB በአሁን ሰዓት 20,835 ብር ነው!
ብዙዎቻችን BNB ለማግኘት Gas fee እንጠየቃለን ግን ያለምንም ክፍያ በነፃ
👇🔥🤑

👉 START

Start ካደረጋችሁ በኋላ 6 ቻናሎች አሉ እነሱን join ታደርጋላችሁ 3 የtweeter አካውንት አለ እሱንም follow ታደርጋላችሁ ከዛ ከTrust wallet ላይ የ bnb አድሬስ አስገብታችሁ Withdraw ማድረግ

ዋሌቱ እንደዚ አይነት ነው👇 bnb ብሎ ነው ሚጀምረው
bnb1486eh8qmhunmht8xzml07y54697plamwfsvlwk
👏 Finally Verified On Google

ከብዙ ሂደቶች በኋላ Dani Apps ን በጉግል ላይ እንደ አንድ የ ቢዝነስ ድርጅት አስመዝግበናል።

5 ኮኮብ ⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️ በመስጠት ድጋፍዎን ያሳዩን

Give Us 5 Stars ⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

👉 https://g.page/r/CYhVwdbaF335EA0/review
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አይነቶች

📍የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓቶች ማከናወን በሚችሉት ተግባር ጥልቀት እና ስፋት መሰረት ጠቅለል ባለ መልኩ በሦስት ምድቦች ይከፈላሉ፡፡ እነዚህም፡-

#Artificial_Narrow_Intelligence (ANI)
#Artificial_General_Intelligence (AGI)
#Artificial_Super_Intelligence (ASI)

📍በዚህ ጽሁፍ Artificial Narrow Intelligence (ነጠላ-ተግባር ተኮር አስተውሎት) ወይም በግርድፍ ትርጉሙ ጠባብ አስተውሎት የተባለውን በአጭሩ ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡

📍የሰው ልጅ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምር እና ትግበራን ከጀመረ አንስቶ በስኬት ተግባር ላይ ያዋለው ይህን የነጠላ-ተግባር ተኮር አስተውሎት መሆኑ ይነገራል፡፡

📍ሚዲየም በተባለው ድረ-ገጽ ሀተታ መሰረት ነጠላ-ተግባር ተኮር አስተውሎት ትኩረቱ በአንድ ነጠላ ተግባር ላይ ብቻ ነው፡፡ በዚህ አይነቱ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማሽኖች በተቀመጠላቸው መለኪያ መሰረት በገደብ የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው "ደካማ" አስብሏቸዋል፡፡

📍ነጠላ-ተግባር ተኮር አስተውሎት በማሽን ለርኒንግ እና ዲፕ ለርኒንግ ታግዞ ባለፉት አስርት ዓመታት በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገብ ችሏል፡፡

📍ለዚህ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አይነት ሲሪ፣ ጎግል አሲስታንት፣ ኮርታና፣ ቼዝ የሚጫወቱ ስልተ ቀመሮች፣ የፊት ገፅታ መታወቂያ ስርዓቶች (facial recognition) እንዲሁም የድምፅ መታወቂያ ስርዓቶች (speech recognition) አይነተኛ ምሳሌ መሆን ይችላሉ፡፡

©️EIIA
©️Dani_Apps
Microsoft Windows 11 Pro'ን ሲጀምር Microsoft Account #የግድ አስፈላጊ መሆኑ አይቀሬ ነው።

©️ethio_techs
©️Dani_Apps
ኢንሳ ስያሜዉን “ከኤጀንሲ” ወደ “አስተዳደር” መለወጡን ገለጸ።

📍የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ(INSA) ስያሜውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር” (Information Network Security Administration (INSA) በሚል መቀየሩን አስታወቀ።

📍ተቋሙ ቀደም ሲል በአዋጅ ቁጥር 808/2006 መሰረት “የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ” ተብሎ ሲጠራ መቆየቱን ገልጿል።

📍በኢፌዴሪ መንግስት አስፈጻሚ አካላት ስልጣን እና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ 1263/2014 አንቀጽ 78(3) በተመለከተዉ መሰረት ነው ስያሜውን “የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር” (Information Network Security Administration (INSA) በሚል የቀየረው።

©tikvahethiopia
©️Dani_Apps