ጥበብን አስተምረው!
፨፨፨፨//////////፨፨፨፨
ከብዙዎች ጋር የጠለቀ ግንኙነት ነበረህ፣ በስሜት፣ በጊዜ እራስህን ሰተሃቸው፣ ማንነትህን ሰውተህላቸው አንተነትህን አጋርተሃቸው ህይወትን በደስታና በፍቅር ለመግፋት ብዙ ጥረሃል። ጥረትህም ፍሬ ያፈራበት ወቅት ነበረ፣ እንዲሁም ያልጠበከውን ክስተት ያመጣብህም ወቅት ነበረ። ነገሮችን መያዝ በምትችለው ልክ ትይዛቸዋለህ፣ ከአቅምህ በላይ ሲሆኑም ትለቃቸዋለህ። ነገር በጥበብ ቢያዙ፣ በማስተዋል ቢሰበሰቡና በተለየ ትኩረት ልትከታተላቸው የሚገቡ የህይወት ስጦታዎች ይኖራሉ። ሁሉን ጥለህ ባዶህን እንዳትቀር፣ ከሁሉ ሸሽተህ በብቸኝነት እንዳትሰቃይ ቢያንስ እራስህን በጥበብ ምራው፤ በእውቀት፣ በማስተዋል አስተዳድረው። ልብ ለልብ ተግባባው፤ ፍቅርን ለግሰው፤ ሰላምን አድለው።
አዎ! ጀግናዬ..! ጥበብን አስተምረው! እውነተኛውን ፍላጎት የሚሰጠው ፈጣሪ ነው፤ በትክክለኛው መንገድ የሚመራው አምላክ ነው፤ ለመልካም ነገር የሚያዘጋጀው፣ በበጎ መንገድ የሚመራው፣ በሩን የሚከፍተው፣ ሁሉን የሚያዘጋጀው እርሱ ድንቅ አባት፣ ቸር አምላክ ነው። የማይቻል የሚመስል ነገር መፈለግህን አትጥላው፤ ለብዙዎች ያልተቻለን ነገር ለመሞከር በመጣርህ አትፍራ፤ የልብህን መሻት፣ የውስጥ ፍላጎትህን ለማሳካት በመነሳትህ ምንም ሃፍረት አይሰማህ፤ በሰዎች ንግግር አትሸበር፤ አትሸነፍ። የመልካም ነገር ሁሉ ምንጭ ፈጣሪ ነውና ባንተ ላይ ስራውን እንዲሰራ፣ ተዓምራትን እንዲያደርግ፣ ጥበቡን እንዲገልፅ ፍቀድ።
አዎ! የተመረጥከው ያለአቅምህ አይደለም፤ ያለችሎታህም አይደለም። መመረጥህ ሰለምትችለው ነው፤ ያንተ የሆነው በምክንያት ነው። እራስህን ብታዳምጥ የምታተርፈው አንተ እንጂ ሌላ ማንም አይደለም፤ ከእራስህ ጋር ብታወራ፣ ያለህበትን ስፍራ ቆም ብለህ ብታስተውል፣ ሌላው ቀርቶ ለእራስህ የዋህ መሆን ብትጀምር፣ ለእራስህ ወደማሰብ ብትመጣ የሚደሰተው ያከበርከው አንተና የምትወዳቸው፣ የሚወዱህ የቅርብ ሰዎችህ ናቸው። ጥበብ የህይወት በር ነች፤ በእርሷ የሚገባም ህይወቱን ያድሳል፤ በአምላኩ ሃይል ይታነፃል፤ መንፈሱን ያነቃል፤ የምድርን ፈተና በብርታት ይሻገራል፤ እራሱን ይሆናል፤ በምርጫውም የሚገባው ስፍራ ላይ ይገኛል። ጥበብን በልብህ፣ ፍቅርን በውስጥህ አንግበህ ተተጓዝ፤ አምላክ እንደ ፍቃዱ እንዲያኖርህም በርህን በአዎንታዊነት ክፈተው።
@createAvision

👍1🥰1
አልተሰበርክም አትሰበርም!
፨፨፨፨፨///////////፨፨፨፨፨፨
ልባችሁ እንደተሰበረ የተሰማችሁ፣ እምነት እንደተነሳችሁ፣ ዋጋ እንዳጣችሁ የምታስቡ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ልባችሁ እንዳልተሰበረ፣ አንደማይሰበር ከዛም በላይ በብዙ እጥፍ እንደሚሻሻልና እንደሚጠነክር በሚገባ ትመለከታላችሁ። ሰብሮኝ ሄደ ባልሽበት አፍሽ ስለመሔዱ የምታመሰግኚበት ጊዜ ይመጣል፤ ከድታኝ ተሰወረች ባልክበት አንደበትህ አስተምራህ እንደሔደች ሰትመሰክር ትገኛለህ። መጠላት፣ መገፋት፣ መወገዝ ከደረሰብህ አድራሹ ይጨነቅ እንጂ አንተ ልታዝን አይገባም። የሚጎዳህ በገዛ ሀሃሳቡና ጥረቱ ነው፤ የሚጠላህ በእራሱ ሰውነት ነው፤ የሚገፋህ በእራሱ የአስተሳሰብ ልክ ነው፤ የሚያወግዝህም የእራሱን ጊዜ ተጠቅሞ ነው።
አዎ! ጀግናዬ..! ለደረሰብህ ነገር ያለህን አመለካከት፣ የሰጠሀውን ግምት አስተካክል እንጂ አልተሰበርክም አትሰበርም፤ አልተጎዳህም አትጎዳም። ነገሮችን ቀድመህ ለመረዳት ብትሞክር መገፋት ያልከው ክስተት ለተሻለው መጠራት፣ ለሚመጥንህ መመረጥ እንደሆነ ይገባሃል፤ አራስህ ላይ በሰራህ ቁጥር አጣዋቸው የምትላቸው ሰዎች እንዳጡህ ትገነዘባለህ፤ እንዳመለጥካቸው የሚገባህ ጊዜ ይመጣል። እንደተሰበርክ ካላመንክ፣ ህመሙን ደጋግመህ ማጣጣም ካልጀመርክ፣ ዋጋቢስነትህን አብዝተህ ለእራስህ ካልነገርክ፣ በሰዎች በደረሰብህ በደል እራስህን ካልመዘንክ፣ በሌሎች ዘንድ ባለህ ስፍራ ቦታህን ካልወሰንክ መውደቅህ ቢፈለግም፣ የስምህ መጥፋት አሳሳቢ ቢሆንም፣ ያንተ ኋላ መቅረት ቢያስጨንቅም ይህ ሁሉ ሊሆን እንደማይችል እርግጠኛ ሁን።
አዎ! በእሳቤህ ልክ ቀና ብለህ መኖር ትችላለህ፤ ለእራስህ በምትሰጠው ቦታ መጠን የተስተካከለና የተረጋጋ ህይወት መመስረት ትችላለህ። መቻል አለመቻልህ ለእራስህ በምትሰጠው ግምት እንደሚወሰን እወቅ። ማረጋገጫ ፍለጋ የምትዞርበት፣ ተቀባይነት ለማግኘት ያልሆንከውን የምትሆንበት፣ ለውድቀትና ለስብራት እራስህን የምታመቻችበት ምክንያት የለም። የደረሱብህን ጫናዎች ሁሉ የተሻልክ አንተን ለመፍጠር እንደመጡልህ መልካም አጋጣሚዎች ማሰብ ጀምር። ያኔ እራስህን መስበር ታቆማለህ፤ ያኔ ለቅሶህ ይገታል፤ ያኔ ህመምህ ያበቃል፤ ያኔ የበታችነትህ ስፍራውን ይለቃል፤ ያኔ እድገትና ከፍታህ ይፋጠናል፤ ያኔ ንቃትና በእራስመተማመንህ ይጎለብታል። በእርግጥ እንደታመምክ ቢሰማህም በስተመጨረሻ ከህመሙ ነፃ የምትሆነው የህመሙን የመጨረሻ እርከን ተቋቁመህ ስታልፍ እንደሆነ አስታውስ።
For any
comment:-@luck2412
JOIN US 👇👇👇👇👇👇👇👇

🥰1
🌊የምታቀው የውሃ ኩሬ ራቅ ብለህ ስትመለስ ደፍርሶ ቢጠብቅህ...ንጹህ ውሃን ለመጠጣት ያለህ አማራጭ ድፍርሱ እስከሚጠራ መጠበቅ ብቻ ይሆናል ። "አፈር የተቀላቀለበትን ውሃ እንዲጠራ ከፈለግክ፤ተወው አታማስለው" ይላል ፈላስፋው አለን ዋትስ። በመተው፤በመረጋጋት፤ በዝምታ፤ ለፍተን ያጣናቸውን ውድ የህይወት ስጦታዎች እናገኛለን።
🌪ልክ እንደዚህ ሁሉ በህይወታችን የሚገጥሙንን ችግርና እንቅፋቶችን አንዳንዴ የምናጠራቸው መሃል ላይ እጃችንን ስለከተትን ብቻ ላይሆን ይችላል ። አንዳንዴ ዝምታችን እና ትእግስታችንም ብዙ ነገሮች በራሳቸው ጊዜና ሁኔታ እንዲስተካከሉልን እድል ይሰጡልናል ። እኛ ችግራችንን ለመፍታት የምናደርገው ጥረት ይበልጥ ችግር ውስጥ እንዳይዘፍቀን መጠንቀቅ ይኖርብናል ። አለዝያ የችግሩ አሳዳጊ እና አባባሽ እንጂ የችግሩ ፈቺ አንሆንም ።
🌊ለተረጋጋ አይምሮ አለም ትገበራለች ብሏል ጥንታዊው ፈላስፋ። ምንም እንኳን ብዙ ነገሮች በጥረትና በሩጫ የሚገኙ ቢሆንም፤ አንዳንድ ወሳኝ ነገሮች ግን በእርጋትና በመተው እንዲሁም በዝምታ የሚገኙ ናቸው።

ኤልያስ ሽታኹን
እኔን ያሳሰበኝ የፍቅርሽ እርጀና
አንቺን ያሳሰበሽ የወሬው ቁንጅና፡፡
* * * * * *
እስቲ
ለቀቅ አርጊውና የሴትነት ወጉን
እወነቱን ተናግረሽ በሰጠሽ ማዕረጉን፡፡
እኔን ያሳሰበኝ መኖር ከራስ እኩል
አስቸገረኝ እንጂ
"ውደድር" ሰይጣኑ ደርሶ ባንቺ በኩል፡፡
የምታሰቢውን
የምታወሪውን
የምትለብሽውን ስታረጊው ኖረሽ ለሴት እኩዮችሽ
እሱ ሲያሳስብሽ ህይወትም ተወችሽ፡፡
ሰው ጉባኤ ሆኖ ይቅር አይሰብሰብ
እየውልሽ ዓለሜ
አንዳንዱ እኮ ነገር ለራስ ነው ሲታሰብ፡፡
ስትፎካከሪ
ስትከራከሪ
ብቻሽን ብትቀሪ
ላያስተዛዝኑሽ ምንም ብትጎጂ
አያባብሉሽም ይለኩሻል እንጂ፡፡
@createAvision
@createAvision
@createAvision
እኔን ያሳሰበኝ የፍቅርሽ እርጀና
አንቺን ያሳሰበሽ የወሬው ቁንጅና፡፡
* * * * * *
እስቲ
ለቀቅ አርጊውና የሴትነት ወጉን
እወነቱን ተናግረሽ በሰጠሽ ማዕረጉን፡፡
እኔን ያሳሰበኝ መኖር ከራስ እኩል
አስቸገረኝ እንጂ
"ውደድር" ሰይጣኑ ደርሶ ባንቺ በኩል፡፡
የምታሰቢውን
የምታወሪውን
የምትለብሽውን ስታረጊው ኖረሽ ለሴት እኩዮችሽ
እሱ ሲያሳስብሽ ህይወትም ተወችሽ፡፡
ሰው ጉባኤ ሆኖ ይቅር አይሰብሰብ
እየውልሽ ዓለሜ
አንዳንዱ እኮ ነገር ለራስ ነው ሲታሰብ፡፡
ስትፎካከሪ
ስትከራከሪ
ብቻሽን ብትቀሪ
ላያስተዛዝኑሽ ምንም ብትጎጂ
አያባብሉሽም ይለኩሻል እንጂ፡፡
@createAvision
@createAvision
@createAvision
👍1🥰1