።CORE NOTE📚
2.24K subscribers
232 photos
99 files
108 links
ᴘʀᴇᴘᴀʀᴇ ʏᴏᴜʀsᴇʟғ ғᴏʀ ᴍᴏʀᴇ.
Contact : @kenny_adane
Follow us:

https://linktr.ee/dr.core1
Download Telegram
የብቃት ምዘና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
___

ጤና ሚኒስቴር በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተና ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ የጤና ባለሙያዎች የፈተና ምዝገባው ከየካቲት 24 - መጋቢት 07/2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ መግለፃችን ይታወሳል። ነገር ግን አንዳንድ ተመራቂዎች የቴምፖራሪ ዲግሪ ያልደረሰላቸው መሆኑንና ምዝገባው እንዲራዘምላቸው በተደጋጋሚ መጠየቃቸው ይታወቃል። ስለሆነም ምዝገባው እስከ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን ለምዝገባው ቴምፖራሪ ዲግሪ መያዝ ግዴታ መሆኑን እናሳስባለን።

© MOH


@core_note
👍2
Best of luck to Jimma University Medical Center Clinical year 2 students who are starting their Qualification Written Exam tomorrow!!

@core_note
57👍4🔥2
ለጤና ባለሙያዎች ለጤናቸው ብቻውን ሚኒስቴር

ከ EMA እና FMOH በተሻለ ለጤና ባለሙያው መብት ተሟግቷል!

የታመሙ የጤና ባለሙያዎች ጎደኞቻችንን ለምኖ አሳክሟል! እየረዳ ይገኛል ።

ከ2011ዓ/ም ጀምሮ ድምፃችን ሆኗል!

EMA /FMOH እውቅና ሲሰጠው አላየንም ። EMA ከሳምንታት በፊት ለተወሰኑ ባለሙያዎች እውቅና እንደሰጠ ልብ ይሏል።

ዶ/ር አብርሃም አርዓያ | የሀኪም ገፅ መስራች እና የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ከልብ እናመሰግናለን ። ሁሌም እኛ የጤና ባለሙያዎች ከጎንህ ነን! በርታ!
40👍4
Best of luck to Arsi University's C2 medical students who are going to start their qualification exam tomorrow.
@core_note
5👍2
ቀድሞ_መፍረድ_ለህሊና_ፀፀት_ይዳርጋል

ዶክተሩ በድንገት ተደውሎለት ለአስቸኳይ የቀዶ ህክምና በጥድፊያ ወደ ሆስፒታሉ እየገባ ነው።

በተቻለው አቅም የስልክ ጥሪውን በአግባቡ አስተናግዷል። የህክምና ልብሱን በአስቸኳይ ቀይሮ ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል እያመራ ሳለ ኮሪደሩ ላይ የዶክተሩን መምጣት እየተንጎራደደ ይጠብቀው የነበረውን ሰው አገኘው።

"እንዴት ለመምጣት ይህን ያህል ግዜ ይፈጅብሀል? የልጄ ህይወት ልትጠፋ አደጋ ላይ እንዳለች አይታይህም? ህሊና የለህም?" ብሎ ዶክተሩ ላይ ጮኸበት።

ዶክተሩም በትንሹ ፈገግ አለና ,,,,
"አዝናለሁ ሆስፒታል ውስጥ አልነበርኩም። የስልኩን ጥሪ ከተቀበልኩ በሗላ በቻልኩት ፍጥነት እዚህ ለመድረስ ጥሬያለሁ አሁን አንተም ብትረጋጋ እኔም ስራዬን ብሰራ መልካም ነው" ብሎ ሊያረጋጋው ሞከረ።

ሰውየው ግን ,,,
"ተረጋጋ ነው ያልከው? ያንተ ልጅ ቢሆንስ አሁን እዚህ ክፍል ውስጥ ሆኖ ትረጋጋ ነበር? ልጅህ ቢሞት ምን ታደርግ ነበር?" አለ አባት በቁጣ።

ዶክተሩ አሁንም በትንሹ ፈገግ አለና እንዲህ መለሰለት
"የአምላክ ፈቃድ ይሁን። ዶክተር ህይወት ሊያራዝም ሊያጠፋም ሊተካም አይችልም ግን የቻልነውን ያህል እንጥራለን። እንደ አምላክ ፍቃድ ልጅህም ይድንልሀል አንተ ብቻ ተረጋጋ" አለው አሁንም ፈገግ እያለ።

ሰውየውም ,,,
" ባልገቡበት ጭንቀት አስተያየትና ምክር መስጠት ቀላል ነው" እያለ አጉረመረመ። ቀዶ ጥገናውም የተወሰነ ሰዓታትን ወስዶ በሰላም ተጠናቀቀ ዶክተሩ በደስታ እየተጣደፈ ከቀዶ ጥገናው ክፍል ውስጥ ወጣ።

ለአባትየውም ,,,,
"ፈጣሪ ይመስገን ልጅህ ተርፏል።" ብሎት የአባትየውን መልስ ሳይጠብቅ "ማንኛውም ጥያቄ ካለህ ሌሎች ረዳት ዶክተሮችን መጠየቅ ትችላህ።" ብሎት ዶክተሩ መንገዱን በሩጫ ቀጠለ።

የልጁም አባት "ለምንድነው ዶክተሩ እንደዚህ ስሜታዊና ችኩል የሆነው? ምናለ አሁን አንድ ደቂቃ ስለ ልጄ ሁኔታ ብጠይቀው?" ሲል ተናገረ።

ይህን የሰማችው ነርስ እንባ በጉንጮቿ እየጎረፈ ,,,,
"ትላንት ነበር የዶክተሩ ልጅ በመኪና አደጋ የሞተው። ለልጅህ ህክምና ስንደውልለት የልጁ ቀብር ላይ ነበር አሁን ያንተን ልጅ ህይወት ታደገ የራሱን ልጅ ደግሞ የቀብር ስርዓት ሊጨርስ በሩጫ ሄደ።" አለችው።

አባት ከሰዓታት በፊት ዶክተሩ ያሳየውን ፈገግታ እያሰበ ተንሰቀሰቀ። የፀፀት ለቅሶ

አንድ ሰው ምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንዳለ ሳታውቅ
ለመፍረድ አትቸኩል

"#ቀድሞ_መፍረድ_ለህሊና_ፀፀት_ይዳርጋል"

#Stolen
😭5👍2
4
"ከ915 በላይ የህክምና ባለሙያዎች ከስራ ለቀዋል፣ " - የትግራይ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር

የትግራይ የህክምና ባለሞያዎች ማኅበር የሰሜኑ ጦርነት ከጀመረ ጀምሮ እስከ አሁን 915 የህክምና ባለሙያዎች ከትግራይ ክልል ከስራ ለቀው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እና ወደ ውጭ ሀገር የተሰደዱ መሆናቸውን የማህበሩ ፕሬዝዳንት ዶክተር ብሩክ ልሳነውርቅ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

በተጨማሪም ከእነዚህ መካከል 200ዎቹ ዶክተሮች ናቸው ያሉት ዶክተር ብሩክ ሌሎቹ ግን በህክምና ሞያዎች ላይ ያሉ ናቸው ብለዋል።

የማህበሩ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ብሩክ ልሳነወርቅ በክልሉ ከዚህ በፊት በነበረው ጦርነት እና ከዛም በኋላ በሚፈጠሩ አለመረጋጋቶች ብዙ የህክምና እስፔሻሊስቶች ከሥራ እየለቀቁ ወደ ጎረቤት አፍሪካ ሀገሮች እንዲሁም ወደ አውሮፓ እንድሰደዱ ምክንያት ሆኗል ብሏል።

የህክምና ባለሙያዎች የገጠማቸው ችግር ምንድን ነው ?

" ከ2013 ዓ.ም ሰኔ ጀምር እስከ 2015 ታህሳስ ድረስ የ17 ወር ደመወዛቸው አልተሰጣቸውም፣ በጦርነቱ ሰዓትም ሥራቸውን ሲሰሩ ነበር፣ እስከ ፌደራል ድረስ ጥያቄ አቅርበናል፣ ምላሻቸው 'እኛን ሳይሆን እንትናን ጠይቁ' ነው፣ ስንጠይቅም 'ወደዛ ሂድ ፣ ወደዛ ሂድ' ነው የሚሉን፣ ብቻ ግን ምላሽ እያገኘን አይደለም " ብለዋል።

" ጥያቄያችን ገንዘብ ሚኒስቴር ደርሶ ነበር፣ የአንድ ዓመት ብቻ ነው በጀት ያለኝ ጥያቄያችሁ ወደ ፖርላማ ይሂደ ብሎን ነበር ገንዘብ ሚኒስቴር ፣ ትግራይ ደግሞ የፖርላማ ተወካይ የላትም ፣ አሁንም ችግሮች እየተባባሱ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ምን ያክል ባለሙያዎች ከስራ ለቀዋል ሲል ቲክቫህ ዶክተር ብሩክን ጠይቋል

የማህበሩ ፕሬዝዳንት በምላሻቸው "እስካሁን ባለን መረጃ 915 የህክምና ባለሙያዎች ለቀዋል፣ አብዛኞቹ ዶክተሮች ናቸው ያሉ ሲሆን የባለሙያዎች መልቀቅ እየጨመረ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

" የሰራበት ደመወዝ ሳይሰጠው ሲቀር የህክምና ባለሙያዎች ወደ አፍሪካ ሀገሮች ነው የሚሄዱት፣ አንጎላ፣ ሶማሌላንድ፣ ሶማሊያ ነው የሚሄዱት፣ አብዛኛው የሚሰደዱት ስፔሻሊስቶች ናቸው "ብለዋል።

"ሌላው ደግሞ ሥራውን እየለቀቁ ተደራጅተው የግል ሥራ እየሰሩ ነው፣ ምክንያቱም የህክምና ባለሙያዎች የሚማሩት እስከ 10 አመት የው፣ ከዛም በሥራ የሚከፈለው ደመወዝ አናሳ ነው፣ አሁን በትግራይ የተከሰተው ከህክምና ባለሙያነት እየለቀቁ ወደ ሌሎች ስራዎች እየገቡ ነው።

ከጦርነት አልፈው እዚህ ቢደርሱም አሁን በክልሉ እየተፈጠረ ያለው አለመስማማት ድጋሜ ወደ ሌላ ጦርነት እንገባለን የሚል ስጋት አድሮባቸዋል፣ በዚህም ባለሙያዎች ስራቸውን ለቀው እንዲሰደዱ አድርጓል " ሲሉ አስረድተዋል።

የባለሙያዎችን ችግር ከመቅረፍ አንፃር ማኅበሩ በርካታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ዶክተር ብሩክ ልሳነወርቅ ተናግረዋል።

በዚህም፥ " የህክምና ባለሙያዎች በአነስተኛ የብድር ወለድ ከባንኮች ገንዘብ እንዲያገኙ ለማድረግ እየሰራን ነው፣ ኤግዚቢሽኖችን በማዘጋጀት ከዚህ በፊት የባለሙያዎችን ችግር ለመንግስት እና ህዝብ ለማሳወቅ ሞክረናል " ብለዋል።

ፕረዚዳንቱ አክለውም በዋናነት ችግሩን ለመቅረፍም "የመኖሪያ ቤት መስሪያ መሬት እንድሰጣቸው ኮሚቴ አዋቅረን እየጠየቅን ነው" ሲሉ ጠቁመዋል።

የህክምና ባለሙያዎች ከስራ ገበታቸው ለቀው መውጣታቸው በክልሉ ምን አሉታዊ ተጽዕኖ አለው ሲል ቲክቫህ ፕሬዝዳንቱን ጠይቋል።

ፕሬዝዳንቱም " የባለሙያዎች መልቀቅ በቀሩት ባለሙያዎች ላይ የስነልቦና መረበሽ ፈጥሯል፣ ስራቸውን ተረጋግተው እንዳይሰሩ አድርጓል፣ አለመረጋጋት፣ ስለቀጣይ ሥራቸው እንዳያስቡ አድርጓል፣ የስራ መደራረብ፣ ጫና ፈጥሯል ሲሉ ገልፀዋል።

" በዚህም ከስራቸው ለቀው ያልተሰደዱ ባለሙያዎች ሌላ አማራጮችን እንዲፈልጉ፣ እንዲመለከቱ እየተገደዱ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

እስካሁን ባለሙያዎች ሥራቸውን እንዳይለቁ አረጋግቶልን የነበረው "ሻይን ፕሮጀት" ነበር ፣ በመጭው ሰኔ ወር ላይ ይጠናቀቃል ያሉ ሲሆን ፕሮጀክቱም ሲጠናቀቅ የመኖሪያ ቦታ ምሪት አስበናል፣ ካልሆነ ግን ችግሩ ይሰፋል ሲሉ አመላክተዋል።

#TIKVAHETHIOPIA

@core_note
😭3👍21
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን::

በዓሉ የሰላም ፣የደስታ ፣ የጤና ይሁን።
—ዒድ ሙባረክ

On this holiday, wishing you a day filled with lots of joy and happy moments.

—Eid Mubarak
@core_note
6👍2
🖊 Laryngomalacia presents in infants with inspiratory stridor that worsens in the supine position and improves in the prone position

Laryngoscopy shows collapse of the supraglottic structures during inspiration. Concurrent gastroesophageal reflux should be treated. 

Laryngomalacia usually resolves spontaneously by age 18 months.
@core_note
4👍1
ፍትሕ ሚንስቴር

ለዐቃቢ ሕግ ከ35% - 50% የደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም ጭማሪ (ማሻሻያ) ተደረገ
35% 24000+11000
35%-40% 20400+11000
40%-50% 18000+11000

የጤና ባለሙያው😁🤧
@core_note
😭20👍3🤯1
We save lives! Now it's time to save ours!
ህይወት ስናድን ኖረናል! አሁን ግን የራሳችንንም ህይወት ማዳን ይኖርብናል!

#HealthProfessionals #Ethiopia #FMOH #MOE #PMO
👍181👏1
Becoming a doctor is anything but easy; it’s years of sacrifice, sleepless nights, and unwavering dedication. Yet, when the system treats us as expendable rather than essential, it’s time to rise up.

We are not martyrs. We are healers, advocates, and now— #VALIANTS

Enough waiting for change. WE are the change. Together, we’ll reclaim our dignity, protect our future, and fix this broken system.

To every doctor, nurse, and healthcare warrior reading this: Your voice matters. Your fight is just. And with Valiants, victory is possible.

Stay strong. Stand united. Be a Valiant.

Dr. Tesfaye G. Sadam, MD, MPH, Forensic medicine and toxicology specialist
11👍5🔥1
ስራዬ አድካሚ ቢሆንም : ደሞዜ ከ10,000ብር  በታች ቢሆንም : የአእምሮ እርካታ ይሰጠኛል። ሆኖም...

እርካታ ቤት ኪራይ አይከፍልም።
እርካታ በቀን 3 ጊዜ መብላት አያስችልም።
እርካታ ልጆቼን ለማስተማር አያስችልም።
እርካታ ልብስ እና ጫማ ለመቀየር አያስችልም።
እርካታ ትዳር መመስረት አያስችልም።
እርካታ ለታክሲ ወረፋ ከመጠበቅ አያድንም።

ጥያቄያችን ለሁሉም ግልፅ የሆነ ነው። የሚገባንን እንኳን ባይሆን የሚያስፈልገን ይደረግልን። ትኩረት ለጤና ባለሞያዎች!

ዶ/ር ሀብታሙ አለሙ: ጠቅላላ ሀኪም

@HakimEthio
13👍4
A Half-Baked, Flimsy, and On-Again, Off-Again Physician Struggle.

Who's at the helm of this campaign? If you ask me, the biggest stumbling block is the physicians themselves. We're our own worst enemies, frankly! To make real headway, we need to bring in the heavy hitters – the ones who can call the shots and make things happen.

The responsibility for fixing this broken system rests squarely on our shoulders, but our own foolishness has cost us our influence and voice.

Look at the Sudanese Physician Association – they have a seat at the table even when it comes to major national issues and the national council. Our Achilles' heel is our lack of true professional standards.

We're knee-deep in Ethiopia's murky politics, we haven't established a clear distinction from those without our training, and we're also part and parcel of ethical divides and playing power games.

Just look at our disastrous movement from 2012 – we snatched defeat from the jaws of victory because of our selfish personal agendas and political loyalties. We need to fight with a clear vision, well-defined goals, and unwavering consistency, or we're dead in the water from the start.

ህይወት ስናድን ኖረናል! አሁን ግን የራሳችንንም ህይወት ማዳን ይኖርብናል!

We save lives! Now it's time to save ours!

Dr. Robel DAmlaku MD, MPH Radiology resident mekelle university.

#HealthProfessionals #Ethiopia #FMOH #MOE #PMO
10👍4
1