Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗
3.62K subscribers
4.28K photos
141 videos
818 files
1.52K links
Addis Ababa, Ethiopia
Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service.

t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Chat us!
Buy ads: https://telega.io/c/consite
Download Telegram
የግንባታ ጨረታዎች +2👷‍♂🚧

አዲስ ዘመን ዛሬ ነሐሴ 14 ቀን/2018 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ
@consite🏗
👍1
የግንባታ ጨረታዎች +2👷‍♂🚧

አዲስ ዘመን ዛሬ ነሐሴ 15 ቀን/2018 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ
@consite🏗
👍3
የግንባታ ጨረታዎች +1👷‍♂🚧

አዲስ ዘመን ዛሬ ነሐሴ 20 ቀን/2018 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ
@consite🏗
👍2
የግንባታ ጨረታዎች +1👷‍♂🚧

አዲስ ዘመን ዛሬ ነሐሴ 20 ቀን/2018 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ
@consite🏗
👍2
የአዲስ አበባ መሬት አስተዳደር ቢሮ እግድ ተነስቶል።
@consite🏗
👍5
3.2 Price Adjustment formula Sheet (1).xlsx
140.5 KB
👉የዋጋ ማሻሻያ (Price Adjustment) – አስፈላጊነቱ እና ተግባራዊነቱ

የዋጋ ማሻሻያ በግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ ከፍተኛ ሚና ያለው የኮንትራት መርህ ሲሆን፣ በፕሮጀክት አፈጻጸም ወቅት የሚከሰቱ የዋጋ ግሽበቶች፣ የገንዘብ ዋጋ መቀነስ እና የግብዓት ዋጋ ለውጦች ተፅዕኖ እንዳያስከትሉ የሚረዳ መንገድ ነው።

ዓላማው ኮንትራክተሩን እና አሠሪውን ከልክ ያልፈ የፋይናንስ አደጋ መጠበቅ እና ፍትሃዊ ክፍያ ማረጋገጥ ነው።

በኢትዮጵያ፣ በተለይም በመንገድ እና በትልቅ የግንባታ ፕሮጀክቶች፣ የነዳጅ፣ ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ቢቱመን፣ የሰራተኛ ኃይል እና የመሳሪያ ዋጋ ፈጣን መለዋወጥ የዋጋ ማሻሻያን የማይተካ አስፈላጊ መሆኑን አሳይቷል።

ይህ መርህ በትክክል ሲተገበር፣ ፕሮጀክቶች እንዳይዘገዩ፣ ኮንትራክተሮች እንዳይጎዱ እና የህዝብ ገንዘብ በአግባቡ እንዲውል ያግዛል።

📎 ለተግባራዊ አጠቃቀም፣ የዋጋ ማሻሻያ ሂሳብ ማስላት የሚያግዝ Excel ፎርማት አብረን አያይዘናል፤ ለወደፊት አጠቃቀምዎ እንዲረዳ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።
@consite🏗
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኮንትራክተሮች የቢሮ መሃንዲሶች ዲዛይን መሃንዲሶች ኮንትራክተር ለመሆን ያሰባቹ እንዲሁም በግንባታ በግዢ አስተዳደርና በማማከር ዙርያ ያላቹ በሙሉ እስከመጨረሻው አድምጣቹ ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር አድርጉላቸው
@consite🏗
👍2
solid slab design G+4 FROM19-32(1).xlsx
324.7 KB
የ G+4 Slab ዲዛይን ሙሉ ቴምፕሌት አሁኑነ አውርደው ይጠቀሙበት
@consite🏗
👍2
Checklist for Concreting.xlsx
17 KB
የሳይት መሃንዲስ ሆናቹ ስትሰሩ ኮንክሪት ከመሞላቱ በፊት ማረጋገጥ ያለብን ነገሮችን inspect ለማድረግ የሚረዳን ቼክ ማድረጊያ ቼክሊስት ነው በዚህ ቴሌግራም ቻናል ገብታቹ አውርዱት ትወዱታላቹ።
@consite🏗
Checklist for Masonry.xlsx
12.9 KB
የሳይት መሃንዲስ ሆናቹ ስትሰሩ ለማሰነሪ ግንባታ ወቅት ማረጋገጥ ያለብን ነገሮችን inspect ለማድረግ የሚረዳን ቼክ ማድረጊያ ቼክሊስት ነው በዚህ ቴሌግራም ቻናል ገብታቹ አውርዱት ትወዱታላቹ።
@consite🏗
Building+Construction+Calculator+.xls
4.2 MB
የኮንክሪት ሚክስ መጠን የብረት ክብደትና ሌሎችንም በቀላሉ ካልኩሌት የምናደርግበት ቴምፕሌት ነው አውርዳቹ ተጠቀሙበት።
@consite🏗
👍4
🏠 አሁን ላይ 94 ካሬ ሜትር ቤት ለመስራት ስንት ብር ያስፈልጋል?
ቤት ለመስራት ሲያስቡ እነዚህ ጥያቄዎች ያጋጥሙዎታል፡ እነዚህን ካዎቁ ግምቱን ያውቃሉ፡፡

የት ነው የሚገነባው? (አዲስ አበባ ወይስ ከከተማ ውጪ?)
🏗 በምን አይነት ማቴሪያል ይሰራል? (ጂ+0፣ ጂ+1፣ በHCB 15 ወይስ?)


ውጤቱስ
ምን ያህል የቁሳቁስ እና የገንዘብ ወጪ ያወጣል? ምን ምን ያስፈልጋል? ምን ያክል ጊዜ ?
እነዚህን ጥያቄዎች በትክክለኛ መረጃ እና በአጭር ጊዜ ለመመለስ 👉 https://estimator.et/ ላይ በመግባት በነጻ ይሞክሩት!

የፕሮሞ ኮድ CONPROXY26 በመጠቀም 100% በነጻ፡ ሙሉ የ BOQ Excel ፋይል ማውረድ ዝርዝር Material Requirement (የሲሚንቶ፣ የብረት፣ የባላስት ወዘተ ፍላጎት) ማግኘት ይችላሉ!
@consite🏗
👍5
🏗️ ከስራ ተቋራጮች ጋር ሲሰሩ ማወቅ የሚገቡዎት 10 ወሳኝ ነጥቦች:-
- ​በግንባታው ዓለም ስኬታማ ጉዞ ለማድረግ እና ገንዘብዎን ከብክነት ለመታደግ ከስራ ተቋራጮች (Contractors) ጋር ሲያደርጉት የሚገባውን ውልና ጥንቃቄዎች በዝርዝር ተመልከቱ፦
​1. ህጋዊ ፈቃድ እና ምዝገባ 📄
ሥራ ከመጀመራቸው በፊት የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ማረጋገጫ መጠየቅ የመጀመሪያው እና ትልቁ የጥንቃቄ እርምጃ ነው።

​2. የብቃት ማረጋገጫ (Grade)
ተቋራጮች በምን ያህል አቅም እና ካፒታል እንደሚሰሩ የሚገልጽ ደረጃ (ከደረጃ 1 እስከ 10) አላቸው። ለሚሰሩት ፕሮጀክት የሚመጥን ደረጃ ያለው መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።

​3. የስራ ልምድ (Portfolio) 🏢
ከዚህ በፊት የሰሩዋቸውን ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች፣ የተጠናቀቁ ህንፃዎች ወይም ሌሎች ግንባታዎች በአካል በመሄድ ወይም በምስል ማየት የብቃታቸው ትልቁ ማሳያ ነው።

​4. ውል እና ስምምነት (Contract) ✍️
በቃል የሚደረግ ንግግር በግንባታ ላይ ቦታ የለውም። የዋጋ ዝርዝር፣ የቁሳቁስ ጥራት፣ የሚጠናቀቅበት ጊዜ እና የክፍያ ሁኔታ በግልጽ የሰፈረበት ውል በህግ ባለሙያ መዘጋጀት አለበት።

​5. የዋጋ ግምት እና ክፍያ (Budget) 💰
ክፍያዎች በሂደት (በደረጃ) እንጂ በአንዴ መፈጸም የለባቸውም። ስራው ሲሰራ እና የጥራት ምርመራ ሲያልፍ ብቻ ክፍያ እንዲለቀቅ ማድረግ ገንዘብን ከብክነት ይታደጋል።

​6. የጊዜ ሰሌዳ (Timeline)
ግንባታው የሚጀምርበትን እና የሚጠናቀቅበትን ቀን በግልጽ የሚያሳይ የጊዜ ሰሌዳ (Schedule) ከውሉ ጋር መያያዝ አለበት። ዘግይቶ የሚጠናቀቅ ስራ ከፍተኛ ተጨማሪ ወጪ ያስከትላል።

​7. የቁሳቁስ ጥራት (Quality Control) 🧱
በውሉ ላይ የተስማሙባቸውን የኮንክሪት መጠን፣ የብረት ዓይነት እና ሌሎች የግንባታ እቃዎች ጥራት በባለሙያ ማስመረመር ለህንፃው ጽናት ዋስትና ነው።

​8. የሰራተኞች ዋስትና እና ደህንነት (Safety) 🦺
በግንባታ ቦታ ላይ ለሚደርሱ አደጋዎች ተቋራጩ ኃላፊነት አለበት። የኢንሹራንስ ሽፋን ያላቸው እና የደህንነት እቃዎች (Safety materials) የሚጠቀሙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተገቢ ነው።

​9. የባለሙያ ቁጥጥር (Supervision) 📐
እርስዎ ራስዎ ኢንጂነር ካልሆኑ፣ የስራውን ሂደት የሚከታተል ገለልተኛ አማካሪ (Consultant) ወይም መሐንዲስ መቅጠር ተቋራጩ ጥራቱን የጠበቀ ስራ እንዲሰራ ይገፋፋል።

​10. የዋስትና ጊዜ (Defect Liability Period) 🔑
ስራው ተጠናቆ ከተረከቡ በኋላም እንኳ ለተወሰነ ጊዜ የሚፈጠሩ ስንጥቆች ወይም ጉድለቶች በባለቤቱ ወጪ ሳይሆን በተቋራጩ እንዲስተካከሉ በውሉ ላይ መካተት አለበት።
@consite🏗
👍6
በግንባታ ሳይት ላይ የብረት እና የካንሰል መታጠፊያ (Bar Bending Board/Bench)! 🏗️

​በምስሉ ላይ እንደምናየው ከእንጨት እና በሁለት የብረት ፒኖች የተሰራው ይህ መሳሪያ በሳይት ላይ የካንሰል (Stirrups) እና የተለያዩ የመዋቅር ብረቶችን በጥራትና በፍጥነት ለማጠፍ ያገለግላል።

በብረት ማጠፍ ስራ ወቅት ትኩረት የሚሹ 3 ዋና ዋና ነጥቦች፦
1. ​Hook Bend Angle (135° Bending)፦ በሴይስሚክ (Seismic) መመዘኛዎች መሰረት የካንሰል መንጠቆዎች (Hooks) በ 135° መታጠፍ አለባቸው፤ በ 90° ማጠፍ መዋቅሩን ለክስረት ይዳርጋል።

2. ​Bend Radius (የመታጠፊያ ራዲየስ)፦ ብረቱ በሚታጠፍበት ጊዜ እንዳይሰነጠቅ ወይም እንዳይዳከም የፒኖቹ ዲያሜትር (Pin Diameter) ከብረቱ ውፍረት ጋር የተመጣጠነ መሆን አለበት።

3. ​Accuracy & Uniformity፦ የካንሰሎች መጠን እኩል መሆን የኮንክሪት ከቨር (Concrete Cover) በሁሉም አቅጣጫ የተስተካከለ እንዲሆን ይረዳል።


በእርስዎ አካባቢ ወይም ሳይት ላይ ይህን የብረት መታጠፊያ መሳሪያ በሀገር ውስጥ ስም "ምን ብላችሁ ትጠሩታላችሁ?" ሃሳብዎን በኮሜንት ያካፍሉን!👇@ConsitesolutionBot

@consite🏗
👍3
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂይ
ጨረታ ቁጥር፡_002/2019
በሸገር ከተማ የመልካ ኖኖ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የመኪና ጎማዎች፣ ፈርኒቸሮችና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ሕጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው የተጫራቾች መመርያ መሠረት ጨረታውን እንድትካፈሉ ተጋብዘዋል።


የጨረታ ዝርዝር ሁኔታዎች፡-
የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ) በሲንቄ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1054472341218 ገቢ በማድረግ ገንዘብ ገቢ የተደረገበትን የባንክ ስሊፕ በመያዝ ወደ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ጽቤት በመሄድ የገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ የጨረታ ሰነዱን ከመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።


የተጫራቾ ግዴታዎች፡-
1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN No ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ተመዝጋቢ መሆናቸውንና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
5. በፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በኦሮሚያ ገንዘብ ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
6. ማንኛውም ተጫራች በባንክ የተመሰከረ የጨረታ ማስከበሪያ CPO 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችል።
7. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ ወጪ ጭኖ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በመውሰድ ገቢ ማድረግ የሚችል።
8. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ላይ የሚያቀርበው ዕቃ በሙሉ ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ ዕቃ ማቅረብ የሚችል።
9. ማንኛውም ተጫራች ባለው ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ዘርፍ ላይ ተመስርቶ የጨረታ ሰነድ የተዘጋጃው በሎት ስለሆነ በፈለገው የሎት ዓይነት ብቻ መርጦ ወይምሙሉውን ሎት ገዝቶ መወዳደር የሚችል።
10. አሸናፊ ተጫራች የውል ማስከበሪያ ዋስትና 10% ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።
11. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በትክክል በመሙላት ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የመንግሥት የሥራ ቀናት ውስጥ በመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላል።
12. ጨረታው በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፦ 
ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በሸገር ከተማ የመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
@consite🏗
👍7
Forwarded from Mule.B Tesfalidet
🧱New Point Bricks factory 新点砖厂🧱 Red brick:- This is the classic brick color that you see Quality with affordable price 🧱ጥራት ያላቸውን እና ለተለያዩ ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የቀይ ሸክላ (ጡቦችን) እናመርታለን።
🧱 ለሙሉ የቤት ግንባታ፣
🧱ለባንክ ቤት ካዝና፣
🧱 ለግቢ አጥር ማጠሪያ፣
🧱 ለመንገድ ዳር ጠርዞች፣
🧱  ለሆቴሎች፣ሬስቶራንት፣እና ካፌዎች ማሳመሪያ ፣
🧱 ለx-ray ክፍሎች፣
🧱 ለፍሳሽ ማንዋሎች፣
🧱 ለኪችን ሲንክ ማስቀመጫ ፣
🧱 ለሻወር ገንዳ ማሰቀመጫ፣
🧱 የPBC ፍሳሽ ማስወገጃ ለመሸፈን፣
🧱 ለአበባ መትከያ
🧱 ለብረት ማቅለጫ ፈርኒስ፣
🧱 ለፒዛ ኦቭን፣
🧱 ለምድጃ፣
🧱 ለቆሻሻ ማቃጠያ፣
*We produced High quality clay bricks for various construction purposes.
🧱 For building construction,
🧱 For bank vaults,
🧱 Fence for the yard,
🧱 For road edges,
🧱 For Hotels,Restaurants,and Cafes decoration,
🧱 For x-ray rooms,
🧱 For manuals,
🧱 For kitchen,
🧱 For shower tray
🧱 To cover PBC drains,
🧱 For garden,
🧱 Furnace For steel factory,
🧱 For pizza oven,
🧱 For waste incinerator.... 🧱 For more information join our telegram channel https://t.me/+d8A-rQlF5p5lZThk & Ticktok account @newpointbricksfactory 🧱Order now 📲0912854327,0902378888 🧱"Quality is our first priority" Thank you 谢谢🧱