COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE
7.1K subscribers
71 photos
7 videos
53 files
103 links
Welcome To Computer & Mobile Maintenance Channel.
It Gives You Some Hints To Repair(Improve Performance Of) Your Computer & Mobile By Yourself. ለጠጋኞችም የሚጠቅም ምርጥ ቻናል ነው!
JOIN @Computer_Mobile21
Contact @seen311 or @seen3bot

Group👉 @Computer_Mobile3
Download Telegram
#pc_board
A particular pc internal components
#techno_news
ጎግል በአይነቱ ልዩ የሆነ የመተርጎሚያ ሲስተም ይፋ አደረገ!


👉እርሶ በሚያውቁት ቋንቋ በሚናገሩበት ጊዜ የራሶን ድምፅ በሌላ ቋንቋ ቢያደምጡት ምን
ሊሰማዎት ይችላል፡፡ በእርግጠኝነት ከመገረም አልፈው ራሶን ሊጠራጠሩ ይችላሉ፡፡ እርሶ
በሚያወሩበት ጊዜ የራሶን ድምፅ ከአናጋገር ስልቶ ጋር በሌላ ቋንቋ ማድመጥ እውነትም
መገረም ብቻ አይደለም ሌላም ነገር ሊያስደርግ ይችላል፡፡ ይሁንና ጎግል
ይፋ ያደረገው አዲስ ሲስተም ይህን መገረም ወደ እውነታ የቀየረ ነበረ፡፡

@computer_mobile_maintenanc_ethio

👉ኩባንያው ልዩ በሆነው በዚህ ፈጠራው ሌሎች ቋንቋዎችን በቀላሉ እንድናውቅ ከማገዙ ባለፈ
በመተርጎም ሂደት ውስጥ የግድ አስፈላጊ የነበረውን የሶስተኛ ወገን አጋዥነት እንዲቀር
አድርጓል፡፡ Translatotron በሚል የተሰየመው አዲሱ ሲስተም ጎግል ከዚህ በፊት ሲሰራቸው
እንደነበሩት የመተርጎሚያ ዘዴዎች ፅሁፍን መሰረት ያደረገ ሳይሆን ንግግርን በንግግር በቀጥታ
በመተርጎም፣ በዚያ ላይ ደግሞ የተናጋሪውን ድምፀት እና የአነጋገር ስልት የሚጠብቅ ነው፡፡
ከዚህ በፊት እንደሚታወቀው ጎግልም ይሁን እና ሌሎች ድርጅቶች የትርጉም ቴክኖሎጂን
ወይም ሲስተምን ሲተገብሩ ሶስት ስቴጆችን ወይም ደረጃዎችን በመጠቀም እንደሚተገብሩ
ይታወቃል፡፡ በዚህም የመጀመሪያው፤ ንግግርን ወደ ፅሁፍ በመቀየር የሚሰራው አውቶማቲክ
የድምፅ መለያ ሲሆን ሁለቱ ቀጣይ ደረጃዎች ደግሞ ፅሁፉን ወደ ሌላ ቋንቋ በመቀየር
የሚሰራው የመተርጎሚያ ማሽን እና የተተረጎመውን ፅሁፍ ወደ ድምፅ መልሶ የሚያመጣ ስቴጅ
ነው፡፡
ይሁንና አዲሱ የጎግል መተርጎሚያ ሲስተም ይህን የተወሳሰበ አካሄድ በአንድ በማምጣት
ምንም የፅሁፍ አጋዥነት ሳያስፈልግ የተናጋሪውን ድምፅ ብቻ በመውሰድ በሚፈለገው ቋንቋ እና
በዛው ድምፅ ለመተርጎም የሚያስችል ነው፡፡ ይህም ለፈጣን ትርጉም ከማገዙ ባለፈ ስህተት
የሚፈጠርበትን እድል በማሳነስ የተሻለ እና የተስተካከለ የመተርጎም ስርዓት ይዘረጋል፡፡
ሲስተሙ እነዚህን ጉዳዮች ለመፈፀም ልዩ ስፔክትሮግራም (spectrograms) እንደ ግብዓት
የሚጠቀም ሲሆን ይህም ትዕዛዞቹን ተቀብሎ ወደሚፈለገው ቋንቋ ለመተርጎም የመጀመሪያውን
ሂደት የሚፈጥር ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሲስተሙ neural vocoder እና speaker encoder
የተባሉ የድምፅ ማስተላለፊ ገብዓቶችን በመውሰድ የተናጋሪውን ድምፀት ከስልቱ ጋር
በማዋሃድ ለመተርጎም የሚያስችል ነው፡፡

Join us @computer_mobile_maintenanc_ethio
avastclear.exe
521.5 KB
#app
if avast antivirus disturbs your pc .....using this avastclear app you can remove it from your pc. https://t.me/computer_mobile_maintenanc_ethio
Baidu WiFiHotspot.rar
9.3 MB
#app
using this app, you can share your pc connections to anyother pc or mobile through wifi. https://t.me/computer_mobile_maintenanc_ethio
#start_menu #software To "refresh" the Start Menu, follow these steps:

👍🏻Open the "Run command" window by pressing WIN+R.
(i.e. hold down the Windows key and then press R.)
👍🏻Type "cmd" at the prompt, and press Enter.
👍🏻Wait for the command prompt to open.
(It will be a flashing cursor block.)
.At the command prompt, type this:
taskkill /IM explorer.exe /F
You should notice these all vanish: Start Menu, Taskbar, any open File Explorer windows.
.Type this at the command prompt:
explorer.exe
Now those components should all load back in.
Close the command prompt and try the Start Menu. Hopefully it should have refreshed.

join https://t.me/computer_mobile_maintenanc_ethio
#RAM #software

HOW TO USE PEN DRIVE AS RAM

1. First of all plug your USB in the USB port and make sure that you do not have any important data on USB.

2. Open your “My Computer” and Right click onto the USB. Which you want to use as RAM.

3. Select “Properties” (the last option) from the drop down menu.

4. A new window will open select “Ready Boost” Tab from there. And tick on the “Use this device” button.

5. Select the space which you want to use for RAM.

6. Finally click onto the “Apply” and then finally “OK” button.

7. That’s it you have successfully used your USB (Pen drive) as a virtual memory (RAM) for your computer.

@computer_mobile_maintenanc_ethio
# Rooting #software
(rooting /jailbreak) ምን ማለት ነው

👉 አንድን ስልክ, ታብ, ወይንም ሌላ ዲቫይስን #ሩት ማድረግ ማለት ያን device ከካምፓኒው ቁጥጥር ነፃ ማድረግ ማለት ነው።

@computer_mobile_maintenanc_ethio

ምን ጥቅም አለው ?

✔️ አንድን ስልክ #ሩት ስናደርግ ስልኩን የሰራው company ለእኛ ከሰጠን ማንኛዉም የአጠቃቀም ገደብ አልፈን ስልኩ ን እንደፈለግን መጠቀም እንችላለን።

✔️ ካምፓኒው እንዲጫኑ የማይፈቅዳቸውን apps access ማድረግ እንችላለን ።

✔️ ስልኩን ስንገዛው ተጭነው የሚመጡትን ሲስተም አፖች ማጥፋት እንችላለን።

ጉዳቱስ

👉 ስልኩን ከሰራው ካምፓኒ ነፃ እስካደረግነው ድረስ ስለስልኩ security ማስተማመኛ የለንም
ይህ ማለት ስልኩ በቫይረስ የመጠቃት እድሉ የሰፋ ነው።

⚠️ ከኢትዮጵያ ውጪ ለሆናችሁ
አብዛኞቹ ሀገራት ስልክዎትን ሩት ማድረግን ቢፈቅዱም በአንዳንድ ሀገራት በወንጀል ያስጠይቃል።

⚠️ስልክዎት በተለይ ሀይኮፒ ስልክ ከሆነ ሩት ባያደርጉ ይመረጣል።
ሩት ማድረግ አስፈላጊ ቢሆን እንኳን ቶሎ unroot ማድረግ ይመረጣል ።

@computer_mobile_maintenanc_ethio
#websites

የኮምፒዩተር ሳይንስ ትምህርትን መማር ለምትፈልጉ በሙሉ

5 የነፃ የኮምፒዩተር ሳይንስ መማሪያ ድህረገፆች:

@computer_mobile_maintenanc_ethio

1᎐ Stanford Engineering Everywhere(SEE)

ይህ ድረገጽ በአሜሪካ ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ የሚዘጋጅ ሲሆን ለተማሪዎችና ለባለሙያዎች ያለምንም ክፍያ ትምህርቶችን በኢንተርኔት የሚያሰራጭ ነው። ድረገጹ በሶስት ዋና ዋና ኮርሶች ላይ ያተኮረ ሲሆን እነርሱም በኮምፒዩተር ሳይንስ፣ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ እና ኤሌክትሪካል ምህንድስና ናቸው።

2᎐ MIT Open Courseware

የማሳቹሴት ቴክኖሎጂ ኢንስቲቱዩት የሚያሰራጨው የድረገጽ ዓይነት ሲሆን ለተማሪዎች ለመምህራን እንዲሁም ለባለሙያዎች የኢንተርኔት ትምህርትን ያለገደብ በነጻ የሚያቀርብ ነው። ይህ ድረገጽ የተለያዩ ኮርሶችን ባማረ አቀራረብ ለተጠቃሚዎች የሚያደርስ ሲሆን ሜካኒካል ምህንድስና፣ ሂሳብ፣ ኮምፒዩተር ሳይንስ እና ሌሎችም የትምህርት ዘርፎች ይሰራጩበታል።

3᎐ GitHub.com

GitHub በአለም ላይ የኮዲንግ ምሳሌዎችን በቀላል አቀራረብ የሚያቀርብ እና ተማሪዎችን ከታወቁ የሶፍትዌር ፕሮግራመሮች ጋር የሚያገናኝ ድህረገጽ ነው። እንዲሁም የተለያዩ ታዋቂ ባለሙያዎች ያበለጸጓቸውን ሶፍትዌሮች በቀላሉ በማቅረብ ተማሪዎች እንዲማሩበትና እንዲለማመዱበት የሚያስችል የድህረገጽ ዓይነት ነው።

4᎐ W3 Schools

ይህ ድህረገጽ በተለየ መልኩ የፕሮግራሚንግ አሰራርንና የኮዲንግን ቋንቋ በተግባር አስደግፎ የሚያሳይ ሲሆን ቀላል ምሳሌዎችን ጥልቀት ካለው ቲቶሪያል ጋር እንደ AJAX፡ SQL፣ ASP፣ CSS፣ JAVA Script እና HTML ባሉ የኮዲንግ አሰራሮች ላይ ትምህርት የሚሰጥ ይሰጣል። በተጨማሪም በድረገጹ የሚቀርቡት የተለያዩ የመማሪያ ግብአቶች ተማሪዎችን በሁሉም ደረጃ የሚፈልጉትን መረጃ እንዲያገኙ በማስቻል ፕሮጀክታቸውን በስኬት እንዲያጠናቅቁ ይረዳቸዋል።

5᎐ Codecademy

አዳዲስ የኮምፒዩተር ሳይንስ ሃሳቦችንና ቴክኒኮችን በቀላሉ የሚያቀርብ ሲሆን ራስን በራስ ለማብቃት የሚረዱ የተለያዩ ኮርሶችንም ያለምንም ክፍያ በማቅረብ የሚታወቅ ድህረገጽ ነው። በተለይ ለኮዲንግ ጀማሪዎች አሰራሩን ከመነሻው እንዲረዱት ከማስቻሉም በላይ አዳዲስ ክህሎቶችንና አሰራሮችን ለማግኘት ተመራጭ ነው።

ብዙ መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ ሼር ያድርጉት::

Join us 👉 @computer_mobile_maintenanc_ethio
#software #disks

ዛሬ የምናየው እንዴት አድርገን አንድ ሎካል ዲስክን ወደ ሁለት ክፍልፋዮች እንደምንቀይር ነው

@computer_mobile_maintenanc_ethio

ለምሳሌ Local disk C: ካለን ከሁለት ለመክፈል

#1_right click on My computer

#2_ከዛ Manage የሚለውን እንነካለን

#3_ከዛ ከሚመጡት ምርጫዎች ውስጥ disk management የሚለውን እንመርጣለን

#4_ከዛ ለመክፈል የምንፈልገውን ዲስክ C:
በመምረጥ right click እናደርጋለን

#5_ከዛ shrink volume የሚለውን እንመርጣለን ትንሽ ሰከንድ ይቆያል

#6-ከዛ የምንፈልገውን መጠን በመፃፍ shrink የሚለውን click አድርጎ መጠበቅ

#7_ከዛ በጥቁር ቀለም ከታች (unlocated) የሚለው ላይ right click ማድረግ

#8_click on "new simple volume
ከዛ next next next እያሉ እስከመጨረሻው መቀጠል::

ይሄን ስናደርግ ምንም አይነት መረጃ አይጠፋብንም።
ካልፈለግን ደግሞ ወደ ነበረበት መመለስ እንችላለን።

@computer_mobile_maintenanc_ethio

ለአስተያየትና ጥያቄ @seen311
#techno_news

ህንድ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ስፔስ ልታደርግ የነበረውን ጉዞ ከአንድ ሰዓት በታች ጊዜ ሲቀረው በቴክኒክ ችግሮች አማካኝነት ሰርዛለች፡፡ ሳተላይቱ በምስራቃዊ ህንድ ስሪሃሪኮታ ስፔስ ሰኞ 2፡51 ለመንቀሳቀስ ፕሮግራም እንደነበረ ቢቢሲ በዘገባው ገልጿል፡፡ የተሰረዘው የስፔስ ጉዞ መቼ እንደሚደረግ በቀጣይ የሚገለፅ መሆኑም ተገልጿል፡፡

@computer_mobile_maintenanc_ethio

Source #ENA
#hardware_disk

This is HARD DRIVE which stores all our computer data including OS

@computer_mobile_maintenanc_ethio
አውሮፕላን እንዴት ነው የሚበረው??


📌📌አሁን ላይ ያሉ የዘመኑ አውሮፕላኖች ቀድሞ ለመጀመሪያ ጊዜ በነ "wright brothers"ከተሰራው አውሮፕላን ጋር ተመሳሳይ ህግን(principle of aerodynamics) በመጠቀም ነው የሚበሩት። አውሮፕላን እንዴት እንደሚበርር ለማወቅ መሠረታዊ የፊዚክስ እውቀት መያዝ አስፈላጊ ነው። እነርሱም :-

1. Forces of flight(የማብራሪያ ጉልበቶች)
2. The Bernoulli's principle
3.Newton's first law and third law

➙➙Forces of flight(የማብራሪያ ጉልበቶች)

#Lift:-አውሮፕላኑ አየር ላይ እንዲቆይ ያደርገዋል። ይህም ጉልበት(force) ከአውሮፕላኑ ክብደት በተቃራኒ አቅጣጫ የሚተገበር ጉልበት ነው።

#weight( ክብደት):- ወደ ምድር እምብርት የሚጎትተው ጉልበት ነው። አውሮፕላኑ እንዲበር ከክብደቱ ተቃራኒ አቅጣጫ የሚተገበር (lift force) ጉልበት ያስፈልጋል።

#Drag:-ይህ አይነት ጉልበት(force) ደግሞ በአውሮፕላኑ እና በአየር መካከል ያለ ጉልበት ነው። ይህም ጉልበት አውሮፕላኑ ላይ ወደ ኋላ የሚተገበር ጉልበት ነው።

#Thrust:- ከአውሮፕላኑ ሞተር የሚመነጭ እና አውሮፕላኑ ወደ ፊት እንዲሄድ የሚያረግ ጉልበት ነው።


📌📌የኒውተንን ህግ በአውሮኘላን ላይ ያለውን ከበርኖሊ ህግ ጋር በማድረግ ለመቃኘት እንሞክራለን።


📌📌Bernoulli's principle:-በርኖሊ ያጠናው ስለ ፈሳሽ እንቅስቃሴ(hydrodynamics) ነው። Hydrodynamics ውስጥ ከገለፃቸው ነገሮች አንዱ ፈሳሽ በፍጥነት በሚሄድበት ግዜ የሚፈጥረው ግፊት ያነሰ ይሆናል። ይህ ሀሳብ በተቃራኒውም ይሰራል። ስለ በርኖሊ ይህን ካልን ወደ አውሮፕላን እንቅስቃሴ እንምጣ። በመጀመሪያ ከአውሮፕላኑ ሞተር በሚመጣው ጉልበት እንቅስቃሴ ይጀምራል። በዚህም ጊዜ የኒውተን የመጀመሪያ ህግ ስራ ላይ ይውላል። ይህም ህግ የሚለው እንቅስቃሴ ላይ ያለ ነገር በእንቅስቃሴ ይቀጥላል ወይም በእረፍት ላይ ያለ ነገር በእረፍት ይቀጥላል ውጫዊ ጉልበት እስካልተተገበረ ድረስ። ከዚያም በአውሮፕላኑ ክንፍ (Airfoil) አማካኝነት አውሮፕላኑ እያለፈበት ያለው አየር ለሁለት ይከፈላል። የላይኛው የክንፍ አካል (curve) በመሆኑ ከላይ ያለው የአየር ፍሰት ፍጥነት በመጨመር ግፊት እንዲቀንስ ይሆናል። በታች በኩል ያለው አየር መጀመሪያ የያዘውን ግፊት ይዞ ይቀጥላል። ትልቅ ግፊት ደግሞ ወደ ዝቅተኛ ግፊት ስለሚሄድ ከታች ወደ ላይ ግፊት ሲሄድ አውሮፕላኑ ወደ ላይ እንዲገፋ ያደርገዋል።ይህም ቀደም ሲል የጠቀስነው "Lift" እንዲፈጠር ያደርጋል።"Lift" ከአውሮፕላኑ ክብደት በሚበልጥ ጊዜ አውሮፕላኑ እንዲሳፈፍ ያደርገዋል። በሶስተኛው የኒውተን ህግ ደግሞ የክንፎቹ ተግባር "lift" እንዲያደርግ ይረዳዋል።

@computer_mobile_maintenanc_ethio

ለአስተያየት @seen311
@computer_mobile_maintenanc_ethio

#techno_news

250 ሚሊየን የጂ ሜይል አድራሻዎች ‘ትሪክቦት‘ በተባለ ቫይረስ መጠቃታቸው ተገለፀ❗️

⚡️ትሪክቦት‘ በመባል በብዛት የሚታወቀው የኮምፒውተር ቫይረስ ተመልሶ በመምጣት መረጃዎችን እየመተነፈ መሆኑ ተሰምቷል።

⚡️እስካሁን ባለው መረጃም ‘ትሪክቦት‘ የተባለው ቫይረስ በዓለም ዙሪያ 250 ሚሊየን የጂ ሜይል አድራሻዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙ ነው ጥናት ያመለከተው።

⚡️ዲፕ ኢኒስቲክት የተባለ ኩባንያ ባወጣው ጥናት መሰረት በቭይረሱ ጥቃት ከደረሰባቸው የጂሜይል አድራሻዎች ውስጥ የተወሰኑት አሜሪካ፣ የብሪታኒያ እና የካናዳ መንግስት መስሪያ ቤት አድራሻዎች መሆናቸውን ያመላክታል።

⚡️ቨይረሱ የተጠቃሚውን አድራሻዎች ከወሰደ በኋላ በወሰዳቸው አድራሻዎች ላይ በራሱ ኢ ሜይል የሚልክ ሲሆን፥ የሚፈልገውን መረጃ ከሰበሰ በኋላም የላካቸውን መልእክቶች መልሶ ያጠፋል ተብሏል።በዚህም ምክንያት ተጠቃሚዎች በቫይረሱ ስለመጠቃታቸው ለማወቅ ይቸግራልም ብሏል ጥናቱ።

⚡️በጥናቱ እንደተለየው ከሆነ ከጂ ሜይል አድራሻዎች በተጨማሪም 19 ሚሊየን የያሆ አድራሻዎች፣ 11 ሚሊየን የሆት ሜይል እድራኛዎች እና በሚሊየን የሚቆጠሩ የAOL፣ MSN እና Yahoo.co.uk አድራሻዎችም ለቫይረሱ ተጋልጠዋል።

@computer_mobile_maintenanc_ethio
@computer_mobile_maintenanc_ethio

#techno_news

#ማይክሮሶፍት የዊንዶው 7 #ማሻሻያን ሊያቋርጥ ነው::
--------------------

#ማይክሮሶፍት ላለፉት 10 አመታት አገልግሎት የሰጠውን #የዊንዶው 7 ኦፕሬቲንግ ሲስተም እንዲቀይሩ ላለፉት ስድስት ወራት #የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን ቢሰራም ተጠቃሚዎች በተፈለገው መጠን ወደ አዲሶቹ #የዊንዶው ምርቶች አለመሳባቸው ተጠቁሟል፡፡

#ኮሌክቲቭ ይፋ ያደረገው ጥናት እንደጠቆመው ከሆነ 18 በመቶ የሚሆኑ ግዙፍ #ኩባንያዎች አሁንም ወደ ዊንዶው 10 ምርት ፊታቸውን #አለማዞራቸወን ይፋ አድርጓል፡፡

#በ2019 መጀመሪያዎቹ 43 በመቶ ኩባንያዎች የዊንዶው 7 ምርቶችን እንደሚጠቀሙ የገለጹት #ተመራማሪዎች ከዚህ ውስጥ 17 በመቶ የዊንዶው 7 ምርት አገልግሎት እደሚቋረጥ እንኳ ምንም #እንደማያውቁ ተጠቅሷል፡፡

ሆኖም #ማይክሮሶፍት ደንበኞቹ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የዊንዶው 7 ምርቶችን ያለምንም ችግር እዲጠቀሙ እያደረገ ይገኛል፡፡

#የማይክሮሶፍት ዊንዶው ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተጠቃሚዎች ብዛት በአለም አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ ከሆኑ የኦፕሬቲንግ ሲስተሞች በ50 በመቶ የሚልቅ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

#የማይክሮሶሰፍት ዊንዶው 10 ምርት የአንበሳውን ድርሻ የሚወስድ ሲሆን የደህንነት ሁኔታውን ጥሩ እንዳደረገው ተጠቁሟል፡፡ የዊንዶው 7 ኦፕሬቲንግ ሲስተም አገልግሎቱ #በፈረንጆቹ ጥር/2020 እንደሚቋረጥ ይጠበቃል፡፡

Join join join 👇👇👇👇👇👇👇
@computer_mobile_maintenanc_ethio
👇👇👇👇👇👇👇

Contact @seen311
#software

How to download youtube video without any software?

Simple,
👉 open your video
👉 look above on search bar
👉 on URL address of the video add 'dl' between www. & YouTube.....
👉 then enter

@computer_mobile_maintenanc_ethio
@computer_mobile_maintenanc_ethio

#software
የሜሞሪ ካርድ ወይም USB ፍላሽ ካርድ መጠን(storage capacity) እንዴት ማሳደግ እንችላለን? በዚህ ዘዴ አማካኝነት እስከ 16GB ማሳደግ እንችላለን::

#ሜሞሪዎ ወይም ፍላሽዎ በቂ ዳታ ስለማይዝልዎት ተጨማሪ
ፍላሽ ወይም ሜሞሪ ለመግዛት አስበው ከሆነ ከመግዛትዎ
በፊት እቺን ያንብቡ፡፡
እርግጥ ነው በየግዜው ሜሞሪያችን ላይ ወይም ፍላሻችን ላይ
የተለያዪ ፋይሎች ስንጭን ሰፔሱ እያነሰ መሄዱ ወይም
መሙላቱ አይቀርም፡፡ ታድያ በዚህ ግዜ የሚመጣልን ሀሳብ
አዲስ መግዛት ሊሆን ይችላል፡፡ አሁን የምናሳይዎት ዘዴ ግን
ከዚህ ሀሳብ ይገላግልዎታል፡፡ በዚህ ዘዴ አማካኝነት 2Gb
Flash ወይም Memory እስከ 16Gb ድረስ ማሳደግ
ይቻላል፡፡ ቀጥለው ያሉትን ስቴፖች ተግባራዊ በማድረግ ፍላሽና
ካርድ ሳይዝ ማሳደግ ይችላሉ፡፡

1. Sdata tool የሚባል software ያውርዱ፡ ሶፍትዌሩን
ለማውረድ የሚከተለውን ሊንክ መጠቀም ይችላሉ https://
www.4shared.com/zip/2kWbL88r/SDATA.html
ጎግል ላይም sdata tool ብላችሁ ብትፈልጉ ታገኙታላችሁ
2. ካወረዳችሁት በህዋላ sdata.zip የሚለውን right click
በማድረግ extract አድርጉት፡ ከዛ sdata tool.exe የሚለው
ራይት ክሊክ በማድረግ run sdata tool as administrator
የሚለውን ይምረጡ፡ አሁን install አድርገነዋል ማለት ነው
3.ፍላሻችሁ ወይም ሜሞሪያቹን ፎርማት አድርጉና
ኮምፒተራችሁ ላይ ሰኩ ፡ አስፈላጊ ፋይል ካለው ፎርማት
ከማድረጋችሁ በፊት PC ላይ ኮፒ አድርጉት፡፡
4.ማሳደግ የምትፈልጉትን drive ይምረጡ፡፡፡ ለምሳሌ
ፍላሻችሁ/ሜሞሪያችሁ Drive E ላይ ከሆነ ያለው E
ትመርጣላችሁ
5. ከዛ To 4Gb,8Gb,16Gb የሚል አማራጭ ይሰጣቹሃል፡፡
ፍላሻችሁ/ሜሞሪያችሁ 2gb ከሆነ መጀመርያ ወደ 4 ነው
የምትቀይሩት በቀጥታ ወደ 16gb ማሳደግ አይቻልም፡፡ 4gb
የሚለው ላይ ትመርጡና E-compress click ታደርጋላችሁ፡፡
4gb ከሆነልን በህዋላ ደግሞ ወደ 8gb ከዛም ወደ 16gb
ማሳደግ ትችላላችሁ፡፡ 4ና8 ጂቢም እነዚህ ስቴፖች ተከትለን
ማሳደግ እንችላለን፡፡
4gb= መጀመሪያ ወደ 8gb ከዛ ወደ 16gb
8gb= በቀጥታ ወደ 16 gb
# Notice እዚህ ላይ ግን አንድ መርሳት የሌለብን ነገር አለ፡፡
ሜሞሪውን/ፍላሹን ካሳደግነው በህዋላ Format ማድረግ
የለብንም፡ Format ካደረግነው ግን ፍላሹ/ሜሞሪው ወደ
Original ሳይዙ ይመለሳል፡፡

@computer_mobile_maintenanc_ethio
👍2
@computer_mobile_maintenanc_ethio

#techno_news
ሰው ሰራሽ ዜና አንባቢ በቻይና ይፋ ሆነ
******************************
ቻይና በአለም የመጀመሪያውን ሰው ሰራሽ ዜና አንባቢ ይፋ
አደረገች፡፡
ሰው ሰራሽ ዜና አንባቢው ማሽን የሰው መልክ ያለው ሮቦት ነው
ተብሏል፡፡
ሮቦቱ በቻይና ብሔራዊ የዜና ተቋም በሆነው ሽንዋ ዜናዎችን
ሲያነብ የድምጽ አወጣጡ፣ የፊትና የእጅ እንቅስቃሴ እውነተኛ
ሰውን እንደሚመስል ተነግሯል፡፡
‹‹ሶጎዮ›› በሚባል የቻይና የኢንተርኔት መረብ እና በሽንዋ
የበለፀገው ሮቦት እረፍት ሳያደርግ በቀን ለ24 ሰዓት መረጃ
የማቀበል አቅም እንዳለው ተነግሯል፡፡
ሮቦቱ በቻይንኛ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች መረጃዎችን
ለተመልካቾች እንደሚያቀርብ ተጠቋሟል፡፡
ምንጭ፦ ዘ ጋርዲያን

@computer_mobile_maintenanc_ethio
አስተያየት @seen311
@computer_mobile_maintenanc_ethio

ፌስቡክ ላይ የምንፅፈውን ፅሁፍ በከለር(በቀለም) ለመፃፍ የሚረዳን ኮድ የሚከተሉት ናቸው።
<fg=b0000000> ....black........ጥቁር
<fg=b0ff7f00>.......Orange........ብርቱካናማ
<fg=b0ffff00>.......yellow......ቢጫ
<fg=b000ff00>......green.......አረንጓዴ
<fg=b0964b00>.......light brown.......ፈዛዛ ቡናማ
<fg=f0f00f0f>.......red.......ቀይ
<fg=b0800000>.......brown.......ቡኒ
.
አጠቃቀም፦
ለምሳሌ.....በቀይ ቀለም ለመፃፍ
<fg=f0f00f0f>ፅሁፉን(text)

@computer_mobile_maintenanc_ethio
@computer_mobile_maintenanc_ethio

#መዝናኛ
የሌለ መርቅኖ እናቱን በስልክ እያወራት ስንት ሰአት ነው ትለዋለች ኪሱን ፈተሸና..
.
.
እማዬ ጉድ ሆንኩልሽ .. ስልኬን ተበላሁ።

@computer_mobile_maintenanc_ethio