COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE
7.11K subscribers
71 photos
7 videos
53 files
103 links
Welcome To Computer & Mobile Maintenance Channel.
It Gives You Some Hints To Repair(Improve Performance Of) Your Computer & Mobile By Yourself. ለጠጋኞችም የሚጠቅም ምርጥ ቻናል ነው!
JOIN @Computer_Mobile21
Contact @seen311 or @seen3bot

Group👉 @Computer_Mobile3
Download Telegram
What is Smart Tv ? ስማርት ቲቪ ምንድነው

Smart Tv ማለት ከ ሌሎች Tv በተለየ መልኩ ኢንተርኔት የሚሰራ በተጨማሪም በ ኢንተርኔት አማካኝነት ሌሎች ፕሮግራሞችን የሚያቀርብ ማየት የሚያስችል Tv ማለት ነው ወይም ደግሞ ኮምፒውተር Tv ውስጥ ገብቶ መጣ ልትሉ ትችላላችሁ

እኛ ሀገር የምንጠቀመው Tv ስማርት ሳላልሆነ
ኢንተርኔት አይሰራም እኛ ሀገር ስማርት Tv ቢኖርም ከ ስንት አንዱ ቤት ነው ደግሞ እኛ ሀገር #ስማርት Tv ሚባለው( ፍላት የሆነ flash የሚቀበል የመሳሰሉ Tvወች ናቸው #ስማርት ሚባሉት

እውነቱ ግን ስማርት Tv ከዛ የሚበልጥ ብዙ ነገሮችን ይሰራል

ምንድነው እስኪ የስማርት Tv እና መደበኛ ወይም Convintional Tv ልዩነቱ

መደበኛ or Convintional Tv የምንለው አብዛኞቻችን ቤት ውስጥ ያለው Tv ሲሆን አንቴና ያለው flash የማይቀበል በ size ትልቅ የሆነ ከ Tv ፕሮግራም ውጭ ሌላ ማይሰራ ነው + በጣም ደባሪ ነው እንዴት ካላቹኝ Tv እያየን ዝናብ ከመጣ ስርጭቱ ይቋረጣል አንቴናው ከተበጠሰ አይሰራም ከቦታ ወደ ቦታ ለማንቀሳቀስ ከባድ ነው flash አይጎርስም Tvው ከተበላሸ መለዋወጫ accessorie ብዙ የለውም ሌላም ብዙ አስቀያሚ ነገር አለበት ማለት ባጭሩ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል ማለት ነው።

@Computer_Mobile21
#ስማርት Tv ከ መደበኛ or Convintional Tv በምን ይለያል

1 በጣም ቀጭን እና ጠፍጣፋ ስለ ሆነ ከ ቦታ ወደ ቦታ ለማንቀሳቀስ አይከብድም ቀላል ነው

2 በስማርት Tv ፕሮግራም እያያችሁ ዝናብ ቢመጣ አይቋጥርም ብዥ አይልም

3 አንቴና የለውም Wireless ነው

4 በከፍተኛ ጥራት ያለው ምስል ያሳያል
720HD 1080 እና 4K የሚባሉትን በከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምስል support ያደርጋል

5 flash እና ሚሞሪ ይቀበላል

6 የራሱ የሆነ file ማስቀመጫ አለው internal storage ማለት ነው

7 ቢበላሽ መለዋወጫ ለማግኝት easy ነዉ

8 የራሱ የሆነ RAM አለው ስለዚህ ስትጠቀሙት ፈጣን ነው

9 Internet ይሰራል Playstore Chrome Opera የመሳሰሉትን

10 እንደ ማንኛውም ስልክ ና ኮምፒውተር የራሱ የሆነ OS Operting System አለው

11 Wifi እና Hotspot Bluetooth አለው

12 ስክሪኑ ትልቅ እና Video ስታዩ ከጥግ እስከ ጥግ ነው
ወይም Full size ነው የሚያሳየው

13 የተለያዩ Application install መጫን ትችላላችሁ

ለምሳሌ
Xender PDF reader Photo editor Music Player Mx player የመሳሰሉትን

13 Wireless ገመድ አልባ ነው

እንግዲህ መደበኛ or Convintional Tv የምንለው Tv
#ስማርት Tv ጋር ስናስተያየው ሰማይና ምድር በሉት ያው ከላይ እንዳያችሁት ጭራሽ አይወዳደሩም + አይገናኙም

የስማርት Tv እና መደበኛ or Convintional Tv የምንለው Tv ልዩነታቸውን አይተናል

አሁን ደግሞ ስማርት Tv ጥቅም እና ጉዳት እንመልከት

Advantage Of Smart Tv የስማርት TV ጥቅም

1 የራሱ የሆነ file ማስቀመጫ internal storage አለው ብለናል ቅድም ማለትም የራሳችን Photo Video Music Application Software የመሳሰሉት ስማርት TVያችን ላይ ማስቀመጥ እንችላለን

ለምሳሌ

ከሰው ላይ የሆነ Application በ xender ለመቀበል ፈልጋቹ የስልካቹ Space ወይም ቦታ Full ከሆነ
አያሳስብም ስማርት TVያቹን ከፍታችሁ መቀበል ትችላላችሁ የምትፍጉትን file ወደ Tvው መላክ እና ከ TVው ወደ ራሳቹ ስል መልሳቹ መቀበል ትችላላችሁ

2 በስማርት Tvያቹ ኢንተርኔት መጠቀም ትችላላችሁ

ለምሳሌ

Chrome - Playstore -Youtube የመሳሰሉትን መጠቀም ትችላላችሁ በተጨማሪም
Chat ታደርጋላቹ Telegram Imo Facebook
የመሳሰሉትን መጠቀም ያስችለናል የፈለጋችሁት Website Access ማድረግ ትችላላችሁ
በ ስልክ እና በ Laptop እንደምትጠቀሙት

3 ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምስል 720 1080 እና 4K የሚባሉትን በከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምስሎችን ያሳያል
8K Support የሚያደርግ ሰ

4 ከ ስልክና ከ Laptop ጋር ይገናኛል Connecte ይሆናል
Wireless ያለምንም ገመድ በ Software በቻ

5 የTvውን ስክሪን እንደ ኮምፒውተር ሞኒተር መጠቀም ትችላላችሁ ማለትም

#ለምሳሌ
በ Laptop Or በ ስልክ ፊልም እያያችሁ የLaptop or የስልካቹሁ Screen Size ትንሽ ከሆነ ከTvው ጋር አገናኝታቹ በTvው ስክሪን ማየት እና መጠቀም ትችላላችሁ
በ Hotspot Bluetooth እና Xender ተጠቅማችሁ ማገናኘት ትችላላችሁ

6 የፈለጋችሁትን Application TVው ላይ መጫን ትችላላችሁ

ለምሳሌ
Netflix YouTube Instagram የመሳሰሉትን TVው ላይ መጫን ትችላላችሁ

7 Memory Crad እና Flash ይቀበላል

8 Earphones ይቀበላል Film በምናይበት ግዜ ጆሮ-ማዳመጭ ማየት እንችላለን

9 Flash እና Memory Crad
ሰክተን ከአንደኛው Flash ወደ Memory Cradዱ File መገልበጥ ማጥፋት Rename ማድረግ እንችላለን

10 የስማርት TVያቹ Remote Control ቢበላሽ ከ ኢንተርኔት ላይ በስልካችሁ የስማርት TV Remote Application አውርዳቹ መጠቀም ትችላላችሁ

11 Timer ሞልታቹ በራሱ እንዲዘጋ ማድረግ ትችላላችሁ

ለምሳሌ
ማታ ፊልም እያያችሁ እንቅልፋችሁ ከመጣ ተነስቶ TVውን መዝጋት ካስጠላቹ Timer ትሞሉና ለ 2 3 4 5 ደቂቃ ትተኛላችሁ ከዛ በ 2ደቂቃ እራሱን በራሱ ይዘጋል እኛ ተነስቶ መዝጋት አይጠበቅብንም

12 ሰአት ቀን/ወር/አመት አለው ሰአት ከሌለን ከTvያችን መመልከት እንችላለን ቀኑንም እንደዛው

13 የስማርት Tv Speakሩ ከፍተኛ ድምፅ ሲያወጣ
High Base አለዉ

14 Energy Save ኤሌክትሪክ ሀይል ይቆጥባል

15 selfi came የፊት ካሜራ አለው በዛ ካሜራ ተጠቅመን Video Chat ማድረግ ትችላላችሁ

ለምሳሌ
Imo Skype WhatsApp የመሳሰሉትን ስትጠቀሙ በ selfi camera ነወየደወላቹለት ሰው እናንተን የሚያያችሁ

ለምሳሌ
Imo WhatsApp Zoom Snap chat የመሳሰሉትን

16 Wifi ይሰራል ፊልም ሙዚቃ መፀሀፍ ማውረድ ትችላላችሁ

17 የተለያዩ ስራወችን ይሰራል ባንዴ እንደ ኮምፒውተር
multitasking

ለምሳሌ
ፊልም እያያችሁ በ Skype Video ለጓደኞቻችሁ መደወል ትችላላችሁ ሙዚቃ እየሰማችሁ ፊልም ማውረድ ትችላላችሁ ሌላም ብዙ ነገር ታደርጋላቹ

18 የራሱ RAM CPU Operating System አለው + በጣም ፈጣን ነው ራማቸዉ 8GB የሆኑ ስማርት Tvወች አሉ Processerራቸው ደግሞ 1.3 GHz የሆኑ አሉ

19 በጨለማ ክፍል ስትከፍቱ ብርሃኑ brightness የተመጣጠነ አይን የማይጎዳ ነው
Disadvantage Of Smart Tv የስማርት TV ጉዳት

1 Security
በ ሀከሮች Tvው ሀክ ሊደረግ ይችላል ሀክ ካደረገ ቦሀላ Tvው ላይ ያስቀመጥነውን File Photo video Application ይወስዳል or ይመለከተዋል ሊያጠፍም ይችላል

2 selfi camera

ሀከሮች የፊት ካሜራ ተጠልፈው እኛ ምን እንደምንሰራ ምን እንደምናደርግ ይመለከታሉ or ይቀዳሉ

3 ስማርት Tvያችን ከ ኢንተርኔት File ስናወርድ virus ሊገባበትና ሊበላሽ ይችላል Anti virus ያስፈልገናል

4 track ይደረጋል

@Computer_Mobile21
4👍4
#mobile_ic #ICs

(IC)አይ ሲ ማለት ምን ማለት ነው ?


አይ ሲ ማለት ብዙ ኮመፖነቶች የሚገኙበት ክፍል ነው::
በውሰጡም Resistor capacitor inductor diode ሌሎቹም ኮምፖነቶች ሊኖሩበት ይችላሉ::
የአይሲ ስራው ብዙ ነው ብቻ ኮምፖነቶችን በመሰብሰብ አንድና ከዛ በላይ የሆነን ስራ ይሰራልናል። ለምሳሌ ሞባይል ላይም ሆነ ቲቪ ላይ ኦዲዬ አይ ሲ፣ ፓወር አይሲ እና ሌሎች አይሲወች ይኖራሉ:: እነዚህ አይሲዎች የራሳቸው ስራ አላቸው።
ለምሳሌ #ፓወር አይሲ የፓወርን አክቲቪቲ ይቆጣጠራል
#ኦዲዬ አይሲ ደሞ የኦዲዬ አክቲቪቲ ይቀጣጠራል ስለ አይሲ ይህን ካልን ወደ ሞባይል ስንገባ ሞባይል ላይም አይሲዎች በብዛት ይገኛሉ::
ማንኛውም ሞባይል ማለትም ሞባይል ከተፈጠረ ጀመሮ እስካሁን ያሉት ሞባይል 9 አይ ሲች አሉት ከድሮ ዳስተር ሞባይል አንስቶ እስከ አይፎን 6+ ደርስ ካሁን በሆላም ለሚፈጠሩት ስልኮች 9 አይሲዎች አሉት ዘጠኙ አይሲ ደሞ ለ3 እንከፍላቸዋለን:

1 ) power and logic part ላይ (6 ic)
2) transmition part of ላይ (2 ic)
3) reception part of ic ላይ (1 ic)
4) power and logic part of ic
5) cpu ic (central processing unit )
ሲ ፒ ዩ ማለት የሞባይላችን ሁሉንም እንቅስቃሴ የሚቆጣጠር የሞባይል አይሲ ነው በአጭሩ የሞባይላችን አእምሮ ይባላል
*የሲፒዩ መበላሸት
Dead phone ,no net work ,no audio out put and
etc….
*እንዴት መጠገን ይቻላል?
አይሲውን ማሞቅ ወይም መለወጥ
* የሲፒዩ ቦታ
በኖኪያ እና በሳምሰንግ ላይ አይሲው በወርቃማ ፍሬም ተከቦ ይገኛል በቻይና ስልክ ደሞ እላዩ ላይ M ወይም speed trum ተብሎ ይጻፍበታል
6) memory ic
ሚሞሪ አይሲ ዳታ እስቶሬጅ ዲቫይስ ነው ለሁለት ይከፈላሉ
a) ROM ( read only memory ) it is permanent data storage ሮም ማለት የስልካችን ዋናው ፕሮግራም ወይም operating system የሚቀመጥበት ማለት ነው buraakiller
* የሮም መበላሸት
Dead phone, black or white screen, dim light
እንዴት መጠገን ይቻላል?
ሶፍትዌሩን ስንጠግን - ፍላሽ ወይም ፎረማት
ሃርድውሩን ስንጠግን - አይሲውን ማሞቅ ወይም መለወጥ
* የሮም ቦታ
ሮም ኖኪያ እና ሳምሰንግ ላይ ብዙ ጊዜ የሚገኘው ከሲፒዩ አጠገብ ነው እና የአይሲው ቅርጽ ሁሌም rectangle ነውይገኛል square ያልሆነ ቻይና ላይ ደግሞ ከሲፒዩ ጋር አብሮ buraakiller
b) RAM (randomly access memory) it is
temporary data storage ራም ማለት የስልካችን ሚሴጅ ኮንታክቶች ሚስኮሎች ሌሎችም ልንደልታቸው የምንችላቸው ነገሮች የሚቀመጥበት ነው
* የራም መበላሸት
No miscall. no dilledcall. no received call . no store photo and music etc…
*እንዴት መጠገን ይቻላል?
ሶፍትዌሩን ስንጠግን - ፍላሽ ወይም ፎረማት
ሃርድውሩን ስንጠግን - አይሲውን ማሞቅ ወይም መለወጥ
* የራም ቦታ ሮም ኖኪያ እና ሳምሰንግ ላይ ብዙ ጊዜ የሚገኘው ከሲፒዩ አጠገብ ነው እና የአይሲው ቅርጽ ሁሌም rectangle ነው square ያልሆነ ቻይና ላይ ደግሞ ከሲፒዩ ጋር አብሮ ይገኛል *note ---- ኖኪያ ስልክ ለይ 1 እሰከ 5 ሮም እና ራም አይሲዎች ይገኝሉ በብዛት ከሮም ራም ያንሳል ልላው ደግሞ ለሰፒዩ በጣም የሚቀርበው ሮም ነው ራም ደግሞ በሳይዝ ከሮም ያንሳል ራም እና ሮም ሚቀመጡበት ቦታ ከኮምፖነት የጸዳ ነው
3) POWER IC
ፓወር አይሲ ዋናው ስራ ከባትሪ ቮለቴጅ ተቀብሎ ለተለያዩ አይሲዎች ፓወር መስጠት ነው
ለምሳሌ ከባትሪ 3.7 ቮልቴጅ ይቀበልና ለሲፒዩ 1.5 ቮልቴጅ ለሚሞሪ አይሲ ደግሞ 2.8ቮልቴጅ ያከፋፍላል
*የፓወር አይሲ መበላሽት
Dead phone ,no net work ,no audio out put and etc….
*እንዴት መጠገን ይቻላል?
አይሲውን ማሞቅ ወይም መለወጥ
***የፓወር አይሲ ቦታ
በኖኪያ ስላክ ለይ ለሁለት ዕንከፍለዋለን
a) የድሮ ኖኪያዎች ከሆኑ ማለትም 1st generation ከሆነ ብቻ ፓወር አይሲ ለብቻው ተነጠወሎ እናገኘዋለን ከአጠገቡም RTC የተባለ ኮሞፖነት እናገኛለን::
b) አሁን የሚገኙ ኖኪያዎች ደግሞ አራት አየሲዎች በአንድ አይሲ ተጠቃለው ይገኛሉ የዚ አይሲ ስም UEM(universal energy management) ይባላል እዚ አይሲ ላይ አራት አይሲዎች ይገኛሉ እነሱም Power ic, audio ic, charge ic, ui ic ይገኛሉ ይሄ አይሲ የምነለየው RTC አጠገቡ በመኖሩ ነው::
ቻይና ስልክ ላይ ደሞ አሁንም ልክ እንደ ሚሞሪ አይሲ ከሲፒዩ ጋር አብር ይገኛል ብቻ ሁሉም ስልክ ላይ RTC የተባለው ኮምፖንት አብሮት ይገኛል።

@Computer_Mobile21
5👍4😁1
እንኳን ለ 2017ዓ.ም አደረሳችሁ! አደረሰን
በአዲሱ ዓመት ምን አቅደዋል? 
👉የሞባይል ጥገና ስልጠና
👉መሠረታዊ የኮምፒዩተር  ስልጠና
👉የሶላር ጥገና ስልጠና
👉 የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስልጠና

በብቁ ባለሙያዎች በተመጣጣኝ ክፍያ መሰልጠን ይፈልጋሉ?
እንግዲያውስ ፈጥነው ይመዝገቡና የሙያው ባለቤት ይሁኑ!
ዛሬ የያዙት ሙያ ለነገ ሕይወትዎ ወሳኝ ነው!

የምዝገባ ቦታ: ዋርካው የገበያ ማዕከል 3ኛ ፎቅ ቁ.50(Bright Candles) ,ባህር ዳር
በቴሌግራም ለመመዝገብ: @tanatech23 ላይ የሚፈልጉትን የስልጠና ዘርፍ: ሙሉ ስምና ስልክ ቁጥር በመላክ መመዝገብ ይችላሉ!
👍3
     @computer_mobile21

💻 ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ እንዴት እንደሚፃፍ ያውቃሉ?ሲጽፉስ ምን ያህል ይፈጥናሉ?


❖መጀመሪያ Ge'ez 10 Software ያወረዱ እና install ያድርጉት ከዛም አማርኛ መፃፍ ስትፈልጉ power ge'ez status phonetic Unicode Mode (ፎ) ላይ ያድርጉት በ English መፃፍ ስትፈልጉ ደግሞ power ge'ez status English Mode (ኢ) ላይ አድርጉት ከዛም የሚከተሉትን ኣጭር መግላጫ በትክክል ይመልከቱ
     @computer_mobile21

◕ሀ➭H_ሁ➭Hu_ሂ➭Hi_ሃ➭Ha_ሄ➭Hy_ህ➭He_ሆ➭Ho

◕ለ➭L_ሉ➭Lu_ሊ➭Li_ላ➭La_ሌ➭Ly_ል➭Le_ሎ➭Lo

❖ሐ➭Shift+h_ሑ➭Shift+hu_ሒ➭Shift+hi_ሓ➭Shift+ha_ሔ➭Shift+hy_ሕ➭Shift+he_ሖ➭Shift+ho

መ➭M_ሙ➭Mu_ሚ➭Mi_ማ➭Ma_ሜ➭My_ም➭Me_ሞ➭Mo

❖ሠ➭Shift+s_ሡ➭Shift+su_ሢ➭Shift+si_ሣ➭Shift+sa_ሤ➭Shift+sy_ሥ➭Shift+se_ሦ➭Shift+so

◕ረ➭R_ሩ➭Ru_ሪ➭Ri_ራ➭Ra_ሬ➭Ry_ር➭Re_ሮ➭Ro

◕ሰ➭S_ሱ➭Su_ሲ➭Si_ሳ➭Sa_ሴ➭Sy_ስ➭Se_ሶ➭So

❖ሸ➭Shift+s_ሹ➭Shift+su_ሺ➭Shift+si_ሻ➭Shift+sa_ሼ➭Shift+sy_ሽ➭Shift+se ሾ➭Shift+so

◕ቀ፡➭Q ቁ፡➭Qu ቂ፡➭Qi ቃ፡➭Qa ቄ፡➭Qy ቅ፡➭Qe ቆ፡➭Qo

◕በ፡➭B ቡ፡➭Bu ቢ፡➭Bi ባ፡➭Ba ቤ፡➭By ብ፡➭Be ቦ፡➭Bo

◕ተ፡➭T ቱ፡➭Tu ቲ፡➭Ti ታ፡➭Ta ቴ፡➭Ty ት፡➭Te ቶ፡➭To

◕ ቸ፡➭C ቹ፡➭Cu ቺ፡➭Ci ቻ፡➭Ca ቼ፡➭Cy ች፡➭Ce ቾ፡➭Co

◕ነ፡➭N ኑ፡➭Nu ኒ፡➭Ni ና፡➭Na ኔ፡➭Ny ን፡➭Ne ኖ፡➭No

❏ኘ፡➭Shift +n ኙ፡➭Shift +nu ኚ➭Shift+ni ኛ፡➭Shift +na ኜ፡➭Shift +ny ኝ፡➭Shift + ne ኞ፡➭Shift +no

◕ከ፡➭Ka ኩ፡➭Ku ኪ፡➭Ki ካ፡➭Ka ኬ፡➭Ky ክ፡➭Ke ኮ፡➭Ko

❖ ኸ ☛capslock + Shift + h
     ኹ ☛capslock + Shift + hu
     ኺ ☛capslock + Shift + hi
     ኻ ☛Capslock + Shift + ha
     ኼ ☛Capslock + Shift + hy
     ኽ ☛Capslock + Shift + he
     ኾ ☛Capslock + Shift + ho

❏ኀ፡➭ Capslock + H ኁ፡➭ Capslock + HU ኂ፡➭Capslock + HI ኃ፡➭Capslock + HA ኄ፡➭Capslock + HY ኅ፡➭Capslock + HE ኆ፡➭Capslock + HO

❏አ፡➭Capslock X ኡ፡➭Xu ኢ፡➭Xi ኣ፡➭Xa ኤ፡➭Xy እ፡➭Xe ኦ፡➭XoDe

❖ዐ፡➭Shift +x ዑ፡➭Shift +xu ዒ➭Shift +xi ዓ፡➭Shift +xa ዔ➭Shift +xy ዕ፡➭Shift +xe ዖ➭Shift +xo

✪ወ፡➭W ዉ፡➭Wu ዊ፡➭Wi ዋ፡➭Wa ዌ፡➭Wy ው፡➭We ዎ፡➭wo

✪ዘ፡➭Z ዙ፡➭Zu ዚ፡➭Zi ዛ፡➭Za ዜ፡➭Zy ዝ፡➭Ze ዞ፡➭Zo

❏ዠ፡➭Shift + Z ዡ፡➭Shift + Zu ዢ፡➭Shift + Zi ዣ፡➭Shift +Zaዤ፡➭Shift + Zy ዥ፡➭Shift +Ze ዦ፡➭Shift + Zo

✪ፈ፡➭F ፉ➭Fu ፊ፡➭Fi ፋ፡➭Fa ፌ፡➭Fy ፍ፡➭Fe ፎ፡➭Fo

✪ ፐ፡➭P ፑ፡➭Pu ፒ፡➭Pi ፓ፡➭Pa ፔ፡➭Py ፕ፡➭Pe ፖ፡➭Po

✪ገ፡➭G ጉ፡➭Gu ጊ፡➭Gi ጋ፡➭Ga ጌ፡➭Gy ግ፡➭Ge ጎ፡➭Go

✪ደ፡➭D ዱ፡➭Du ዲ፡➭Di ዳ፡➭Da ዴ፡➭Dy ድ፡➭ዶ፡Do

❏ጠ፡➭Shift + t ጡ፡➭Shift + tu ጢ፡➭Shift + ti ጣ፡➭Shift+ta ጤ፡➭Shift + ty ጥ፡➭Shift + te ጦ፡➭Shift + to

❏ጨ፡➭Shift +c ጩ፡➭Shift +cu ጪ፡➭Shift +ci ጫ፡➭Shift+caጬ፡➭Shift +cy ጭ፡➭Shift +ce ጮ: ➭Shift +co

❏ጸ፡➭Capslock + t ጹ፡➭Capslock + tu ጺ፡➭Capslock + ti ጻ፡➭Capslock + ta ጼ፡➭Capslock + ty ጽ፡➭Capslock + t ጾ፡➭Capslock + to

❖ ፀ➭☞Capslock+Shift+t
     ፁ➭☞Capslock+Shift+tu
     ፂ➭☞Capslock + Shift + ti
     ፃ➭☞Capslock + Shift + t
     ፄ➭☞Capslock + Shift + ty
     ፅ➭☞Capslock + Shift + te
     ፆ➭☞Capslock + Shift + to

✪ጀ፡➭J ጁ፡➭Gu ጂ፡➭Ji ጃ፡➭Ga ጄ፡➭Gy ጅ፡➭Ge ጆ፡➭Jo

✪ቨ፡➭V ቩ፡➭Vu ቪ፡➭Vi ቫ፡➭Va ቬ፡➭Vy ቭ፡➭Ve ቮ፡➭Vo
▁▁▁▁▁▁▁▁▁▁

ቋ➭Capslock+qwa ቧ➭Capslock+bwa
ቷ➭Capslock+twa
ኟ➭Capslock +Shift+nwa
ቿ➭Capslock+cwa ሟ➭Capslock+mwa
ቷ➭Capslock+twa ጓ➭Capslock  gwa
ፏ➭Capslock+fwa ሯ➭Capslock +rwa ዷ➭Capslock+dwa ቯ➭Capslock+vwa ኋ➭Capslock+hwa ዟ➭Capslock+zwa ዧ➭Capslock+Shif+zwa
ኗ➭Capslock+nwa ሏ➭Capslock+lwa
ኳ➭Capslock+kwa ሷ➭Capslock+swa
ጇ➭Capslock+jwa ጧ➭Capslock+twa

ለሌሎች እንዲደርሳቸው #FORWARD  ያድርጉ
     @computer_mobile21
👍159🔥1🥰1
#mobile #security
ጎግል የተሰረቁ ሞባይል ቀፎዎች ዳግም እንዳይሰሩ የሚያደርግ ፈጠራ መተግበሩን አሳወቀ::
ኩባንያው ኤአይን በመጠቀም ስልካቸውን የተሰረቁ ሰዎች ወደ ስልኩ አምራች ተቋም ሪፖርት የሚያደርጉበት አሰራርን ዘርግቻለሁ ብሏል

አዲሱ የጎግል አሰራር የስልክ ንጥቂያ ወንጀሎችን ሊቀንስ እንደሚችል ተገልጿል።

እንደ አልዓይን ዘገባ ከሆነ ሌቦች የስልክ ቀፎን ከወሰዱ በኋላ ለመደበቅ ቢሞክሩ እና ዳግም ጥቅም ላይ ለማዋል ሲሞክሩ ኤአይን በመጠቀም ለዘለቄታው ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆን የሚያደርግም ነው፡፡

ለአንድሮይድ ስልክ የተገጠመለት ኤአይ ቴክኖሎጂ ቀፎው ላይ በተገጠመለት ሴንሰር አማካኝነት እንዳይከፈት አድርጎ መዝጋት ይችላልም ተብሏል፡፡

contact @seen311

JOIN👇👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21

#SHARE #SHARE
👍171
የኮምፒዩተራቹ operating system window 10 ነው?

በምትከፍቱት እና በምትጠቀሙበት  ሰአት እየተንቀራፈፈ አማሯችዋል? እንግዲያውስ ፍጥነቱን ሊጨምሩ የሚችሉ ነገሮችን እናያለን።

#1_Power_option
Start menu ላይ power option ብላቹ ፈልጉ ከሚመጣላቹ window ውስጥ high performance የሚለውን ምረጡ

#2_Disable_unwanted_start_up_programs
ይሄ ኮምፒዩተራችንን በምንከፍትበት ጊዜ ያለ እኛ ፍቃድ ፕሮግራሞችን እየከፈተ
ፍጥነቱን ከሚቀንሱ ነገሮች አንዱ ነው። ይሄን ለመከላከል Task manager ላይ መግባት (ይሄን ለማግኘት start menu ላይ right
click አድርጎ ማግኘት ይቻላል አልያም Ctrl Alt እና delete
የሚለውን አንድ ላይ መጫን)
ከሚመጣው window ውስጥ start up ላይ በማድረግ የማትፈልጉትን ፕሮግራሞች disable ማድረግ። እዚህ ጋር impact የሚለው high ከሆነ
disable ባታረጉ ይመረጣል።

#3_Defragment_and_optimize_drive
Start menu search bar ላይ defragment ብሎ መፈለግ Window ሲመጣላቹ የምትፈልጉትን driver መርጣቹ
optimize ማድረግ

#4_Delete_unnecessary_temporary_file
Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን
መምረጥ አልያም
window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን
%temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን
የሚመጣላቹ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን
ሁሉንም ሲመርጥልን
ማጥፋት
ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላቹ
folder ውስጥ
ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት
አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ
የሚመጣላቹ
folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት።
እነዚህን የምናጠፋበት ምክንያት ጊዜያዊ እና space የያዙ
ፋይሎች ስለሆኑ
ነው። ምንም አይነት ችግር አያመጡም።

#5_Clean_up_Memory
This pc ውስጥ ገብታቹ የምፈልጉት local ዲስክ ላይ right click በማድረግ property መምረጥ Disk clean up የምትለውን icon click ማድረግ የሚመጣውን የ warning box ok ማድረግ
እዚህ ጋ recycle bin ውስጥ ያሉ ፋይሎች ሳይቀሩ ነው የሚጠፉ ት

#6_Reduce_run_time_service
Run box ከፍታቹ msconfig ብሎ መጻፍ ቀጥሎ ከሚመጣው window service የሚለውን መጫን በመቀጠል hide all microsoft service የሚለውን tickvማድረግ
በመቀጠል disable የምትለዋን icon click ማድረግ

#7_Registry_tweaks
Run box መክፈት(window key + R) regedit ብሎ መጻፍ
Hkey -current user
Control panel Mouse
Mouse hover time
valueን ወደ 10 መቀየር
እዛው folder ላይ desktop መምረጥ Menu show delay
Valueን ወደ 10 መቀየር

#8_visual_effects
Start menu ላይ System ብሎ መፈለግ Advanced system setting መምረጥ
Advance ውስጥ በመግባት setting መምረጥ Adjust for best performance መምረጥ ቀጥሎ የምትፈልጉት ነገር ካለ ቲክ በማድረግ መምረጥ
በመጨረሻም ከላይ ያሉትን ከጨረስን በኋላ ኮምፒዩተራችንን
Restart ማድረግ::

contact @seen311

JOIN👇👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21

#SHARE #SHARE
👍182
#TV
ፍላት ስክሪን ቲቪዎችን  የሚያበላሹ 5 ነገሮች

1️⃣ ሀይል መቆራረጥ (የቮልቴጅ መጨመር መቀነሰ)

⚠️ሁሉም እቃዎችን የሚያበላሸው የተለመደው የአገራችን ችግር የመብራት ሃይል (የቮልቴጅ )መጨመር እና መቀነስ ነው አብዛኛው ቲቪዎች የራሳቸው Voltage መቆጣጠሪያ ስለሌላቻው ቦርዳቸው ቶሎ ለመቃጠል ይዳረጋል ስለዚህ እንደየሚጠቀሙት የዲቫይሶች ብዛት: ከ 500 - 5000V ያሉትን  Stabilizer ገዝተው ይጠቀሙ። ማስጠንቀቂያ 500 V Stabilizer ሲጠቀሙ ፍሪጅ በተጨማሪነት አይሰኩ


2️⃣ ድምፅ አለው ምስሉ ጠቁሮ ይታያል ወይም (አይታይም) 90% የቲቪ የጀርባ መብራቶች.  (Backlight) መቃጠል ነው ባክ ላይት መቃጠሉን መለያ መንገድ በቤት ውስጥ ብርሀን ወደሌለበት ቦታ ቴሌቪዥንኑን መውሰድ የስልካችንን መብራት በማብራት ወደ እስክሪኑ አስጠግተን ምስል መታየት አለመታየቱን ቼክ ማድረግ ከታየ Backlight ችግር አለበት ካልታየ Backlight V አልደረሰውም ወይም ወደ እስክሪኑ  v አልደረሰውም ወይም ቴኮኑ ወይም ቦርዱ ላይ ችግር አለ ወዘተ
ለጠቅላላ እውቀት የአንድ ፍላት ቴሌቪዥን ባክላይት ዲዛይን የተደረገው (የአገልግሎት ቆይታ ጊዜው) ለ5አመት ነው ይህ ማለት ግን 5አመት ብቻ ያገለግላል ማለት አይደለም ሊጨምርም ሊያንስም ይችላል

3️⃣ ፅዳት: ውሀ (ፀበል) መርጨት

⚠️ ስክሪኑ ላይ Spray ረጭቶ ማፅዳት በፍፁም ሊደረግ እማይገባ ነው። ስክሪኑ በጣም Sensitive ስለሆነ ውስጥ ውሀ ገብቶ  በቀላሉ ይበላሻል።  ውሀ ወይም ፀበል ሲረጩ ቲቢው እንዳይፈስ ይጠንቀቁ ለማፅዳት ሲፈልጉ በንፁህ ለስላሳ ጨርቅ ላይ ስፕሬውን በትንሹ በመርጨት  ማፅዳት ይችላሉ።

4️⃣ ኬብል

⚠️በክረምት ወቅት HDMI ኬብል አይጠቀሙ  መብረቅ በዲሹ ኬብል አልፎ  በHDMI አማካኝነት ቲቪዎን ቀጥታ ያገኘዋል በዚ ጊዜ  Av ጃክ መጠቀም የተሻለ ነው።

5️⃣ የስክሪን መሰበር ነው።

⚠️ በተለያዩ አጋጣሚዎች ስክሪን ይሰበራል ይሰነጠቃሉ ማስጠንቀቂያ እስክሪኑ 75% የቴሌቭዥኑን ዋጋ ይይዛል #በጣም_ውድ ነው፤ ስለዚህ ልንጠነቀቅላቸው ይገባል። ስክሪኑን ላይገኝ ስለሚችል በደንብ ልንጠነቀቅለት ይገባል።
           መፍትሔ
⚠️ ቤት ውስጥ ልጆች ካሉ ወይም የንግድ ስራ ቦታ ላይ ቲቪዎን ከፍ አርጎ ግድግዳ ላይ መስቀል ያስፈልጋል።

⚠️ ደብል እስክሪን ብትገዙ ይመረጣል

contact @seen311

JOIN👇👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21

#SHARE #SHARE
👍228
የኤሌክትሪክ አደጋን ለመከላከል የጥንቃቄ መንገዶች

የኤሌክትሪክ አደጋ በኤሌክትሪክ ምክንያት የሚመጣ በማንኛውም ጊዜና ቦታ ሊከሰት የሚችል ሲሆን በሰው ህይወትና አካል፣ እንዲሁም በንብረት ላይ ጊዜያዊ ወይም ዘላቂ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል፡፡

በመሆኑም ራስዎን ከኤሌክትሪክ አደጋ ለመጠበቅ፡-

👉 በረገቡ የኤሌክትሪክ መስመሮች ስር ሾልኮ ለማለፍ አይሞክሩ፤
👉 ኃይለኛ ንፋስ በሚነፍስበት ወቅት ከኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ርቀትዎን ጠብቀው ይንቀሳቀሱ፤
👉 ተበጥሶ የወደቀና የተንጠለጠለ የኤሌክትሪክ ገመድ ወይም ሽቦ ሲያዩ ከመንካት በመቆጠብ ለሚመለከተው አካል ያሳውቁ፤
👉 በከፍተኛ ቮልቴጅ የኤሌክትሪክ መስመሮች ስር ወይም አጠገብ ማንኛውንም የግንባታ ሥራ ከማከናወን ይጠበቁ፤
👉 ህንፃዎች ሲገነቡ ከኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲከናወኑ፤ዛፎች ሲቆረጡ የኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ እንዳይወድቁ ጥንቃቄ ያድርጉ፤
👉 የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች ከቆርቆሮ ጣሪያ፣ አጥር፣ ከልብስ ማስጫ ገመዶች ጋር እንዳይገናኙ ያድርጉ፤
👉 የቤት ውስጥ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋት በባለሞያ እንዲከናወን ያድርጉ፤
👉 ደረጃቸውን የጠበቁ የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶችን ይጠቀሙ፤
👉 በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መሳሪያዎች ላይ ቃጠሎ ሲነሳ በውሀ ከማጥፋት በመቆጠብ ትክክለኛውን የእሳት ማጥፊያ ይጠቀሙ፤
👉 የኤሌክትሪክ መስመሩን ከመቆጣጠሪያው ሳያጠፉ በኤሌክትሪክ የተያዘን ሰው ለማዳን አይሞክሩ፤
👉 የኤሌክትሪክ ሀይልን ከራስዎ ቆጣሪ ወደ ሌላ ሰው ቤት አሳልፎ ከመዘርጋት ይቆጠቡ፤
👉 ብረት ነክ የሆኑ ቁሳቁሶችን ከኤሌክትሪክ ሶኬቶች ወይም ማከፋፈያዎች ጋር በፍፁም አያገናኙ፤
👉 በአንድ ማከፋፈያ ላይ ብዙ ኬብሎችን ማገናኘት ለአደጋ ስለሚያጋልጥ በፍፁም አያድርጉ፤
👉 በኤሌክትሪክ ሥራ ሲሰሩ ርጥብ ነገሮች ለአደጋ ሊያጋልጥዎ ስለሚችሉ መጠንቀቅ አይዘንጉ፤

contact @seen311

JOIN👇👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21

#SHARE #SHARE
👍165
ስልካችሁ ወይም ኮምፒውተራችሁ ላይ Microsoft word, microsoft excel, Microsoft powerpoint ካልጫናችሁ በቀላሉ ብሮዘራችሁን ከፍታችሁ የሚከተሉትን ሊንኮች ብታስገቡ በቀላሉ ይከፍትላችኋል።
docs.new = Google docs
slides.new = Google slides
sheets.new = Google sheets
meet.new = Google meet
forms.new = Google forms
እነዚህን ለመጠቀም የGoogle account መክፈት አለባችሁ።

JOIN👇👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21

#SHARE #SHARE
👍8🥰3👏32😁2
#computer

① Motherboard

Motherboard የኮምፒውተር ክፍል ዋናው የኤሌክትሪክ ሰርኪዩት ሰሉዳ ሲሆን ተለቅ ያለ እና ዋና የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
ሁሉም የኮምፒውተር ክፍሎች ከ Motherboard ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተገናኙ ሲሆን ይህም በመሰረታዊነት የኮምፒውተሩ ክፍሎች እርስ በርስ መረጃ እና ትዕዛዞችን እንዲለዋወጡ ያስችላል፡፡
❖ ካለ Motherboard ኮምፒውተር የማይታሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የኮምፒውተሩ ኤሌክትሪክ አቅራቢ(Power Supply) ለሲዲ ማንበቢያው (CD drive) የኤሌክትሪክ ሃይል መስጠት ካልቻለ ሲዲ ማንበቢያው መስራት አይችልም፡፡

②Central Processing Unit (CPU)

❖ CPU የኮምፒውተሩ ማዕከላዊ ማቀነባበሪያ ክፍል ሲሆን ማቀናበሪያ(processor) አልያም የኮምፒውተር #አዕምሮ ሌላኛው መታወቂያ ስሞቹ ናቸው፡፡
❖ CPU ከተጠቃሚ ወደ ኮምፒውተሩ የሚገቡትን ትዕዛዞች በሙሉ በመቀበል ኮምፒውተሩ በአግባቡ ትዕዛዙን እንዲከውን የሚያደርገው በ motherboard ላይ የሚገኝ ትንሽ የኤሌክትሮኒክ ቺፕ ነው፡፡
❖የማቀናበር ሃይል(processing power) የኮምፒውተርን ፍጥነት ግልፅ በሆነ መልኩ ይጨምራል፡፡
ስለሆነም ፈጣን ማቀነባበሪያ ኮምፒውተሮችን ፈጣን ያደርጋቸዋል፡፡

③ Random Access Memory (RAM)

❖RAM ማሕደረ-ትውስታ የኮምፒውተሩ ጊዜያዊ መረጃዎችን አልያም ስሌቶችን የሚያኖርበት እና በሚያስፈልግ ጊዜ(ኮምፒውተሩን ከማጥፋታችን አልያም ዳግም ከማስነሳታችን በፊት) መረጃዎችን ወይንም ስሌቶችን የሚሰጠን ነው፡፡
❖RAM ከ CPU ጋር በመተባበር ዳታዎች በተሳካ ሁኔታ የሚያቀነባብር ወሳኝ የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
❖የRAM መጠን በመጨመር የኮምፒውተሮችን የማህደረ-ትውስታ በማስፋት የማቀነባበር አቅሙን ማሻሻል ይችላል

④Hard Drive

❖Hard drive ለኮምፒውተሮች እንደ ትልቅ ቤተ-መፀሃፍት ነው፡፡ ምክኒያቱም ፋይሎችን፤ሙዚቃዎችን፤ምስሎችን፤ሰነዶችን፤ ወዘተ ለዘለቄታው የምናኖርበት ሁነኛ ክፍል ነው፡፡
❖Hard drive በግል ከምናኖራቸው መረጃዎች ባለፈ የኮምፒውተሩ አሰራር ሂደት(operating system) የሚጫንበት እና በአግባቡ ኮምፒውተሩ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ የሚያደርጉትን የአሰራር ሂደት ፋይሎች(operating system files) የሚቀመጡበት የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡

⑤Power Supply Unit

❖Power supply unit የኮምፒውተሩ የሃይል አቅርቦት ክፍል ሲሆን ከግርግዳ ወይንም ከኤሌክትሪክ ማከፋፈያ የሚቀበለውን ኤሌክትሪክ ለኮምፒውተሩ በሚመጥን የኤሌክትሪክ መጠን እና አቅርቦት ለክቶ እና መጥኖ ወደ ኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚያዳርስ የኮምፒውተር ቁልፍ ክፍል ነው፡፡

JOIN👇👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21

#SHARE #SHARE
👍187🔥4
ማይክሮሶፍት የዊንዶውስ 10 ተጠቃሚዎች ወደ ዊንዶውስ 11 እንዲያሻሽሉ አሳሰበ

ማይክሮሶፍት እ.ኤ.አ. ከጥር 10/2023 ጀምሮ ለዊንዶውስ 8.1 ሁሉንም የደህንነት ዝመናዎች እና ቴክኒካዊ ድጋፎች ማቆሙን አስታውቆ ነበር። በተመሳሳይ የዊንዶውስ 7 ድጋፍ በጥር 14/2020 ማብቃቱ ይታወሳል። አሁን ደግሞ የዊንዶውስ 10 ድጋፍ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 14/2025 ጀምሮ እንደሚያቆም ማይክሮሶፍት ገልጿል። ይህም እነዚህ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ከተጠቀሰው ጊዜ በኋላ ሁሉንም አይነት ዝመናዎችን ስለማያገኙ ለደህንነት ስጋቶች ተጋላጭ ይሆናሉ።

በአሁኑ ጊዜ ዊንዶውስ 7ን፣ ዊንዶውስ 8.1ን ወይም ዊንዶውስ 10ን ለሚጠቀሙ ስርዓቶች፡-
• ኮምፒውተርዎ ዊንዶውስ 11ን ለመጫን አነስተኛ መስፈርቶችን የሚያሟላ መሆኑን እንዲያረጋግጡ፤
• በዊንዶውስ ዝመና ውስጥ ያለውን የማሻሻያ አማራጭ እንዲከተሉ፤
• ኮምፒውተርዎ መስፈርቶቹን የማያሟላ ከሆነ ወይም ምትክ የሚያስፈልገው ከሆነ ዊንዶውስ 11ን ወደሚደግፍ አዲስ ኮምፒውተር ለመሸጋገር የሚያስችልዎትን አማራጭ እንዲወስዱ ማይክሮሶፍት በሰጠው ማሳሰቢያ ገልጿል፡፡

JOIN👇👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21

#SHARE #SHARE
👍196👎2😁2
Attention‼️
አደገኛ መተግበሪያ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ መሆኑን ንግድ ባንክ አስታወቀ‼️
👉 መተግበሪያው ያለደንበኛው ፈቃድ ገንዘብ ይቆርጣል
ደምበኞች በዋትስ አፕ እና በቴልግራም የሚሠራጭ Pharma+/CBE Vacancy መተግበሪያን እንዳይጭኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሳሰበ።

ባንኩ ባስተላለፈው የማስጠንቀቂያ መልዕክት፤ ባደረገው ምርመራ መሠረት አደገኛ መተግበሪያ ማግኘቱን ገልጿል።

ይህ Pharma+/CBE Vacancy የተሰኘ አሳሳች መተግበሪያ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሰፊው እየተሰራጨ እንደሆነ በመጥቀስ፤ ይህ መተግበሪያ በቴሌግራም እና ዋትስአፕ ወደ ደንበኞቹ እየደረሰ መሆኑን ጠቁሟል።

መተግበሪያው በስልክ ላይ ከተጫነ ያለ ፈቃድ ገንዘብ ማስተላለፍ እንደሚችልም አሳውቋል።

ባንኩ ከዚህ አይነት አደጋ ለመጠበቅ ከቴሌግራም ወይም ዋትስአፕ መተግበሪያዎችን አታውርዱ ብሏል።

ደንበኞች መሰል ተግባራት ሲገጥሟቸው በ951 ነጻ የስልክ መስመር ደውለው እንዲያሳውቁ አሳስቧል።
JOIN👇👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21

#SHARE #SHARE
👍159
ሞባይል (ተንቀሳቃሽ ስልክ) ሲፈጠር የታሰበው በድምፅ አንድን ሰው ከሌላው ለማገናኘት ነበረ። እየቆየ ድምፅ መቅረጫ ሆነ። ድምፅን ለመቅረፅ የተሰሩ መሳሪያዎችን ከገበያ እያወጣ ሄደ። ከዚያ በፅሁፍ መልዕክት መላክያ ሆነ። ፖስታን ከገበያ አወጣ። ቀጥሎ ምስል መቅረጫ ሆነ። ቪድዮን ከገበያ እያወጣ ሄደ። ሰዓትን ተካ። ካልኩሌተርን ተካ። ካላንደርን ተካ። ሙዚቃ ማዳመጫ ዎክማንን ተካ። ሬዲዮና ቴሌቭዥንን ተካ። ማስታወሻ መያዥያ ደብተርን ተካ። ብዙ አገልግሎት የሚሰጡ መሳሪያዎችን ከገበያ አወጣ። አሁን ሞባይል የባንክ ደብተር ነው። ገንዘብ መያዥያ ዋሌት ነው። ሀኪም ነው። መንገድ መሪ ጂፒኤስ ነው። ቋንቋ አስተርጓሚ ነው። አጫዋች ነው። ከጠቀስኳቸው ውጪ ያሉ፣ ሞባይል የተካቸው መሳሪያዎች በጣም ብዙ ናቸው።

JOIN👇👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21

#SHARE #SHARE
23👍5
ኢንተርኔትን ስንጠቀም ልንጠነቀቅ የሚገቡን 10 ጉዳዮች

1. የግል መረጃችንን ከማጋራት መቆጠብ፤

2. የምናውቃቸውን ሰዎች ብቻ ማነጋገር

3. በኦንላይን ብቻ የምናውቃቸውን ሰዎች ከፍተኛ እምነት አለመጣል፤

4. የጓደኝነት ጥያቄን በአካል ከምናውቃቸው ሰዎች ብቻ እንቀበል፤

5. ሁልጊዜ ስለምንለጥፈው ነገር በጥንቃቄ ደጋግሞ ማንበብ

6. በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎች ላይ የግላዊነት(privacy 🔏) መጠበቂያዎችን መጠቀም፤

7. ሁሉም ሰው በኦንላይን እሱ እንደሆነ የሚነግረን ሁሉ እውነት አድርጎ አለመቀበል፤

8. ተገቢ ያልሆነ ይዘትን ሲያጋጥመን ወዲያውኑ ሪፖርት እናድርግ፤

9. ከጓደኞቻችን እና ከቤተሰባችን ጋር ስንመለከታቸው ምቾት የሚሰጡንን ምስሎች ብቻ ማጋራት፤

10. የይለፍ ቃላችንን በፍጹም ከማጋራት መቆጠብ፤

INSA

JOIN👇👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21

#SHARE #SHARE
20👍6👎1
ቻርጀርን ከተጠቀሙ በኋላ ከኤሌክትሪክ መንቀል ለምን #ጠቃሚ ነው?🔌

በየቀኑ የምንጠቀምባቸውን ስልኮች፣ ላፕቶፖች እና ሌሎች ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ቻርጀር ከተጠቀምን በኋላ ከሶኬት ላይ መንቀል እንዳለብን ያውቃሉ?

አንድ የኤሌክትሪክ ባለሙያ እንደሚለው፣ ይህን ማድረግ ለደህንነት እና ለገንዘብ ቁጠባ ወሳኝ ነው።

ቻርጀርን አለመንቀል የሚያስከትላቸው ጉዳቶች የኃይል ፍጆታ እና የኤሌክትሪክ ሂሳብ መጨመር ፣ አንድ ቻርጀር ከስልክዎ ጋር ባይገናኝም እንኳ ከሶኬት ላይ ከተሰካ ትንሽ መጠን ያለው ኤሌክትሪክ መሳብ ይቀጥላል።

ይህ "Vampire energy" ወይም "phantom load" በመባል ይታወቃል።

የኤሌክትሪክ ባለሙያው ባሬት አብራሞው እንዳሉት፣ በየቀኑ ብዙ ቻርጀሮች ያለአግባብ ኃይል የሚስቡ ከሆነ፣ በወር መጨረሻ ላይ የኤሌክትሪክ ሂሳብዎ ላይ ያልተጠበቀ ጭማሪ ሊያስከትል ይችላል።

የእሳት አደጋ: ቻርጀሮችን ለረጅም ጊዜ ከኤሌክትሪክ ጋር ተሰክተው መተው የእሳት አደጋ ሊያስከትል ይችላል።

በተለይ ዝቅተኛ ጥራት ያላቸው ቻርጀሮች በቀላሉ ሊሞቁና አጭር ዙር ሊፈጥሩ ስለሚችሉ፣ ይህ ለቤትዎ እና ለመሳሪያዎችዎ ትልቅ አደጋ ነው።

የቻርጀር ዕድሜን ማሳጠር ፣ ቻርጀር ከኤሌክትሪክ ጋር ሁልጊዜ ተሰክቶ ሲቆይ፣ የውስጥ አካሎቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየደከሙ ይሄዳሉ።

ይህ ደግሞ የቻርጀሩን ዕድሜ ያሳጥራል።

የቻርጀርን የመንቀል ልምድ ለማዳበር የሚረዱ መንገዶች ቻርጀርን የመንቀል ልምድ ለማዳበር የሚከተሉትን ቀላል መንገዶች መጠቀም ይችላሉ።

የቻርጅ ማደያ ቦታ ይፍጠሩ ፣ ሁሉንም ቻርጀሮችዎን በአንድ ቦታ ላይ ሰብስበው ያስቀምጡ።

በዚህ መንገድ ከመውጣትዎ በፊት በአንድ ጊዜ ሁሉንም መንቀል ይችላሉ።

የኃይል ማከፋፈያ (Power Strip) ይጠቀሙ: ብዙ ቻርጀሮችን ወደ አንድ የኃይል ማከፋፈያ ይሰኩና ስራ ላይ በማይውልበት ጊዜ ማጥፋት ይችላሉ።

ስማርት ሶኬቶችን ይጠቀሙ: አውቶማቲክ በሆነ መንገድ የሚሰሩና በፕሮግራም የሚጠፉ ስማርት ሶኬቶችን መጠቀምም ሌላው አማራጭ ነው።


JOIN👇👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21

#SHARE #SHARE
20👍6
ሻንጋይ የሮቦት ትራፊክ ፖሊስ ሥራ ላይ አዋለች

የቻይናዋ ከተማ ሻንጋይ የትራፊክ ፖሊስ ሥራ ላይ ማዋሏ ታውቋል።

ዣዎ ሁ (ትንሹ ነብር) የሚል ስም የተሰጠው ይህ ሮቦት የተጨናነቁ መንገዶች ላይ መኪኖችን በየተራ የሚያስተናግድ እንዲሁም ለመኪኖች ምልክት በመስጠት እግረኞችን እንደሚያሳልፍ ተገልጸል።

ይህን ለማድረግም የእጅ ምልክቶችን፣ ድምፅ እና የትራፊክ ፊሽካ እንደሚጠቀም ተነግሯል። ከዚህ ባለፈም የትራፊክ ትምህርቶችን ያስተላልፋልል።

የትራፊክ ፖሊሶች አይነት ዩኒፎርም ለብሶ በሻንጋይ ጎዳና የሙከራ ግዳጁን የተወጣው ዣን ሁ ልክ እንደ ትራፊክ ፖሊስ ሥራውን በትክክል ሲፈፅም መታየቱን ኒውዮርክ ፖስት ዘግቧል።

የሻንጋይ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ሮቦቱን ለመስራት አራት ዓመታትን ፈጅቶባቸዋል።
Via EBC

JOIN👇👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21

@seen311
17👎1
Live stream finished (12 minutes)