COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE
7.1K subscribers
71 photos
7 videos
53 files
103 links
Welcome To Computer & Mobile Maintenance Channel.
It Gives You Some Hints To Repair(Improve Performance Of) Your Computer & Mobile By Yourself. ለጠጋኞችም የሚጠቅም ምርጥ ቻናል ነው!
JOIN @Computer_Mobile21
Contact @seen311 or @seen3bot

Group👉 @Computer_Mobile3
Download Telegram
Forwarded from COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE (Seen above)
እንዴት ከሌላ ስልክ📲 ላይ ቻርጅ #ማስተላለፍ እንደሚቻል ያውቃሉ!

ስልካችንን📲 እንዴት ከሌላ ስልክ ላይ ቻርጅ ማድረግ እንችላለን?

#አስፈላጊ ነገሮች⬇️⬇️⬇️

ሌላኛው ስልክ
OTG
data cable

1⃣. አሰራር፦ ኬብሉን #OTG ላይ ይሰኩና በቀላሉ #OTG ያለበትን ጫፍ ቻርጅ ሰጪው ስልክ📲 ላይ ይሰኩት።

2⃣. ሌላኛውን ጫፍ ቻርጅ ማድረግ የሚፈልጉት ስልክ ላይ ይሰኩት።

@computer_mobile21

Read more👇👇
https://www.technologysage.com/how-to-charge-android-phone-using-another-phone/
KMSAuto Lite 1.5.5 Portable.iso
4.7 MB
Windows & MS office Activator

Contact: @seen3bot

@computer_mobile21
@computer_mobile21

የሞባይል ስልክ ቁጥርዎ ሰሞኑን ሾልኮ ከወጣው የፌስቡክ ዝርዝር ውስጥ ካለ እንዴት ማረጋገጥ ይችላሉ?

ሰሞኑን ከ530 ሚልዮን በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ዳታ (ስልክ፣ ኢሜይል ወዘተ) በጠላፊዎች ሾልኮ እንደወጣ ተሰምቷል፣ ከዚህ ውስጥ 12,000 ኢትዮጵያውያን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች እንደሚገኙበትም ታውቋል።

@computer_mobile21

(ይህን እና ሌሎች መረጃዎችን ድረ-ገፃችን ላይ ለማንበብ:
https://ethiopiacheck.org/analysis/how-can-you-check-if-your-phone-number-is-on-the-list-of-numbers-facebook-released/)

ታድያ የእርስዎ ስልክ ወይም ኢሜይል እዚህ ዝርዝር ውስጥ ከተገኘ ማረጋገጫ እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ጠይቀው ሊሆን ይችላል። Have I Been Pwned (https://haveibeenpwned.com/) የተባለ ድረ-ገፅ ይህን ማረጋገጥ ይችላል።

አጠቃቀሙ እንዲህ ነው: https://haveibeenpwned.com/ ድረ-ገፅን ሲከፍቱ የመፃፍያ/መፈለግያ ቦታ ያገኛሉ። ባዶ ቦታው ላይ ስልክዎን ወይም ኢሜይልዎን ያስገቡ። ከዛም "pwned?" የሚለውን ይጫኑ።

"Oh no- pwned" የሚል መልስ ካገኙ ስልክዎ ወይም ኢሜይልዎ ለጠላፊዎች ተጋልጦ ነበር ማለት ነው። "Good news- no pwnage found!" የሚል ምላሽ ካገኙ ለጠላፊዎች አልተጋለጡም ማለት ነው።
@computer_mobile21
@computer_mobile21
#textTovoice #Elocance
ለአይናችን እረፍት የሚሰጥ መተግበሪያ

መቼም የአይን ነገር ሲነሳ በተለይ የኮምፒውተርና የስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች ምን ተባለ ይሆን ማለት አለባቸው ብለን እናስባለን፡፡ ምክንያቱም ከኮምፒውተርና ከስልካችን ስክሪኖች የሚፈነጥቀው ሰማያዊ ብርሃን በከፍተኛ ሁኔታ አይናችንን እየጎዳው በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ችግር ከቴክኖሎጂና ከአጠቃቀም ጉድለት ጋር ተያይዞ የሚከሰት ቢሆንም መፍትሔውንም ቴክኖሎጂ ይዞልን ቀርቧል፡፡ ይኸውም ጽሁፍን ወደ ድምጽ የሚቀይር መተግበሪያ ነው፡፡
ቴክኖሎጂን መጠቀም ማቆም የሚመከር ጉዳይ ባይሆንም አማራጭ መፍትሔዎችን መጠቀም ግን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህም ነው የፈጠራ ባለሙያዎች Elocance የተሰኘ ጽሁፍን በንባብ የሚያሰማ መተግበሪያን ሰርተው ያቀረቡት፡፡ ይህም መተግበሪያ አንዴ በስልካችን ከጫንነው በኋላ ለሁል ጊዜ መስራት የሚችል ነው፡፡ በተጨማሪም መተግበሪያው በስልካችን ያሉ ጽሁፎችን (PDFs) የተለያዩ ህትመቶችንና የስብሰባ ማጠቃለያዎችን ወደድምጽ በመቀየር እንድንሰማቸው ያስችለናል፡፡ በመሆኑም መተግበሪያው እያንዳንዱን ጽሁፍ የሚያነብልን ረዳትና አደጋ ካለው ሰማያዊ ብርሃን የሚጠብቀን ትልቅ መፍትሔ ሆኖ ቀርቧል፡፡
በጣም ተፈላጊ የሆነው ይህ መተግበሪያ በመተግበሪያ መደብር (App Store) ውስጥ የ4.4 ኮኮብ ደረጃ ተሰጥቶታል፡፡ መተግበሪያው ግልጽ የሆነ አነጋገርን የሚከተል ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የድምጽ ጥራትም እንዳለው ተነግሮለታል፡፡ የሆነው ሆኖ የዋጋውስ ነገር ያላችሁ እንደሆን 34.99 የአሜሪካን ዶላር ከፍለን ለሁልጊዜ መጠቀም እንድንችል የቀረበ ነው፡፡

@computer_mobile21
@computer_mobile21

Get the apk 👇👇👇
Article,Newsletter, PDF reader app"
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.mindthetea.elocance
#phone_copy_original

ስልኬ #ኮፒ ነው ወይም #ኦርጅናል ነው? የሚለውን ለመለየት ጥያቄ ለመመለስ ቀጥሎ ያለውን ዘዴ ተጠቀሙ

ጥሩ ዘዴ የሚባለው ወደ internet በመግባት imei.info ወይም #imei check በማለት search ማድረግ ከዚያም መጀመርያ ወደ ሚመጣው #website በመግባት የስልካችሁን #imei መጻፍና check የሚለውን መጫን።

#imei ቁጥራችሁን ስታዩ ልብ ልትሉት የሚገባው ነገር *#06# ብላችሁ የሚመጣውና የስልካችሁን ባትሪ አውጥታችሁ ከስልካችሁ ጀርባ የምታዩት መመሳሰል አለበት።ታድያ ይህንን አድርገን original መሆኑን እንዴት እናውቃለን?

👍#imei ቀጥራችሁን ጽፋችሁ ምንም ካልመጣ ያለጥርጥር ስልካችሁ #highcopy ነው። ነገርግን ስለስልካችሁ የተለያዩ መረጃዎችን የሚያመጣ ከሆነ ስልካችሁ ኦርጅናል ነው።ይህንን ስልት አብዛኛው ሰው ይህን ዘዴ አያቅም::
ከላይ እንዳያችሁት የራሳችሁን ስልክ check አድርጉት!

@computer_mobile21
@computer_mobile21

Read more👇👇
https://www.google.com/amp/s/www.gizbot.com/amphtml/how-to/tips-tricks/3-ways-find-if-your-android-smartphone-or-iphone-is-original-034919.html
#ScamAlert

የፌስቡክ ገፆችን ፓስወርድ ለመንጠቅ የሚደረግ ሙከራ!

@computer_mobile21

የፌስቡክ ገፆች ላይ ያነጣጠረ አንድ የማጭበርበርያ ዘዴ ለበርካታ ሰዎች እየተላከ ይገኛል። ይህ በተለይ በርካታ ተከታዮች ያላቸው የፌስቡክ ገፆች ላይ ኢላማውን ያደረገ ዘዴ በኢትዮጵያ ለሚገኙ በርካታ ገፆችም ተልኳል።

ይህ ዘዴ የሚሰራው እንዲህ ነው: የማጭበርበርያ ገፁ "Pages security and privacy" በሚል ስም እና በፌስቡክ የገፆች አርማ/ሎጎ የተከፈተ ነው። የፌስቡክ ገፆች ላላቸው "ገፆት የመዋሸት እና የማጭበርበር ድርጊት እንደፈፀመ ሰዎች ሪፖርት አርገዋል። ይህን ለመከላከል አካውንቶትን ማረጋገጥ አለብን" ብሎ አንድ የፌስቡክ ድርጅት ንብረት ያልሆነ ሊንክ ያስቀምጣል።

ሊንኩ ሲከፈት የፌስቡክ መግቢያ (ኢሜይል/ስልክ እና ፓስወርድ) ይጠይቃል። ከዛም ተታለው/ተሳስተው ይህን መረጃ ያስገቡ ገፆችን ይጠልፋሉ። ይህም በዘርፉ ባለሞያዎች fishing attack በመባል ይጠራል።

በማይታወቁ አድራሻዎች ላይ ኢሜይል/ስልክ እና ፓስወርድ ባለማስገባት ከእንዲህ አይነት ማጭበርበርያ ድርጊቶች ራስዎን ይጠብቁ።

@computer_mobile21
@computer_mobile21
#mobile_problems
ተደጋጋሚ የሞባይል ስልክ ችግሮች እና መፍትሔዎች

1. ለሌላ ሰዉ ድምጽ ይሰማል፡፡ ነገር ግን በጣም አነስተኛ ሲሆን ወይም የራቀ ድምጽ ሲሆን 909 ወይም 904 መደወል ጥሪዉ ሲጀምር የድምፅ መጨመሪያ ቁልፍን በመጫን ድምጥን መጨመር
ችግሩ ካልተፈታ ስፒከር
ቀዳዳን ማፅዳት ከላይ
የተገለጡት መንገዶች ካልተፈታ
ስፒከሩን መቀየር ይኖርብናል፡፡

2. የስልካችን ጥሪ ከተወሰኑ
ሰከንዶች ወይም ደቂቃዎች
በኋላ ይቋረጣል፡፡ የስልካችን
የጥሪ መቼት ላይ የጥሪ ገደብ /
ኮል ታይም ሊሚት/Call time
limit/ የሚለውን ማጥፍት
በተለይ ቻይና ስልክ ላይ auto
quick end የሚል መቼትን
ማጥፍት፡፡
👉call record
👉General call setting
👉More
👉Auto quick -end
👍Off

3. የቻይና ስልኮች ላይ ኪፓዱ ላይ
ያለዉ ብርሀን ይታያል፣ በተጨማሪም ስክሪኑ ላይ ምስሎች ይታያሉ፡፡ ነገር ግን የስክሪኑ ብርሀን የማይታይ ከሆነ
ሁሉም የቻይና ስልኮች ስክሪናቸዉ ላይ ሶስት፣አራት ወይም አምስት የስክሪን ዳዩድ መስመሮች
ይገኛሉ፡፡ እነኝህ መስመሮች ከስክሪኑ ጋር የተበየዱበት ሊድ ሊለቅ ወይም ስክሪኑ ከቦርዱ
ጋር የተበየደበት ቦታ ላይ የስክሪን ብርሀን መስመሮች ተላቀዉ ከሆነ በድጋሜ ፔስትና ሊድ በመጠቀም እያንዳንዱን እግር በአግባቡ
መበየድ፡፡

4.Insert SIM የሚል ጽሁፍ
የሚያሳይ ከሆነ ሲም ካርዱ የሚሰራ መሆን አለመሆኑን የሚሰራ ስልክ በመጠቀም ማየት
የሲም መርገጫ ብረቱን በእጃችን መጫን ሲም ኮኔክተሩን በቲነር ማጠብ

5. እንደ 1110,6030,2600,2610,2310,1600 ያሉ ኖኪያ ስልኮች ላይ የሚሰራ ሲም ተጠቅመን Insert Sim የሚል ጽሁፍ
የሚያሳይ ከሆነ ቻርጅ ኮኔክተሩን ማፅዳት ወይም መቀየር ቻርጅ ኢንተርፌስ አካባቢ በቲነር ማፅዳት

6. ባትሪ ሲገባበት ቫይብሬተር
የሚያደርግ ከሆነ / ስልኩን ሳናበራዉ ልክ ባትሪ እንደገባበት በራሱ ቫይብሬት የሚያደርግ ከሆነ/
DCT3 ስልክ ከሆነ ዩአይ አይሲን መቀየር ሌሎች ስልኮች ላይ ፓወር አይሲ መቀየር

7. ኔትወርክ የሌለው ስልክ
አንቴና ኢንተርፌስ ወይም ከቦርዱ ጋር በአግባቡ መግጠሙን ማረጋገጥ ቦርዱን በቲነር ማጠብ
አንቴና ስዊቹን ማሞቅ ኔትወርኩ አሁንም ካልተስተካከለ ደግሞ አንቴና ስዊች መቀየር

8. እኔ የምናገረው ይሰማል ሌላ
ሰዉ የሚናገረዉ አይሰማኝም
ስፒከሩን መቀየር

9. ሰዉ የሚያወራው የሚሰማ ከሆነ ነገር ግን እኛ የምናወራው የማይሰማ ከሆነ
ማይኩን መቀየር

10. ወጭ ጥሪ ያደርጋል ነገር ግን
አይቀበልም ኮል ዳይቨርት በርቶ ከሆነ ማጥፍት፤ blacklist እና whitelist ማጥፋት

11. ከቁጥሮቹ መካከል አንዱ ብቻ ተነጥሎ የማይሰራ ከሆነ ቁጥሩ ላይ የሚያርፈዉን አልሙኒየም ማፅዳት

12.ተንሸራታች ስልክ ላይ ያሉት
ቁልፎች አይሰሩም ፣ከታች ያሉት
ቁጥሮች በሙሉ ይሰራሉ
ኬብል መቀየር

13.የምንሰማዉ ድምጽ ይንጫጫል/ ከሌላ ሰዉ ጋር ስንነጋገር/
ስፒከር መቀየር

14.ቁጥሮች መደዳ የማይሰሩ ከሆነ ኪፓድ አይሲን ማሞቅ ወይም መቀየር

15. ስልኩ ክፍለሃገር ሲሄድ ኔትወርኩ አይሰራም
ኔትወርክ ፊልተሩን መቀየር

16. ይሰራ የነበረ ሳምሰንግ ስልክ
ኔትወርኩ ሲጠፋ ወይም ያልተለመደ ባህሪ ሲያሳይ ( ምንም አይነት ጉዳት
ሳይደርስበት ፣ ሳይወድቅ እና ዉሀ
ሳይገባበት)፡፡
*2767*2878# በመጫን ስልኩን ፎርማት
ማድረግ ይቻላል፡፡

17. ስልክ ስናወራ የቁልፍ መጫን
ድምፅ ይሰማናል/ ሳንነካዉ በራሱ
ቁጥር ይደረድራል/
ኪፓድ አይሲን መቀየር

18.ኔትወርክ ሙሉ ሁኖ ልክ ስንደዉል ኔትወርኩ ዜሮ ይሆናል
ፓወር አምፕሊፋየሩን ማሞቅ ወይም መቀየር::
ከወደዱት ለወዳጅዎ #ያጋሩ!

@computer_mobile21
@computer_mobile21
#ethiotelecom #news
#ኢትዮ_ቴሌኮም #የሞባይል_ክፍያ አገልግሎት በቅርቡ ሊጀምር ነው

ኢትዮ ቴሌኮም በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ደንበኞች ስልካቸውን በመጠቀም ብቻ ገንዘብ እንዲልኩ፣ እንዲቀበሉና ግዢ እንዲፈፅሙ የሚያስችል የሞባይል ክፍያ አገልግሎት ሊጀምር መሆኑ ተነገረ፡፡ #ቴሌብር የተሰኘው የክፍያ ስርዓቱ ደንበኞች ካሽ ወይም ቼክ ሳያስፈልጋቸው ዘርፈ ብዙ ክፍያዎችን እንዲፈፅሙ የሚያደርግ ነው፡፡

ቴሌብር ደንበኞች በሀገር ውስጥም ሆነ ዓለም አቀፍ ደረጃ በሁሉም የትስስር መንገዶች ላይ ገንዘብ መላላክን፣ ለዕቃና አገልግሎቶች ግዢ የሚደረጉ ክፍያዎችን መፈፀም እንዲያስችል ተደርጎ መሰራቱ ተገልጿል፡፡ በዚህም ደንበኞች ለምሳሌ የትምህርት ቤት፣ የውሃና ኤሌክትሪክ እንዲሁም ሌሎች መሰል ክፍያዎችን በስልካቸው እንዲፈፅሙ ያስችላቸዋል፡፡ በተጨማሪም በኢትዮ ቴሌኮም ለሚቀርቡ እንደ አየር ሰዓት ግዢ ላሉ አገልግሎቶች ክፍያን እንዲፈፅሙ ያመቻቸ ነው፡፡ በሌላ መልኩ አገልግሎቱ የኩባንያው ደንበኞች ከሀገር ውጪ ካለው ዲያስቦራ ገንዘብ እንዲቀበሉ፣ ገንዘባቸውን እንዲቆጥቡ፣ ብድር እንዲያገኙና የባንክ አካውንታቸውን ከቴሌብር ጋራ እንዲያስተሳስሩ የሚፈቅድ ይሆናል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቱን ያስጀምር ዘንድ ከአንድ ዓመት በፊት ለዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ፍቀድ ለሚሰጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጥያቄውን አቅርቦ ነበር፡፡ ባንኩም ለአገልግሎቱ አረንጓዴ መብራት ከሰጠ በኋላ ነው ኩባንያው እንቅስቃሴውን የጀመረው፡፡

ደንበኞች ለቴሌብር ለመመዝገብ የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ ያለበት ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን እና ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ይዘው ወደ ቴሌብር ወኪሎች አልያም የኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ማዕከላት በማምራት መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
ምንጭ Capital

@computer_mobile21
@computer_mobile21
በወረቀት ያለን ጽሁፍ ወደ Soft copy መቀየር የሚችል apk Image በመጠቀም

Downlaod it
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=image.to.text.ocr
#speedup_pc
ኮምፒውተርዎን ፈጣን የሚያደርጉ 9 ዘዴዎች

1. ትላልቅ መጠን ያላቸውን ፎቶዎች #ዎልፔፐር አይጠቀሙ፡፡
2. ሁሌም ኮምፒዩተሩ ከፍቶ ሳይጨርስ# አፕሊኬሽን ለመክፈትም ሆነ
ለመነካካት አይሞክሩ፡፡
3. አፕሊኬሽን ከዘጉ በሁዋላ ዴስክቶፑን #ሪፍሬሽ ያድርጉ፤ ይህም
ራም ሜሞሪን ነፃ ያደርጋል፡፡

4. የማይጠቀሙበት ሶፍትዌር ካለ ከኮምፒውተሩ #ይሰርዙ (uninstall) ያድርጉት
5. ዴስክቶፕ ላይ #ፋይል አያስቀምጡ፤ ሾርትከትም መብዛት
የለበትም፡፡
6. ኮምፒዩተሩ ሲከፈት በራሳቸው የሚከፈቱ ለምሳሌ: ስካይፕ አይነት
አፕሊኬሽኖች ካሉ #disable ያድርጉ

7. Recycle binን ሁሌም #ባዶ ያድርጉ::
8. ሀርድ ዲስኩን ሁለት #ፓርቲሽን ይፍጠሩለት፡፡
9. ብዙ #ሶፍትዌሮችን ባንዴ አይክፈቱ::

@computer_mobile21
@computer_mobile21
👍1
#mobile_problems
ተደጋጋሚ የሞባይል ስልክ ችግሮች እና መፍትሔዎች
@computer_mobile21

#1.ለሌላ ሰዉ ድምጽ ይሰማል፡፡ ነገር ግን በጣም አነስተኛ ሲሆን ወይም የራቀ ድምጽ ሲሆን 909 ወይም 904 መደወል ጥሪዉ ሲጀምር የድምፅ መጨመሪያ ቁልፍን በመጫን ድምጹን መጨመር ችግሩ ካልተፈታ ስፒከር ቀዳዳን ማፅዳት ከላይ በተገለጡት መንገዶች ካልተፈታ ስፒከሩን መቀየር ይኖርብናል፡፡

#2.የስልካችን ጥሪ ከተወሰኑ ሰከንዶች ወይም ደቂቃዎች በኋላ ይቋረጣል፡፡ የስልካችን የጥሪ መቼት ላይ የጥሪ ገደብ /ኮል ታይም ሊሚት/Call time limit/ የሚለውን ማጥፍት በተለይ ቻይና ስልክ ላይ auto quick end የሚል መቼትን ማጥፍት፡፡
👉call record
👉General call setting
👉More
👉Auto quick -end
👉Off
@computer_mobile21

#3.የቻይና ስልኮች ላይ ኪፓዱ ላይ ያለዉ ብርሀን ይታያል፣ በተጨማሪም ስክሪኑ ላይ ምስሎች ይታያሉ፡፡ ነገር ግን የስክሪኑ ብርሀን የማይታይ ከሆነ
ሁሉም የቻይና ስልኮች ስክሪናቸዉ ላይ ሶስት፣ አራት ወይም አምስት የስክሪን ዳዩድ መስመሮች ይገኛሉ፡፡ እነኝህ መስመሮች ከስክሪኑ ጋር የተበየዱበት ሊድ ሊለቅ ወይም ስክሪኑ ከቦርዱ ጋር የተበየደበት ቦታ ላይ የስክሪን ብርሀን መስመሮች ተላቀዉ ከሆነ በድጋሜ ፔስትና ሊድ በመጠቀም እያንዳንዱን እግር በአግባቡ መበየድ፡፡

#4.Insert SIM የሚል ጥሁፍ የሚያሳይ ከሆነ ሲም ካርዱ የሚሰራ መሆን አለመሆኑን የሚሰራ ስልክ በመጠቀም ማየት የሲም መርገጫ ብረቱን በእጃችን መጫን ሲም ኮኔክተሩን በቲነር ማጠብ እንደ 1110,6030,2600,2610,2310,1600 ያሉ ኖኪያ ስልኮች ላይ የሚሰራ ሲም ተጠቅመን Insert
Sim የሚል ጥሁፍ የሚያሳይ ከሆነ ቻርጅ ኮኔክተሩን ማፅዳት ወይም መቀየር ቻርጅ ኢንተርፌስ አካባቢ በቲነር ማፅዳት

#5.ባትሪ ሲገባበት ቫይብሬተር የሚያደርግ ከሆነ / ስልኩን ሳናበራዉ ልክ ባትሪ እንደገባበት በራሱ ቫይብሬት የሚያደርግ ከሆነ/ DCT3 ስልክ ከሆነ ዩአይ አይሲን መቀየር ሌሎች ስልኮች ላይ ፓወር አይሲ መቀየር

#6.ኔት ወርክ የሌለው ስልክ አንቴና ኢንተርፌስ ወይም ከቦርዱ ጋር በአግባቡ መግጠሙን ማረጋገጥ ቦርዱን በቲነር ማጠብ አንቴና ስዊቹን ማሞቅ ኔትወርኩ አሁንም ካልተስተካከለ ደግሞ አንቴና ስዊች መቀየር

#7.እኔ የምናገረው ይሰማል ሌላ ሰዉ የሚናገረዉ አይሰማኝም ስፒከሩን መቀየር
@computer_mobile21

#8.ሰዉ የሚያወራው የሚሰማ ከሆነ ነገር ግን እኛ የምናወራው የማይሰማ ከሆነ ማይኩን መቀየር

#9.ወጭ ጥሪ ያደርጋል ነገር ግን አይቀበልም ኮል ዳይቨርት በርቶ ከሆነ ማጥፍት

#10.ከቁጥሮቹ መካከል አንዱ ብቻ ተነጥሎ የማይሰራ ከሆነ ቁጥሩ ላይ የሚያርፈዉን አልሙኒየም ማፅዳት

#11.ተንሸራታች ስልክ ላይ ያሉት ቁልፎች አይሰሩም ፣ከታች ያሉት ቁጥሮች በሙሉ ይሰራሉ
ኬብል መቀየር

#12.የምን ሰማዉ ድምጽ ይንጫጫል/ ከሌላ ሰዉ ጋር ስንነጋገር/ ስፒከር መቀየር

#13.ቁጥሮች መደዳ የማይሰሩ ከሆነ ኪፓድ አይሲን ማሞቅ ወይም መቀየር

#14.ስልኩ ክፍለሃገር ሲሄድ ኔትወርኩ አይሰራም ኔትወርክ ፊልተሩን መቀየር

#15.ስልክ ስናወራ የቁልፍ መጫን ድምፅ ይሰማናል/ ሳንነካዉ በራሱ ቁጥር ይደረድራል/ ኪፓድ አይሲን መቀየር

#16. ኔትወርክ ሙሉ ሁኖ ልክ ስንደዉል ኔትወርኩ ዜሮ ይሆናል ፓወር አምፕሊፋየሩን ማሞቅ ወይም መቀር

JOIN👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21
Share share
#pc_manufacturing_date

የኮምፒውተራችን እድሜ ስንት እንደሆነ ለማወቅ👇

1. System information በመጠቀም
👉Search bar ላይ System information ብላችሁ ጻፉ

👉 ክሊክ ስትሉት ከሚመጡት ዝርዝር አማራጮች BIOS Version/date ላይ ኮምፒተሩ የተገጣጠመበትን ቀን ታገኛላችሁ

2. CMD በመጠቀም

👉አሁንም Search bar ላይ CMD ብላችሁ ጻፉ

👉 open CMD

👉CMD ሲከፍት systeminfo.exe ብላችሁ ጻፉና ENTER በሉት ከሚመጡት ዝርዝር አማራጮች BIOS Version ላይ ኮምፒተሩ የተገጣጠመበትን ቀን ታገኛላችሁ::

@computer_mobile21
Using System information
#tech_news

አዲሱ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከአንድሮይድ እና አይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች የተለየ ነው!

#ህዋዌ ‘ሀርመኒ’ የተሰኘ የራሱን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከትናንት ጀምሮ ወደ ስራ ማስገባቱን አስታውቋል።አዲሱ የሁዋዌ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ከትናት ምሽት ጀምሮ በርከት ላሉ የስማርት ስልክ ሞዴሎች መልቀቅ መጀመሩም ተነግሯል።በዚህም ሁዋዌ አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ስልኮች የሚጠቀሙ ሰዎች ኦፕሬቲንግ ሲስተማቸውን ወደ አዲሱ ‘ሀርመኒ’ ኦፕሬቲንግ ሲስተም እንዲቀይሩ እድል ሰጥቷል።
@computer_mobile21
ሁዋዌ ‘ሀርመኒ’ የተባለ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ይፋ ማድረጉ ከዚህ በኋላ የአሜሪካ ምርት ከሆነው የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ጥገኝነት የሚገላግለው ሆናልም ተብሏል።
የቻይናው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሁዋዌ የስማርት ስልክ ገበያውን ከጎዳው የአሜሪካ የኢኮኖሚ ማእቀብ ለማገገም እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል።የአሜሪካ ማእቀብ ጎግል አልፋ ቤት ግሩፕ ለአዳዲስ የሁዋዌ ስማርት ስልክ ሞዴሎች የቴክኒክ ድጋፍን እንዳይሰጥ የሚከለከል መሆኑ ይታወሳል።
@computer_mobile21
ይህንን ተከትሎም ሁዋዌ አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለመተካት የሚያስችለውን አማራጭ የራሱን ኦፕሬቲንግ ሲስተም መስራት መጀመሩም ይታወሳል።
አዲሱ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከአንድሮይድ እና አይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች የተለየ መሆኑን ሁዋዌ አስታውቋል።‘ሀርመኒ’ የተባለውን ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማንኛውም ስማርት ስልክ ላይ መገልገል እንዲቻል ተደርጎ መሰራቱም ነው የተገለፀው::

@computer_mobile21

Read more👇
https://techcrunch.com/2021/06/02/huawei-officially-launches-android-alternative-harmonyos-for-smartphones/?guccounter=1
#shutdown #Hibernate #sleep

ኮምፒውተራችን ላይ Sleep, Hibernate, Shutdown ልዩነታቸው ምንድን ነው?

#ኮምፒውተርም እንደ ሰው ይደክማል፤ ጫና ሲበዛበትም ከተለመደው ፍጥነቱ ዘግይቶ መንቀራፈፍ ይጀምራል። በመሆኑም ስራችንን ከጨረስን በኋላ በተለያዩ መንገዶች ኮምፒውተራችን ማጥፋት ወይም ማሳረፍ ያስፈልጋል።
@computer_mobile21

ኮምፒውተራችን “ተርን ኦፍ”፣ “ስሊፕ” አልያም “ሀይበርኔት” በማድረግ እረፍት እንዲያገኝ ማድረግ እንችላለን። ይሁን እንጂ የትኛው የተሻለ መንገድ ነው የሚለው የሚያከራክር ጉዳይ ነው። እናም ከዚህ በታች ስለ ሶስቱ ኮምፒውተር ማሳረፊያ ዘዴዎች ጥቅሞች እና ጉዳቶች በዝርዝር እንመለከታለን።

#1 “ስሊፕ” #Sleep

በቀደሙ የዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ባላቸው ኮምፒውተሮች ላይ “ስታንድ ባይ” የሚል ስያሜ የነበረው “ስሊፕ” የኮምፒውተራችን የሀይል ፍጆታ የሚቀንስ ነው።

ላፕቶፕ ኮምፒውተራችን “ስሊፕ” ሞድ ላይ ስናደርገው ከራሙ በስተቀር ወደ ሁሉም የኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚሰራጨው ሀይል ይቋረጣል። የስሊፕ ሌላኛው ጥቅሙ ኮምፒውተራችን ከመዝጋታችን በፊት የተከፈቱ ስራዎችን ሴቭ ማድረጉ ነው። ከዚህም ባሻገር ያቆምነውን ስራ በፍጥነት ለመጀመር ይረዳል።

ይሁን እንጂ ስሊፕ ማድረግ ከሸት ዳውን እና ሃይበርኔት የበለጠ ሀይል ይወስዳል። በመሀል የሀይል መቋረጥ ከተከሰተም ሴቭ ሳናደርግ የተውናቸው ስራዎች ሊጠፉ ይችላሉ። በመሆኑም ኮምፒውተራችን “ስሊፕ” ከማድረጋችን በፊት የተጀመሩ ስራዎችን ሴቭ ማድረግ ተገቢ ነው።
@computer_mobile21

#2 “ሸት ዳውን” shutdown
ብዙዎቻችን ኮምፒውተራችን የምናጠፋው “ሸት ዳውን” የሚለውን አማራጭ በመጠቀም ነው። በዚህ ጊዜ ሁሉም ነገር ይዘጋል፤ የራም (ራንደም አክሰስ ሚሞሪ) ሚሞሪም ይጠፋል፤በአጠቃላይ ኮምፒውተሩ ምንም እንቅስቃሴ አይኖረውም። በ”ሸት ዳውን” የተዘጋ ኮምፒውተር ምንም ሀይል አይጠቀምም። ይሁንና ኮምፒውተራችን በድጋሚ ስንከፍት ዘለግ ያለ ጊዜ (ከ“ስሊፕ” አንፃር) ይወስዳል።

#3“ሀይበርኔት” #Hibernate

ይህ አማራጭ ደግሞ በ”ስሊፕ” እና በ”ሸት ዳውን” መሀል የሚገኝ ነው። “ሀይበርኔት” ስናደርግ እያከናወንናቸው የነበሩ ስራዎች በራም ሳይሆን በኮምፒውተራችን ሀርድ ድራይቭ ላይ ይቀመጣሉ። ኮምፒውተራችን ስናስነሳም ሴቭ ሳናደርግ ትተናቸው የነበሩ ስራዎችን የምናገኛቸው ሲሆን፥ ከ“ስሊፕ” አንፃር አነስተኛ ሀይል ይወስዳል። ነገር ግን ስሊፕ ያደረግነውን ኮምፒውተር ስንከፍት ከሚወስደው ጊዜ ዘግየት የማለት ባህሪ አለው። በሀይበርኔትም ሆነ “ሸት ዳውን” ኮምፒውተራችን ስናጠፋ እና ስንከፍት የምንጠቀመው ሀይል ተመሳሳይ ነው።

ኮምፒውተራችን ሀይል በመጨረስ ላይ ከሆነ “ሀይበርኔት” ተመራጭ ነው።

መቼ ነው “ስሊፕ”፣ “ሸት ዳውን” ወይም “ሀይበርኔት ማድረግ የሚኖርብን?

በቀን ውስጥ ለተከታታይ ስአታት ኮምፒውተራችንን የምንጠቀምበት ከሆነ ሙሉ በሙሉማጥፋት (ሸት ዳውን) አይጠበቅብንም። ይሁን እንጂ በቀን ውስጥ ለአንድ ስአት አልያም ለሁለት ስአት የምንጠቀም ከሆነ ሙሉ በሙሉ ቢጠፋ መልካም ነው።

ካቆምንበት በአጭር ጊዜ ተመልሰን ስራችንን ለመቀጠል “ስሊፕ” ተመራጭ ነው።“ስሊፕ” ስናደርግ ኮምፒውተራችን በፈለግነው ቅፅበት ዝግጁ ይሆናል።

ለስአታት አልያም ለቀናት ኮምፒውተራችን እንዲያርፍ ስንፈልግ ደግሞ “ሸት ዳውን”ማድረጋችን መዘንጋት የለብንም።በርካታ ሰዎች የዘጉት ኮምፒውተር በፍጥነት እንዲከፈት በማሰብ “ሸት ዳውን” ከማድረግ ይልቅ “ሀይበርኔት”ን ይመርጣሉ። ነገር ግን አንዳንድ ኮምፒውተሮች እና ሶፍትዌሮች ከ”ሀይበርኔት” መልስ ተግባራቸውን በአግባቡ ማከናወን ሊሳናቸው ይችላል። እንዲህ አይነት ችግር ሲያጋጥም “ሸት ዳውን” ማድረጉ ተመራጭ ነው።

ከ“ስሊፕ” ይልቅ “ሀይበርኔት” ሀይል በመቆጠብ ረገድ የተሻለ ነው። ረዘም ላለ ስአታት የጀመርነውን ስራ ማቋረጥ ከፈለግን “ሀይበርኔት” ማድረግ ይመከራል። ለምሳሌ ለእንቅፍል ወደ መኝታ ክፍላችን ስናመራ። “ሀይበርኔት” የኤሌክትሪክ ሀይልን እና የኮምፒውተር ባትሪን ሀይል ለመቆጠብ ይረዳል።በአጠቃላይ ኮምፒውተራችን እንደምንጠቀምበት አግባብ የእረፍት ጊዜ እነዲኖረው ከላይ የጠቀስናቸውን ማሳረፊያዎች መጠቀም ይገባል።

@computer_mobile21
@computer_mobile21

Read more👇
https://www.howtogeek.com/128507/htg-explains-should-you-shut-down-sleep-or-hibernate-your-laptop/
#windows_11

የዊንዶውስ 10 ኦፐሬቲንግ ሲስተም ይተካል ተብሎ የታሰበው አዲሱ የዊንዶውስ 11 ኦፐሬቲንግ ሲስተም ይፋ ሁኖል በጣም ብዙ አዳዲስ እና ማራኪ ነገሮዎችን ይዞ የቀረበው ይህ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ሰኔ(ጁን) 24 ሙሉ በሙሉ ይለቀቃል፡፡
Windows starting menu ከበፊቱ ዊንዶስ 10 ጋር ይመሳሰላል።

የዊንዶውስ 11 ኦፐሬቲንግ ሲስተም አዳዲስ ፊውቸሮዎች መካከል
#1.አዲስ አንሜሽን አክቶል(New Animation)

#2 ብዙ ስራዎችን በቀላሉ እንድንሰራ የሚስችል መልቲ ታስኪንግ(Multi Tasking)
#3 ተች ኮንትሮል(Touch Controls)

#4. አዲስ እና ምርጥ ሳውንድ(Fresh Sounds)

#5.ዳርክ ሞድ (Dark Mode)

#6 የጠርዝ እጥፋት (Rounded Corner)

#7.አዳዲስ አይከኖዎችን(New Icons)

#8.ቨርችዎል ዴስክቶፕ(Virtual Desktop)

#9.ዊጀት(Widgets)

#10.አክሽን ሴንተር (Action Center)
@computer_mobile21

Read more👇👇
https://www.techradar.com/news/windows-11
#memory #originality
ኦርጂናል እና ፌክ ሚሞሪ እንዴት መለየት ይቻላል
ኦርጂናል ሚሞሪ ከፌኩ በምን ይለያል?
:::::::::::::::::::::::::::
#1ኛ. ኦርጂናል ሚሞሪዎችን የምናረጋግጥበት የመጀመሪያው ና ቀላሉ መንገድ የሚሆነው ሚሞሪውን ስልካችን ውስጥ በማስገባት ፎርማት(Format)
ማድረግ ነው። ሚሞሪውን ፎርማት(Format) ስናረገው ኦርጂናል ከሆነ ፎርማቱን ያለ
ምንም ችግር ይጨርሳል
ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ ፎርማት መሆን ስለ ማይችል ኢረር(Error) ቦክስ ያሳያቹና ይቋረጣል
@computer_mobile21
==================
#2ኛ.በኮምፒውተሮ ወይም በስልኮ ወደ ሚሞሪው ፍይሎችን ኮፒ በማድረግ ማረጋገጥ ይቻላል ለምሳሌ አንድ 1GB የሚሆን
ፊልም ወይም ሌላ ፍይል ወደ ገዛነው ሚሞሪ ኮፒ ስናደርግ በሚወስደው ሰዓት ማወቅ
ይቻላል ኦርጂናል ከሆነ 1GB ፍይል ኮፒ ለማረግ በጣም በዛ ከተባለ 5 ደቂቃ ይወስዳል
ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ 1GB ፍይል ኮፒ ለማረግ 10 - 30 ደቂቃ ሊወስድ ይችላል። ይህ ማለት ሚሞሪው በጣም ደካማ ነው ማለት ነው።
@computer_mobile21
===============
#3ኛ.ሶስተኛው መንገድ ደሞ ስልካችን ውስጥ በማስገባት ይህን SD insight የተባለ አፕፕ(App) ተጠቅመን ማወቅ እንችላለን አፑን ከዚህ ዳውንሎድ መድረግ ይችላሉ
https://www.apkmirror.com/apk/humanlogic/sd-insight-2/sd-
insight-2-1-5-9-release/sd-insight-1-5-9-android-apk-download/
ስልካችን ውስጥ ሚሞሪ አስገብተን ይህን አፕፕ ስንከፍተው ስለ ሚሞሪው ምርት መረጃ ካሳየን ሚሞሪው ኦርጂናል ነው ማለት ነው
ለምሳሌ ሲሪያል ቁጥር እና የትአይነት እንደተመረተ እናም ሌሎችን ማለት ነው።
ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ ምንም መረጃ አያሳየንም ይህ ማለት
ሚሞሪው የት እንደተመረተ እና ሲሪያል ቁጥር የለውም ማለት ነው ስለዚህ የማይታወቅ ሚሞሪ ነው ማለት ነው።

@computer_mobile21
@computer_mobile21

Read more 👇👇👇
https://photographylife.com/fake-memory-cards/amp

Share በማድረግ ይተባበሩን!
👍1
#pdf_reader_background_and_text color

🔰አብዛኛውን ጊዜ በኮምፒውተር soft copy pdf reader'ን ተጠቅመን ስናነብ white background እና black text ሆኖ ነው የምናገኘው። ነገር ግን ለአንዳንዶቻችን ይህ ለአይናችን ምቾት ላይሰጠን ይችላል:: ከታች ያለውን ቅደም ተከተል በመጠቀም ወደ የምንፈልገው መቀየር እንችላለን።

#1. open pdf files using PDF reader

#2. 🔝 Click on 'Edit'

#3. click on 'Preference'

#4. select 'Accessible'

#5. tick on 'Replace document color'

#6. tick on 'In Custom color'
'Page background'
'Document text'
እነዚህ ሁለቱ ላይ የምንፈልገውን እንመርጣለን

#7. Click 'ok'
ለውጡ ወዲያው ይመጣል::
👍ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት❗️

@computer_mobile21

Read More👇👇👇
https://aavtech.site/2018/01/change-background-color-in-pdf-readers/
ለ3 ቀናት የሚቆይ : #ነፃ አገልግሎት
# Ethiopia | ኢትዮ-ቴሌኮም ለ3 ቀናት የሚቆይ ነፃ አገልግሎት ለደንበኞቹ አቅርቧል
በዚህም👉 1GB የኢንተርኔት እና
👉303 Flexi Unit ነፃ ስጦታ ቀርቧል::
ይህም ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ቀናት ማለትም ከሀምሌ 6 እስከ ሀምሌ 9 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ነዉ::
የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደተናገሩት ይህ ከክፍያ ነፃ የሆነዉ አገልግሎት ከሌሊት 6 ሰዓት እስከ ምሽት 12 ሰዓት ብቻ ስራ ላይ የሚዉል ነዉ::
ኢትዮ-ቴሌኮም ይህን ነፃ አገልግሎት ለደንበኞቹ ለማቅረቡ በ2013 በጀት ዓመት የ56 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በመቶኛ ሲሰላ የ101 ነጥብ 1 በመቶ ገቢ ማስገባቱ በምክንያትነት ተጠቅሷል::

Join👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21
Share
How to Fix Windows 10 is installing very slowly (Extremely Slow)

https://www.techsupportall.com/how-to-fix-windows-10-is-installing-very-slowly-extremely-slow/

Contact @seen311 or @seen3bot

Group👉 @Computer_Mobile3
#software_speedup
#የኮምፒዩተራቹ_operating_system_window_10 ነው?

በምትከፍቱት እና በምትጠቀሙበት ሰአት #እየተንቀራፈፈ_አማሯችዋል? እንግዲያውስ #ፍጥነቱን ሊጨምሩ የሚችሉ ነገሮችን እናያለን።

#1_Power_option
Start menu ላይ power option ብላቹ ፈልጉ ከሚመጣላቹ window ውስጥ high performance የሚለውን ምረጡ

#2_Disable_unwanted_start_up_programs
ይሄ ኮምፒዩተራችንን በምንከፍትበት ጊዜ ያለ እኛ ፍቃድ ፕሮግራሞችን እየከፈተ
ፍጥነቱን ከሚቀንሱ ነገሮች አንዱ ነው። ይሄን ለመከላከል Task manager ላይ መግባት (ይሄን ለማግኘት start menu ላይ right
click አድርጎ ማግኘት ይቻላል አልያም Ctrl Alt እና delete
የሚለውን አንድ ላይ መጫን)
ከሚመጣው window ውስጥ start up ላይ በማድረግ የማትፈልጉትን ፕሮግራሞች disable ማድረግ። እዚህ ጋር impact የሚለው high ከሆነ
disable ባታረጉ ይመረጣል።

#3_Defragment_and_optimize_drive
Start menu search bar ላይ defragment ብሎ መፈለግ Window ሲመጣላቹ የምትፈልጉትን driver መርጣቹ
optimize ማድረግ

#4_Delete_unnecessary_temporary_file
Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን
መምረጥ አልያም
window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን
%temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን
የሚመጣላቹ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን
ሁሉንም ሲመርጥልን
ማጥፋት
ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላቹ
folder ውስጥ
ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት
አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ
የሚመጣላቹ
folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት።
እነዚህን የምናጠፋበት ምክንያት ጊዜያዊ እና space የያዙ
ፋይሎች ስለሆኑ
ነው። ምንም አይነት ችግር አያመጡም።

#5_Clean_up_Memory
This pc ውስጥ ገብታቹ የምፈልጉት local ዲስክ ላይ right click በማድረግ property መምረጥ Disk clean up የምትለውን icon click ማድረግ የሚመጣውን የ warning box ok ማድረግ
እዚህ ጋ recycle bin ውስጥ ያሉ ፋይሎች ሳይቀሩ ነው የሚጠፉ ት

#6_Reduce_run_time_service
Run box ከፍታቹ msconfig ብሎ መጻፍ ቀጥሎ ከሚመጣው window service የሚለውን መጫን በመቀጠል hide all microsoft service የሚለውን tickvማድረግ
በመቀጠል disable የምትለዋን icon click ማድረግ

#7_Registry_tweaks
Run box መክፈት(window key + R) regedit ብሎ መጻፍ
Hkey -current user
Control panel Mouse
Mouse hover time
valueን ወደ 10 መቀየር
እዛው folder ላይ desktop መምረጥ Menu show delay
Valueን ወደ 10 መቀየር

#8_visual_effects
Start menu ላይ System ብሎ መፈለግ Advanced system setting መምረጥ
Advance ውስጥ በመግባት setting መምረጥ Adjust for best performance መምረጥ ቀጥሎ የምትፈልጉት ነገር ካለ ቲክ በማድረግ መምረጥ
በመጨረሻም ከላይ ያሉትን ከጨረስን በኋላ ኮምፒዩተራችንን
Restart ማድረግ::

@computer_mobile21