COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE
7.1K subscribers
71 photos
7 videos
53 files
103 links
Welcome To Computer & Mobile Maintenance Channel.
It Gives You Some Hints To Repair(Improve Performance Of) Your Computer & Mobile By Yourself. ለጠጋኞችም የሚጠቅም ምርጥ ቻናል ነው!
JOIN @Computer_Mobile21
Contact @seen311 or @seen3bot

Group👉 @Computer_Mobile3
Download Telegram
#boot_key

የኮምፒውተሮን OS ለመቀየር ወይንም በሆነ አጋጣሚ Boot Menu ውስጥ መግባት ፈልገው በየትኛው Key እንደሚገባ ግራ ገብቶዎታል?

ከዚህ በታች የትኛው Laptop/Desktop በየትኛው Key Boot Menu ወይም BIOS setting ማምጣት እንደምንችል እንመልከት:

👉Acer = Esc,F12,F9,F2
👉Apple = Option Button
👉ASUS = F8,ESC,DEL,F9,F2
👉COMPAQ = ESC,F9,F10
👉Dell = F12,F2
👉Emachines = F12,Tab,Del
👉Hp = F9,F10,F1,ESC
👉intel = F10
👉Lenovo = F8,F10,F1,F12,F1,F2,Fn + F11
👉NEC = F5,F2
👉PACKARD BELL = F8,F1,Del
👉Samsung = F1,ESC,F2
👉SHARP = F2
👉SONY = F10,F11,F1,F2,F3
👉TOSHIBA = F12,F1,ESC

@computer_mobile21

Read more👇👇
https://www.wikigain.com/boot-menu-option-keys-for-all-laptops-desktops/
#online_jobs

# ኦንላይን_ስራዎች_ለምትፈልጉ

አንዳንዶቻችን ኮምፒውተርና ኢንተርኔት በመጠቀም ቤታችን ቁጭ ብለን ኦንላይን የምንሰራው ስራ ካለ ብትጠቁመን ብላችሁ ትጠይቁኛላችሁ፡፡

በዚህ ቴክኖሎጂ በተራቀቀበት ዘመን ሁሉም ስራዎች ኦንላይን እየሆኑ መጥቷል፡፡ ሰዎች በኮምፒውተርና ኢንተርኔት አማካኝነት ቤታቸው ቁጭ ብለው የተለያዩ ስራዎች ለተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ኩባንያዎች በመስራት ከፍተኛ ገቢ ያገኛሉ፡፡

ኦንላይን ስራ በጣም እየተለመደ መጥቷል፡፡ የተለያዩ ኩባንያዎች ብዙም ማሰላሰል የማይጠይቁ ስራዎች ለምሳሌ፡- ዳታ መመዝገብ፡ መፅሀፎችን ፊደል ማረም፤ድምፅን ወደ ፁሁፍ መገልበጥ፤ወዘተ ስራዎች በስፋት ኦንላይን ያሰራሉ፡፡
ኦንላይን ስራዎችን በመስራት ጥሩ ገቢ ማግኘት እያሰባችሁ ያላችሁ ሰዎች ካላችሁ ኦንላይን ልትሰሯቸው የሚችሉ 3 ስራዎች እንጠቁማችሁ፡፡

#1ኛ፡- Copy Editor
ጥሩ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እውቀት ካላችሁ ይህ ስራ በጣም ጥሩ ነው፡፡ በዚህ ዘርፍ ብዙ ኦንላይን ስራዎች አሉ፡፡
በዚህ ዘርፍ ከናንተ የሚጠበቀው ስራ የተለያዩ ፁሁፎች ይሰጣችኋል ። ከዚያ ያንን ፁሁፍ ፊደል ማረም ነው፡፡ፊደል ማረም ሲባል ፁሁፉ ላይ ቃላት የተገደፉ ካሉ ማስተካከልና ማረም የመሳሰሉት ማለት ነው፡፡
በዚህ ዘርፍ ዌብሳይቶች፤መፅሀፍት፤መፅሔቶች እና የመሳሰሉትን እንድታርሙ ትጠየቃላችሁ፡፡
ጥሩ ስራ ይመስለናል፡፡
እንዲህ ዓይነት ኦንላይን ስራ ከፈለጋችሁ
"copy editor online jobs" ብላችሁ ጎግል ብታደርጉ ብዙ ስራዎችን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

#2ኛ፤- Transcriber
ይህ ኦንላይን ስራ ሪከርድ የተደረገ ድምፅ ይሰጣችኋል፡፡ድምፁን እያዳመጣችሁ ወደ ፁሁፍ መተርጎም ነው፡፡ለምሳሌ በፈረንሳይኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ንግግር ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ በፁሁፍ መተርጎም ነው፡፡ በተለይ እንግሊዘኛ እና ፈረንሳይኛ ቋንቋ ችሎታ ያላችሁ ይህ ጥሩ ስራ ይመስለናል።
የሚሰጣችሁ ድምፅ ንግግር፤ስብሰባ ላይ የተደረገ ንግግር፤ቪዲዮ ኮንፈረንስ ሊሆን ይችላል፤ትምህርቶች ሊሆን ይችላል፡፡ወዘተ
Online Transcriber Jobs ብላችሁ ጎግል ብታደርጉ ብዙ ስራዎችን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

#3ኛ፡- Data Entry
ይህ ኦንላይን ስራ የተለያዩ መልክ ያልያዙ ዳታዎችን መመዝገብ ነው፡፡ ለምሳሌ የትምህርት ቤቶች ወይም የሆስፒታል ትልልቅ ዳታዎችን ወደ Excel ማስገባት ወይም መመዝገብ ማለት ሊሆን ይችላል።፡
በተለይ ቁጭ ብሎ የመስራት ትዕግስት ያላችሁ ሰዎች ይህ ስራ ጥሩ ይመስለናል፡፡
እንደዚህ ዓይነት ኦንላይን ስራዎች ለመስራት ኢንተርኔትና ኮምፒውተር ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡
ከላይ ከገለፅኳቻው ስራዎች ውጪ ሌሎች ብዙ ኦንላይን ስራዎችን ብትፈልጉ ታገኛላችሁ፡፡ሞክሩ::

@computer_mobile21

#SHARE

Read More 👇👇👇
https://www.thebalancecareers.com/make-money-typing-from-home-3542490
#phone_addiction

ስልክዎን በመነካካት #ሱሰ ተጠምደዋል፤ መፍትሄ እንጠቁመዎ:

በስልክዎ ማለቂያ አልባ ይዘት (content) ተውጠው ያውቃሉ ?
በተደጋጋሚስ ስልኮትን ይነካካሉ?

አንዳቸውም የእርስዎ ጥፋት አለመሆኑን ብንነግርዎስ፤ ይልቁንም ስልኮችዎ እንዲህ እንዲያደርግዎት ታስበው ነው የተሰሩት ፤ በኪሶቻችን ውስጥ ስላሉት ስለእነዚህ ኃይለኛ መሣሪያዎች ንድፍ (አሰራር) የበለጠ ባወቅን መጠን በጤንነት፣ ግንኙነታችን እና በወደፊቱ ስኬታችን ላይ እንዴት ተፅእኖ እንደሚፈጥሩ ለመቆጣጠር የበለጠ እንረዳለን።

👉 ስልካችን እንዴት ነው የተነደፈው? እኛስ ምን ማድረግ አለብን?

ስልኮቻችን የተሰሩት የእኛን ስነ-ልቦና በመከተል ስለሆነ ትኩረታችንን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ በትክክል ያውቃሉ፡፡ ታድያ ስልኮቻችን ሱስ እንዲያስይዙን ተደርገው ነው የተሰሩት? ስልኮቻችንን መልሰን መቆጣጠር እንችላለን?

የኮምፒዩተርና ሞባይል ጥገና በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ስልኮቻችን እንዴት ጊዜያችንን ለመውሰድ እንደተፈጠሩና እኛም ማድረግ የምንችላቸውን ጥቂትና ቀላል እርምጃዎችን ያሳየናል👇

1⃣ ማሳወቂያዎች (notifications) እንዳይደርሱን ማድረግ፤
በህይወታችን አስፈላጊ ከሆኑ ሰዎች በስተቀረ ለሌሎቹ ምላሽ አይስጡ፡፡ ሁሉንም ዜናዎች በተከሰቱበት ቅፅበት ማወቅ ምን ያደርግልዎታል? ሁሉንም ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት በቀን የተወሰነ ጊዜ መመደብ ብቻ በቂ ነው፡፡

2⃣ የስልክዎን ብርሀን ያደብዝዙ፤
በእይታችን ውስጥ የገቡ ቀለም እና ምልክቶች ትኩረት እንድንሰጣቸው ያነሳሱናል፡፡ ስለሆነም ቀለማቱን ከሰወርን አዕምሮአችንን ወደ ስልከላችን የሚማርክ ምንም ነገር አይኖርም፡፡

3⃣ የመነሻ ገጽዎን (home screen) ያስተካክሉ፤
በዚህ ተግባር ውስጥ ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ጠቃሚ የሆኑትን መተግበሪያዎችን (የቀን መቁጠሪያ፣ አድራሻዎች፣ ካርታ፣ የባንክ አገልግሎት…) ብቻ በማቆየት ሌሎቹን ከመነሻ ገጽዎ ያንሷቸው፡፡ እነዚህ ያነሳችዋቸው የማህበራዊ ሚዲያ እና ሌሎች መተግበሪያዎችን በመሰብሰብ በቀላሉ ሊያገኟቸው በማይችሉበት ቦታ ያስቀምጡ፡፡

4⃣ ስልክዎን በቀላሉ በማይደርሱበት ስፍራ ያስቀምጡ፤
ይህ ቀለል ያለ መፍትሄ ነው፤ ስልክ ከጎንዎ ከሌለ ጊዜዎትን ሊወስድ አይችልም።

5⃣ ሱስ የሚያስይዙትን እነዚህን ባህሪያትን ለበጎ የሚጠቀሙ መተግበሪያዎችን ያውርዱ፤
ጤናማ ባህርያት ወይም ልምዶችን እንድናዳብር የሚያግዙን የሚያግዙ ብዙ መተግበሪያዎች አሉ፡፡ እነዚህን አይነት መተግበሪያዎች ማህበራዊ ትስስርን የሚያበረታቱና ጤናማ አኳን እንዲኖረን የሚያደርጉ ናቸው፡፡

በመጨረሻም ቴክኖሎጂ አይቆጣጠርዎት እርሶ ይቆጣጠሩት እንጂ፤ ቴክኖሎጂ በጣም ጥሩ ነው በመሠረቱ በሕይወታችን ውስጥ የበለጠ እንድንሰራ ለማገዝ የተፈጠረ ነው:: የመጀመሪያው አላማው ጊዜያችንን ሙሉ በሙሉ ማባከን አልነበረም:: ግን የስልኮቻችን አሰራር በእኛ ላይ እንዴት ተጽዕንዎ እንደሚያሳድር ሁላችንም ብዙ እናውቃለን እናም ይህንን አውቀን ወደፊት ለመሄድ እና እድገትን እንዲያመጣልን ቴክኖሎጂን መልሰን ልንቆጣጠረው ይገባል❗️

በዚህ ወቅት የብዙዎቻችን የጋራ ችግር በመሆኑ መፍትሄዎቹን ሞክሯቸው!

#share ያስፈልገዋል! እባክዎ ለወዳጅዎ #ያጋሩ

@computer_mobile21
@computer_mobile21

Read more👇👇
https://time.com/5139859/smartphone-addiction-solutions/
👆👆👆👆👆👆👆👆
ከላይ ያሉት ፋይሎች በሙሉ እዚህ ቻናል ከአሁን በፊት ለአባላት ከአባላት የተለቀቁ ናቸው:: ይጠቀሙባቸው!

እባክዎ #share በማድረግ ይተባበሩን
Join 👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21
#ethio_telecom #package

'We are delighted to introduce #Flexi_mobile_package, a plan that gives you the flexibility of using your purchased packages for Voice, Data and SMS as per your needs. When you buy a Flexi package, you will be provided with a fixed number of Flexi Units which will then be deducted based on a predetermined rate of conversion.'

#ፍሌክሲ የሞባይል ጥቅል አገልግሎት ማለት በገዙት ጥቅል እንደምርጫዎ የሞባይል ኢንተርኔት፤ የድምፅ እና አጭር የጽሁፍ መልዕክት አገልግሎቶችን በአንድ ጥቅል አማርጠዉ መጠቀም የሚያስችልዎት አገልግሎት ነዉ፡፡
Convertion
6 flexi =1 minute
2 flexi=1MB
2 flexi=1SMS

999 ደውለው ምርጫዎችን ይመልከቱ

Join👇👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21
💻💻💻 💻 📱📱📱📱📱
' #FREE COMPUTER & MOBILE maintenance center' in each Technology Campuse'
💻💻💻 💻 📱📱📱📱📱
@computer_mobile21

'ነፃ የኮምፒዩተርና ሞባይል ጥገና ማዕከል' በየቴክኖሎጂው ግቢ!!!

ሰላም 🙏
እስኪ ዛሬ አንድ ርዕሰ ጉዳይ እናንሳ:
በየዩኒቨርሲቲያችሁ የቴክኖሎጂ ግቢ ለተማሪዎች #ነፃ አገልግሎት የሚሰጥ የኮምፒዩተርና የሞባይል ጥገና ማዕከል(ቢሮ/ቡድን) አለ??

ካለ እስኪ የት ግቢ: እንዴት አገልግሎቱን እንደሚሰጥ: ምን ምን መሰሪያ እቃዎች እንዳሉትና ምን እንደጎደሉት......የመሳሰሉ መረጃዎችን አካፍሉን @seen3bot

ከሌለ ደግሞ ይሄን ስራ ለማስደመርና ለመስራት ፈቃደኛ የሆናችሁ በውስጥ መስመር የት ግቢና ስማችሁን አሳውቁን @seen3bot
ማዕከሉ እንዲቋቋም የበኩላችንን እንወጣለን

የማዕከሉ አስፈላጊነት በእኛ እምነት:
1. በተለያዬ ችግር ውስጥ ያለን የሀገራችን ተማሪ ለመርዳት
2. በማዕከሉ ውስጥ ለሚሰሩ ደግሞ የስራ ልምድ እንዲያገኙ
3. የግቢውን ደረጃ ከፍ ለማድረግ.....

ሀሳቡን ከወደዱት ከጎናችን ይሁኑ!
ስለርዕሰ ጉዳዩ ያለዎትን ማንኛውም ሀሳብ @seen3bot ላይ ያድርሱን🙏

እባክዎ መልዕክቱን በየዩኒቨርሲቲው የቴሌግራም GROUP #SHARE ያድርጉልን

JOIN 👇👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21

#SHARE SHARE SHARE
COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE via @like
💻💻💻 💻 📱📱📱📱📱 ' #FREE COMPUTER & MOBILE maintenance center' in each Technology Campuse' 💻💻💻 💻 📱📱📱📱📱 @computer_mobile21 'ነፃ የኮምፒዩተርና ሞባይል ጥገና ማዕከል' በየቴክኖሎጂው ግቢ!!! ሰላም 🙏 እስኪ ዛሬ አንድ ርዕሰ ጉዳይ እናንሳ: በየዩኒቨርሲቲያችሁ የቴክኖሎጂ ግቢ ለተማሪዎች #ነፃ አገልግሎት የሚሰጥ የኮምፒዩተርና የሞባይል…
ስለተነሳው ጉዳይ ብዙ አባላት በውስጥ መስመር ገንቢና የማበረታቻ አስተያየቶቻቸውን እሰጡን ነው!
ከየዩኒቨርሲቲው ያላችሁ ተማሪዎችም አለን ከጎናችሁ ነን: ለመስራት ፈቃደኛ ነን እያላችሁን ነው :
አሁንም ተሳተፉ በጋራ ሆነን እቅዳችንን እውን እናደርጋለን!

በእኛ እድሜ ውስጥ እስኪ ሰራን ብለን የምናወራው ለተተኪ ወንድም እህቶቻችን የሚጠቅም ታሪክ እናስቀምጥ!

ለግቢው በቂ የሆነ ሰው ስናገኝ እየተከታተልን እናሳውቃለን!

ለሁላችሁም ከልብ እናመሰግናለን🙏

@computer_mobile21
@computer_mobile21
#SD_CARD
የዘመናችን አስደናቂ ፈጠራዎች ከሆኑት መካከል ስለ #ሜሞሪ_ካርድ ወይም SD(Secure Digital) CARD በጥቂቱ:

ይህች SD(Secure Digital) Card የምንላት መሳሪያ ኤሌክትሮኒክ የመረጃ #ማከማቻ ስትሆን ዲጅታል ኢንፎርሜሽኖችን ለማስቀመጥ ወይም Store ለማድረግ ያገለግላል፡፡ ይቺ ዳታ ማከማቻ በዲጅታል ካሜራዎች፣ በተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ በላፕቶፖችና በኮንፒውተሮች፣ በታብሌቶች ፣በmp3 ማጫዋቻዎችና በቪድዮ ጌም ኮንስሎች ትገኛለች፡፡

◽️ የሚሞሪ ካርድ #በመጀመሪያ ወደ አለም ብቅ ያለው በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1995 ሲሆን ይሄውም PC Card (PCMAIA) የሚል ስያሜ ነበራቸው፡፡ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ሚሞሪዎች አሁን በስፋት ተሰራጭተው ከሚገኙ ሚሞሪዎች በመጠን ከፍ ያሉ ሲሆን መረጃ የመያዝ አቅማቸውም በጣም አነስተኛ ነበር፡፡

◽️ በአሁኑ ወቅት እነዚህ ቀደምት ሚሞሪዎች በስፋት እያገለገሉ ያሉት በእንዱስትሪያል አፕልኬሽኖችና እንደ ሞደም ያሉ ኤሌክትሪካል ዲቫይሶችን ለማገናኘት ብቻ ነው፡፡ አብዛሃኞቹ ሚሞሪ ካርዶች መረጃዎችን እንደገና መላልሶ ማጥፋትና መጫን የሚያስችሉ ሲሆን መረጃዎችንም የሚይዙት ያለምንም ፓዎር ነው፡፡

◽️ ከአመታት በኋላ መሻሻሎችን በማሳየት የተላየዩ ሚሞሪዎች ገበያውን መቀላቀል ጀመሩ በተለይ ከመጀመሪያዎቹ PC Card በመጠን አነስ ያሉና መረጃ የመያዝ አቀማቸው ከፍ ያሉ በመሆናቸው ተቀባይነት ለማገኘት ብዙ ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡ ከነዚህም ውስጥም Compact Flash, Smart Media, እና Miniature Card ይገኝበታል፡፡

◽️ በ2001 (እ.ኤ.አ) Smart Media ሚሞሪ ካርድ 50% የዲጅታል ካሜራ ገበያውን ተቆጣጥሮ ነበር፡፡ Compact Flash, የተባለው የሚሞሪ ካርድ አይነት ደግሞ በአብዛኛው የፕሮፌሽናል ዲጅታል ካሜራዎች ላይ ነግሶ ነበር፡፡ እነዚህ የሚሞሪ ካርድ አይነቶች ተፈላጊነታቸው ጥያቄ ውስጥ የገባው በ2010 (እ.ኤ.አ) Micro SD ሚሞሪ ካርዶች መምጣታቸውን ተከትሎ ሲሆን በብዙ የሞባይል ብራንዶች ላይ እና ታብሌቶች ላይ በመገጠም ተፈላጊነታቸው በጣም ሊንር ችሏል፡፡

◽️ እስከ 2010 (እ.ኤ.አ) የሶኒ ካምፓኒ ለምርቶቹ ሚሞሪ እስቲክን ብቻ ይጠቀም ነበር በተመሳሳይ ታዋቂው የዲጅታል ካሜራዎች አምራች Olympus ኩባንያ sd CARD ብቻ የሚጠቀሙ ካሜራዎችን ያመርት የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ግን ሶኒም ሆነ ኦሎምፐስ በምርቶቻቸው ላይ SD MEMORY CARD እንደተጨማሪ የሚያስገቡ ካሜራዎችን ማምረት ግድ ብሏቸዋል፡፡

◽️ አሁን ላይ በብዛት የምንጠቀምባቸው Micro SD ሚሞሪ ካርድ 1.4 mm ቲክነስ ያላቸው ሲሆን በቅርቡ ይፋ በተደረገው መረጃ መሰረት እስከ 1 TB ወይም 1000 GB መረጃን የመሸከም አቅም እንዲኖራቸው ተደርጎ ለመስራት ተችሏል፡፡ ልብ በሉ የመጀመሪያዎቹ ሚሞሪ ካርዶች መረጃ የመሸከም አቅም 32 MB ነበረ ይህ ማለት ከ30 ፎቶዎች በላይ የመያዝ አቅሙ ያልነበረው ነው፡፡ ለ25 አመታት የፍላሽ ስቶሬጅ (Flash Storage) ገበያውን እየመራ ያለው San የተባለው እውቅ ካንፓኒ አሁን ላይ ባለው ቴክኖሎጂ 128 GB SDXC Memory Card (1.4 mm) ማምረቱን ያስታወቀ ሲሆን መረጃን በስሌት ለማስርዳት ያህል አዲሱ ሜሞሪ፡-
🔳16 ሰዓት HD ቪድዮዎች
🔊7500 ሙዚቃዎችን
🔲3200 ፎቶዎችን
🔽 ከ125 በላይ አፕልኬሽኖችንም በዛች ጉደኛ SDXC ሚሞሪ ካርድ (1.4mm) ከላይ የተጠቀሱትን ሚዲያ ፋይሎች በሙሉ በአንድ ላይ ማስቀመጥ ተችሏል ይለናል፡፡
ከወደዱት ለወዳጅዎ #ያጋሩ!
©teleport

JOIN👇👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21
@computer_mobile21

Read more 👇👇👇
https://en.m.wikipedia.org/wiki/Memory_card
👍1
SD(Secure Digital) Card

@computer_mobile21
ስለተነሳው ጉዳይ ብዙ አባላት በውስጥ መስመር ገንቢና የማበረታቻ አስተያየቶቻቸውን እሰጡን ነው!
ከየዩኒቨርሲቲው ያላችሁ ተማሪዎችም አለን ከጎናችሁ ነን: ለመስራት ፈቃደኛ ነን እያላችሁን ነው :
አሁንም ተሳተፉ በጋራ ሆነን እቅዳችንን እውን እናደርጋለን!

መልዕክታችሁን @seen311 ላኩልን

በእኛ እድሜ ውስጥ እስኪ ሰራን ብለን የምናወራው ለተተኪ ወንድም እህቶቻችን የሚጠቅም ታሪክ እናስቀምጥ!

ለግቢው በቂ የሆነ ሰው ስናገኝ እየተከታተልን እናሳውቃለን!

ለሁላችሁም ከልብ እናመሰግናለን🙏

በተጨማሪም መወያያ 'ግሩፕ' ላይ እየገባችሁ ሀሳብ ስጡበት👇
@Computer_Mobile3
@Computer_Mobile3
👆👆👆👆👆👆

ሀሳቡ ይፋ የወጣበት ቀን : 29/04/2013 ዓ.ም

@computer_mobile21
@computer_mobile21
ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጠቃሚ የቻናል ጥቆማ !
JOIN 👇👇👇
@amharictutorialclass
@amharictutorialclass
@amharictutorialclass
👆👆👆👆
#Repairing_toolsEquipment
ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና የሚያስፈልጉን መሳሪያወች:

1. #መፍቻ ፦ ስልካችን ለመፍታት እና ለመግጠም ይጠቅማል ።
2. #መልቲ_ሜትር:- ሬዚስታንስ ፣ ቮልቴጅ እንዲሁም ከረንት ለመለካት እና የሰርኪዩት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ይጠቅመናል ።
3. #ቲነር ፦ ዝገት ለመከላከል እና ቆሻሻ ለማስወገድ ይጠቅማል ።
4. #ፔስት ፦ አይሲዎችን በመንቀያና በማስቀመጫ ሰአት ቦርዳችንና የሚነቀለዉ አይሲ በሙቀት እንዳይጓዳ ይጠቅማል ።
5. #ብሎወር ፦ ሙቀትን በመስጠት አይሲዎችን ለመንቀልና ለማስቀመጥ ይጠቅማል ።
@computer_mobile21
6. #ካዉያ ፦ ሁለት የተላቀቁ ክፍሎችን ለመበየድ ይጠቅማል ።
7. #ሊድ ፦ ሁለት የተላቀቁ ክፍሎችን ለመበየድ እንደ ቀላጭ የምንጠቀምበት ነዉ ።
8. #ማራዘሚያ_ገመድ(jumper wire) ፦ ሁለት የተለያዩ የሰርኪዩት ክፍሎችን /የተላቀቁ ክፍሎችን/ ለማያያዝ የሚጠቅም ቀጭን ሽቦ ነዉ ።
9. #ትዊዘር(ፒከር) ፦ አይሲ ወይንም ሌሎች የሞባይል ክፍሎች በብሎወር ስናሞቅ እንደ መቆንጠጫ የምንይዝበት ነዉ ።
10. #ዲሲ ፓወር ሰፕላይ ፦ ከባትሪ የምናገኘዉን 3.7 ቮልት የሚሆን ቮልቴጅ የሚሰጥ ክፍል ነዉ። ከዚህም በተጨማሪ ስልካችን ኦፕን(open) ይሁን ሾርት(short) ወይም ስልኮች የሶፍትዌር ችግር እንዳላቸዉና እንደሌላቸዉ ሊያሳየን የሚችል በጣም ጠቃሚ መሳሪያ ነዉ ።
በተጨማሪም ስፒከርን ወይም ሪንገርን ለመፈተሽ ይጠቅመናል።
@computer_mobile21
11. #ኮምፒውተር ፦ ለሶፍትዌር ጥገና ፣ ለሃርድዌር ላይብረሪ እና ሙዚቃ ለመጫን ይጠቅመናል ።
12. #ፍላሽ_ቦክስ ፦ በሶፍትዌር ጥገና ሰአት በሞባይልና በኮምፒዉተር መሃል የሚገኝና ሁለቱን አካሎች የሚያግባባቸዉ መሳሪያ ነዉ ።
13. #ቦርድ_ፕሌት :- የስልካችንን ቦርድ በምንበይድበት ጊዜ ወይም አይሲ በምንነቅልበት ጊዜ ቦርዱ እንዳይነቃነቅ የሚያደርግ መሳሪያ ነዉ ።
#14. ሶፍትዌር ኬብል ፦ በሶፍትዌር ጥገና ስአት ስልካችንን ከፍላሸር ቦክስ ጋር የሚያግባባ ነዉ
15. #ቫይብሬተር ፦ ዉሃ ዉስጥ ገብቶ ወይም ስታክ ያደረገ ስልክ እንዲሰራ ቫይብሬተር ዉስጥ ተዘፍዝፎ ፣ የተወሰነ ደቂቃ ይቆያል::
©MuhammedComputerTechnology
ከወደዱት ለወዳጅዎ #ያጋሩ! SHARE

Join us👇👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21

Read more👇👇👇
http://www.mobilecellphonerepairing.com/mobile-phone-repairing-tools.html
#windows_10x
ዊንዶውስ 10X ወንጀልን ለመከላከል የሚያግዝ #የፀረ-ሌብነት ጥበቃ ሊጨመርበት ነው!
💻💻💻💻💻💻💻

👍ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ #ማይክሮሶፍት የተሰረቁ ኮምፒውተሮች እንደገና ተስተካክለው ወይም (resetting) ተደርገው ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የሚያስችል አዲስ የፀረ-ሌብነት ጥበቃ (anti-theft protection) በዊንዶውስ 10X ላይ እያዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል፡፡
👉ይህ ዊንዶውስ የተጫነባቸው ኮምፒውተሮች የፀረ-ሌብነት ጥበቃ ሞድ ከተጨመረላቸው በኋላ የግድ በተሰጣቸው የማይክሮሶፍት አካውንት የይለፍ ቃል የሚገለገሉ ሲሆን ይህን ኮምፒውተር ዳግም ለማስጀመር የሚፈልግ ሰውም ይህን የይለፍ ቃል የግድ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
👉ይህ ደግሞ ማንኛውም የተሰረቀ ኮምፒውተር እንደገና ተስተካክሎ ወይም (reset) ተደርጎ ጥቅም ላይ እንዳይውል በማድረግ የሌብነት ወንጀልን ለመቀነስ ሊያግዝ ይችላል፡፡
👉 በዚህ ዊንዶውስ የሚገለጉ ሰዎች ንብረታቸው ቢሰረቅ እንኳን በአዲሱ ጥበቃ አማካኝነት ኮምፒውተራቸውን በማንኛውም ቦታ ሆነው መቆለፍ የሚያስችላቸው ሲሆን፤ ጎግል ባቀረበው ‘Find my device’ በተባለው የመፈለጊያ አማራጭ ደግሞ የኮምፒውተሩን መገኛ ሊረዱ ይችላሉ፡፡
👉 የማይክሮሶፍት ባለሙያዎች እንደጠቀሱት አዲሱ የፀረ-ሌብነት ጥበቃ አሁን ላይ ሊሰራበት የታሰበው የዊንዶውስ አይነት መደበኛው ዊንዶውስ 10 ሳይሆን በሱ ቨርዥን በቀረበው ዊንዶውስ 10X ላይ የሚሰራ ሲሆን ወደፊት በሌሎች የዊንዶውስ አይነቶች ላይ የመተግበር እቅድ እንዳለም አስረድተዋል፡፡

👉 ዊንዶውስ 10X አሁን ላይ ባለሁለት ስክሪን ባላቸው የኮምፒውተር አይነቶች ላይ እየተሞከረ ያለ ቢሆንም ወደፊት በሌሎች መደበኛ የላፕቶፕ አይነቶች እና የኮምፒውተር ዝርያዎች ላይ የመጠቀም እድል ሊኖር ይችላል፡፡
ከወደዱት ለወዳጅዎ #ያጋሩ!

Join 👇👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21

Read more👇👇👇
https://www.techradar.com/news/windows-10x-will-feature-clever-anti-theft-protection-to-deter-thieves
#ethiosat

#የኢትዮሳት ብቸኛ ጥቅሞች
Ethiosat Exclusive Benefits
ሀ. የሳተላይት ክፍያ
የሳተላይት ቻናሎች ክፍያ በሚይዙት ባንድዊድዝ የሚወሰን ቢሆንም ኢትዮሳት ላይ የሚገኙት ቻናሎች ክፍያ ከሌላ ሳተላይት ጋር ሲነፃፀር በግማሽ ይቀንሳሉ። ይህ ደግሞ ሌላ ሳተላይት ላይ በSD ጥራት ያስተላልፉ ከነበረ በHD እንዲያደርጉት እድል ይፈጥርላቸዋል። በተጨማሪም ለሌሎች የፕሮዳክሽን ሥራዎች ትርፍ ይኖራቸዋል።

ለ. የቻናሎች ይዘት
በሌሎች ሳተላይቶች የሚገኙ ቻናሎች የአገራቸውን ጥቅም ከማስጠበቃቸው የተነሳ በርካታ ቻናሎች ከፍላጎታችን ውጭ ይገባሉ። በተጨማሪም እያንዳንዱ ተፈላጊ ኢትዮጵያዊ ቻናል የተለያየ ፍርኩየንሲ ያለው ከመሆኑ እንፃር ቻናሎችን ፈልጎ ቅደም ተከተል ለማስያዝ ብዙ ሰዓት ይወስዳል። ኢትዮሳት ላይ ያሉ ፍሪኩየንሲዎች ግን ለጊዜው ከ125 በላይ ናቸው ሰርች በሚደረግበት ሰዓትም የሚገቡት ጠቃሚዎቹና የተመረጡ ኢትዮጵያዊ ቻናሎች ብቻ ናቸው።
ሐ. የቻናሎች ጥራት
እኛ ኢትዮጵያዊያን ጥራት ይገባናል። ስለሆነም ኢትዮሳት ላይ የሚገኙ አብዛኛዎቹ ቻናሎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው (HD) ናቸው። ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሰዎች SD ሪሲቨር ያላቸው መሆኑንም በመገንዘብ ለ6 ወራት የሚቆዩ የተወሰኑ ቻናሎች በSD ይሰራሉ ። ነገር ግን በዘላቂነት ቻናሎቹን በጥራት ለመመልከት HD ሪሲቨር ያስፈልጋል።
መ. በዛፍ እና በግንብ የመከለል ሁኔታ
ይህ ሳተላይት 57°E እንደመሆኑ መጠን ከፊት ለፊት በሚኖር ዛፍ ወይም ግንብ የመከለል ሁኔታው ዝቅተኛ ነው። በተለይ ኮንዶሚኒዬሞች ላይ ሀገርኛ ቻናሎችን ለማግኘት ሲቸገር ለነበረ ሰው ችግሩን ያቃልልለታል። በዛፍ የተከበቡ መኖሪያ ቤቶችም እንዲሁ።
ሠ. ኳስ የማግኘት ሁኔታ
ከዚህ በፊት ብዙ የእግርኳስ ተጠቃሚ ያለው ቫርዚሽ ቲቢ ከኢትዮሳት የሚርቀው 4.5° ስለሆነ ሌላ ተጨማሪ ዲሽ ሳያስፈልግ በቀላሉ አንድ LNB እና ስዊች በመጨመር ተጠቃሚ መሆን ይቻላል። ምናልባት ሌሎች ሳተላይቶች ላይ የማናገኛቸው የፊልም ቻናሎችንም እዚሁ ሳተላይት ላይ እናገኛለን።
ረ. የቀጣይነት ሁኔታ
የዚህ ሳተላይት ባለቤት በቀመጫውን ሉግዘንበርግ ያደረገው SES ካምፓኒ ሲሆን ኢትዮሳት በብቸኛነት የተከራየው ለኢትዮጵያውያን የተዘጋጀ ሳተላይት ነው። ሆኖም የሳተላይቱ "Orbital Position" ኢትዮጵያ አናት ላይ ስለሆነ ኢትዮጵያ የራሷን የኮሙኒኬሽን ሳተላይት ከ3 ዓመት በኋላ ስታመጥቅ 58.3°E ላይ ያርፋል። ስለሆነም ምንም አይነት ተጨማሪ የዲሽ እንቅስቃሴ ሳይደረግ ፍሪኩየንሲ ብቻ በመሙላት ኢትዮጵያዊ ቻናሎችን በቀጣይነት መጠቀም ይቻላል።
ሰ. ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ ቻናሎች
በዚህ ሳተላይት የሚተላለፉ ቻናሎች ሐይማኖታዊም ይሁን ፖለቲካዊ ይዘት ይኑራቸው ገደብ የለባቸውም። ነገር ግን ሀገርን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ቻናሎች ላይ እንደስከዚህ በፊቱ በ"Jaming" የሚዘጉ ሳይሆኑ ስርዓት ባለው መንገድ ኢትዮሳት ከሳተላይት ካንፓኒው ጋር የሚደራደርባቸው እና ማስተካከያ የሚደረግባቸው ይሆናል። በዚህ በኩል የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የራሱ የሆነ ድርሻ አለው።
©Muhammed Computer Technology

Join 👇👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21
#free_promotion
#ነፃ ማስታወቂያ

ብቃት ያላቸው በኢትዮጵያ ለሚገኙ #ለኮምፒዩተርና_ሞባይል_ማሰልጠኛ ተቋማት ብቻ!

የተቋሙ ስም
በስልጠናው የሚካተቱ ርዕሶች በአጭሩ
አድራሻ
ስልክ ቁጥር

ያለምንም ክፍያ ቀንና ሰዓት መድበን እናስተዋውቅ?
እስኪ ስሜታችሁን ግለፁልን
#free_promotion

#MasterTech Computer & Software Training Center
Computer software & Hardware maintenance
#አድራሻ: ባ/ዳር ቀበሌ 04 ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ ፊት ለፊት
#ስልክ: 058 320 5640/0932 87 14 36

@computer_mobile21