COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE
7.1K subscribers
71 photos
7 videos
53 files
103 links
Welcome To Computer & Mobile Maintenance Channel.
It Gives You Some Hints To Repair(Improve Performance Of) Your Computer & Mobile By Yourself. ለጠጋኞችም የሚጠቅም ምርጥ ቻናል ነው!
JOIN @Computer_Mobile21
Contact @seen311 or @seen3bot

Group👉 @Computer_Mobile3
Download Telegram
#mobile_ic

(IC)አይ ሲ ማለት ምን ማለት ነው ?


አይ ሲ ማለት ብዙ ኮመፖነቶች የሚገኙበት ክፍል ነው::
በውሰጡም Resistor capacitor inductor diode ሌሎቹም ኮምፖነቶች ሊኖሩበት ይችላሉ::
የአይሲ ስራው ብዙ ነው ብቻ ኮምፖነቶችን በመሰብሰብ አንድና ከዛ በላይ የሆነን ስራ ይሰራልናል። ለምሳሌ ሞባይል ላይም ሆነ ቲቪ ላይ ኦዲዬ አይ ሲ፣ ፓወር አይሲ እና ሌሎች አይሲወች ይኖራሉ:: እነዚህ አይሲዎች የራሳቸው ስራ አላቸው።
ለምሳሌ #ፓወር አይሲ የፓወርን አክቲቪቲ ይቆጣጠራል
#ኦዲዬ አይሲ ደሞ የኦዲዬ አክቲቪቲ ይቀጣጠራል ስለ አይሲ ይህን ካልን ወደ ሞባይል ስንገባ ሞባይል ላይም አይሲዎች በብዛት ይገኛሉ::
ማንኛውም ሞባይል ማለትም ሞባይል ከተፈጠረ ጀመሮ እስካሁን ያሉት ሞባይል 9 አይ ሲች አሉት ከድሮ ዳስተር ሞባይል አንስቶ እስከ አይፎን 6+ ደርስ ካሁን በሆላም ለሚፈጠሩት ስልኮች 9 አይሲዎች አሉት ዘጠኙ አይሲ ደሞ ለ3 እንከፍላቸዋለን:

1 ) power and logic part ላይ (6 ic)
2) transmition part of ላይ (2 ic)
3) reception part of ic ላይ (1 ic)
4) power and logic part of ic
5) cpu ic (central processing unit )
ሲ ፒ ዩ ማለት የሞባይላችን ሁሉንም እንቅስቃሴ የሚቆጣጠር የሞባይል አይሲ ነው በአጭሩ የሞባይላችን አእምሮ ይባላል
*የሲፒዩ መበላሸት
Dead phone ,no net work ,no audio out put and
etc….
*እንዴት መጠገን ይቻላል?
አይሲውን ማሞቅ ወይም መለወጥ
* የሲፒዩ ቦታ
በኖኪያ እና በሳምሰንግ ላይ አይሲው በወርቃማ ፍሬም ተከቦ ይገኛል በቻይና ስልክ ደሞ እላዩ ላይ M ወይም speed trum ተብሎ ይጻፍበታል
6) memory ic
ሚሞሪ አይሲ ዳታ እስቶሬጅ ዲቫይስ ነው ለሁለት ይከፈላሉ
a) ROM ( read only memory ) it is permanent data storage ሮም ማለት የስልካችን ዋናው ፕሮግራም ወይም operating system የሚቀመጥበት ማለት ነው buraakiller
* የሮም መበላሸት
Dead phone, black or white screen, dim light
እንዴት መጠገን ይቻላል?
ሶፍትዌሩን ስንጠግን - ፍላሽ ወይም ፎረማት
ሃርድውሩን ስንጠግን - አይሲውን ማሞቅ ወይም መለወጥ
* የሮም ቦታ
ሮም ኖኪያ እና ሳምሰንግ ላይ ብዙ ጊዜ የሚገኘው ከሲፒዩ አጠገብ ነው እና የአይሲው ቅርጽ ሁሌም rectangle ነውይገኛል square ያልሆነ ቻይና ላይ ደግሞ ከሲፒዩ ጋር አብሮ buraakiller
b) RAM (randomly access memory) it is
temporary data storage ራም ማለት የስልካችን ሚሴጅ ኮንታክቶች ሚስኮሎች ሌሎችም ልንደልታቸው የምንችላቸው ነገሮች የሚቀመጥበት ነው
* የራም መበላሸት
No miscall. no dilledcall. no received call . no store photo and music etc…
*እንዴት መጠገን ይቻላል?
ሶፍትዌሩን ስንጠግን - ፍላሽ ወይም ፎረማት
ሃርድውሩን ስንጠግን - አይሲውን ማሞቅ ወይም መለወጥ
* የራም ቦታ ሮም ኖኪያ እና ሳምሰንግ ላይ ብዙ ጊዜ የሚገኘው ከሲፒዩ አጠገብ ነው እና የአይሲው ቅርጽ ሁሌም rectangle ነው square ያልሆነ ቻይና ላይ ደግሞ ከሲፒዩ ጋር አብሮ ይገኛል *note ---- ኖኪያ ስልክ ለይ 1 እሰከ 5 ሮም እና ራም አይሲዎች ይገኝሉ በብዛት ከሮም ራም ያንሳል ልላው ደግሞ ለሰፒዩ በጣም የሚቀርበው ሮም ነው ራም ደግሞ በሳይዝ ከሮም ያንሳል ራም እና ሮም ሚቀመጡበት ቦታ ከኮምፖነት የጸዳ ነው
3) POWER IC
ፓወር አይሲ ዋናው ስራ ከባትሪ ቮለቴጅ ተቀብሎ ለተለያዩ አይሲዎች ፓወር መስጠት ነው
ለምሳሌ ከባትሪ 3.7 ቮልቴጅ ይቀበልና ለሲፒዩ 1.5 ቮልቴጅ ለሚሞሪ አይሲ ደግሞ 2.8ቮልቴጅ ያከፋፍላል
*የፓወር አይሲ መበላሽት
Dead phone ,no net work ,no audio out put and etc….
*እንዴት መጠገን ይቻላል?
አይሲውን ማሞቅ ወይም መለወጥ
***የፓወር አይሲ ቦታ
በኖኪያ ስላክ ለይ ለሁለት ዕንከፍለዋለን
a) የድሮ ኖኪያዎች ከሆኑ ማለትም 1st generation ከሆነ ብቻ ፓወር አይሲ ለብቻው ተነጠወሎ እናገኘዋለን ከአጠገቡም RTC የተባለ ኮሞፖነት እናገኛለን::
b) አሁን የሚገኙ ኖኪያዎች ደግሞ አራት አየሲዎች በአንድ አይሲ ተጠቃለው ይገኛሉ የዚ አይሲ ስም UEM(universal energy management) ይባላል እዚ አይሲ ላይ አራት አይሲዎች ይገኛሉ እነሱም Power ic, audio ic, charge ic, ui ic ይገኛሉ ይሄ አይሲ የምነለየው RTC አጠገቡ በመኖሩ ነው::
ቻይና ስልክ ላይ ደሞ አሁንም ልክ እንደ ሚሞሪ አይሲ ከሲፒዩ ጋር አብር ይገኛል ብቻ ሁሉም ስልክ ላይ RTC የተባለው ኮምፖንት አብሮት ይገኛል።

@computer_mobile21
#pc_password

የኮንፒውተራችን ፓስዋርድ ሲጠፋን ኮምፒውተራችን እንዴት መክፈት እንችላለን?
☞☞አይበለውና የኮምፒውተርዎ ፓስዋርድ ከነአካቴው ቢጠፋብዎት ብዙም አይጭነቅዎ… አንድ መላ አይጠፋም፡፡ የሚያስፈልገው ሶፍትዌር “Spotmou Bootsuite.iso” ሲሆን ቀጣዮቹን 10 ስቴፖች ተከትለው ኮምፒውተርዎን መክፈትና መጠቀም ይችላሉ፡፡

Step1: መጀመረያ ሶፍትዌሩን በፍላሽ ወይም CD ላይ እንጭናላን
Step2: ኮምፒዩተራችንን Turn OFF ማድረግ፡፡
Step3: ፍላሹ ን ሰክተን ኮመፒዩተሩን Turn ON ማድረግ፣ ከዛF12 (Boot key) መንካት፡፡
Step4: “Boot Sequence” የሚል ሲመጣልን “USB” የሚለዉን መርጠን “Enter”ን መንካት ከዛ ትዕዛዙን መከተል፡፡
Step5: ኮምፒዩተሩ ከከፈተ በኃላ “Spotmou Bootsuite 2012 Application” ይከፈትልናል፡፡
Step6: ከአፕልኬሽኑ ላይ “Password and Key Finder”የሚለዉን “Menu” እንመርጣለን፡፡
Step7: “Admin Password Resetter” የሚል መንካት፡፡
Step8: “Please select the target widows” ከሚለዉ ሥር የኮምፒዩተሩን “Window Version (XP/7/8/8.1/010)” ይመርጣሉ፡፡ ቀጥሎ “please select the targetuser” ከሚለዉ ሥር ደግሞ መክፈት የሚፈልጉትን “UserAccount” መርጠዉ “Reset” የሚለዉን መጫን፣ ከዛ “OK” ከዛ “YES” የሚለዉን እንጫናለን፡፡
Step9: መጨረሻ ላይ “Password is reset
successfully” የሚል መልዕክት ይደርሶታል፡፡
Step10: ኮምፒዩተሩን ዘግተዉ ይክፈቱት (Reboot).
በትክክል ይሰራል… ከወደዳቹት ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያድርሱ።

@computer_mobile21
👍1
ከታች ባለው ግሩፕ ላይ እየገባችሁ ስለ ሞባይልና ኮምፒዩተር መወያየት: መጠየቅ: መመለስ: አስተያት መስጠት ይቻላል! Join 👇👇👇👇

Group👉
@Computer_Mobile21
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
How to #Flash/Update

Samsung Galaxy A50S to Android Q 10 with One UI 2 / Android Pie 9
የተበላሸ ሚሞሪ ካርድን/ፍላሽ እንደገና ጥቅም ላይ ለማዋል
👍👍👍👍👍👏👏👏👏👏

1⃣2⃣ ደረጃዎች

የተበላሸ ወይም ኮራብት ያደረገ ሚሞሪ ካርድ እንደገና ጥቅም ላይ ለማዋል
እነዚህን #12 ስቴፓች ይጠቀሙ።

⚠️ግን ሚሞሪ ካርዱ ውስጥ የነበሩት ፋይሎች መጥፋታቸው የማይቀር ነገር ነው።

step 1⃣ ሚሞሪ ካርዱን የኮምፒውተርዎ💻 “USB port” ላይ ይሰኩት።

*
step 2⃣ ከዚያም “my computer” ውስጥ ገብተው ኮምፒውተሩ ሚሞሪ
ካርዱን እንዳነበበው ቼክ ያድርጉ።

***


step 3⃣ ከዚያም “Start” በተኑን በመጫን “cmd” ብለው በመፃፍ
“Enter”ን ይጫኑ።

*

step 4⃣ ከዚያም “Command prompt” ውስጥ "DISKPART" ብለው
ይፃፋና “Ok”ን ይጫኑ።

*

step 5⃣ ከዚያም “list disk there” ብለው ይፃፋና የሚቀርቡ
አማራጮችን ይዩ።

step 6⃣ ከሚመጡት አማራጮች ውስጥ ሚሞሪ ካርዱን ከነ ቁጥሩ
ያገኛሉ።

**

step 7⃣ ከዚያም “select disk (disk_number)” ብለው ይፃፋና
“Enter”ን ይጫኑ።

*

step8: ከዚያም “clear” ብለው ይፃፋና Enterን ይጫኑ።

**

step 9⃣ ከዚያም “create partition primary” ብለው ይፃፋና
“Enter”ን ይጫኑ።

***

step 1⃣0⃣ ከዚያም “active” ብለው ይፃፋና “Enter” ይጫኑ።

***

step 1⃣1⃣ ከዚያም “format fs=fat32” ብለው ይፃፋና “Enter” ይጫኑ።

****

step1⃣2⃣ ከዚያም ኮምፒውተሩ💻 ሚሞሪ ካርዱን ፎርማት ያደርገዋል።

@computer_mobile21
ፍላሽን በ cmd እንደ bootable media ማዘጋጀት

1⃣2⃣ ደረጃዎች

step 1⃣ ፍላሹን የኮምፒውተርዎ💻 “USB port” ላይ ይሰኩት።

*
step 2⃣ ከዚያም “my computer” ውስጥ ገብተው ኮምፒውተሩ ፍላሹን እንዳነበበው 'ቼክ' ያድርጉ።

*

step 3⃣ ከዚያም “Start” በተኑን በመጫን “cmd” ብለው በመፃፍ 'run as administrator'
“Enter”ን ይጫኑ።

*

step 4⃣ ከዚያም “Command prompt” ውስጥ "DISKPART" ብለው
ይፃፋና “enter”ን ይጫኑ።

*

step 5⃣ ከዚያም “list disk part” ብለው ይፃፋና የሚቀርቡ
አማራጮችን ይዩ።

step 6⃣ ከሚመጡት አማራጮች ውስጥ ፍላሹን ከነ ቁጥሩ
ያገኛሉ።



step 7⃣ ከዚያም “select disk (disk_number)” ብለው ይፃፋና
“Enter”ን ይጫኑ።

*

step8: ከዚያም “clean” ብለው ይፃፋና Enterን ይጫኑ።



step 9⃣ ከዚያም “create partition primary” ብለው ይፃፋና
“Enter”ን ይጫኑ።

*


step 1⃣0⃣ ከዚያም “active” ብለው ይፃፋና “Enter” ይጫኑ።

***

step 1⃣1⃣ ከዚያም “format fs=ntfs quick” ብለው ይፃፋና “Enter” ይጫኑ

👉በመጨረሻም extract(unzip) windows file ወደ ፍላሹ መላክ(extract ሲሆን አንድ folder ብቻ ከሆነ folder ሩ ውስጥ ያሉትን በሙሉ መርጣችሁ በብትን ወደ ፍላሹ መላክ ይኖርባችኋል)
👉 አሁን ፍላሹ ready ነው ማለት ነው👍

@computer_mobile21
#YouTube Go #Apk

💠ብዙዎቻችን youtube መጠቀም እንፈልጋለን ነገር ግን በዳታ ለምትጠቀሙ አስቸጋሪ ነዉ።

💠ይህን ታስቦ የተሰራ አንድ ምርጥ አፕ ላስተዋዉቃቹ። ስሙም youtube Go ይሰኛል።

💠በዚህ አፕ ተጠቅማቹ የyoutube ቪድዮ ለማየት ከፈለጋቹ ያንን ቪድዮ ለማየት የሚያስፈልጋቹ የዳታ መጠን ምን ያህል እንደሆነ ይነግራቹሀል።

💠አፑን በመጠቀም ቪድዮም ማዉረድ ይችላሉ ነገር ግን ያወረዱት ቪድዮ እዛዉ አፑ ዉስጥ እንጂ ወደ ስልካችሁ አይገባም።

@computer_mobile21

Group👉 @computer_mobile3
#imei
ቅድመ ማስጠንቀቅያ ለ smart phone ተጠቃሚዎች

የጠፋብን ወይም የተሰረቀ ሞባይል በቀላሉ ማግኘት የምቻልበት መንገድ።
ሞባይላችን ከጠፋ ወይም ከተሰረቅን በኋላ ወደ ፖሊስ ከመሄድ፥ እግራችን እና እጃችን ሰብስብን ከመቀመጥ፥በሞባይላችን ያስቀመጥናቸው ኣስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች ከጥንቃቄ ጉድለት ጠፍቶብን ወይኔ ከማለት የምያድነን ቀላሉ መንገድ።ሞባይል የተለየ የራሱ የሆነ IMEI ኣለው፡ ማለትም international mobile equipment Identity የይህንን ቁጥር በመጠቀም ሞባይላችን ያለበት ቦታ ማወቅ እንችላለን። የሚከተለው መንገድ መከተል እንችላለን።
1) *#06# ይደውሉ
2)የሞባይላች የተለየ 15 ቁጥሮች ወይም ልዩ ኮድ IMEI ያሳየናል።
3) የይህንን ቁጥር ማስታወሻችን ላይ ማስፈር ፡
ምክንያቱም የይህንን ቁጥር ሞባይላችን ከጠፋብን ወይም ከተሰረቅን የምንፈልግበት መንገድ ኣንዱ ዘዴ ነው ። ሞባይላችን ከጠፋ ወይም ከተሰረቀ ይህንን ምስጥራዊ ኮድ IMEI በ ኢሜል( e mail ) ወደ cop@vsnl.net ከምከተለው ዝርዝር ጋር እንልካለን።
# Your name .......................
# Address .......
# Phone model ....
# Make ..........
# Last used number ,................
# E mail for comunication .........
# Missed date ....
#.IMEI number
# በ24 ሰዓታት ውስጥ በተራቀቀው GPRS system በመጠቀም ኣድራሻውን ማግኘት እንችላለን፡ ሞባይላችን ከማን እጅ ጋር እንዳለና ማን እየተጠቀመበት እንዳለ ፡ እየተጠቀመበት ያለው ግለሰብ ቁጥር በ email ይላካል::

Group👉 @Computer_Mobile3

@computer_mobile21
share share
#apk #update

የምፈልገውን #አፕ ከ PlayStore እያገኘሁ አይደለም?

''አብዛኛው ጊዜ #Search አርጌ ስፈልግ አይመጣም''

#Update ያላቸው አፕሊኬሽኖች #PlayStore ላይ #ማደስ አልቻልኩም?

PlayStore ጭራሹም #Download ማድረግ አቁሟል መሰል እምቢ አለኝ?


🛃አብዛኛው ጊዜ የምንፈልገውን አፕ ከ #PlayStore ላይ ለመጫን ፈልገን ነገር ግን አይመጣልንም! ይህ ችግር የሚፈጠረው የስልካችን #Version ከመተግበሪያው ጋር የማይሄድ ሲሆን ነው! ይህ ጥያቄ ምላሽ ያገኘ ይመስለኛል!

🛃 #Update ያላቸው ነገር ግን #PlayStore ላይ #Update የሚል ነገር አይመጣም! ይሄ ሙሉ ለሙሉ የስልኩ ችግር ነው! ያረጀ ነው አልያም #ሶፍትዌሩ የድሮ ነው! አዳዲስ ነገራቶች መቀበል አይችልም!

🛃 #Download አያረግም ''Waiting For Network'' ብሎ ይቀራል! ይህ ቀለል ያሉ አማራጮችን እንጠቀም
✔️ #PlayStore የምንጠቀምበት #አካውንት (Gmail) መቀየር!
✔️ የስልካችን #Settings (Apk Manager) ውስጥ በመግባት #ClearData ማድረግ!
✔️Google Play Service #Update ማድረግ ቀጥታ #VidMate, #Aptiude, #ApkPure ላይ ታገኙታላችሁ!
✔️ስልክዎን #Restart አርጋችሁ መሞከር!
💠በነዚህ መንገዶች ካልተስተካከለ #ስልክዎን #Restore አርገው ይሞክሩት! ምናልባትም ሙሉ ለሙሉ ይሰራ ይሆናል!

@computer_mobile21
#​​Cloud_Storage

◽️[Cloud_Storage]ክላውድ ስቶሬጅ የምንለው በኮምፒውተር ወይም በሞባይል ስልክዎት የትኛውም ክፍል ላይ የተቀመጠ ፋይልና ዳታ በሌላ ድርጅት በተዘጋጀ የዳታ ማስቀመጫ ላይ የኢንተርኔት ግንኙነትን በመጠቀም የምናስቀምጥበት ነው፡፡

◽️ በአሁን ሰዓት ይሄን አገልግሎት የተለያዮ ድርጅቶች እየሰጡ ሲሆን በዋናነት #Microsoft, #Google, and #Amazon ትልቁን ቦታ በመያዝ የሚጠቀሱ ሲሆኑ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ለማስቀመጫ ድርጅቶቹ ለመጠቀሚያ የሚያስፈልግ ስም እና የይለፍ ቃል በማዘጋጀት የተወሰኑ ፋይሎችን በነፃ እንዲሁም በክፍያ እንድናስቀምጥ ያደርጋል፡፡

◽️ መጠባበቂያ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ክላውድ ስቶሬጂ አገልግሎትን መጠቀም ፍላጎት እየጨመረ የመጣ እና የተለያዮ ጥቅሞች ሲኖሩት ከነዚህም ውስጥ ፋይሎች ጥብቅ በሆነ ቦታ መቀመጣቸው፣ የምናስቀምጠውን ፋይል ከየትኛውም ቦታና በማንኛውም ኮምፒውተር ላይ ሆነን መጠቀም እንችላለን እንዲሁም የግል ፋይሎቻችን የተቀመጠበት ኮምፒውተር ቢሰረቅ፣ ቢበላሽ ወይም በእሳት ቢቃጠል ካስቀመጥንበት ድርጂት ፋይሎቹን ካለምንም ችግር እናገኛለን፡፡

◽️ 'ባክአፕ ክላውድ' በመጠቀም ፋይል እና ዳታ ስናስቀምጥ ኮምፒውተራችን የተገናኘበት የኢንተርኔት ግንኙነት ፍጥነት የሚወስነው ይሆናል ትልቅ መጠን ያላቸውን ፋይሎች ለማስቀመጥ ቀናትን ሊፈጅ የሚችል ሲሆን አገልግሎቱን ለመስጠት Amazon S3፣ Google Mozy እና Microsoft Sky Drive የሚሉ ሶፍትዌሮችን አዘጋጅተዋል፡፡

◽️ ማክሮሶፍት ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Sky Driveን በመጠቀም እስከ 25 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን፣ አገልግሎቱን እንደተጠቀምነው ብዛት እንዲሁም የፋይሎቹ ቁጥር ነው፡፡ 

◽️ በተጨማሪም Google ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Google Driveን በመጠቀም እስከ 15 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ከስልክዎ ላይ ያሉትን ፎቶና የመሳሰሉት መረጃዎች ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን ስቶሬጅ በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን፣ አገልግሎቱን እንደተጠቀምነው ብዛት እንዲሁም የፋይሎቹ ቁጥር ነው::
Group👉@computer_mobile3

@computer_mobile21
@computer_mobile21

Read more 👇👇👇
https://searchstorage.techtarget.com/definition/cloud-storage
#pc #shortcuts
ኮምፒውተር ላይ ልታውቋቸው የሚገቡ አቋራጭ የኪቦርድ መንገዶችን (Shortcuts)
Ctrl+C እና Ctrl+X

Ctrl+C የመርጥነውን ጽሁፍ ወይንም ፎልደር ይሁን ፋይል ኮፒ ለማድረግ ይረዳናል። አይ ድግግሞሽ አልፈልግም ቆርጬ (Cut) ነው መውሰድ የምፈልገው ካልን ደሞ Ctrl+Xን መንካት ነው። ከት ካደረግንበት ቦታ ፋይሉን ወይም ጽሁፉን ያጠፋዋል።
ለአፕል ኮምፑተር ተጠቃሚዎች Ctrlን በcommand(cmd) በመተካት መጠቀም ይችላሉ።

Ctrl+V

ይህ አቋራጭ የሚጠቅመን ከላይ ኮፒ ወይም ከት ያደርግነውን በምፈልገው ቦታ ላይ ለማቀመጥ ነው። የንምፈልገው ቦታ ላይ ሄደን Ctrl+V ስንነካ ፋይሉን ያስቀምጥልናል።
ለአፕል ተጥቃሚዎች Cmd+Vን መጠቀም ይችላሉ

Ctrl+F

Ctrl+F በመካት የመፈለጊያ ሳጥን (Search) መክፈት እንችላለን። የህም የፈለግነዉን ጽሁፍ(text) እና ፋይል ለማግኘት ይረዳናል።
ለአፕል ተጠቃዎች Cmd+F በመንካት መጠቀም ይችላሉ።

Alt+Tab

Alt+Tab መጫን በተከፈቱ ፕሮግራሞች መሃል እንደፈለግን እንድቀያይር ያደርገናል። ለምሳሌ በብራውዘር ኢንተርኔት እየተጠቀምን ከነበር እና ወደ መፈትነው ወርድ ፋይል መሄድ ብንፈልግ Alt+Tab በመንካት መለወጥ እንችላለን።
ለአፕል ተጠቃሚዎች cmd+Tab ተጥቀሙ።

Ctrl+Backspace እና Ctrl+Left ወይም Right arrow

Backspace የጽሁፍ ፋይል ላይ አንድ ፊደልን ወይም ምልክትን ለማጥፋት ይጠቅምናል። ነገር ግን Ctrl+Backspace ሁሉንም ነገር አንድ ሳያስቀር ያጠፋልናል።
Ctrlን ተጭነን የግራ(left) እና ቀኝ(Right) ቀስቶችን ስንነካ እንደ ከርሰር ተጥቅመን የምንፈሊገዉን ተከታታይ ፋይል ወይም ጽሁፍ በጅምላ እንድንመርጥ ይረዳናል።

Ctrl+S

ዶክመንቶች ላይ እየሰራን የሰራበውን ቶሎ ሴቭ ማድረግ ቢያስፈልህልገን የምንጠቀመው Ctrl+S ነው። በተለይ እንደኛ አገር ላሉ የመብራት ችግር ላለባቨው አገሮች ዶችመታቭን ሴቭ ሳናደርግ እንዳይጠፋ ፍቱን መፍትሄ ነው።
ለአፕል ተጠቃሚዎች cmd+S ተጠቀሙ።

Ctrl+Home እና Ctrl+End

Ctrl+Home ከርሳችንን ወደ ዶክመንታችም መጅውመሪያ ይመልሰዋል። በተቃራኒው Ctrl+End ደሞ ከርሰራችንን ወደ. ዶክመንታችን መጨረሻ ይወስዋል።

Ctrl+P

ፒሪንት ማድረግ የምንፈልገው ፋይል ወንም ዶቹመንት ካለ Ctrl+P ስንነካ የፕሪንትን መስኮት በመክፈት የፕሪንት አማራጮችን ያሳየናል።
ለአፕል ተጠቃሚዎች cmd+Pን ተጠቀሙ።

PageUp ፣ Spacebar እና Pagedown

ከስሙ መገመት እንደሚቻለው PageUp እና Pagedown ዶክመንታችን ላይ ወደ ቀጣይ ገጽ ወንም ወደ ቀድሞ ገጽ ለመሄድ ይጠቅመናል። የኢንተርኔት ብራውዘር በመጠቀምበት ሰአት ደሞ Spacebar ወይም Shift+Spacebar አንድ ገጽ ለመዝለል ያስችለናል።

@computer_mobile21
#windows_10_version_1809

የዊንዶዉስ-10 ቨርዥን "1809" በሚቀጥለዉ ሳምንት አገልግሎቱ ይቋረጣል

ግዙፉ #የቴክኖሎጂ ኩባንያ ማይክሮሶፍት የዊንዶዉስ-10 የቨርዥን (version-1809) ምርቱ ከሚቀጥለዉ ሳምንት ጀምሮ አገልግሎቱን እንደሚያቋርጥ ገለጸ፡፡
አገልግሎታቸዉ ላበቃ ምርቶች ቴክኒካዊ ድጋፎችን እንደማያቀርብ የገለጸዉ ማይክሮሶፍት ይህን ተከትሎ በሶፍትዌሮቹ ላይ ለሚከሰቱ የሶፍትዌር ክፍተቶች እና ተጋላጭነቶችም ማዘመኛዎችን እንደማያቀርብ እና የደህንነት ጥገናዎችንም እንደማያደርግ አሳውቋል።

የአገልግሎት ጊዜያቸዉ ያበቃ ሶፍትዌሮችን አሁንም ድረስ የሚጠቀሙ ደንበኞች የሲስተሞቻቸዉን ከጉዳት ነፃ እንዲሆኑ እና ከመረጃ ጥቃቶች እንዲጠበቁ በፍጥነት ምርቶቻቸዉን ወደ ቅርብ ጊዜ የዊንዶዉ-10 ቨርዥኖች እንዲያሻሽሉ ማይክሮሶፍት አሳስቧል፡፡
የኢንተርፕራይዝ (Enterprise)፣ የኢዱኬሽን (Education) እና ከኢንተርኔት ጋር የተቆራኙ ቁሶች (IoT Enterprise) ሆነዉ የዊንዶዉስ-10 ቨርዥን 1809 ተጠቃሚዎ አገልግሎቱን እስከ ፈረንጆቹ ግንቦት 11/2021 እንደሚቆይላቸዉ ታዉቋል፡፡
በመሆኑን እርስዎ እየተገለገሉበት ያለዉ ኮምፒዉተር ዊንዶዉስ-10 ቨርዥን 1809 ከሆነ በመጀመሪያ ወደ ዊንዶዉስ-10 ቨርዥን 1903 ካዘመኑ በኋላ ወደ የዊንዶዉስ-10 ቨርዥን 2004 ማሳደግ እና በኮምፒዉተሩ በመተግበር (installed) ይኖርዎታል፡፡
ይህንን የዝመና አማራጭ ማይክሮሶፍት ባያበረታታዉም ተጠቃሚዎች Media Creation Tool ተጠቅመዉ ምርቶቻቸዉን ማዘመን ይችላሉ፡፡
እርስዎ እየተጠቀሙበት ያለዉን የዊንዶዉ ቨርዥን ለማወቅ በመጀመሪያ Start የሚለዉን በመጫን > "Settings" የሚለዉን መምረጥ > ከዚያም "System" ሲስተምን በመጫን > "About" የሚለዉን መምረጥ የኮምፒዉተርዎን ቨርዥን ማወቅ ይችላሉ፡፡ አልያም window + R ተጭነው በሚመጣላቹ ዊንዶውስ ላይ winver ብላቹ enter ስትሉት ያሳያችዋል።

@computer_mobile21
ስልካችሁ📲 ላይ #አፕልኬሽን ስትከፍቱ

This Application Stopped Working‼️
Crashing‼️
Won’t open‼️
Won’t respond‼️
Isn’t working properly‼️

🔆እያለ ላስቸገራችሁ መፍትሔ⬇️

1⃣.#Restart እና #Update ይሞክሩ፤ እንደዚህ ስታደርጉ በአብዛኛው ጊዜ ይስተካከላል።👍

⚠️ስልካችሁን📲 #Restart አድርጉት።

⚠️Setting➡️ Software Update ውስጥ ገብታችሁ የስልካችሁን📲 Operating System #Update አድርጉ።

⚠️_Playstore ላይ ገብታችሁ አፑን #Update አድርጉት።

2⃣.*Update Google Play Services *

⚠️ስትከፍቱ #Update አድርጉት ይላችኋል።

3⃣. አፑን የማትጠቀሙበት ከሆነ *Setting* ውስጥ ገብታችሁ #Forced\Stop አድርጉት።

⚠️System App ካልሆነ #Uninstall ያድርጉት።

4⃣. Clear App and Cache ይሞክሩ።

⚠️Setting➡️ Manage apps➡️ ያስቸገራችሁን አፕ➡️ Clear Data and Clear Cache.

5⃣. እኔ እንዳየሁት ከሆነ ከላይ በነገርኳችሁ መፍትሔ 95% ስልኮች📲 ይስተካከላሉ👍 ለተቀሩት ስልኮች #Hard_Reset መሞከር ይቻላል።

⚠️ኮፒ ስልኮችንና ብዙ ጊዜ Hard Reset የተደረጉ ስልኮችን አይጨምርም‼️ እነሱ ስልኮች እንደዚህ ብታደርጉም ላይስታከሉ ይችላሉ።

@computer_mobile21
#telegram
ሰለ ቴሌግራም ማወቅ ያለብን 10 ወሳኝ ነገሮች

1ኛ :- ያለንበትን #ቦታ ለጓደኞቻችን መላክ እንችላለን መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የምንልክለትን ሰዉ እንመርጣለን ከዛ መላኪያዋን ከፍተን location የሚለውን ተጭነን ያለንበትን ቦታ መላክ ይቻላል ::

2ኛ :- ከኛ ወጪ ማንም ሰው ቴሌግራማችንን ማንም ሰዉ እንደይጠቀም ከፈለግን #password ማዘጋጀት ይቻላል መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ላይ ሦስት መሰመር አለ እሱን አንዴ እንነካለን ከዛ setting የምለውን እንነካለን ከዛ privacy and security የሚለውን እንነካለን ከዛ passcode የሚለውን እንነካለን ከዛ passcode lock on እናደርጋለን ከዛ የምንፈልገውን password እናስገባለን ::

3ኛ:- እንዴት ቴሌግራም #ብር_እንዳይበላ ማድረግ ይቻላል
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፍ ያለውን ሦስቷን መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ data and storage የሚለዉን እንነካለን ከዛ
when using mobile data -OF-አድርጉት ::

4ኛ :- የላክነዉን message ከደረሰ በኃላ #delete ማድረግ ይቻላል እንዴት መጀመሪያ የላክነዉን message እንከፍታለን ከዛ ቦታዉ ላይ አጥብቀን እንዛለን ከዛ ከላይ የሚለውን Also delete receive የሚለውን ራይት እናደርጋለን ከዛ ሁለቱም ጋ delete ይሆናል ::
5ኛ :- እንዴት በአንድ የቴሌግራም አፕሊኬሽን ሁለት account እንጠቀማለን
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ
በቴሌግራሙ ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ ይህችን ምልክት ይንኩ ( v ) ከዛ new account ይለናል ከዛ መክፈት

6ኛ :- በተለይ ማታ ማታ ስንጠቀም ዓይናችን እንደይጎዳ ቴሌግራማችን #በጥቁር መልክ እንድሆን ከፍለግን dark ,, black ,, colour እንድትሆን ከፈለግን ...
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የቴሌግራም ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ ገብተን ከሚሰጠን የመልክ ምርጫ የፈለግነዉን እንመርጣለን ::

7ኛ :- ቴሌግራም ያሉ ጽሁፎች አልነበብ እያሎት ተቸግረዋል ማለት ፊደሎቹ አንሰዉ ለዓይን አልታይ ካለ #ፊደሎቹን_ትልቅ ማድረግ ይቻላል እንዴት ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ እንገባለን ከዛ message text size የምል አለ እሱን እንነካና የፈለግነዉን ያህል ትልቅ ማድረግ ይቻላል ::

8ኛ:- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራም #ቻናል መክፈት እንችላለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን
ከዛ በቴሌግራም ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ New channel የሚለውን ነክተን create new channel የሚለውን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፈት የፈለግነዉን የቻናል ስም እናስገባለን ::

9ኛ :- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራም #ግሩፕ እንከፍታለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ ያለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ new group የሚለውን እንነካለን ከዛ create new group የሚለዉን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፍት የፈለግነዉን የግሩፕ ስም እናስገባለን ::

10ኛ :- እንዴት አድርገን #profile_photo መቀየር እንችላለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ ያለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ set profile photo የሚለውን በመንካት የፈለግነዉን ፎቶ መቀየር ይቻላል ።

ከወደዱት ለወዳጅዎ #ያጋሩ!
Group👉 @computer_mobile3

@computer_mobile21
የሞባይል ስልክን #operating_System አፕዴት የማድረግ ጠቀሜታው ....

#1.በፊት ከነበረው ሶፍትዌር በተጨማሪ #አዳዲስ ሶፍትዌሮችና መገልገያዋችን ያመጣል

#2. ሞባይሉ አንዳንድ የሶፍትዌር ችግሮች ካሉበት 'አፕዴት' አድርጎ ሲጨርስ የነበሩበትን ችግሮች #ያስተካክለዋል

#3 . ሞባይሉ በፊት ከነበረው ይዘት በተለያዪ ነገሮች ለውጥን ያመጣል

ማስጠንቀቂያ
ሞባይል ስልክ 'አፕዴት' ከማድረጋችን በፊት ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዋች
- ሞባይሉ ትክክለኛ(Original ) መሆኑን ማረጋገጥ
-ሞባይሉ Root ያልተደረገ መሆን ይኖርበታል
- ሞባይሉ አፕዴት እያደረገ ባትሪ መነቀል የለበትም
- ባትሪ ከ50% በላይ ቻርጅ ሊኖረው ይገባል
በተጨማሪም ሞባይሉን እራሳችን አፕዴት ማድረግ ከፈለግን ጥሩ ፍጥነት ያለው
WiFi internet ብንጠቀም ጥሩ ነው
ሞባይሉ በ WiFi internet አፕዴት ለማድረግ
1. ከ WiFi internet ማገናኘት
2. Settings የሚለውን መክፈት
3. ወደ ታች በመውረድ About መንካት
4. Check for Updates መንካት
5. Update
በዳታ አፕዴት ማድረግ ብዙ ብር ይበላል።ስለዚህ በWiFi update አድርጉ።

@computer_mobile21
#apk

#Application's ሲጭኑ App Not Installed እያላችሁ ለተቸገራችሁ #መፍትሔ:

1⃣. ይሄ ችግር በአብዛኛው የሚፈጠረው አሁን የጫናችሁት አፕ አይነት ተመሳሳይ ስልካችሁ ላይ ሲኖር ነው።

⚠️ካለ መጀመሪያ ፈልጉትና #Uninstall አድርጉት።

2⃣.አሁን ሊጭኑት ያሰቡት አፕ አዲስ Android Version Support የሚያደርግ ሆኖ የእርስዎ ስልክ📲 የድሮ Android Version ሲሆን ወይም በተቃራኒው ሲፈጠር።

⚠️Step 1: 'apk editor' የሚባል apk. ያዉርዱ

Step 2: አፑን install ካደረጋችሁ በኋላ
Select APK from APP-->common edit

Step 4: install location የሚለዉን default አድርጉት።

Step 5: እና ዋነኛው "version code " የሚለዉን ቁጥር መቀየር ነዉ።
ኮዱን ስትቀይሩ ከ ስልካችሁ ጋር የሚሄድ መሆን አለበት(ሌላ install ከሆነ app ላይ አይታችሁ ኮዱን መቀየር ትችላላችሁ)።

Step 6: Save አድርጎ install ማድረግ ነዉ።

3⃣.ስልካችሁ ጊዜያዊ የሲስተም ችግር ሲያጋጥመው አዲስ አፕልኬሽን መቀበል ያቆማል።

⚠️#Restart ካደረጉት ይስተካከላል።👍

4⃣. በቀጥታ #Install ማድረግ የማንችላቸው የሚከፋፈሉ Apk'ዎች አሉ ለምሳሌ Base.APK, Config-Archi.APK.

⚠️"Split Apk" አፕልኬሽን ከ Playstore አውርደው ይጠቀሙ

5⃣.Reset app preferences

⚠️Settings➡️ Apps or Apps manager➡️ menu ➡️ Reset App Preferences.

6⃣. Apk'ው የተቀመጠው ሚሞሪ ላይ ከሆነ ወደ Internal Storage #Move አድርገው ይሞክሩት።

7⃣.#Package_Installer ችግር ሲያጋጥመው።

⚠️setting➡️ Manage apps ➡️Package Installer➡️ Clear data and Clear cache.

8⃣. ስልክዎ Free Space እንዳለው እርግጠኛ ይሁኑ።

@computer_mobile21
#tech_news
አስገራሚ🤔
@computer_mobile21

ተመራማሪዎች በተለይ ወታደሮችን ከሰዎች እይታ መሰወር የሚያስችላቸውን ፈጠራ መስራታቸው ተሰማ‼️

↘️ ይህ ፈጠራ ወታደሮች በግዳጅ ወቅት በተለይ በጠላት ቀጠና አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የሚለብሱትና ከአካባቢው እይታ ጋር የመመሳሰል ብቃት ያለው ሰው ሰራሽ ቆዳ ነው፡፡


↘️ በደቡብ ኮሪያ የሚገኝ የተመራማሪዎች ቡድን ወታደሮችን በአካባቢያቸው ካለ ከማንኛውም ነገር መሰወር የሚያስችላቸውን ልዩ ፈጠራ በማበልጸግ ላይ መሆናቸውን የዘገበው futurism.com ነው፡፡

↘️ ይህ ፈጠራም ወታደሮችን ከመደበኛ ካሜራም ብቻ ሳይሆን ከምሽት እይታም (Infrared-Based Night Vision) ጭምር መሰወር እንደሚችል ዘገባው አመልክቷል፡፡

↘️ ፈጠራው ከእይታ ውጭ ከመሆን በተጨማሪ እንደ አካባቢው ሁኔታ የመሞቅና የመቀዝቀዝ ብቃት ያለው እንደሆነ ተገልጿል፡፡

@computer_mobile21
1
Distance From Me_v3.5_apkpure.com.apk
2.8 MB
👉 ያሉበትን #ቦታ የሚያሳይ
👉 ማወቅ የሚፈልጉትን አካባቢ በትክክል የሚረዱበት የሞባይል app ነው። ተጠቀሙበት

@computer_mobile21
#facebook_security
#የፌስቡክ አካውንቶትን ሌላ ሰው ሲጠቀም አጭር የፅሁፍ መልዕክት ሞባይሎት ላይ እንዲደርሶት ማድረግ የሚችሉበትን ቀለል ያለ ዘዴ
@computer_mobile21

#1.የፌስ ቡክ አካውንቶት ውስጥ በተለመደው ሁኔታ ከገቡ በኋላ #setting የሚለውን አማራጭ ይጫናሉ ሴቲንግ የሚለው ቦታ እንደ ምትጠቀሙት ብሮዘራችሁ ሰለሚለያይ ፈልጉት

#2. በመቀጠልም ከሚመጡት አማራጮች security setting የሚለውን አማራጭ እንመርጣለን ከዚህ በኋላ login alert የሚለውን አማራጭ እንጫናለን።

#3. ከዚህ በኋላም ከተቀመጡት ሶስት አማራጮች ውስጥ text message የሚለው አማራጭን በመጫን የሞባይል ቁጥሮን ያስገባሉ፡፡

#4. በመቀጠልም save የሚለውን ቁልፍ ሲጫኑ ወደ ሞባይሎ የማረጋገጫ ኮድ ይልክሎታል ይህ ኮድ ሞባይሉ የእርሶ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚላክ ሲሆን ያንን ኮድ ኮምፒተሩ ላይ በተቀመጠው ክፍት ቦታ በማስገባት ሴቭ ማለት በመጨረሻም ቁጥሮ የገባበትን ምርጫ በመጫን save changes የሚለውን ስትጫኑ አክቲቭ ይሆናል፡፡ ከዛም በኋላ የትኛውም ኮምፒውተር ወይም ሞባይል ላይ ፌስ ቡኮት ላይ ሲገቡ መግባቶን በአጭር
ጽሁፍ መልእክት ሞባይሎ ላይ ይደርሶታል ማለት ነው፡፡

አስተውሉ⚠️ ይሄን አክቲቬት አድርገው በስልኮ አጭር የጽሁፍ መልእክት ከተላኮለት ያኔ የፌስቡክ አካውንቶን ሌላ ሰው እየተጠቀመ ነው ማለት ነው ያኔ ቶሎ ብለው የአካውንቶን ሚስጥር ቁጥሮን መቀየር አሎበት።

@computer_mobile21