COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE
7.1K subscribers
71 photos
7 videos
53 files
103 links
Welcome To Computer & Mobile Maintenance Channel.
It Gives You Some Hints To Repair(Improve Performance Of) Your Computer & Mobile By Yourself. ለጠጋኞችም የሚጠቅም ምርጥ ቻናል ነው!
JOIN @Computer_Mobile21
Contact @seen311 or @seen3bot

Group👉 @Computer_Mobile3
Download Telegram
#Fake_website
ማስጠንቀቂያ!
ይሄን ሊንክ በጭራሽ እንዳትሞክሩት
አጭበርባሪ ነው

Hi! I found new site https://bit.ly/2BaJDwR for earning $50-100 everyday for doing jobs. You can register with telegram. And site give you tasks. Good luck!


Look out for the new scam on Telegram where you'll receive a friendly chat message from a friend, a group/channel you follow that tells you about a newfound website that gives a new opportunity for a job or money... (ex. freelance
work.co). Which will take you to a website that will ask for your phone number and asks you to put in a code that is sent to you on Telegram. DO NOT put in that code because that's a code telegram uses to identify you as you and once you give that code your telegram is hacked (the system/hacker will have access to your telegram account) and also using your account will send a similar message to all you friends and groups you manage. If you have already made the mistake of sending out your code... then you can do the following to terminate all other sessions.

Go to Telegram Settings > Privacy and Security > Active Sessions > Terminate all other sessions


P.S - Telegram Rule to Live By - Never give you telegram access code to anyone/anything except telegram itself.

Register ካደረጋችሁ telegram አካውንታችሁ delete ይደረጋል።

እባክዎ ለወዳጅዎ ያጋሩ
#Share
JOIN👇👇👇
@computer_mobile21
@computer_mobile21
1
#tech_facts

ኪቦርድ ላይ የኢንግሊዘኛ ቃላት አደራደር 'Q' 'W' 'E' 'R' 'T' 'Y' እያለ ነው የሚቀጥለው። ይህም የአልፋቤት ተርታውን የጠበቀ አይደለም። ይህ ደሞ የሆነበት ምክንያት አለው።
👉 ኪቦርድ መጀመሪያ ሲፈበረክ የትክክለኛ አልፋቤት ተርታ ነበረው። ይህም ሰዎች በጣም በፍጥነት መፃፍ እንዲችሉ አርጓቸው ነበር። ይህም በጊዜው የነበሩት #ኮምፒውተሮች⌨️ ፍጥነታቸው ቀርፉፉ ስለነበር በጣም እንዲዘገዩ እና ስታክ አርገው እንዲቆዩ እያረጋቸው ነበር።
👉ስለዚህ ለተጠቃሚዎች ፍጥነታቸውን #እንዲቀንሱ በማሰብ አሁን የምንጠቀምበትን የተዘበራረቀ ተርታ ያለውን ኪቦርድ⌨️ ተሰራ።

@computer_mobile21
🙏ሰላምና ጤና ለምናከብራችሁ የቻናላችን አባላት!

ኮምፒዩተርና ሞባይል ጥገና አገልግሎቱን ከቴሌግራም በተጨማሪ በ 'ፌስቡክ' ገጽ ይዞላችሁ ቀርቧል! ይቀላቀሉን!👇

Like 👇👇👇
Facebook.com//ComputerMobile21
Facebook.com//ComputerMobile21
Facebook.com//ComputerMobile21
com.psiphon3.subscription.apk
22.1 MB
Facebook ላስቸገራችሁ ይሄን apk ተጠቀሙ
#Mobile_data_symbol

የሞባይል #ዳታ ስናበራ ከስልካችን እስክሪን አናት ላይ የምንመለከታቸው የ G፣E፣3G፣H፣H+፣4G እና የ4G LTE ምልክቶች ትርጉም ምንድነው?

እንደሚታወቀው ኢንተርኔት ለመጠቀም የሞባይል ስልካችንን ዳታ ስናበራ ከኔት-ወርክ ምልክት አጠገብ ሁልጊዜ ተጨማሪ ምልክቶች ይመጣሉ። ታዲያ እነዚህ ምልክቶች በምርጫችን የምንጠቀማቸውን የተለያዩ የዳታ አይነቶችን እና የኢንተርኔት ፍጥነት የሚያሳዩን ናቸው።

ምልክቶቹ እና መለኪያዎቹ እንደሚከተለው ነው።

(ይህ መረጃ በሀገራችን ያለውን ሁኔታ ብቻ እንጂ አጠቃላይ የኢንተርኔት ኔትዎርክ Download Speed እና Upload Speed አያካትትም)

G = 14KB/s
E = 48KB/s
3G = 395KB/s
H = 1.75MB/s
H+ = 21MB/s
4G = 37MB/s
4G LTE= 56 MB/s (በአዲስአበባ ጥቂት ቦታዎች ብቻ)
>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
What are the Meaning of G, E, 3G, H, H+, 4G and 4G LTE Internet Connection?

Each of the symbols mentioned above shows the Kind of data connection that you are connected at and this varies according to the speed and Mark features of each ISP (Internet Service Provide)

#1 Symbol G on mobile phone signal status
The G symbol means GPRS (General Packet Radio Service) and this allows for voice calls and an Internet Speed of up to 50 kb/s. This will work for all normal data usage such as emails and app notifications but will not work for video.

#2 Symbol E
The E symbol means EDGE (Enhanced Data GSM Evolution) and this allows for voice calls and an Internet Speed of up to 100 kb/s. This will work for all normal data usage such as emails and app notifications but will not work for video.

#3 Symbol 3G
The 3G symbol means Third Generation which is also known as UMTS / WCDMA / CDMA2000 and this allows for voice calls and an Internet Speed of up to 2 Mb/s. This will work for all normal data usage such as emails and app notifications including video.

#4 Symbol H/H+
The H/H+ symbol means HSPA (High-Speed Packet Access) and this allows for voice calls and an Internet Speed of up to 10 to 100 Mb/s. This will work for all normal data usage such as emails and app notifications including video.

#5 Symbol 4G (LTE)
The 4G (LTE) symbol means Fourth generation or Long term evolution which is also known as LTE or WiMax and this allows for voice calls and an Internet Speed of up to 100 Mb/s. This will work for all normal data usage such as emails and app notifications including video.

@computer_mobile21
@computer_mobile21
💽 ከኮምፒተራችን ላይ ምናጠፋቸው ፋይሎች ወዴት ነው የሚሄዱት ?
@computer_mobile21

ኮምፒተራችን ምንም ነገር አያጠፋም። ያጠፋነው የሚመስለን ፋይል ሁሉ እዛው #ሀርድ_ዲስካችን ላይ ነው ሚቀመጠው !

ፋይል አጠፋን የምንለው የፋይላችን መኖር ሲነግረን የነበረን (Pointer የሚባል ዳታ) ጠቋሚው (Pointer), እንዲጠፋ የፈለግነውን ፋይል መጠቆሙን እንዲያቆምና ወደ ሌላ አዲስ አድራሻ እንዲጠቁም ስለምናደረገው ነው!

የጠፋብንን ፋይል መመለስ የሚቻለውም ፋይሉ ተቀምጦበት የነበረው ቦታ ላይ ኮምፒተሩ መልሶ ሌላ ፋይል እስካላስቀመጠበት ሲሆን፣ ምስጢር ነክ የሆኑ ፋይሎችን የያዙ ኮምፒተሮች ፎርማት ከማረግ ሰባብሮ ከጥቅም ውጪ ማድረግ የሚመከረውም በዚህ ምክንያት ነው !

@computer_mobile21
@computer_mobile21

Read more👇👇
https://www.quora.com/Where-do-deleted-files-go-1
#file_extension
ስለ ፋይል ፎርማቶች ምን ያህል ያውቃሉ

🔅ለምሳሌ xender.apk ሚል ፋይል ብናገኝ ምን ማለት ነው

🔅ካሉት ብዙ ፎርማቶች ዋነኞቹ

👇👇👇

.exe 👉 windows (pc) app setup

.Apk 👉 android app setup

.IPA 👉 for iOS (iPhone, iPad...)

.xap/.appx 👉 app for windows phone

.txt 👉 text file

.bat 👉 batch file

@computer_mobile21
# mobile_virus
ስለ ስልክ ቫይረስ ምን ያህል ያቃሉ?
What is Virus ??
# Virus ማለት የ Computer Code ወይም Program ሲሆን ብዙ ግዜ የሚሰራው ወይም
የሚፈጠረው የ Computer እውቀት ባላቸው ሰወች እና ስለ Computer ጠልቀው በ ተማሩ ሰወች ነው
ቫይረስ ስንል ብዙ አይነት ቫይረሶች አሉ
➲Spyware Virus
➲Malware Virus
➲Ransonware Virus
➲Adware Virus
➲Trojan Horse Virus ናቸው
እንደ ስማቸው ሁሉ ስራቸውም ይለያያል
@computer_mobile21

የ#Virus ዋና አላማው እና ስራው ምን ምን ናቸው
⓵ ስልካችንን ማበላሸት (Damage) ማድረግ
የስልኩን Software ቫይረሱ በሚያጠቃበት ግዜ ስልኩ Dead ይሆናል ይህ ማለት ስልካችን Samsung ከሆነ ስንከፍተው Samsung ይልና ቀጥ ብሎ ይቆማል አይከፈትም ማለት ነው
⓶ በጣም ጠቃሚ ፋይል ማጥፋት እና መደበቅ
ስልካችን ላይ ሆነ MemoryCard ላይ ያሉትን ማንኛውም (File)
ለምሳሌ
Music Photo Video Application Document ያለ ምንም ምህረት ያጠፋል (Format) ያደረጋቸዋል ያለኛ ትዛዝ እና ፍቃድ
⓷ ስልካችንን በማናውቀው Password ወይም Pattern መቆለፍ እና መዝጋት
ይህ ማለት ስልካችንን የዘጋንበትን የሚስጥር Password ይቀይርና የራሱን Password
በማስገባት ይቆልፍብናል ማለትም ስልካችንን
ሙሉ በ ሙሉ በራሱ ቁጥጥር ስር ያደርገዋል እኛ ስልኩን ማዘዝ አንችልም ማለት ነው
⓸ ስልካችንን(OS)Operating System ስራ ማዛባት እና ስልኩ እንዲዘባርቅ ማድረግ
ይህ ማለት ስልካችን ስራውን በትክክል እንዳይሰራ እንቅፋት ይሆናል ይህ ማለት እኛ ስልኩን
ሳንነካው ሳናዘው በራሱ (File)መክፈት መዝጋት
ስልኩን Flight Mode ላይ ማድረግ
ስልኩን Switch Off ማድረግ ከዛ ስልኩን መልሶ መክፈት. ሌላም ብዙ ብዙ ነገሮችን በራሱ ይሰራል
⓹ Software File ማጥፋት
የ ስልካችንን Software File Delete ማድረግ
=> Software File Delete ከሆነ ስልኩን ማስተካከል ከባድ ይሆናል
ከላይ የተጠቀሱትን ሁሉ ያለ ባለቤቱ ፍቃድ በራሱ መብት ይሰራል.
ስለ # ቫይረስ አደገኛነት ጉዳት እና አላማ ይህን ካልን ስለ መከላከያው እና ስለ መፍትሄው ደግሞ እናያለን

@computer_mobile21
እንዴት አድርገን ስልካችንን ከአደገኛ ቫይረስ መጠበቅ እና መከላከል እንችላለን
⓵ ካልታወቀ እና # Fake ከሆነ ዌብሳይት ማንኛውንም ነገር ከ ማውረድ መቆጠብ
ለምሳሌ ካልታወቀ እና # Fake ከሆነ
ዌብሳይት Application ወይም File (Download) በምናደርግበት time # ቫይረሱ Download ከምናረገው Application ወይም File ጋር አብሮ ወደ ስልካችን በቀላሉ ይገባል
ለምን ቢባል Fake የሆኑ # ድረገጾች ላይ # ቫይረሶች ብዙግዜ ስለሚለቀቁ ነው ሰለዚህ ከታወቀ እና ታማኝነት ካለው ዌብሳይት ብቻ የምንፈልገውን File ማውረድ ይጠበቅብናል
⓶ Bluetooth Email እና G-mail ክፍት አድርጎ አለመተው ተጠቅመን ከ ጨረስን በኋላ መዘጋቱን
# Check Up ማድረግ
⓷ የስልካችንን # Software Update ማድረግ
በሰአቱ እና በግዜ
ስልካችን የSoftware Update ጥያቄ ሲጠይቀን
# ችላ አለማለት ወድያውኑ ስልኩን Update መድረግ
የስልካችን Software Update ከተደረገ ስልካችን በ ቫይረስ የመጠቃት እድል በጣም ዝቅተኛ ነው
የ ስልካችንን Software Update ለማድረግ መጀመሪያ
# Setting ውስጥ እንገባለን ከዛ መጨረሻ ላይ
# About Phone
የሚል አለ እሱን እንዴ # Click እንላለን ከዛ
Software Update የሚለውን # Click ማለት
⓸ ትክክለኛ እና # Original Antivirus መጠቀም
ስልካችን ላይ ያለውን ሁሉኑም Application እና File # Scan ማድረግ Scan በምናደርግበት ግዜ Virus ያለበት Application ወይም File ከተገኘ ወዲያውኑ ማጥፋት
# Remove ማድረግ
እነዚህን Original Antivirus
ከ PlayStore በ ማዉረድ ተጠቀሙ።

@computer_mobile21
➷➷➷➷➷➷
➊ # Norton Antivirus
➋ # KasperskyAntiVirus
➌ # BT Virus Protect: Mobile Anti-Virus & Security App
እነዚህ Antivirusሶች የሚሰሩት በ Data እና በ Wifi Connection
⓹ ቫይረስ በዋናነት ከሚገባበት መንገድ አንዱ በ
# Email ለምሳሌ በ
# G -mail ነው
Email ለምሳሌ በ G-mail በምንጠቀምበት ግዜ ከማናውቃቸው ሰወች # Link ሲላክልን ቶሎ መክፈት የለብንም ምክንያቱም የተላከው ከ # Hackerሮች (Linkኩም) ቫይረስ ሊሆን ስለሚችል በፍፁም መክፍት የለብንም
⓺ ስልካችን ላይ ያሉትን ሁሉኑም Application # Update ማድረግ ለምን ቢባል አንዳንድ
Applicationኖች ከ ቆይታ ብዛት የተነሳ ወደ ቫይረስ ይቀየራሉ ስለዚህ ሁሉኑም Application በየጊዜው Update ማድረግ አለብን
ስልካችን ላይ ያሉ Applicationኖችን Update ለማድረግ መጀመሪያ ወደ PlayStore ላይ እንገባለን ከዛ (My APP) ዉስጥ እንገባለን ከዛ Update መሆን ያለበት Application ካለ እራሱ ይህን Application Update አድርግ ብሎ ይጠቁመናል ከዛ Update የሚለውን # Click ማድረግ
⓻ Wifi በምንጠቀምበት ግዜ ከባድ ጥንቃቄ ማድረግ
Wifi ከፍተን በምንጠቀምበት ሰአት ብዙ
Notification ወደ ስልካችን ይገባሉ በዚህ ግዜ
ወድያውኑ Notificationኑ ፍቃድ ይጠይቀናል
(Allow or Decline) ብሎ ይጠይቀናል ?
Notificationኑ ቫይረስ ይሁን አይሁን እኛ
አናውቅም ነገርግን እኛ ችላ በማለት ወይም ትኩረት ባለመስጠት (Allow) ብለን እንፈቅዳለን በዛን ሰአት Notification መስሎ የመጣው # ቫይረስ በፍጥነት ወደ ስልካችን በመግባት ስልካችንን ያበላሻል ስለዚህ ማንኛውንም Notification
ወደ ስልካችን ሲመጣ ዝምብለን ከመክፈት መታቀብ አለብን
⓼ ማንኛውንም Application ከሰው ስንቀበል
ስለ Applicationኑ ምንነት እና ስራ በደንብ መረዳት አለብን ይህ ማለት Applicationኑ ጎጂ ሆነ ጥሩ የሚለውን እንድናውቅ ይረዳናል
ስለዚህ ማንኛውንም Application ስልካችን
ላይ ከመጫናችን እና ከ መቀበላችን በፊት ስለ
Applicationኑ በደንብ መገንዘብ ያስፈልጋል::
# Share

Join us
Facebook: @ComputeMobile21

@computer_mobile21
@computer_mobile21

Read more👇👇👇
https://www.techopedia.com/definition/15794/mobile-phone-virus
#laptop #safety
💻💻💻💻💻💻💻💻💻
ለላፕቶፕ ኮምፕዩተራችን ልናደርግ የሚገቡ ጥንቃቄዎች
💻💻💻💻💻💻💻💻

1⃣ ሁሌም ተጠቅመን ስንጨርስ shutdown ‼️ ማድረግ

⚠️(በ power button ማጥፋት ኮምፒውተሮትን ይጎዳል )

2⃣ የላፕቶፕዎን ቅዝቃዜ ይጠብቁ

⚠️ እግር ላይ, ትራስ ላይ, አልጋ ላይ አስቀምጦ መጠቀም የላፕቶፕ ኮምፒውተሮት 💻 በቶሎ እንዲግል እና ማቀዝቀዣው (fan) እንዳይሰራ ያደርጋል ።

3⃣ በሚጠቀሙበት ጊዜ ባትሪ አይንቀሉ።

4⃣ በማይጠቀሙበት ጊዜ ማንኛውንም accessories ይንቀሉ ምክንያቱም ኮምፕዩተሮትን 🖥 እንዲግል ወይንም አላስፈላጊ ስራ እንዲሰራ ያደርጋሉ።

5⃣ አንቲ ቫይረስ ይጫኑ ⚠️ Update መደረጉን እርግጠኛ ይሁኑ።

6⃣ ከውሀና ከአቧራ ይጠብቁት።

7⃣ ቢያንስ በአመት 1 ጊዜ service ያስደርጉ

Join
@computer_mobile21
@computer_mobile21

Read more 👇👇👇
https://www.lifewire.com/top-laptop-computer-safety-tips-2378147
#mobile_battery

የሞባይል ባትሪን እድሜ ለመጨመር 5 ቁምነገሮች

አንዳንድ ጊዜ ከበሽታ ባልተናነሰ በእለት ተእለት ኑሯችን ጤና የሚነሱን አይነት ችግሮች ይገጥሙናል፡፡ ጥቃቅን የሚመስሉ ነገር ግን የእለት ተዕለት ህይወታችን ውስጥ የሚጎረብጡ ጉዳዮች ይገጥሙናል፡፡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አብዛኛዎቻችንን ከሚጎረብጡ ጉዳዮች መካከል አንዱ የሞባይል ባትሪ ጉዳይ ነው፡፡
ብዙዎቻችን የምንጠቀምባቸው ሞባይል ስልኮች የሚጠቀሙት ባትሪ የተሰሩት ከሊትየም-አይኦን (lithium-ion) ሲሆን ይሄም ባትሪ በአግባቡ ካለመጠቀም መስጠት ከሚችለው አገልግሎት ባነሰ ሁኔታ በቶሎ ይደክማል፤ ያረጃል፡፡ ይሄም ማለት ባትሪው ቻርጅ ተደርጎ በሰዓታት ውስጥ በማለቅ ተጠቃሚውን ያስቸግራል፡፡ የሞባይል ባትሪዎች ሲሰሩ ተጠቃሚው በአግባቡ ከተጠቀመበት ከ3 እስከ 5 አመት እንዲያገለግሉ ተደርገው ሲሆን ከዚህ ከተቀመጠላቸው ጊዜ ባነሰ ሁኔታ የሚያስግሩባቸውን ምክንያች እና ባትሪን በተሻለ መጠቀም የሚቻልባቸውን ዘዴዎች እንደሚከተለው እንጠቁማችኋለን፡፡
የሞባይል ባትሪችን እድሜ ለማስረዘም ማድረግ የሚገባን 5 ነጥቦች፡-

#1. የሞባይል አምራቹ ለገበያ ያላቀረበውን ቻርጀር አለመጠቀም
ትክክለኛ ሳይሆኑ ለገንዘብ ተብለው በርካሽ ዋጋ ለገበያ የሚቀርቡ ቻርጀሮች በዋጋ ደረጃ ርካሽ ቢሆኑም ጥራታቸውን ያልጠበቁ በመሆናቸው ቻርጅ በምናደርግበት ጊዜ ለሞባይሉ ባትሪ ያልተመጣጠነ የኤሌትሪክ ሀይል በመስጠት ባትሪውን ይጎዳዋል፡፡ ይህም የባትሪውን እድሜ ያሳጥረዋል፡፡ በጣም ፈጣን ቻርጀር መጠቀም ባትሪን ያዳክማል።

#2. ሞባይል ቻርጅ ላይ እያለ አለመጠቀም
ሞባይል ስልኮች ቻርጅ በሚደረጉበት ጊዜ ስልክ መደወል፣ ጌም መጫወት፣ ኢንተርኔት መጠቀም የባትሪውን እድሜ ከማሳጠር ባለፈ ለእኛ ለተጠቃሚዎቹ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከዚህም ባለፈ ሞባይሉ ራሱ ሊፈነዳ እንደሚችል ልብ ልንል ይገባል፡፡

#3. ሞባይልን ሌሊት ሙሉ ቻርጅ አለማድረግ፤ ጃርጅ ላይ ሰክቶ አለማሳደር
በምሽት ወደ መኝት ከመሄዳችን በፊት ሞባይሉን ለነገ ሞልቶ እንዲያድር ብለን ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ እንዲያደርግ ማድረግ አንዱ ባትሪን ከሚገድሉ ስህተቶች መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡ ባትሪው ከምሽት ጀምሮ ሌሊት ሙሉ ቻርጂ ሲያደርግ 100 ፐርሰንት መሙላቱ የማይቀር ሲሆን ከሞላ በኋላ የኤሌክትሪክ ፓወሩ ባትሪውን መደብደቡ የማይቀር ነው፡፡ የሞላ ነገር ሁሉ መፍሰሱ እንደማይቀር ሁሉ ሞቶ የሚፈስ ነገር ደግሞ እቃው ላይ ጉዳት ያስከትላል፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰክቶ ያደረ ባትሪ ከአቅሙ በላይ ስራ ይበዛበታል፡፡

#4. ሞባይል ስልክን አልፎ አልፎ ማጥፋት
ሞባይል ስልክን አለማጥፋት ሌላው የባትሪን እድሜ ከሚቀንሱ ውስጥ አንዱ ሲሆን ሞባይል ስልኮች እንደማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ማሽን እረፍት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ቢቻል በምሽት ወደ መኝታ ስንሄድ አልፎ አልፎ ስልኮቻችንን ብናጠፋ ይመከራል፡፡ ብዙዎቻችን የሞባይል ስልካችን በስራ ላይ የሚመስለን ስንደውል፣ ሲደወልልን፣ አንዳንድ ነገሮችን በስልኮቻችን ስንጠቀም ብቻ ባትሪ የሚጠቀም ይመስለናል፤ ሆኖም ግን የባትሪው የመጠቀም መጠን ይለያያል እንጂ ሞባይሉ ሲከፈት በላዩ ላይ ያሉት ክፍት የተደረጉ ሰርቪሶች(ሰዓት፣ ብሉቱዝ፣ ዋይፋጥ፣ ጂፒኤስ፣ ዳታ ኮኔክሽን ወዘተ) ባትሪውን ይጠቀማሉ፡፡

#5. ባትሪው 0% እስኪሆን ድረስ አለመጠበቅ
የማባይል ባትሪዎች የያዙትን ፓወር ጨርሰው 0% እስኪሆን ድረስ እየጠበቁ ቻርጅ ማድረግ የባትሪውን እድሜ የሚያሳጥር ሲሆን ባትሪው ግማሽም ይሁን ሩብ ሲቀረው ቻርጅ ብናደርገው ዜሮ እስኪሆን ድረስ ጠብቀን ከምናደርገው በተሻለ እድሜው እንዲጨምር ያደርጋል፡፡

@computer_mobile21
@computer_mobile21

Read more👇👇👇
https://medium.com/@lauren.c.stephen/13-tips-to-extend-the-lifespan-of-your-phone-battery-16c2af5ca59f
👍1
#Facebook #Instagram

በዛሬው እለት በኢትዮጽያ ታግዶ የነበረው ፌስቡክ በመላው ኢትዮጽያ ተከፍቷል:: እስካሁን ድረስ Facebook እና Instagram ከኢትዮጵያ ተዘግተው ነበር ዛሬ ነሐሴ 1 ደግሞ ይኸው ከንደገና ስራቸውን ጀምሯል:: እንደሚታወሰው ከተዘጋበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ሁለቱም ካለ VPN አይሰሩም ነበር::
#internet_controllers
ለመሆኑ ኢንተርኔትን የሚቆጣጠረው ማነው?

የኢንተርኔትን ደህንነት የሚቆጣጠሩት 14 ሰዎች እንደሆኑ ታውቁ ኖሯል?

እነዚህ በተለያየ የአለም ክፍል የሚኖሩ ሰዎች ይህን የሚፈጽሙት በከፍተኛ ሚስጥር የተያዙ ሰባት የቁልፍ ቁጥሮችን በተናጠል በ 3 ወር እየተቀያየሩ በመያዝ ነው። ይህ ከሳይንስ ፊክሽን ላይ የተወሰደ ታሪክ እንጂ እውነት ላይመስል ይችላል።

"crypto officers" በሚል ስም የሚጠሩት እነዚህ14 ግለሰቦች "internet corporation for assigned names and numbers (ICANN) የሚባል ለድረ ገጾች የ IP አድራሻ ሰውኛ ትርጉም ያለው አድራሻ የሚሰጥና የማስተደደር ስልጣን ያለው ተቋም አባላት ሲሆኑ ዋና ኋላፊነታቸውም የ Domain name system (DNS) አሰራርን የሚያስተናግዱ የኮምፕዩተር ሰርቨሮችን በከፍተኛ ደረጃ ምንም እክል እንዳይገጥማቸው መጠበቅ ነው።

በ ኦክቶበር 2016 ዲን በተሰኘ ኩባንያ ላይ በሀከሮች በተሰነዘረ ጥቃት አማዞንን እና ትዊተርን ጨምሮ በርካታ ድረ ገጾች ጥቃት ደርሶባቸው ለደቂቃዎች ተቋርጠው ነበር። ዲን የ DNS አገልግሎትን ከሚሰጡ ተቋማት ውስጥ ተቀዳሚው ነው። የ DNS አሰራር ዋና ተግባር በሰው ጭንቅላት መነበብ የሚችልን (ለምሳሌ www.amazon.com) የድረገጽ አድራሻ በኮምፒዩተር መነበብ ወደ ሚችል (ለምሳሌ http፡//173.252.110.27) የ Ip አድራሻ መቀየር ነው። ይህ አሰራር ባይኖር ኖሮ እያንዳንዷን ለመጠቀም የምንፈልገውን ድረገጽ ከላይ በተጠቀሰው አይነት የ IP አድራሻ አስታውሰን መጠቀም ይኖርብን ነበር።
ሀከሮች ተሳክቶላቸው የዲን ኩባንያን ባጠቁበት መንገድ የ ICANN ቤተመረጃ ሰብረው መግባት ቢችሉ በአጠቃላይ የአለምን የኢንተርኔት አሰራር መቆጣጠር ይችላሉ። ለምሳሌ ሰዎችን ትክክለኛ ወዳልሆነና ገንዘባቸውን ሊያዘርፋቸው ወደሚችል የባንክ መሳይ ድረገጽ አታለው ሊወስዷቸው ይችላል።
ለዚህም ነው ይህ ከፍተኛ ጥበቃ የሚያስፈልገው የ DNS server አንድ ሰው ብቻ እንዲቆጣጠረው ላለማድረግ ሰባት ሰዎች ለየብቻ በሚይዙት ልዩ የሚስጥር ኮድ ተቆልፎ አንድ ላይ ተገናኝተው በአንድነት ሲያቀናብሩት ብቻ መስራት በሚችል አሰራር ይጠበቃል። ሌሎች ሰባት ሰዎች ደግሞ በተጠባባቂነት የተመረጡ የሚስጥር ቁልፎች ተሰጥቷቸው በተጠባባቂነት ይቆያሉ!

@computer_mobile21
#telegram
ቴሌግራም 'Video Call' ጀመረ!

ዛሬ ቴሌግራም ሰባት (7) ዓመቱን ይዟል ፤ ይህ መተግበሪያ አገልግሎት መሰጠት የጀመረበትን ሰባተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ አዲስ ይዘት ይዞ ቀርቧል ይኸውም 'Video Call' ነው።

ቴሌግራም አሁን ላይ በዓለም '400 ሚሊዮን' ተጠቃሚዎች ያሉት እና ከ10 በብዛት ዳውንሎድ ከተደረጉ መተገበሪያዎች አንዱ መሆን ችሏል።

ቴሌግራም'Video Call'ለመጠቀም በመጀመሪያ አሁን ላይ እየተጠቀማችሁ የምትገኙትን መተግበሪያ PlayStore ላይ ገብታችሁ #update ልታደርጉት ይገባል።

@computer_mobile21

👇👇👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=org.telegram.messenger