COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE
7.1K subscribers
71 photos
7 videos
53 files
103 links
Welcome To Computer & Mobile Maintenance Channel.
It Gives You Some Hints To Repair(Improve Performance Of) Your Computer & Mobile By Yourself. ለጠጋኞችም የሚጠቅም ምርጥ ቻናል ነው!
JOIN @Computer_Mobile21
Contact @seen311 or @seen3bot

Group👉 @Computer_Mobile3
Download Telegram
COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE
#mobile_share_me_account 🖐 Use another phone no Voice, Internet & Message #package 🖐 እንዴት አድርገን እኛ በራሳችን ስልክ ኢንተርኔት:ስንደውልና መልዕክት ስንልክ #ከሌላ_ሰው_እንዲቆጥር ማድረግ እንደምንችል ያውቃሉ እኛ እንድንጠቀምበት የምንፈልገው ስልክ ላይ 👇👇 1 👉 ወደ *999# ይደውሉ 2 👉 ቁጥር 4 ላይ…
#share_me_account

ከዚህ በፊት 'ከአካውንትዎ ያጋሩኝ' እንዴት ማስጀመርና መጠቀም እንደምንችል አቅርበን ነበር።
በውስጥ መስመር '... አገልግሎቱን እንዴት እናቋርጣለን?' የሚሉ ጥያቄዎች እየደረሱን ነው። ሌሎቻችሁንም ካስቸገራችሁ @seen3bot ላይ ጠይቁ እናስተናግዳለን።

@computer_mobile_maintenanc_ethio
#pc_mobile_filesharing

💻📲 💻📲 💻📲
አንድሮይድ ስልካችን እና ላፕቶፓችን እንዴት #Xender ተጠቅመን በማገናኘት መረጃዎችን መላክ እንደምንችል ያውቃሉ?

አንዳንዴ ከላፕቶፓችን ወደ ሞባይል ወይም ከሞባይል ወደ ከላፕቶፓችን መረጃዎችን ለመላክ USB ኬብል ላናገኝ እንችላለን። በዚህ ጊዜ የስልካችንን Xender: የኮምፒዩተራችንን wifi እና browser(pc app: chrome,opera,..)ተጠቅመን ማገናኘት እንችላለን።

አሰራሩም:
1️.📱Update የሆንዉን Xender ስልካችን ላይ እንጭናለን

2️.📱Xender እንከፍታለን

3️.📱Connect to PC የሚለዉን እንጫናለን
connect to pc የሚለው ከሌለ የ Xender profile picture ላይ በመጫን more የሚለውን በመንካት ማገኘት

4️.📱WI-Fi Hotspot የሚለዉን እንጫንና Create hotspot እንለዋለን

5️.💻 ወደ ላፕቶፓችን እንሄድና WI Fi ከፍተን ስልካችን ላይ በሚነግረን የ Xender ስም አይተን Connect እንላለን። Xender_AP6911 ብዙ ጊዜ ይሄ ነው የሚሆነው ሌላም ሊሆን ይችላል።

6️. 💻Connect መሆኑን ካረጋገጥን በኋላ ማንኛዉንም ኢንተርኔት የምንጠቀምበተን ብሮውዘር ከፍተን ስልካችን ላይ የሚያሳየንን አይፒ(IP) “ http://192.168.43.1:334/
55/ ” አስገብተን Connect እንላለን። ሌላም IP ሊሆን
ይችላል።

7️.📱 ስልካችን ላይ Accpet እንላለን አበቃ።
ከዚያ ላፕቶፓችን ላይ ከስልካችን ላይ ያሉን መተግበሪያዎች ጨምሮ ሁሉንም ፋይሎችን እንደ ፎቶ ቪዲዮ ልክ ኢንተርኔት እምንጠቀም እስኪመስለን
እናገኛቸዋለን፡፡ ከፈለግን ላፕቶፓችን ላይ Backup መውሰድ ፡ ኮፒ ማድረግ ወደ ስልካችን መጫን እንችላለን።

ከስልክ ወደ ኮምፒውተር መረጃ ለመላክ 📱➡️💻
👉 ኮምፒውተሩ ላይ connect ካደረግንበት browser ስንገባ የስልካችንን መረጃዎች እናገኛለን። ከዚያም የምንፈልገውን ፋይል ስንመርጥ ከላይ የ download ምልክትን መጫን ወይም drag በማድረግ መውሰድ
ከኮምፒውተር ወደ ስልክ መረጃ ለመላክ 💻 ➡️📱
👉 መረጃውን ኮምፒውተር ላይ drag በማድረግ ስልካችንን connected ካደረግንበት browser በመውድን move የሚል ሲመጣ መልቀቅ(drop)

#ማሳሰቢያ ፡- ይህን ስንሰራ ሞባይል ዳታ መዝጋት ይኖርብናል ፡ ምክንያቱም ወደ ላፕቶፓችን ሼር ስለሚሆን ከስልካችንን ካርድ ስለሚቆርጥ ነው፡፡
👍ከወደዱት ለወዳጅዎ #ያጋሩት

@seen3bot
@computer_mobile_maintenanc_ethio
Join 👆👆👆👆👆👆👆
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#baidu_browser_crashing
how can you solve it? answer @Computer_Mobile3
COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE
#baidu_browser_crashing how can you solve it? answer @Computer_Mobile3
#Baidu_browser_crashing

Here is simple Answer
1. On search bar write 'baidu browser'
2. Right click on it
3. Open file location
4. Find the file name 'bdstatreport' & delete it
5. Solved! Then check it

Have you any other solution?

@computer_mobile_maintenanc_ethio
#ubuntu_operating_system

#ኡቡንቱ(Ubuntu Operating system)

1980ዎቹ ዩኒክስ ኦፕሬትንግ ሲስተም ብዙ ኮምፒዩተሮች ይጠቀሙ ስለነበር የተለያዩ ሰዎች የኦፕሬትንግ ሲስተምን ኮድ(source code) ባለቤትነት ጥያቄ በማቅረብ የኒክስ ኮዱን ማጋራት አንዲከለከል ወሰኑ፡፡ ይህን ቀድሞ ያየው ተዋቂዉ የኮምፒዩተር ባለሙያ #ሪቻርድ_ስታልማን ዩኒክስ ኦፕሬትንግ ሲስተም ተመሳሳይ ግለባጭ ለመስራት ወስነ፡፡

በሪቻርድ ስታልማን እምነት ሶፍትዎር መጋራት(share) ምንም ጉዳት አንደሌለው እና የሶፍትዌር ጥራትንም እደሚጨምር ያምን ነበር፡፡ ሪቻርድ ስታልማን የሰራውን ዩኒክስ ኦፕሬትንግ ሲስተም ለማንም ሰው እዲጠቀመው በነጻ ለቀቀው፡፡

በሪቻርድ ስታልማን እና ኮናኪያል ዩኒክስ ኦፕሬትንግ ሲስተም በማሻሻል አንዲሁም ለአንድ ኦፕሬትንግ ሲስተም ከሃርድዌር ጋር ለመግባባት ወሳኝ የሆነው ከርንል በማካተት 2004 ለመጀመሪያ ግዜ ተለቀቀ፡፡ሰሙም #ኡቡንቱ ተብሎ ተሰየመ፡፡

ኡቡንቱ ማለት አፍሪካዊ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “ለሌላው ማስብ” ወይም “ሰብአዊነት” ማለት ነው፡፡ ኡቡንቱ ተወዳጂነት ያተረፈው ወዲያው ነበር ከሌላው ሉኔክስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም #ቀላል እና ለመልመድ #የማያስቸግር በመሆኑ ተወዳጅነትን አትርፏል፡፡ኡቡንቱ ከፈተኛ ድጋፍ ከሚደረግላቸው ትልልቅ ኦፕሬትንግ ሲስተም አንዱ ስለሆነ በየስድስት ወር ይዘምናል(update)፡፡

ኡቡንቱ ከሌሎች ኦፕሬትንግ ሲስተም #በምን_ይለያል?

የቫይረስ ትቃት ነጻ መሆኑ
በፍጥነት የተሻለ በመሆኑ
ድራይቨር መጫን አለመጠየቁ ወይም አለማስፈለጉ
የራም አና የሲፒዩ አጠቃቀሙ የተሻለ በመሆኑ
ለሪሰርች ትልቅ ድጋፍ ስላለው
ለሳይንቲፊክ ጥናት ተመራጭ በመሆኑ
👍ከወደዱት ለወዳጅዎ #ያጋሩት!

@computer_mobile_maintenanc_ethio

Read More 👇👇👇👇
https://www.lifewire.com/beginners-guide-to-ubuntu-2205722
#Shopping

#ኮምፒዩተር #መግዛትም ሆነ #መሸጥ የሚፈልጉ ከሆነ @shopPcbot ላይ የሚገዙትን ወይም የሚሸጡትን ኮምፒዩተር አጠቃላይ ሁኔታ ይጻፉልን!
🖥🖥🖥🖥🖥🖥🖥🖥🖥🖥
@shopPcbot @shopPcbot
🖥 💻💻💻💻💻💻
#basic_computer 🖥💻

@computer_mobile_maintenanc_ethio

💻🖥 #ኮምፒውተር ምንድን ነው?

ኮምፒውተር ማለት በሰውም ይሁን በፕሮግራም በታዘዘው የተለያዩ ትእዛዞች መሰረት ስራ የሚያከናውን #ማሽን ነው፡፡ ይህ ስራ ለምሳሌ ሰነድ ለመጻፍ፣ ሂሳብ ለማስላት፣ ኢንተርኔት ለመቅዘፍ፣ ለመጫወት፣ ለመሳል፣ ፎቶና ቪዲዮ ለማዘጋጀት ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንን የስራ ክንውን ለመፈጸም ኮምፕዩተር #በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፡፡

ከታች የቀረቡት ሶስቱ መሰረታዊ ክፍሎች ኮምፕዩተሩ እንደ ኮምፕዩተር እንዲሆንና ትእዛዞቹም እንዲፈጸሙ ያስችሉታል፡፡
በአይነትም ሆነ በትልቅነት የተለያዩ ኮምፕዩተሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ የጭን፣ የቤት፣ የመስሪያ ቤት ኮምፕዩተሮች አሉ፡፡ ከአካል መጠናቸው፣ ከፍጥነታቸውና ከአቅማቸው ልዩነት በስተቀር መሰረታዊ አሰራራቸው ይመሳሰላል፡፡

💻አንደኛው #የውስጥ አካላዊ ክፍሎቹ ለምሳሌ Harddrive HDD (ካዝና)፣ RAM ራም (ጊዜያዊ ተሸካሚ)፣ Motherboard ዋና ካርድ፣ Sound card የድምጽ ካርድ፣ Video card የቪዲዮ ካርድ፣ CPU አማካይ አዛዥ ይገኙበታል፡፡

💻 #የውጭ አካላዊ ክፍሎቹ ደግሞ Display ማሳያ፣ Keyboard መጻፊያ፣ CD/DVD-rom የሲዲ/ዲቪዲ ቤት፣ printer ማተሚያ፣ Mouse (አይጥ)፣ ይገኙበታል፡፡

የሁሉም የውስጥና የውጭ አካል የጋራ ስም ደግሞ #ሃርድዌር(hardware) ይባላል፡፡ ይህ ሃርድዌር በአካል የሚታይና የሚነካ ነው፡፡

💻ሁለተኛው ክፍል ደግሞ አካላዊ ያልሆኑ #ፕሮግራም(software) ተብለው የሚጠሩ ናቸው፡፡ እነዚህም ለምሳሌ ሰነድ መጻፊያወች፣ ሂሳብ ማስያዎች፣ ኢንተርኔት መቅዘፊያዎች፣ ጨዋታዎች፣ ስእል መሳያዎች፣ ፎቶና ቪዲዮ ማቀናበሪያዎች ወዘተ የሚያገለግሉ ፕሮግራሞች ናቸው፡፡
እንደተጠቃሚው ፍላጎትና ስራ በመቶና በሺህ የሚቆጠሩ ፕሮግራሞች አሉ፡፡ የሁሉም ፕሮግራሞች አጭር የጋራ ስም #software ወይም የትእዛዝ ጥርቅሞች ሊባል ይችላል፡፡ ሶፍትዌር ልክ እንደ ሃርድዌር የሚነካና የሚጨበጥ አይደለም፡፡ ሶፍትዌር ግን የማይነካና የማይጨበጥ ቢሆንም ክስተት የሚያሳይ የትእዛዝ ጥርቅም ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የኮምፕዩተር የእያንዳንዱ የውስጥና የውጭ አካሎች የራሳቸው ድራይቨር (አስማሚ) የሚባል ሶፍትዌር አላቸው፡፡ ለምሳሌ የድምጽ ካርዱ የድምጽ ካርድ መሆኑን ኮምፕዩተሩ ውስጥ እንዲታወቅ ለማድረግ ነው፡፡

💻 ሶስተኛው ክፍል ደግሞ #Operating_System(ግብረተ ሲስትም) ይባላል፡፡ የግብረተ ሲስተሙ ዋና ዋና ሚና ካላቸው አንዱ ክፍል ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ግብረተ ሲስተሙንና ሁለተኛው ነጥብ ላይ የተጠቀሰውን ሶፍትዌር አደባልቀውና አደናግረው ይነጋራሉ፡፡ ነግር ግን በቀጥታ ትክክል አይደለም፡፡ ባጭሩ ዋናው የግብረተ ሲስተሙ ስራ የኮምፕዩተር የውስጥና የውጭ አካል እና ሶፍትዌሮች በአንድ ላይ ተጣጥመው ወይም እጅና ጓንት ሆነው እንዲሰሩ የሚያስችል ነው፡፡ ለምሳሌ Windows ዊንዶውስ፣ Mac ማክ፣ Linux ሊነክስ የመሳሰሉት ግብረተ ሲስተም ናቸው፡፡

👍 ኮምፕዩተሩ እንዲሰራ ሶስቱም ክፍሎች ማለትም አካላዊ ክፍሎቹ፣ ፕሮግራሞቹና ግብረተ ሲስተሙ በአንድ ላይ ተቀናጅተውና ተስማምተው መስራት አለባቸው፡፡

Join 👇👇👇👇👇 @computer_mobile_maintenanc_ethio
SHARE SHARE
#computer_types_parts

#የኮምፒዩተር_ዐይነቶች

1. ሜን ፍሪም(main frame)
2. ሱፐር ኮምፒዩተር(super computer)
3. ሰርቨር (server computer)
4. ማይክሮ ኮምፒዩተር-(ዴስክቶፕ፣ ላፕቶፕ፣ ፓልምቶፕ)
5. ሚኒ ኮምፒዩተር(Mini computer)
@computer_mobile_maintenanc_ethio

💻💻🖥🖥🖥💻💻
የኮምፒዩተር ዋና ዋና #ክፍሎች

የኮምፕዩተር የውስጥ ክፍሎች የሚከተሉት ናቸው፡-

1. #ሞኒተር(monitor)
የምንሰራውን ነገር የሚያሳየን፤ምስል፣ጽሑፍ፣ ቪዲዮ ወይም ማንኛውም ነገር ሊሆን ይችላል።

ሞኒተር 14 ኢንች፣ 15 ኢንች፣ ወዘተ. እየተባለ ይገላጻል፡፡

14 ኢንች 15 ኢንች እያልን ስንናገር አለካኩ ከምስል ማሳያው አንድ ጥግ እስከ ሌላኛው ጥግ ያለውን ርቀት በመለካት ነው፡፡

በፊት የነበሩት የላፕቶፕና ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች ሬሾ (ርዝመት ሲካፈል ለወርድ) 4በ3(በትክክል ሲጻፍ 4:3 ይሆናል) ነበር፡፡

አሁን ደግሞ የቲያትር ሞድ የሚባለው ባለ 16፡9 ሬሾ ወይም ዋይድ ስክሪን (wide screen) በመጠቀም ላይ ናቸው፡፡

2. #ማዘርቦርድ(Motherboard-እናት ሰሌዳ
ሁሉም የኮምፕዩተር ክፍሎች(ዕቃዎች)የሚቀዳጁበት ክፍል ነው።

3. #ሲፒዩ(CPU)
የኮምፕዩተሩ አእማሮ እንደማለት ነው፡፡ይህ ሲባል ግን ሲፒዩን ከሰው አእምሮ ጋር አንድ ነው ማለት አይደለም፡፡

4. #ሜሞሪ(Memory)-ማስታወሻ
የምንሰራውን ስራ ወይም ፋይል በጊዚያዊነት አስቀምጠን የምንሰራበት ነው።

#ሜሞሪ(ማስታወሻ) በባይት (Bytes) ይለካል፡፡ ከ Bytes ፊት Kilo፣ ማለትም ኪሎባይት (kilobytes)([1,024 ባይቶች ወይም Bytes ማለት ነው፡፡ ] ፣ Mega[1,048,576 ባይቶች ወይም Bytes ] ፣ Giga [1,073,741,824 ባይቶች ወይም Bytes]፣ ወዘተ የሚሉትን ቃላት በመጠቀም ኪሎባይት(kilobyte)፣ ሜጋባይት (megabyte)፣ ጊጋባይት (gigabyte) እያልን የኮምፒዩተር ሜሞሪ መግለፅ እንገልጻለን፡፡

ለምሳሌ 10 MegaBytes ወይም ባጭሩ ሲጸፍ 10MB ይህ ማለት 10,485,760 Bytes ይሆናል ማለት ነው፡፡

5. #ኤክስፓንሽ_ስሎት(expansion slot)

6. #የኤሌክትሪክ_ሀይል_ማቅረቢያ (power supply)

7. #የሲዲ_ማሰሪያ (CD drive)

8. #ሀርድ_ዲስክ (Hard Disk)
የምንሰራውን ወይም የምንጠቀምበትን ፋይል በቋሚነት ለማስቀመጥ ይረዳናል።

9. #ማውስ(mouse)-መሎጊያ

10. #ኪቦርድ(Keyboard)-የፊደል ገበታ
ከታች ያለውን ምስል(image) ከቁጥሩ ጋር ማነጻጸር ይቻላል፡፡

💻💻🖥🖥🖥💻💻
ታዋቂ ዋና ዋና የኮምፕዩተር #አምራቾች

ታዋቂ የኮምፕዩተር አምራቾች የሚከተሉት ናቸው፡፡ ይህ ማለት ግን እያንዳዱን የኮምፕዩተር ክፍል(ዕቃዎች)ይሠራሉ ማለት አይደለም፡፡

1. #አይቢኤም[IBM]
አሁን እንኳ የፒሲ(pc) ክፍሉን እ.ኤ.አ. በ2004 ለቻይናው ሊኖቮ ሸጦታል፡፡ አሁን ሜን ፍሬም[Main Frame] ኮምፒዩተር ነው በብዛት የሚያመርቱት/የሚሠሩት፡፡
ድረ ገጽ www.ibm.com

2. #ዴል[Dell]

ድረ ገጽ www.dell.com 

3. #ኤሰር[Acer]

ድረ ገጽ www.acer.com

4. #ቶሺባ [Toshiba]

ድረ ገጽ www.toshiba.com

5. #አፕል [Apple]

ድረ ገጽ www.apple.com

6. #ኤችፒ[HP]

ድረ ገጽ  www.hp.com

የመጀመሪያቹ ኮምፕዩተሮች የሚሠሩት #በእንግሊዝኛ ፊደል ብቻ ነበር። ቀስ በቀስ ግን የተለያዩ አገሮች ሊቃውንት በየራሳቸው ፊደላት እንዲሠሩ አደረጉ። ኮምፕዩተር በእያንዳንዱ የግዕዝ ፊደል፣ አኃዝና ምልክት እንዲሠራ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈጠረው ኢትዮጵያዊው #ዶክተር_አበራ_ሞላ ነው። በቅርቡም አያንዳንዱ የግዕዝ ፊደል፣ አኃዝና ምልክት ዩኒኮድ(Unicode) የሚባል የዓለም ፊደላት መደብ ውስጥ መግባት ቀጥሏል።

Contact @seen3bot
Join 👇👇👇
@computer_mobile_maintenanc_ethio
Share share share
ለተሳታፊዎች በሙሉ እናመሰግናለን!
በቅርቡ ይጠብቁን! ሞቅ ያለ ውድድር ይዘን እንመለሳለን!
መልካም ጊዜ
@computer_mobile_maintenanc_ethio
#basic_computer_components
5 ዋና የኮምፒውተር #ክፍሎች

💻💻💻🖥🖥🖥🖥

👉በየሁላችን ጠረጴዛ፤ በጀርባችን ላይ በቦርሳ ሸክፈን የሚገኘው ኮምፒውተር ስንፈልግ የሂሳብ ስሌት፤ ሲነሽጠን ቃላቶችን ከምስል አዋደን የምንፅፍበት፤ ለውስጣችን ሀሴት ሙዚቃ የምንዳምጥበት ብዙ ተግባራትን በተመሳሳይ ወቅት መከየን የምችል #የኤሌክትሮኒክስ ውጤት ነው፡፡

👉 ኮምፒውተር ታዲያ እንደ አሁኑ በመጠን አንሶ፤ በማቀናበር አቅም አይሎ ከመምጣቱ በፊት ኮምፒውተር በመጠን ትልቅ እና የማቀናበር እንዲሁም ነገሮችን የመከወን አቅሙ ውስን ነበር፡፡

👉 ታዲያ አሁን ላይ ሆነን ኮምፒውተር በውስጡ ምን አይነት ክፍሎች እንዳሉት እና የክፍሎች ተግባሮቹን ማወቅ ወሳኝ ነው፡፡

👉 ምንም እንኳን ሁሉም የኮምፒውተር ክፍሎች በጣም አስፈላጊ እና እያንዳንዳቸው የራሳቸው ተግባር ያላቸው ቢሆንም በጣም አስፈላጊ እና በጣም መሰረታዊ የሚባሉትን 5 ክፍሎችን እንቃኛለን።
@computer_mobile_maintenanc_ethio share share share
1. #motherboard ❖ Motherboard የኮምፒውተር ክፍል ዋናው የኤሌክትሪክ ሰርኪዩት ሰሉዳ ሲሆን ተለቅ ያለ እና ዋና የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
ሁሉም የኮምፒውተር ክፍሎች ከ Motherboard ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተገናኙ ሲሆን ይህም በመሰረታዊነት የኮምፒውተሩ ክፍሎች እርስ በርስ መረጃ እና ትዕዛዞችን እንዲለዋወጡ ያስችላል፡፡

❖ ካለ Motherboard ኮምፒውተር የማይታሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የኮምፒውተሩ ኤሌክትሪክ አቅራቢ(Power Supply) ለሲዲ ማንበቢያው (CD drive) የኤሌክትሪክ ሃይል መስጠት ካልቻለ ሲዲ ማንበቢያው መስራት አይችልም፡: @computer_mobile_maintenanc_ethio
2. #Central_Processing_Unit (CPU)

❖ CPU የኮምፒውተሩ ማዕከላዊ ማቀነባበሪያ ክፍል ሲሆን ማቀናበሪያ(processor) አልያም የኮምፒውተር አዕምሮ ሌላኛው መታወቂያ ስሞቹ ናቸው፡፡

❖ CPU ከተጠቃሚ ወደ ኮምፒውተሩ የሚገቡትን ትዕዛዞች በሙሉ በመቀበል ኮምፒውተሩ በአግባቡ ትዕዛዙን እንዲከውን የሚያደርገው በ motherboard ላይ የሚገኝ ትንሽ የኤሌክትሮኒክ ቺፕ ነው፡፡

❖የማቀናበር ሃይል(processing power) የኮምፒውተርን ፍጥነት ግልፅ በሆነ መልኩ ይጨምራል፡፡
ስለሆነም ፈጣን ማቀነባበሪያ ኮምፒውተሮችን ፈጣን ያደርጋቸዋል:: @computer_mobile_maintenanc_ethio
3. #Random_Access_Memory (RAM)

❖RAM ማሕደረ-ትውስታ የኮምፒውተሩ ጊዜያዊ መረጃዎችን አልያም ስሌቶችን የሚያኖርበት እና በሚያስፈልግ ጊዜ(ኮምፒውተሩን ከማጥፋታችን አልያም ዳግም ከማስነሳታችን በፊት) መረጃዎችን ወይንም ስሌቶችን የሚሰጠን ነው፡፡

❖RAM ከ CPU ጋር በመተባበር ዳታዎች በተሳካ ሁኔታ የሚያቀነባብር ወሳኝ የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡

❖የRAM መጠን በመጨመር የኮምፒውተሮችን የማህደረ-ትውስታ በማስፋት የማቀነባበር አቅሙን ማሻሻል ይችላል::
@computer_mobile_maintenanc_ethio
4. #Hard_Drive

❖Hard drive ለኮምፒውተሮች እንደ ትልቅ ቤተ-መፀሃፍት ነው፡፡ ምክኒያቱም ፋይሎችን፤ሙዚቃዎችን፤ምስሎችን፤ሰነዶችን፤ ወዘተ ለዘለቄታው የምናኖርበት ሁነኛ ክፍል ነው፡፡

❖Hard drive በግል ከምናኖራቸው መረጃዎች ባለፈ የኮምፒውተሩ አሰራር ሂደት(operating system) የሚጫንበት እና በአግባቡ ኮምፒውተሩ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ የሚያደርጉትን የአሰራር ሂደት ፋይሎች(operating system files) የሚቀመጡበት የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
@computer_mobile_maintenanc_ethio
5. #Power_Supply_Unit

❖Power supply unit የኮምፒውተሩ የሃይል አቅርቦት ክፍል ሲሆን ከግርግዳ ወይንም ከኤሌክትሪክ ማከፋፈያ የሚቀበለውን ኤሌክትሪክ ለኮምፒውተሩ በሚመጥን የኤሌክትሪክ መጠን እና አቅርቦት ለክቶ እና መጥኖ ወደ ኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚያዳርስ የኮምፒውተር ቁልፍ ክፍል ነው፡፡
@computer_mobile_maintenanc_ethio
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#BASIC_PC_SYSTEM_PARTS
Use Wi-Fi to open, Large size to open with data
@computer_mobile_maintenanc_ethio
Forwarded from COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE (Seen above)
@computer_mobile_maintenanc_ethio

#mobile_internet_data_Saving
ሞባይል ዳታ በሚከፈትበት ጊዜ ካርድ ወይም የተሞላውን የዳታ
ጥቅል በቶሎ የሚጨርስበት ምክንያትቶችና መፍትሔዎች:

ምክንያቶች :-
1.#የሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሳይዘጋ ሲቀር
2.#ኢንተርኔት ክፍት ሆኖ ከተለያዩ ደህረ ገፆች ላይ ቀጥታ
ቪዲዮች ሲታዩ
3.#System settings እና Applications በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ
4.#በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቃሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ
5.#በሞባይል ስልኩ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር

መፍትሔዎች :-
👉ሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሲቆይ እንደ ሶሻል ሚዲያና
ኦንላይን የሚሰሩ አፕሊኬሽኖች ከተጠቃሚው እይታ ውጪ
ስራቸውን ያከናውናሉ። በዚህ ጊዜ በሞባይሉ ላይ የተሞላው
ክሬዲት ሰዓት ይቀንሳል ወይም ያልቃል ስለዚህም ኢንተርኔት
ተጠቅመው ከጨረሱ በኋላ የሞባይሉን ዳታ ያጥፉ።

👉በሞባይል ዳታ ኢንተርኔት ከፍቶ ከተለያዪ ድህ ገፆች ላይ
በቀጥታ ቪዲዮ መመልከት የተሞላውን ካርድ መጠን በጊዜ
ከሚያሳጥሩት ነገሮች ወስጥ አንደኛው ሲሆን ለዚህም ዋነኛው
ምክንያት በኢንተርኔት ቪዲዮ ቀጥታ መመልከት የሚቆጥረው
የዳታ መጠን ከፍተኛ ስለሆነ ነው ስለዚህ ቪዲዮ ማየቱ ግዴታ
ከሆነ በ Vidmate እና በሌሉች ቪዲዮ ዳውሎደር
አፕሊኬሽኖች የቪዲዮ ይዘት በመቀነስ ጭኖ መመልከቱ ወጪን
ይቆጥባል።

👉System settings እና Application በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ የተሞላውን ዳታ(ካርድ) ይወስዳሉ ታዲያ ይህን ለማስቀረት Free wifi ከተገኘ አፕዴት ማድረግ ይህ ማድረግ የማይቻል ከሆነ system settings አፕዴት እንዳያደርግ ማስቆም:
👍Settings ----About----Software Update---
Automatic update የሚለውን ማጥፋት
Applications አፕዴት እንዳያደርጉ ከተፈለገ ደግሞ
-Google Play መክፈት.
- hamburger የሚመስለውን በለ ሶስት ሆሪዞንታል ምልክት
ያለበትንም አናት ላይ በስተግራ በኩል Settings በመንካት
Auto-update apps.- disable automatic app
updates, የሚለውን በመክፈት እና በመምረጥ መዝጋት
ይቻላል

👉በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቀሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ ከእይታ ውጪ በመሆን የክሬዲት መጠን ይቀንሳሉ ታዲያ ይህን ለመከላከል:
👍Settings----
data usage ---Restricted Background data
የሚለውን መክፈት... ከዚህ ይበልጥ ደግሞ Mobile data
saver አፕሊኬሽኖች በመጫን መጠቀም

👉በሞባይል ሰልክ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር የተሞላውን ሞባይል
ዳታ ከመቅስፈት እድሜው እንዲያጥር ያደርጋል ብሎም ቫይረሱ በራሱ ጊዜ የሞባይሉን ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማዘዝ ያለማንም ትዕዛዝ ዳታ ይከፍታል ዳውንሎድ ያደርጋል አላስፈላጊ ነገሮችና ማስታወቂያዋች ይለቃል ከዚህም የተነሳ በፍጥነት የሞባይል ካርድ( ዳታ ጥቅል) ይጨርሳል ይህ ነገር በሞባይሉ ላይ ቢከሰት አንቲ ቫይረስ በመጫ ሰካን ማድረግ ይህ መፍትሔ
የማይሆን ከሆነ ለባለሙያ ማሳየቱ ተገቢ ነው::

ለአስተያየትና ጥያቄ @seen311

@computer_mobile_maintenanc_ethio
Forwarded from COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE (Seen above)
@computer_mobile_maintenanc_ethio

#battery_mobile
የስማርት ስልካችንን #ባትሪ ለረጅም ሰአት ለመጠቀም ምን ምን ማድረግ አለብን?

#1. በመጀመሪያ #ባትሪዎን በጣም የሚመጠውን አፕ ለይቶ ማወቅና uninstall ማድረግ።
👉 Setting battery ብዙ ባትሪ የተተቀመውን መለየት

#2. e-mail, Twitter, Instagram, messenger....የመሣሰሉትን ከፍቶ አለመተው

#3. Bluetooth, WiFi, GPS
እነዚህን በስልክዎ ሲጠቀሙ ስልክዎ ሁልጊዜ search ስለሚያደርግ ባትሪዎን ይገሉታል።

👉በተለይ GPS ለብዙ ሰአት መጠቀም ከሁሉም የበለጠ አደገኛ ነው።

#4. ስልክዎን በማይጠቀሙበት ጊዜ ultra power saving የሚለውን ማብራት ስልክዎ ስልክ ከመደወልና ሜሴጅ ከመቀበል በቀር ሌላ አገልግሎት እንዳይሰጥ ስለሚያደርግ #ባትሪዎን ለረጅም ሰአት መጠቀም ይችላሉ።

#5. background process የሚያደርጉ አፖችን ማስቆም።

👉 Setting-manage apps-process
የማይጠቅሙበትን አፕ stop ማድረግ።

#6. animated የሆነ wallpaper አይጠቀሙ።

#7. የስልክዎን brightness 🔆🔅🔅 ይቀንሱ።

👉ብዙዎቻችን ባትሪን ይበላል ብለን የማናስበው auto brightness ባትሪ በቶሎ እንዲያልቅ ያደርጋል።

#8. ያሉበት ቦታ ኔትወርክ በደንብ የሌለበት ከሆነ ስልክዎት የሚበቃውን ያህል signal 📶 strength ለማግኘት በሚያደርገው ጥረት የስልክዎ ባትሪ ቶሎ ያልቃል።

#9.ስልክዎ ላይ ሙሉ ቀን ሙጭጭ🤳 አይበሉ።

#10. ኦርጅናል #ባትሪ ይጠቀሙ።

#11. battery case መግዛት የሚችሉ ከሆነ ይጠቀሙ።

#12. የስልክዎ የቻርጅ መጠን ከ 40-90% ቢሆን የተሻለ ነው።

👉️ እነዚህን መፍትሄዎች ተግብረውም ለውጥ ከሌለው ባትሪ ይቀይሩ ወይም ችግሩ የ power ic ሊሆን ስለሚችል ለባለሙያ ያሳዩት::

Contact me @seen311

@computer_mobile_maintenanc_ethio
@computer_mobile_maintenanc_ethio