COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE
7.1K subscribers
71 photos
7 videos
53 files
103 links
Welcome To Computer & Mobile Maintenance Channel.
It Gives You Some Hints To Repair(Improve Performance Of) Your Computer & Mobile By Yourself. ለጠጋኞችም የሚጠቅም ምርጥ ቻናል ነው!
JOIN @Computer_Mobile21
Contact @seen311 or @seen3bot

Group👉 @Computer_Mobile3
Download Telegram
ቴሌግራምን hack እንዳይደረግብዎ ይፈልጋሉ?
መፍትሄውን እነ


❖ቴሌግራም ማለት እንደ ማንኛውም የ messaging application ነው ማለትም እንደ⇝whatsapp, viber, imo, tango.....etc
📌ቴሌግራም እንደ whatsapp, viber,imo...ሁሉ በቀላሉ በ "sms-based verification process" hack ሊደረግ ይችላል

ይህ ዘዴ ሌሎች hack ማድረጊያ hacking Tricks ሳያስፈልገን አፕሊኬሽኖች በመጠቀም
ማለትም የራሳችን ቴሌግራም አፕሊኬሽን ላይ ወይም pc ላይ ቴሌግራም install በማድረግ የምንፈልገውን ቁጥር በማስገባት ኮዱን ካስላክን ብኋላ ኮዱን የምናገኝበት አጋጣሚ ካለ....

በመጀመሪያም ይህ መሆኑን እና አለመሆኑን ለማረጋገጥ አሁን step by step ተከታተሉ
❶Telegram⇢seting⇢privecy and security⇢active session ላይ በመግባት በእናንተ አካውንት የገባ ሰው እንዳለና እንደሌለ ማወቅ ያስችላል።

■Note: እራስዎ በሌላ አፕ ከገቡም ያመጣልዎታል ስለዚህ በደንብ ይመልከቱ።

📌ከዛም Terminate all other sessions ክሊክ በሉት።
☛ ይህ ሚጠቅመው በሌላ ስልክ የእናንተን አካውንት የሚጠቀም ሰው ካለ remove ያደርገዋል።

⓶ Security ደግሞ ለማጠናከር
seting⇢privecy and security⇢two step verification⇢set aditional pasword ከዛ የፈለጉትን password ***..ግን የ gmail አካውንት ሊኖራቹ ይገባል።

❖ ይህ ጠንካራ የሚባለው #የቴሌግራም security ነው።

❖ የሚጠቅመው እንደፌስቡክ ሁላ በሌላ ስልክ ስንገባ password ይጠይቀናል (log in) እያልን ነው የምንገባው ማለት ነው።
====================
❖ ሌላ ሰው በsms የተላከውን ኮዳችሁን አግኝቶ እንኳ ቢከፍተው
ወደቴሌግራማችሁ በጭራሽ መግባት አይችልም።
====================
❖ ማንም ሰው ለመግባት በኢሜል የሰጣችሁት ኮድ ማወቅ ስለማይችል በጭራሽ መግባት አይችልም።

⚠️የፃፋችሁትን password እንዳትረሱት።

⚠️ከላይ ያሳየናችሁ ዘዴ ቴሌግራማችሁን በቀላሉ ኮዱን ወስደው በናንተ ቁጥር እንዳይጠቀሙ ነው እንጂ የተለያዩ hacking ዘዴን በመጠቀም ሃክ ከመደረግ አይከለክልም::
👍2
ለሞባይል ጥገና የሚያስፈልጉን

Join us https://t.me/ElectronicsMntc

1. መፍቻ ፦ ስልኮችን ለመፍታት እና ለመግጠም ይጠቅማል ፡፡

2.መልቲ ሜትር ፦ ሬዚስታንስ ፣ ቮልቴጅ እንዲሁም ከረንት ለመሰካት እና
የሰርኪዩት
ቀጣይነት ለማረጋገጥ ይጠቅመናል ፡፡

3. ቲነር ፦ ዝገት ለመከላከል እና ቆሻሻ ለማስወገድ ይጠቅማል ፡፡

4. ፔስት ፦ አይሲዎችን በመንቀያና በማስቀመጫ ሰአት ቦርዳችንና የሚነቀሰዉ
አይሲ
በሙቀት እንዳይጎዳ ይጠቅማል ፡፡

5. ብሎወር ፦ ሙቀትን በመስጠት አይሲዎችን ለመንቀልና ለማስቀመጥ
ይጠቅማል ፡፡

6. ካዉያ ፦ ሁለት የተላቀቁ ክፍሎችን ለመበየድ ይጠቅማል

7. ሊድ ፦ ሁለት የተላቀቁ ክፍሎችን ለመበየድ እንደ ቀላጭ የምንጠቀምበት
ነዉ ፡፡

8. ጃምፐር ዋየር ፦ ሁለት የተለያዩ የሰርኪዩት ክፍሎችን /የተላቀቁ ክፍሎችን/
ለማያያዝ
የሚጠቅም ቀጭን ሽቦ ነዉ ፡፡

9. ትዊዘር(ፒከር) ፦ አይሲ ወይንም ሌሎች የሞባይል ክፍሎች በብሎወር
ስናሞቅ እንደ
መቆንጠጫ የምንይዝበት ነዉ ፡፡

10.ዲሲ ፓወር ሰፕላይ ፦ ከባትሪ የምናገኘዉን 3.7 ቮልት የሚሆን ቮልቴጅ
የሚሰጥ ክፍል
ነዉ ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስልካችን ኦፕን ይሆን ሾርት ወይም ስልኮች
የሶፍትዌር ችግር
እንዳላቸዉና እንደሌላቸዉ ሊያሳየን የሚችል መሳሪያ ነዉ።
10 ነፃ ሶፍትዌር ማውረጃ ድረ-ገፆች
"""""""""""""""""""""""""""""""""""
1) www.FileHippo.com
2) www.Ninite.com
3) www.Cnet.com
4) www.Softpedia.com
5) www.MajorGeeks.com
6) www.FilePuma.com
7) www.DownloadCrew.com
8)· www.FileHorse.com
9) www.SnapFiles.com
10) www.DonationCoder.com
The computer is slow...Solution?

 Restart your computer.

 Verify that there is at least 200-500 MB of free hard drive space.
To do so,
select Start and click on My Computer or Computer.
Then highlight the local C drive by clicking on it once.
Select the Properties button at the top left-hand corner of the window; this will display a window showing how much free and used space you have.
If you need to recapture space: - Empty your recycle bin by right-clicking on the Recycle Bin' icon (usually on the desktop), then selecting Empty Recycle Bin.

Remove temporary files from the Internet.
To do so:
o Click Start button | My Computer or Computer.
o Click Open Control Panel at the top of the window.
o Click Network | Internet |Internet Options.
o Select the General tab and click Delete under Browsing History.

Perform a disk cleanup.
To do so:
o Click Start button | My Computer or Computer.
o Highlight the local C drive by clicking on it once.
o Select the properties button at the top left of the window.
o Go to the General tab and select Disk Cleanup. o Once the Disk Cleanup finishes running, click on Clean up System Files; this will delete any unnecessary system-related files from your local disk.
Information in computer files changes often, resulting in gaps or spaces within the file. This takes up more space on the computer and can cause the computer to slow down.
To reclaim these gaps in space, run disk defrag. To do so:
o Click start | My Computer or Computer.
o Highlight the local C drive by clicking on it once. o Select the properties button at the top left of the window.
o Go to the Tools tab and select Run Defragmentation.
 Old or unused programs that aren’t being used may still have components running behind the scenes when you start your computer, which can slow down the system. You can prevent these programs from running when you start your computer by removing unused shortcuts and turning off unused program services.

- Remove unused shortcuts from Windows startup
o Click Start button | Select All Programs | Click Startup
o Right-click the shortcuts that you do not use and click delete

- Disable unused program services
o Click Start button | Control Panel | Administrative Tools | Services
o For each program/service that you are certain that you do not need, click on the Service to highlight it, click the Stop link to stop the service from running, then double-click the service, choose Startup Type of Disabled, and click OK.
 Run a virus scan to remove potential viruses that can slow down your computer.
Join us @ElectronicsMntc
ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ለመግዛት አስባችኀል?? እንግዲያውስ
ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ከመግዛቶ በፊት ሊያውቋቸው የሚገቡ 10 ነገሮች !

ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ለመግዛት ስንመርጥ ብዙ ነገሮችን
አስበን ነው፤ከነዚህ ውስጥ የተለመዱ ነገሮች አሉ
ለምሳሌ አይነቱና ዋጋው፤አሁን ግን የማሳያችሁ ምርጥ 10 ቲፖች ናችው: :
1. ካገለገለ ኮምፒውተር ይልቅ አዲስ ኮምፒውተር
ይምረጡ

2. PCI Express x16 slot ያለው ማዘረቦርድ መሆን
አለበት ይህም ሌሎች ካርዶችን ለመጨመር ይረዳዎታል::
ለምሳሌ ቲቪ ካርድ፣ ግራፊክስ ካርድና ሌሎች

3. ሚሞሪው ቢያንስ 4GB of RAM መሆን አለበት
ይህም ኮምፒውተሮ እንዳይጨናነቅና ፈጣን እንዲሆን
ያደርገዋል::

4. ፕሮሰሰሩ Quad-core processor ያለውን ይምረጡ
ይህም ኮምፒውተሮ ፈጣንና ብዙ ፕሮግራሞችን ባንዴ
የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል::

5. ኮምፒውተሮን ለቤት ከሆነ የፈለጉት ፉኑ የማይጮህና
የማይረብሽ ይምረጡ::

6. An All-in-one PC ሁሉንም በአንድ ላይ የያዘ
ኮምፒውተር ይምረጡ (ሞኒተሩ ፍላት ስክሪን፣እና
ሌሎችንም የኮምፒውተር አክሰሰሪዎች ያሟላ)

7. a single, high-powered graphics card ያለው
ይምረጡ ይህም ኮምፒውተሮ ላይ ጌም የሚጫወቱ ከሆነ
ይጠቅሞታል

8. የሃርድ ዲስኩ ሳይዝ 500GB እና ከዛ በላይ ቢሆን
ይመረጣል ይህም ኮምፒውተሮ ላይ ብዙ ፋይሎችን የሚያስቀምጡ ከሆነ ነው

9. ሃይል ቆጣቢና አነስተኛ ወጪ የሚያወጣ ይምረጡ

10. ኮምፒውተሮን ሲገዙ አብረው external hard
drive ይግዙ ይህም ዳታዎችዎን ባክ አፕ (መጠባበቂያ)
ለማረግ ነው : :
Join us @ElectronicsMntc
🌐ዓለም ከኮምፒውተር ጋር ከተዋወቀ በርካታ ዓመታት ቢቆጠሩም የብዙዎች የኢንተርኔት አጠቃቀም መስመርን የሳተ ነው።
===================

ከመረጃ ደህንነት ጋር የተያያዙ የትየለሌ እሮሮዎች በተደጋጋሚ የሚሰሙትም ከአጠቃቀም ስህተቶች ጋር በተያያዘ ነው።

የኢንተርኔት አጠቃቀም ስህተት ለአካላዊ ወይም አእምሯዊ ጉዳት እንደሚያጋልጥ
ተመራማሪዎች ይናገራሉ።

በስፔን የሚገኘው የበይነ-መረብ ደህንነት ተቋም ኢንተርኔት ሰክዩሪቲ ኦፊስ (ኢኤስኦ) በተደጋጋሚ የሚሰሩ ስህተቶችን ይፋ አድርጓል።

ከኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች ራሳችሁን ለመታደግ ስህተቶቹን ከመፈጸም ተቆጠቡም ብሏል።

#የማይታወቁ_ማስፈንጠሪያዎች

የኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች ሰዎችን ከሚያጠምዱባቸው መንገዶች አንዱ የተሳሳቱ ማስፈንጠሪያዎች መላክ ነው። ሰዎችን በቀላሉ ማማለል የሚችሉ 'የዋጋ ቅናሽ' ወይም 'በነጻ የሚታደሉ ምርቶች' ማስታወቂያ ይጠቀሳሉ። ማስፈንጠሪያዎቹ ቫይረስ ወደተሸከሙ ገጾች ስለሚወስዱ የተጠቃሚዎችን የመረጃ ደህንነት አደጋ ውስጥ ይጥላሉ።
ኢኤስኦ "ማስፈንጠሪያዎች ከመከተልዎ በፊት ቆም ብለው ያስቡ" ይላል።

#ያረጁ_ሶፍትዌሮች

በስልክ ወይም በኮምፒውተር የሚጫኑ ሶፍትዌሮች በየግዜው መታደስ አለባቸው። ሳይታደሱ ከቆዩ የኮምፒውተር ወንጀለኞች በየግዜው ለሚሰሯቸው አደገኛ ቫይረሶች ያጋልጣሉ።

#አጠራጣሪ_መተግበሪያዎች

መተግበሪያዎችን (apps) ከተለያዩ ድረ ገጾች መጫን ለደህንነት አስጊ ነወ። ትክክለኛ የሚመስሉ ነገር ግን ለቫይረስ የሚያጋልጡ መተግበሪያዎች ብዙ ናቸው። ብዙዎችም ያለማወቅ ይጭኗቸዋል።

#ቀላል_የይለፍ_ቃል

የኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች የተጠቃሚዎችን የግል መረጃ ለመስረቅ የይለፍ ቃላቸውን ይሰብራሉ።
ስለዚህም ኢኤስኦ "ጠንካራ የይለፍ ቃል ይኑራችሁ" ይላል። ምክንያቱም በቀላሉ
የሚገመቱ የይለፍ ቃሎች በርካቶችን ለአደጋ አጋልጠዋል።

#የመረጃ_ቅጂ_አለማስቀመጥ

በኮምፒውተር ወይም በስልክ ላይ ያሚገኙ መረጃዎችን ቅጂ አለማስቀመጥ ሌላው ችግር
ነው። የኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች የግል መረጃ ካገኙ ለባለቤቱ ለመመለስ ገንዘብ ይጠይቃሉ። ተጠቃሚዎች የመረጃቸው ቅጂ ካላቸው ግን ከመዝባሪዎች ጋር መደራደር አያስፈልጋቸውም::
Join us @ElectronicsMntc
አፕል(Apple)ኩባንያ ተጠቃሚዎች በድመፅ ማዘዝ የሚችሉት  ገመድ አልባ ድምፅ ማዳመጫ ወይንም ኢርፎን ይፋ አደረገ

ይህም ተጠቃሚዎች ምንም አይነት ነገር ሳይጫኑ  ሃይ ሲሪ(Hi Siri) የሚል ድምፅ በማሰማት ብቻ የድምፅ ማዳመጫውን ማዘዝ እንደሚችሉ ነው የተነገረው፡፡

ከዚህ ባለፈ ኤርፖድስ የተባለው ገመድ አልባ ድምፅ ማዳመጫ ተጠቃሚዎች ባትሪ ካለቀባቸው እንዲያስተካክሉ ተጨማሪ ሰዓትን በቅድሚያ እንደሚሰጥ ነው የተነገረው፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት የሰጡ ባለሙያዎች  ኤርፖድስ የተሰኘው የድምፅ ማዳመጫ በእጅጉ እየዘመነ መምጣቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

ይህ አዲሱ ድምፅ ማዳመጫ 159 የአሜሪካ ዶላር የሚያወጣ ሲሆን ገመድ አልባ ቻርጀርን የሚያካትት ከሆነ ተጨማሪ 40 ዶላር ያስፈልጋል ተብሏል፡፡
Join us @ElectronicsMntc
👍1
#የዌብሳይት_ጥቆማ

👉 http://www.imei.info/

እዚህ ዌብሳይት ውስጥ በመግባት የስልክዎን IMEI no (*#06#) ያስገቡና የሚመጣልዎ #መረጃ ስለራስዎ ስልክ ከሆነ ስልኩ ኦርጅናል ነው፤ የሌላ #ስልክ ከሆነ ግን

✔️አሁን ላይ በተለይ በብዛት የሚስተዋለው አዲስም ሆነ ያገለገሉ የሚገዟቸው #ስልኮች (አንዳንድ ከስልክ ቤቶች የሚገዟቸውንም ይጨምራል) የሚሸጡልዎ IMEI number በመቀየር ነው ይህም #ስልክዎ ለጊዜው ቢሰራም ከዋናው ስልክ ጥራቱ የወረደ ነው። (RAM, internal storage, camera qualityው እንዲሁም የአገልግሎት ጊዜው ከኦርጅናሉ ስልክ ይቀንሳል)

✔️ስለዚህም ቼክ ሲያደርጉ የሌላ ስልክ መረጃ ከመጣልዎ ስልኩን ከመግዛት ይቆጥቡ።
Join us @ElectronicsMntc
ሌላ ሰው የፌስቡክ አካውንታችሁን ሲጠቀም እንዴት ፌስቡክ በሞባይል ስልካችሁ
ሚሴጅ(SMS) እንዲልክላቹ ማድረግ እንደምትችሉ:-

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መንገዶች ተጠቅማቹ ደህንነታቹን መጠበቅ ትችላላቹ።

1. ውደ ፌስቡክ አካውንቶ ይግቡ

2. የ ፌስቡክ “Settings” ዉሰጥ ይግቡ

3. ከዛም “Settings” ውሰጥ በ ግራ በኩል ከሚመጡት ምርጫዎች
“Security” የሚለውን ይመርጣሉ

4. ቀጥሎ ከሚመጡት ምርጫዎች “login alerts”🔔 የሚለውን “Edit” ይሉታል

5. “Text messages” ከሚለው ምርጫ ስር ቀደም ብለው ለ ፌስቡክ የሞባይል ቁጥሮን ሰጥተው ከሆነ/አካውንቱ በስልክ ቁጥር የተከፈተ ከሆነ
“text login alerts to ….” የሚለውን ሳጥን ማርክ በማድረግ “save changes” የሚለውን ክሊክ ያድርጉት፡፡ ቀደም ብለው ለ ፌስቡክ የሞባይል ቁጥሮን ያልሰጡ ከሆነ ግን “connect your phone number” የሚለውን ላይ በመግባት የሞባይል ቁጥሮን ያስገቡ ከዛም በሞባይሎ የሚላከውን ቁጥር በሚመጣው ሳጥን ውስጥ ያስገቡ (verify) ያድርጉ ከዛም “save changes” የሚለውን ክሊክ ያድርጉና ይውጡ አለቀ፡፡ ከአሁን በኋላ አካውንቶ በአዲስ "browser" በተከፈተ ቁጥር ሚሴጅ ይላክሎታል።👍
Join us @ElectronicsMntc
ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅ እና ማየት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች

1. የመሳሪያ ስርዓት (Operating system)
2 .የስክሪን መጠን (Screen Size)
3 .ሲፒዩ(CPU)
4. ራም(RAM)
5. የሃርድ ድራይቭ አይነት (Hard Drive Type)
6 .የምስል ጥራት (Image Quality)
7 .የባትሪ ቆይታ (Battery Life)
8. ብራንድ (Brand)
Core-i3 core-i5 core-i7 ምንድናቸው?

በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን በርከት ያሉ የላፕቶፕ እና
የኮምፒውተር ሱቆች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ለገቢያም የተለያዩ
የላፕቶፕ አይነቶች.በተለያየ ይዘት ይገኛሉ፡፡ እንዚህን
የተለያየ
ይዘት ያላቸውን የላፕቶፕ አይነቶች ለመግዛት በዋናነት መታየት
ያለበትን ከዚህ በታች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡

1. የመሳሪያ ስርዓት (platform) Windows, Mac and Linux
ለአጠቃቀም ምቹ እንደሆነ የሚነገርለት Windows የብዙ
ሰዎች ምርጫ ነው፡፡ቀላል፣ ምቹ እና ተለዋዋጭ ነው፤ በዋጋም ደረጃ ጥሩ የሚባል ነው፡፡
ማክ( Mac) የአፕል ድርጅት ምርት ሲሆን ለዲዛይን ተመራጭ
የሆነ ፕላትፎረም ነው፡፡ለደህንነትም ከWindows እንደሚሻል ይነገርለታል፡፡

2. የስክሪን መጠን ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ ወደ ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ
ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደየስክሪን መጠናቸው የተከፋፈሉ ናቸው፡፡
• 11 to 12 inches(27.94cm-30.48cm) ፡በጣም ቀጭን
እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡፡ ከ1.1ኪሎ እስከ1.5ኪሎ ይመዝናል፡፡
• 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ
የስክርን ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability
ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
• 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን ሳይዝ
ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ እንመክራለን ፡፡
• 17 to 18 inches (43.18cm- 45.72cm)፡
ላፕቶፖን ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ትልቅ የስክሪን ሳይዝ
ከፈለጉ ይህንን ይግዙ፡፡ ለጌመሮች እና ትልልቅ የሶፈተዌር ዲዛይን ለሚያደርጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ የላፕቶፕ አይነት ነው፡፡
3. ሲፒዩ(CPU)
የኮምፒዉተር አይምሮ በመባል የሚታወቀው ሲፒዩ(CPU),
ላፕቶፕ ለመግዛት ሁላችንም ማየት ያለብን ዝርዝር ነው፡፡
• AMD A series or Intel Core i3 / i5: በየቀኑ
ለምንጠቀማቸው ስራዎች የሚሆኑ የሲፒዩ አይነቶች ሲሆኑ
Core i5 ለሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት እና አነስተኛ የዲዛይን ስራዎችን
ለምሳሌ እንደ Photoshop, Archicad, AutoCadን
የመሳሰሉ በጥሩ ሁኔታ እንድንሰራ ይጠቅሙናል፡፡ በተጨማሪም
ግራፊክስ ካርድ ያለውና የሌለው በማለትም ይለያያሉ፡፡ ግራፊክስ
ካርድ ያለቸው የተሻለ የዲዛይን እና አኒሜሽን ስራዎችን
ያከናውኑልናል፡፡ በዋጋውም ተመጣጣኝ ነው፡፡
• Intel Core i7፡ በጣም አስደማሚ የጌም እና የዲዛይን
እንዲሁም ልዩ የሆኑ የኮምፒውተር ስራችን ለምሳሌ አንደ ሜትሮሎጂ፤ውስብስብ ስሌቶችን እንድንሰራ የሚረዳን
የላፐቶፕ አይነት ነው፡፡

4 .ራም(RAM): ለፍጥነት 4ጂቢ እና ከዛ በላይ የሆነ RAM
እንዲጠቀሙ እንመክሮታለን፡፡ ዋጋቸው አነስ ያሉ ላፕቶፖች
በ2ጂቢ ይመጣሉ፡፡ የዲዛይን ስራዎችን እና የሶፈትዌር
ዴቨሎፕመንት ስራዎችን ለመስራት 6ጂቢ ራም እና ከዚያ
በላይ ያለው ላፕቶፕ ቢገዙ ይመረጣል፡፡

5.የሃርድ ድራይቭ አይነት፡ ሁለት አይነት የሃርድ ድራይቭ አይነቶች ያሉ( HDDrive እና SSDrive) ሲሆን በሃገራችን ያልተለመደው SSDrive ከHDDrive የተሻለ የፍጥነት አቅም እና ድራይቩ ላይ ያለውን ዳታ በፍጥነት መድረስ እና
መገልበጥ (copy)ያስችለናል፡፡

6 .የምስል ጥራት፡ የተሻለ ጥራት የተሻለ ምስል እንድናገኝ
ይረዳናል፡፡ 1366 x 768 ጥሩ የሚባል የምስል ጥራት
ያለው ሲሆን ከዚህ የተሻለ ወጪ በማውጣት 1920 x 1080
የተሻለ ምስል ማግኘት እንችላለን፡፡Full HD 1080P በመባልም ይታወቃል፡፡

7 .የባትሪ ቆይታ፡ አብዛኛው ሃገር ውስጥ የሚገቡት የላፕቶፕ አይነቶች 4 ሰዓታት የሚቆዩ ሲሆን ከ6-8 ሰዓታትም የሚቆዩ ኦርጅናል ላፕቶፖች አሉ፡፡

8 . ብራንድ፡ የተላያዩ የላፕቶፕ ብራንዶጭ ባሉበት ገቢያ
የተኛውን መግዛት እንዳለብን አስቀድመን ማወቅ አለብን፡፡
Join us @ElectronicsMntc
1
የኮምፒዩተራቹ operating system window 10 ነው?

በምትከፍቱት እና በምትጠቀሙበት ሰአት እየተንቀራፈፈ አማሯችዋል? እንግዲያውስ ፍጥነቱን ሊጨምሩ የሚችሉ ነገሮችን እናያለን።

#1_Power_option
Start menu ላይ power option ብላቹ ፈልጉ ከሚመጣላቹ window ውስጥ high performance የሚለውን ምረጡ

#2_Disable_unwanted_start_up_programs
ይሄ ኮምፒዩተራችንን በምንከፍትበት ጊዜ ያለ እኛ ፍቃድ ፕሮግራሞችን እየከፈተ
ፍጥነቱን ከሚቀንሱ ነገሮች አንዱ ነው። ይሄን ለመከላከል Task manager ላይ መግባት (ይሄን ለማግኘት start menu ላይ right
click አድርጎ ማግኘት ይቻላል አልያም Ctrl Alt እና delete
የሚለውን አንድ ላይ መጫን)
ከሚመጣው window ውስጥ start up ላይ በማድረግ የማትፈልጉትን ፕሮግራሞች disable ማድረግ። እዚህ ጋር impact የሚለው high ከሆነ
disable ባታረጉ ይመረጣል።

#3_Defragment_and_optimize_drive
Start menu search bar ላይ defragment ብሎ መፈለግ Window ሲመጣላቹ የምትፈልጉትን driver መርጣቹ
optimize ማድረግ

#4_Delete_unnecessary_temporary_file
Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን
መምረጥ አልያም
window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን
%temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን
የሚመጣላቹ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን
ሁሉንም ሲመርጥልን
ማጥፋት
ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላቹ
folder ውስጥ
ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት
አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ
የሚመጣላቹ
folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት።
እነዚህን የምናጠፋበት ምክንያት ጊዜያዊ እና space የያዙ
ፋይሎች ስለሆኑ
ነው። ምንም አይነት ችግር አያመጡም።

#5_Clean_up_Memory
This pc ውስጥ ገብታቹ የምፈልጉት local ዲስክ ላይ right click በማድረግ property መምረጥ Disk clean up የምትለውን icon click ማድረግ የሚመጣውን የ warning box ok ማድረግ
እዚህ ጋ recycle bin ውስጥ ያሉ ፋይሎች ሳይቀሩ ነው የሚጠፉ ት

#6_Reduce_run_time_service
Run box ከፍታቹ msconfig ብሎ መጻፍ ቀጥሎ ከሚመጣው window service የሚለውን መጫን በመቀጠል hide all microsoft service የሚለውን tickvማድረግ
በመቀጠል disable የምትለዋን icon click ማድረግ

#7_Registry_tweaks
Run box መክፈት(window key + R) regedit ብሎ መጻፍ
Hkey -current user
Control panel Mouse
Mouse hover time
valueን ወደ 10 መቀየር
እዛው folder ላይ desktop መምረጥ Menu show delay
Valueን ወደ 10 መቀየር

#8_visual_effects
Start menu ላይ System ብሎ መፈለግ Advanced system setting መምረጥ
Advance ውስጥ በመግባት setting መምረጥ Adjust for best performance መምረጥ ቀጥሎ የምትፈልጉት ነገር ካለ ቲክ በማድረግ መምረጥ
በመጨረሻም ከላይ ያሉትን ከጨረስን በኋላ ኮምፒዩተራችንን
Restart ማድረግ::

Join us @ElectronicsMntc
1
RAM (Random Aaccess Memory)

ሲፒዩ መረጃን ለማብላላት በሚጠቀምበት ወቅት በስፋት
ከሚያገለግሉ ዋና ማስታወሻ አካል ወይም ሜሞሪ አንዱ
በምህፃረ ቃሉ RAM የምንለው ነው:: በኮምፒውተር ውስጥ
ሰፊውን ስፍራ የያዘው የመረጃ ማስታወሻ አካል RAM ወይም
RAM ቺፕስ እንለዋለን:: ራንደም አክሰስ የምንለው ቃል የተጠቀምንበት ዋናው ምክንያት በሜሞሪ አካል ላይ የኤሌክትሪክ ሀይል እስካለ ድረስ በላዩ ላይ የተፃፈውን መረጃ ለማንበብም ሆነ ለማስተካከል የሚፈቅድ በመሆኑ ነው:: በራም ውስጥ የሚገኘው ማንኛውም መረጃ መቆየት የሚችለው ኮምፒውተሩ የኤሌክትሪክ ሀይል እስካገኘ ጊዜ ብቻ ነው::
በሌላው አነጋገር የኤሌክትሪክ ሀይል በጠፋ ወቅት በራም ላይ
የሚገኙ መረጃዎች በሙሉ ይጠፋሉ::
በምሳሌ ለመግለፅ እንዲመቸን ራም ማስታወሻን ከጥቁር ሰሌዳ
ጋር ልናነፃፅረው እንችላለን:: በጥቁር ሰሌዳ በመጠቀም
በተደጋጋሚ አጥፍተን የፈለግነውን መረጃ ሀሳብ ልንፅፍበት
እንችላለን::
ኮምፒውተሩ የሚፈልገውን መረጃ አንብቦ ስራውን መቀጠል
በሚፈልግበት ወቅት የተፈለገውን መረጃ በየትኛውም የማስታወሻ አድራሻ ላይ እንደተፃፈ ከሚያነበው የመረጃ አይነት
ፈልጎ ሊያገኘው ይችላል:: ከሲፒዩ ወደ ራም የሚላከውም አድራሻ ቀጭን የኤሌክትሪክ መስመር #አድሬስ_ባስ (Address bus) እንለዋለን:: ከራም የተገኘው መረጃ መልሶ ወደ ሲፒዩ ለተጨማሪ ስራ መሄድ ካስፈለገው በሌላ የኤሌክትሪክ መስመር ዳታ ባስ ይመለሳል:: በሲፒዩ ውስጥ
መረጃ ለማስተላለፍ የምንጠቀመው የመረጃ መስመር "DATA PATH" እንለዋለን::
የራም ማስታወሻን ለመዘርጋት የሚያገለግሉን መስመሮች
በሁለት ዋና ክፍሎች እንከፍላቸውለን:: እነዚህም:-

1. #Dynamic_RAM (ተቀያያሪ ራም)
2. #Static_RAM (የማይቀያየር ራም) እንላቸዋለን::
Join us @ElectronicsMntc
#ስልኮዎ_በቫይረስ_መጠቃቱን_እንዴ_ማወቅ_ይችላሉ_?➡️
How to Know if your android phone is infected by virus or malware?
በተለይ ቁጥር 6. ጠቃሚ ምልክት ነው!
ስልኮዎንስ ከቫይረስ እንዴት ነጻ ማድረግ እንደሚችሉ
ስልኮዎ በቫይረስ መጠቃቱን እንዴት ማወቅ ይችላሉ ?

1፡በስልኮዎ ውሰጥ ያሉ
ፐሮግራሞቸ አልከፍት ይላሉ::

2፡በሚሞሪ ካርድዎ እና በስልክዎ ውስጥ ያሉ የራስዎ ፋይሎች ራሳቸውን ይቀይራሉ በተለይ ደግሞ በቫይረስ የተጠቃው ስልክዎ ከሆነ ፋይሎችን አልያ ሶፍትዌሮችን ለመክፈት ሲሞክሩ application not supported or file
dasn’t exist የሚል ሜሴጅ ሊመጣ ይችላል::

3፡የስልክዎ የባትሪ ጉልበት በጣም እየደከመ ይመጣል ይሀ ምልክት ግነ በኖርማል ስልኮች ላይም ሊስተዋል ይችላል ያ የሚሆነው ደግሞ የሚጠቀሙት
ባትሪ ኦርጅናል ባለመሆኑና በሌሎችም ችግሮች ሊሆን ይችላል
ለምሳሌ የስልክዎ ባትሪ ኮኔክተር ችግር ካለበት ባትሪዎን ቶሎ ቶሎ ይጨርስቦታል::

4:ምናልባት ስልክ ደውለው እያናገሩ እያለ አልያ ደግሞ ገና እየደወሉ እያለ ስልክዎ ይቋረጣል:: ይህም ሌላ ምክነያትሊኖረው ይችላል ለምሳሌ የስልክዎ
ስክሪን ችግር ካለበትና ስልክዎ ባጋጣሚ የሚጠፋ ከሆነ፣የባትሪዎ ችግርም ሊሆን ይችላል::

5: በስልክዎ ላይ በጫኑት አፕልኬሽን እየተጠቀሙ እያሉ ፕሮግራሙ በራሱ ጊዜ
ሊዘጋቦ ይችላል::

6: እንደ አጠቃላይ ልናየው የምንችለው ደግሞ የስልክዎ ነገራቶችን በፍጥነት የመከወን ብቃት እጅጉን ይቀንሳል ተሰላችተ እስከመወርወር ድረስ ሊያናድድዎም ይችላል
#ስለምለክቶቹ ይህን ያክል ካልን እንዴት መከላከል እንዳለብንና እንዴትስ ሁነቱ ከተከሰተ በኋላ ማስወገድ እንደምንችል አንዳንድ ነገራቶችን እንጥቀስ ብርቱ ቴክ

1፡ ኢንተርኔት እየተጠቀሙ እያለ ከሆነ ክስተቱ የተፈጠረው ስልክዎን ወዲያውኑ
አጥፍተው ያብሩት/ ያስነሱት ይህን ማድረግዎ ኦንላይን የተለቀቁ ቫይረሶች በስልክዎ ላይ ለውጥ ማምጣት እንዳይችሉ ይረዳወ ዘንድ ነው::

2:የተጠራጠሩትን ፕሮግራም ከሞባይልዎ ሾርትከት ላይ ለማጥፋት ይሞክሩ
ይህ አልሆን ካለ

3:ከስልክዎ ውሰጥ setting የሚለውን በተን ተጭነው app የሚለውን ጠቅ
ሲያደርጉ ብዙ ፕሮግራሞች ይታያሉ ከነኛ መካከልእርስዎ የተጠራጠሩትን
ያጥፉት select and then press uninstall

4: ከ setting ሳይወጡ ወደሆላ በመመለስ security የሚለውን ይምረጡ
ከዚክ ጋ device adminstartore የሚለውን ይጫኑትና በ ቼክ ቦክስ
cheekbox ቲክ የተደረጉትን በሙሉ አጥፍተው ስልክዎን ሪስታርት ያድርጉት
ምናልባት ስልክዎ ቫይረስ ከሌለው ይህኛው አማራጭ በ ቼክ ቦክስ cheekbox ቲክ የተደረጉነ ፕሮግራሞችን ላያመጣ ይችላል::

5.ስልኮን አጥፍተው የድምፅ መቀነሻው ይጫኑና እሲከበራ አይልቀቁ በዚህን ጊዜ ስልኮ ሴፍ ሞድ የሚል ፅሁፍ ያመጣልናል: ይህ የሚጠቅመን አልጠፋም
ያሉ የቫይረስ አፕሊኬሽኖችን ከሴቲንግ መተግበሪያ ውስጥ በቀላሉ ለማጥፋት ነው::
Join us @ElectronicsMntc
#የአንድሮይድ_ስማርት_ስልኮች የዕለት ተዕለት ግንኙነታችንን
የምናከናውንባቸው አለፍ ሲልም ለመዝናኛና ሌሎች ዘርፈ ብዙ
ግልጋሎቶች የምንጠቀምባቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች ናቸው።
ለዛሬ ለእነዚ አገልግሎት የሚጠቅሙ እና ኮሚኒኬሽናችን ቀልጣፍ
የሚያደርጉ አፕሊኬሽኖች ውስጥ ለእናንተ ጠቃሚ ይሆናሉ ያልናቸውን ይዘንላችሁ ቀርበናል።

1. #SHAREit
SHAREit በአንድሮይድ ስልኮቻችን ዳታ ለመላላክ የሚያገለግለን
አፕሊኬሽን ሲሆን ትላልቅ መጠን ያላቸውን ፋይሎችን (ቪድዮዎች፣
ፎቶዎች...) በፍጥነት ያስተላልፍልናል።
የዚህ አፕሊኬሽን ዋነኛ ጥቅሙ እና ከሌሎች ዳታ ማስተላለፊያ
አፕሊኬሽኖች ያለምንም ኬብል ከኮምፒውተራችን ጋር ለመገናኘት እና
ፍይሎችን ለማስተላለፍ ማስቻሉ ነው። ይህ አፕ ካለዎት ፍይል
ከኮምፒውተርዎ ወይም ወደ ኮምፒውተርዎ ለመላክ ኬብል ፍለጋ
ይገላግሎታል።

2. #DiskDigger
DiskDigger ከስልካችን በስህተት ያጠፋናቸውን ፎቶዎች፣ ሙዚቃዎች፣
ቪዲዮዎችና ሌሎች ፋይሎቻችንን የስልኩን ጥልቅ ዳታ ስቶሬጅ በማሰስ
ይመልስልናል። በጣም አስፈላጊ ፍይሎቻችንን በስህተት ወይም በሌላ
ሰው delete ከተደረጉብን DiskDigger አፕ መፍትሄያችን ይሆናል ማለት
ነው።

3. #IDM download manager
በኮምፒውተራችን ፋይሎችን በፍጥነት ዳውንሎድ ለማድረግ
የምንጠቀምበት IDM, በቅርቡ ደግሞ ለአንድሮይድ ስልኮች የሚያገለግል
አፕ ለቋል። IDM የስልካችን ብሮውዘር ዳውንሎድ ለማድረግ
የሚወስድበትን ጊዜ በእጅጉ በመቀነስ የምንፈልገውን ፍይል በአጭር ጊዜ
ያወርድልናል።

4. #Whistle_phone_finder
ለመሆኑ ቤት ውስጥ ወይም ስራ ቦታ ስልክዎን ያስቀመጡበት ቦታ
ጠፍቶዎት ያውቃል? የሚያውቅ ከሆነ ፍለጋውንና ከሌሎች ስልክ ተውሶ
ወደራስ ስልክ ለመደወል የሚደረገውን ድካም በደንብ ያውቁታል። ይሄንን
አፕሊኬሽን ስልክዎት ላይ አስቀድመው ከጫኑ, ስልክዎን ያስቀመጡበት
ቦታ ሲጠፋዎት ከእርስዎ የሚጠበቀው ማፏጨት ብቻ ነው። የፉጨትዎ
ድምጽ አፕሊኬሽኑን በማንቃት ስልክዎ የመጥሪያ ደወል እንዲያሰማ
በማድረግ ስልኩን በቀላሉ በድምጹ ተመርተው እንዲያገኙት ይረዳዎታል።

5. #WiFi_Map
በሆቴሎች ወይም በሌሎች ስፍራዎች የምናገኛቸው አብዛኞቹ ዋይ ፋይ
ኔትወርኮች በይለፍ ቃል (password) የተዘጉ ናቸው። ይህም ማለት
የዋይ ፋዩ ፓስወርድ ከሌለን ዋይ ፋዩን ለመጠቀም አንችልም ማለት ነው።
ይህ አፕሊኬሽን በአለማችን የሚገኙትን በሆ ፋዮች ሁሉንም በሚባል
መልኩ ፓስወርዳቸውን በቀላሉ ይነግረናል። ከእኛ የሚጠበው አፑን
ከጫንን በኋላ ከሚመጣልን የአለም ከርታ ላይ ኢትዮጵያን፤ ከዚያም
የምንፈልገውን ከተማ መምረጥ ሲሆን በከተማው ውስጥ ያሉትን ዋይ ፋይ
ኔትወርኮችና ፓስወርዳቸውን ያመጣልናል። ዋይ ፋይ ኔትወርክ
በአቅራቢያችሁ ኖሮ ፓስወርድ ለገደባችሁ ሁሉ ቀላል መፍትሄ ነው።

6. #Battery_doctor
የስማርት ፎኖች ቀዳሚ ችግር ተብሎ የሚጠቀሰው የባትሪ ቆይታቸው
አጭር መሆን ሲሆን ሁሉም በሚባል መልኩ ለሚያከናውኑት እያንዳንዱ
የሚታይና የማይታይ ስራ ከፍተኛ የሆነ የባትሪ ሃይል ይጠይቃሉ። ይህ አፕ
አላስፈላጊ የሆኑ ፕሮሰሶችንና ሰርቪሶችን በማስቆም ባትሪያችንን ለረጅም
ጊዜ እንድንጠቀምበት ይረዳናል። ከዚህም በተጨማሪ የስልኩን ራም ነጻ
በማድረግ ፈጣን ስልክን ይፈጥርልናል።

7. #Avast_anti_virus
በኮምፒውተር ደህንነት ጥሩ ዝና ያለው አቫስት አንቲ ቫይረስ ስልካችንን
ከቫይረስ፣ ማል ዌር እና ትሮጃኖች በመከላከል ረገድ የተዋጣለት አፕ
ለተጠቃሚዎች እነሆ ብሏል። በዚህም ከስልካችን ቀርፋፋነት እስከ ሙሉ
የኦፕሬቲንግ ሲስተም ብልሽት የሚያደርሱ የአንድሮይድ ቫይረሶችን
አስቀድሞ በመከላከል ስልካችንን ከችግር ይጠብቅልናል።

8. #Titanium_backup
አይበለውና ስልካችን በስህተት ወይንም ፈልገነው factory reset ቢሆን
ወይንም በሌላ የስልኩ ችግር ምክንያት የጫንናቸው አፕሊኬሽኖች፣
መልዕክቶቻችን እና ሴቭ ያደረግናቸው ሰዎች ዳታ ቢጠፋ ምን ያደርጋሉ?
Titanium backup ለዚህ መፍትሔ የሚሆን አፕ ሲሆን ሙሉ ስልካችንን
የራሱ የስልኩን አፕሊኬሽኖችና በሚደንቅ ሁኔታ ራሱን አንድሮይዱን
ጭምር backup የሚያደርግ አስገራሚ አፕ ነው። አንድ ጊዜ backup
ከያዝን በኋላ backup ፋይሉን ኮምፕዩተር ላይ ለማስቀመጥ በሚያስችል
መልኩ አዘጋጅቶ ያስቀምጥልናል በዚህም ስልኩ የሆነ ችግር ቢያጋጥመው
እንኴን ፋይሉ ኮምፒዩተራችን ላይ ስላለ ያለምንም ስጋት ስልካችንን
ወደነበረበት ለመመለስ እንችላለን ማለት ነው።

9. #Amharic_dictionary
ይህ በኢትዮጵያውያን የተሰራ አፕ የእንግሊዝኛ ቃላትን የአማርኛ ትርጉም
በቀላሉ ያቀርብልናል(ሜሪት ዲክሺነሪን በኪሳችን ማለት ነው)። ከዚህም
በተጨማሪ የአንዳንድ የአማርኛ ቃላትን የእንግሊዝኛ ፍቺ ለማወቅ
ከፈለግን በመፈለጊያ ሳጥኑ ውስጥ የአማርኛውን ቃል ማስገባት ብቻ ነው
አፑ የቃሉን የእንግሊዝኛ አቻ ፍቺ ያቀርብልናል። ለሰራተኞች በተለይም
ለተማሪዎችጠቃሚ አፕ ነው።

10. #Agerigna አገርኛ
ይህ አፕ ለአንድሮይድ ስማርት ፎን ተጠቃሚ ኢትዮጵያውያንናኤርትራውያን
የተዘጋጀ የግዕዝ ፊደላትን በቀላሉ ለመጻፍ የሚያስችል ኪ ቦርድ አፕ ነው።
የግዕዝ ፊደላትን በፍጥነትና በቀላሉ ለማጻፍ ከማስቻሉ የተነሳ በስልካችን
አማርኛን ለመጻፍ በብዙዎች ዘንድ ተመራጭ አፕ ለመሆን ችሏል።
===================
CLICK IT

@ElectronicsMntc
@ElectronicsMntc

💻 ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ እንዴት እንደሚፃፍ ያውቃሉ?ሲጽፉስ ምን ያህል ይፈጥናሉ?


❖መጀመሪያ Ge'ez 10 Software ያወረዱ እና install ያድርጉት ከዛም አማርኛ መፃፍ ስትፈልጉ power ge'ez status phonetic Unicode Mode (ፎ) ላይ ያድርጉት በ English መፃፍ ስትፈልጉ ደግሞ power ge'ez status English Mode (ኢ) ላይ አድርጉት ከዛም የሚከተሉትን ኣጭር መግላጫ በትክክል ይመልከቱ
@ElectronicsMntc

◕ሀ➭H_ሁ➭Hu_ሂ➭Hi_ሃ➭Ha_ሄ➭Hy_ህ➭He_ሆ➭Ho

◕ለ➭L_ሉ➭Lu_ሊ➭Li_ላ➭La_ሌ➭Ly_ል➭Le_ሎ➭Lo

❖ሐ➭Shift+h_ሑ➭Shift+hu_ሒ➭Shift+hi_ሓ➭Shift+ha_ሔ➭Shift+hy_ሕ➭Shift+he_ሖ➭Shift+ho

መ➭M_ሙ➭Mu_ሚ➭Mi_ማ➭Ma_ሜ➭My_ም➭Me_ሞ➭Mo

❖ሠ➭Shift+s_ሡ➭Shift+su_ሢ➭Shift+si_ሣ➭Shift+sa_ሤ➭Shift+sy_ሥ➭Shift+se_ሦ➭Shift+so

◕ረ➭R_ሩ➭Ru_ሪ➭Ri_ራ➭Ra_ሬ➭Ry_ር➭Re_ሮ➭Ro

◕ሰ➭S_ሱ➭Su_ሲ➭Si_ሳ➭Sa_ሴ➭Sy_ስ➭Se_ሶ➭So

❖ሸ➭Shift+s_ሹ➭Shift+su_ሺ➭Shift+si_ሻ➭Shift+sa_ሼ➭Shift+sy_ሽ➭Shift+se ሾ➭Shift+so

◕ቀ፡➭Q ቁ፡➭Qu ቂ፡➭Qi ቃ፡➭Qa ቄ፡➭Qy ቅ፡➭Qe ቆ፡➭Qo

◕በ፡➭B ቡ፡➭Bu ቢ፡➭Bi ባ፡➭Ba ቤ፡➭By ብ፡➭Be ቦ፡➭Bo

◕ተ፡➭T ቱ፡➭Tu ቲ፡➭Ti ታ፡➭Ta ቴ፡➭Ty ት፡➭Te ቶ፡➭To

◕ ቸ፡➭C ቹ፡➭Cu ቺ፡➭Ci ቻ፡➭Ca ቼ፡➭Cy ች፡➭Ce ቾ፡➭Co

◕ነ፡➭N ኑ፡➭Nu ኒ፡➭Ni ና፡➭Na ኔ፡➭Ny ን፡➭Ne ኖ፡➭No

❏ኘ፡➭Shift +n ኙ፡➭Shift +nu ኚ➭Shift+ni ኛ፡➭Shift +na ኜ፡➭Shift +ny ኝ፡➭Shift + ne ኞ፡➭Shift +no

◕ከ፡➭Ka ኩ፡➭Ku ኪ፡➭Ki ካ፡➭Ka ኬ፡➭Ky ክ፡➭Ke ኮ፡➭Ko

❖ ኸ ☛capslock + Shift + h
ኹ ☛capslock + Shift + hu
ኺ ☛capslock + Shift + hi
ኻ ☛Capslock + Shift + ha
ኼ ☛Capslock + Shift + hy
ኽ ☛Capslock + Shift + he
ኾ ☛Capslock + Shift + ho

❏ኀ፡➭ Capslock + H ኁ፡➭ Capslock + HU ኂ፡➭Capslock + HI ኃ፡➭Capslock + HA ኄ፡➭Capslock + HY ኅ፡➭Capslock + HE ኆ፡➭Capslock + HO

❏አ፡➭Capslock X ኡ፡➭Xu ኢ፡➭Xi ኣ፡➭Xa ኤ፡➭Xy እ፡➭Xe ኦ፡➭XoDe

❖ዐ፡➭Shift +x ዑ፡➭Shift +xu ዒ➭Shift +xi ዓ፡➭Shift +xa ዔ➭Shift +xy ዕ፡➭Shift +xe ዖ➭Shift +xo

✪ወ፡➭W ዉ፡➭Wu ዊ፡➭Wi ዋ፡➭Wa ዌ፡➭Wy ው፡➭We ዎ፡➭wo

✪ዘ፡➭Z ዙ፡➭Zu ዚ፡➭Zi ዛ፡➭Za ዜ፡➭Zy ዝ፡➭Ze ዞ፡➭Zo

❏ዠ፡➭Shift + Z ዡ፡➭Shift + Zu ዢ፡➭Shift + Zi ዣ፡➭Shift +Zaዤ፡➭Shift + Zy ዥ፡➭Shift +Ze ዦ፡➭Shift + Zo

✪ፈ፡➭F ፉ➭Fu ፊ፡➭Fi ፋ፡➭Fa ፌ፡➭Fy ፍ፡➭Fe ፎ፡➭Fo

✪ ፐ፡➭P ፑ፡➭Pu ፒ፡➭Pi ፓ፡➭Pa ፔ፡➭Py ፕ፡➭Pe ፖ፡➭Po

✪ገ፡➭G ጉ፡➭Gu ጊ፡➭Gi ጋ፡➭Ga ጌ፡➭Gy ግ፡➭Ge ጎ፡➭Go

✪ደ፡➭D ዱ፡➭Du ዲ፡➭Di ዳ፡➭Da ዴ፡➭Dy ድ፡➭ዶ፡Do

❏ጠ፡➭Shift + t ጡ፡➭Shift + tu ጢ፡➭Shift + ti ጣ፡➭Shift+ta ጤ፡➭Shift + ty ጥ፡➭Shift + te ጦ፡➭Shift + to

❏ጨ፡➭Shift +c ጩ፡➭Shift +cu ጪ፡➭Shift +ci ጫ፡➭Shift+caጬ፡➭Shift +cy ጭ፡➭Shift +ce ጮ: ➭Shift +co

❏ጸ፡➭Capslock + t ጹ፡➭Capslock + tu ጺ፡➭Capslock + ti ጻ፡➭Capslock + ta ጼ፡➭Capslock + ty ጽ፡➭Capslock + t ጾ፡➭Capslock + to

❖ ፀ➭☞Capslock+Shift+t
ፁ➭☞Capslock+Shift+tu
ፂ➭☞Capslock + Shift + ti
ፃ➭☞Capslock + Shift + t
ፄ➭☞Capslock + Shift + ty
ፅ➭☞Capslock + Shift + te
ፆ➭☞Capslock + Shift + to

✪ጀ፡➭J ጁ፡➭Gu ጂ፡➭Ji ጃ፡➭Ga ጄ፡➭Gy ጅ፡➭Ge ጆ፡➭Jo

✪ቨ፡➭V ቩ፡➭Vu ቪ፡➭Vi ቫ፡➭Va ቬ፡➭Vy ቭ፡➭Ve ቮ፡➭Vo
▁▁▁▁▁▁▁▁▁▁

ቋ➭Capslock+qwa ቧ➭Capslock+bwa
ቷ➭Capslock+twa
ኟ➭Capslock +Shift+nwa
ቿ➭Capslock+cwa ሟ➭Capslock+mwa
ቷ➭Capslock+twa ጓ➭Capslock gwa
ፏ➭Capslock+fwa ሯ➭Capslock +rwa ዷ➭Capslock+dwa ቯ➭Capslock+vwa ኋ➭Capslock+hwa ዟ➭Capslock+zwa ዧ➭Capslock+Shif+zwa
ኗ➭Capslock+nwa ሏ➭Capslock+lwa
ኳ➭Capslock+kwa ሷ➭Capslock+swa
ጇ➭Capslock+jwa ጧ➭Capslock+twa

ለሌሎች እንዲደርሳቸው #FORWARD ያድርጉ
@ElectronicsMntc
DriverPack Solution Online (drp online) is a program that automates the process of installing hardware drivers. No longer do you have to deal with any more problems regarding searching for the rig ht drivers and then installing them as this software will allow you to install all the required drivers on any Windows-based computer (from XP onwards) with just a few clicks of the mouse. It also supports 64 bit systems. The program is designed to be used by anyone from home users to system administrators, offering you an easy, quick and efficient way of installing the correct drivers for the devices attached to your computer and then keeping them up to date.

This software also has the widest range of support, covering all sorts of devices including USB devices, PCI, ACPI, PNP and much more. When you start using the software, the driver installation process will be fully automated, and since it already contains a comprehensive database of drivers, you don't even need to be connected to the Internet at the time. Drp online contain 1,131,989 manually selected and tested drivers!

Join us on @ElectronicsMntc
Wondershare Filmora is an simple video editor that ignites your stories, makes it fun to transform precious moments into stunning videos for sharing anywhere. use Filmora video editor to express your creativity and amaze with beautiful results. A modern and intuitive design that you'll be delighted to use again and again.

Installation Guide

1. Download and extract the file.
2. Disable the connection to the internet and install the software.
3. Run (Block-Hosts.bat) file as an Administrator.
4. Open the (Keygen.exe) file and click on generate then use the generated serial code to activate the software.
5. Exit software and restart your computer.


Wondershare Website
_
System Requirements :

-Supported OS: Windows 7/Windows 8.1/Windows 10 (64 bit OS)
- Processor: Intel i3 or better multicore processor, 2GHz or above.
- (Intel 6th Gen or newer CPU recommended for HD and 4K Videos)
- RAM: 4 GB RAM (8GB required for HD and 4K videos)
- 2 GB vRAM (4GB required for HD and 4K videos)
- Graphics: Intel HD Graphics 5000 or later; NVIDIA GeForce GTX 700 or later; AMD Radeon R5 or later
- Disk: At least 10GB free hard-disk space for installation (SSD-Solid State Disk recommended for editing HD and 4K videos)

Join us on @ElectronicsMntc