COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE
7.1K subscribers
71 photos
7 videos
53 files
103 links
Welcome To Computer & Mobile Maintenance Channel.
It Gives You Some Hints To Repair(Improve Performance Of) Your Computer & Mobile By Yourself. ለጠጋኞችም የሚጠቅም ምርጥ ቻናል ነው!
JOIN @Computer_Mobile21
Contact @seen311 or @seen3bot

Group👉 @Computer_Mobile3
Download Telegram
#mobile_security

#Android_ስልኮቻችን ለጥቃት እንዳይጋለጡ የሚያግዙ
አማራጭ ነጥቦች:

1. የስማርት ስልኮችን ሲገዙ ለስልኩ #ክፍተት_መሙያዎችን
( patches) በየወቅቱ ከሚያቀርቡ ተቋማት ቢሆኑ ይመረጣል:

2. ስልኩን #መቆለፍ( Lock your phone) ፡ ሆኖም የስልኩን ምስጢር ቁጥር
( PIN) 1234 የመሳሰሉ ቀላል የምስጢር ቁጥሮችን አለመጠቀም:

3. የሁለት ወገን የባለቤትንት ማረጋገጫ መጠቀም( two-factor
authentication)

4. ለስልኮቻችን የምንጠቀማቸውን አፕሊኬሽኖች ከጉግል ፕሌይ
ስቶር( Google Play Store) ማውረድ

5. ስልኩን #መመስጠር( Use device encryption) ይህን
ለመከወንም፡- Settings > Security > Encrypt Device
የሚለው በመግባት የሚጠይቀውን በመሙላት መመስጠር:

6. የቨርቿል ፕራይቬት ኔትዎርክ(VPN) መጠቀም: በይበልጥ
የህዝብ የዋይፋይ በምንጠቀምበት ጊዜ ወሳኝ ነው::

7. #የይለፍ ቃል አስተዳደሮችን መፈተሸ፡- ይህም አንድ አይነት የይለፍ ቃሎችን ለተለያዩ አካውንቶች ከመጠቀም መቆጠብ ፣ልናስታውሳቸው የምንቸላቸው የይለፍ ቃሎችን መጠቀም እና የይለፍ ቃሎቹ በቀላሉ የማይገመቱ መሆናቸውን ማረጋገጥ:

8. #ጸረ-ቫይረስ ሶፍትዌሮችን መጠቀም:

9. የኔትወርክ ግንኙነቶችን በማንፈልግበት ጊዜ ግንኙነቱን ማጥፋት( Turn off connections)

10. በስልኮቻችን ውስጥ ያሉ እና #የማንጠቀምባቸውን አፕሊኬሽኖች ማስወገድ ወይም አለመተግበር(uninstall)

@seen311
@computer_mobile_maintenanc_ethio

Read more👇👇👇👇👇👇
https://googleweblight.com/i?u=https://www.lifehack.org/articles/technology/how-protect-your-privacy-your-mobile-devices.html&hl=en-ET
👍1
MOBILE maintenance TVT p30.pdf
1.7 MB
Contents #mobile
📱Components
📱Repairing tools
📱IC types
📱Hardware
📱Software problems With solutions
☝️the pdf is in AMHARIC

@seen311
@computer_mobile_maintenanc_ethio
#Hard_Disk_Bad_symptoms

💽Hard Disk ችግር ከገጠመው ምን ምን ምልክቶችን ያሳያል?

የኮምፒውተራችን #ሃርድ_ዲስክ_ሲበላሽ ብዙ መረጃዎችን ልናጣ እንችላለን: በዚህም ምክንያት ልንበሳጭ እንችላለን:: ስለዚህ ሃርድ ዲስኩ መረጃዎችን ከማጥፋቱ በፊት በሚያሳያቸው ምልክቶች ተጠቅመን መረጃችንን ሌላ ቦታ ማስቀመጥ መልካም ነው።


1. ኮምፒዩተራችሁ #የመዝገም (slow) የማለት ባህሪ ሲያጋጥም

2. #ሰማያዊ_ነጭ ቀለም ያለው ፊደላትን ሲታይ

3. በተደጋጋሚ #መቆም (stuck) ሲጀምር

4. የተለያዩ #ችግሮችን (errors)ማሳየት ሲጀምር

5. ኮምፒዩተሩ #ጠፍቶ_ሲበራ የተለያዩት ችግሮች ካሉት

6.የተለያዩ ሶፍትዌሮች #ክራሽ ሲያደረጉ

7. #አላስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ሲያወጣ
ለምሳሌ፦ ፕሪንት ሊደረግ ሲል የተለየ ነገር የሚያወጣ ከሆነ

8. መረጃዎችን በራሱ ጊዜ #ሲያጠፋ(corrupt)

9. አንድን መረጃ(file) ለመክፈት #ብዙ_ቆይታ ካለው

10. የተለያዩ አላስፈላጊ የሆኑ #ድምጽ ከኮምፒዩተሩ ሲወጣ

🖥ኮምፒዩተሩ ይህንን ሁሉ ምልክት የሚያሳይ ከሆነ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሃርድ ዲስክ ሊበላሽ ይችላል ማለት ነው::

ሰለዚህ ይህ ብልሽት ችግር እንዳያስከትል መፍትሔ መውሰድ የተመረጠ ነው። ለምሳሌ:

S.M.A.R.T (Self-Monitoring, Analysis and Reporting Technology) የተባለን ሶፍትዌር በማውረድ ብልሽቱ ከመፈጠሩ በፊት በማስታወስ ኮምፒዩተሩ ላይ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉ ፍንጮችን ያሳውቃል።

ኮምፒዩተሩ ውስጥ ያሉትን ፋይሎች በየጊዜው ሌላ ኮፒ (Buckup) በማስቀመጥ መጠንቀቅ እና ሊጠፉ የሚችሉ ፋይሎችን መታደግ እንችላለን።

@seen311
@computer_mobile_maintenanc_ethio

Read more 👇👇👇👇👇
https://www.google.com/amp/s/m.wikihow.com/Tell-if-a-Hard-Drive-Is-Bad%3Famp=1
#mobile_Originality

#ሳምሰንግ_ስልክ_ኦርጅናል_ወይም_ኮፒ
መሆኑን እንዴት መለየት እንችላለን ?
ከሌሎች ይበልጥ ሳምሰንግ ስልኮች ተፈላጊነታቸዉ እየጨመረ
በመጣ ቁጥር፣ ከኦርጂናሉ ጋር ተመሳስለዉ በቻይና የሚመረቱ #ኮፒ_ሳምሰንግ ስልኮችም በዚያዉ መጠን ይጨምራሉ፡፡
ሳምሰንግ የጉግልን #አንድሮይድ_ኦፐሬቲንግ_ስርዓት ይጠቃማል፣የአንድሮይድ ስርዓት ኮድ ደግሞ ማንኛዉም ፍላጎት ያለዉ አካል ኮዱን እንዲጠቀም የሚያስችል ፍቃድ ስለሚሰጥ፣ አጭበርባሪ ድርጅቶች #ከኦርጂናሉ_ስልክ ከፍተኛ ቅናሽ ያለዉን ተመሳሳይ ኮፒ ሳምሰንግ ስልክ በማምረት ገበያዉን ያጥለቀልቁታል፡፡

ኦርጂናሉን ስልክ ከፌኩ በቀላሉ መለየት ያስቸግራል፣ ነገር ግን
ከታች የተዘረዘሩትን መንገዶች በመጠቀም ፌክ ሳምሰንግ ስልኮችን መለየት ይችላሉ።

የስልኩን ቀፎ አካላዊ ገጽታዎች በመገምገም

#ኮፒ_ሳምሰንግ ስልክ፡
1) የስክሪኑ መስታወት ጥራት የለዉም
2) ስክሪኑ ከቀፎዉ ጠርዝ በጣም ይርቃል
3) ስክሪኑ ድምቀት ይጎድለዋል
4) የሳምሰንግ ሎጎ (ሳምሰንግ የሚለዉ ጽሁፍ) ሲነካ
ይሻክራል፣ በደንብ ከተጫኑት ይለቃል
5) ከኦርጂናል ስልኮች ጋር ሲያስተያዩት፤ የባትሪ መክደኛዉን
ሲከፍቱ የሚታዩ ትንንሽ አካሎች እና ባትሪዉ ላይ የሚገኙት መረጃዎች የተለያዩ መሆናቸዉን ይመለከታሉ፡፡

የስልኩን #ፍጥነት_እና_የትእዛዞች_አፈጻፀም በመገምገም
1) በስልኩ ፎቶዎችን ለማንሳት ይሞክሩ፣ በፌክ ሳምሰንግ
ስልኮች የሚያነሱት ፎቶ ጥራት የወረደ ይሆናል
2) በተመሳሳይ ጊዜ በርካታ ጌሞች እና አፕሊኬሽኖችን
ለመክፈት ይሞክሩ፣ ፌክ ስልኮች ቀጥ(stuck)የማለት ባህሪይ
ያሳያሉ፡፡
3) ስልኩን አጥፍተዉ ያብሩት፣ ፌክ ስልኮች ቶሎ አይከፍቱም::

የስልኩን #የምርት_መረጃዎች በመገምገም
1) ከአፕሊኬሽን ማዉጫዉ ላይ፣ #Settings የሚለዉን ይጫኑ
2) ከ Settings ላይ More የሚለዉን ይጫኑ እና #Storage
የሚለዉን በመጫን ስልኩ ላይ መያዝ ሚችሉትን የዳታ መጠን ይመልከቱ፤ #ከኦርጂናሎቹ ስልኮች በጣም ያነሰ ከሆነ ፌክ ነው ማለት ነው፡፡
3) እንዲሁም About device የሚለዉን ይጫኑ እና
የስልኩን ሞዴል ቁጥር እና baseband, build number
ጉግል ላይ ይፈልጉት፣ የሚያገኙት መልስ ፌክ ወይም #ኦርጅናል
መሆኑን ይነግሮታል፡፡

የሳምሰንግ #ኮዶችን በመጠቀም
ወደ ስልክ መደወያዉ በመሄድ፣ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ኮዶች
ያስገቡ እና Call የሚለዉን ይጫኑ፤ ስልኩ ያስገቡትን ኮድ አዉቆ መልስ መስጠት ከቻለ ኦርጅናል ነው፡፡ ካልሆነ ግን ፌክ ስልክ ነዉ፡፡
1) *#0*# አጠቃላይ መገምገሚያ
2) *#1234# or *#9999# ስልኩ የሚጠቀመዉን ሶፍትዌር እና ሞደም ማወቂያ
3) *#12580*369# ስለ ስልኩ ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ማወቂያ
4) *#06# የስልኩን ኢንተርናሽናል መለያ ቁጥር(IMEI)
5) *#9998*246# የስልኩን የባትሪ እና ሚሞሪ መረጃዎች
ማወቂያ

ሳምሰንግ ኪይስ(Samsung Kies) ሶፍትዌርን በመጠቀም
ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች ፌክ ሳምሰንግ ስልክን መለየት ካልቻሉ
ይህን ሶፍትዌር ይጠቀሙት፡፡
1) Samsung Kies ሶፍትዌርን ኮምፒዉተሮት ላይ ይጫኑት
2) ለማረጋገጥ የፈለጉትን ስልክ ከኮምፒዉተሮት ጋር ያገኛኙት
3) ሶፍትዌሩ ስልኩን ያነበዉ እና የስልኩን ስም ፣የሚጠቀመዉን
ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ያሳያል፤
ሶፍትዌሩ ስልኩን ማንበብ ካልቻለ በድጋሚ ይሞክሩት በድጋሚ ማንበብ ካልቻለ ሰልኩ ኮፒ ነው ማለት ነው፡፡

@seen311
@computer_mobile_maintenanc_ethio

Read more👇👇👇👇
https://www.pulse.ng/fake-phones-how-to-identify-cloned-samsung-galaxy/s9xqfef
👍1
Commn PC problem & solution.pdf
451.9 KB
PC problems with solution:
⚠️keyboard,mouse,printer aren't working
⚠️computer is frozen
⚠️A program is not responding
⚠️New hardware or software is working incorrectly
⚠️computer is slow
👍1
#techno #AI

ሰውን መተካት የሚችል ወይም ከሠው የተሻለ ማሽን መፍጠር ይቻላልን

#Deep_Blue ለመጀመሪያ ጊዜ ሰውን ቼዝ በመግጠም ያሸነፈ ማሽን ነው።ይህ ማሽን በ #IBM የተሰራ የቼዝ መጫወቻ ኮምፒውተር ሲሆን በ1996 ኤ.አ ከአለም የቼዝ ሻምፒየን #ጋሪ_ካስፕሮቭ ጋር በተደረገ ጨዋታ ነበር ይህ ኮምፒውተር ሰውን ማሸነፍ የቻለው።

☑️ የኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ሲፈጠር የሰውን ስራ በተቀላጠፈ ሁኔታና በጥራት ለመስራት ሲባል ነው። ይህም የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂ በመጀመሪያ #ካልኩሌተር፣ ከዚያም #አባከስ እያለ፣ እያደገ እያደገ መጣና አሁን ያለንበት ደረጃ ላይ ደርሷል።

☑️ #አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ,AI Technology, (በሰው ሰራሽ መንገድ ማሽኖች የማሰብ ችሎታ እንዲኖራቸው ማስቻል) በአሁን ጊዜ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ወይም በኮምፒውተር ዘርፍ ትልቅና ውስብስብ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ሆኗል። የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ መነሻ ሃሳብ የተለያዩ ቀመሮችን በመቀመር፣ ዘዴዎችን በመንደፍና ሲስተሞችን ወይም ሶፍትዌሮችን በማበልጸግ ከተለያዩ ኮምፒውተሮችና ማሽኖች ጋር በማቀናጀት ምጡቅ፣ ብልህና እንደ ሰው ማሰብ የሚችል ማሽን ማጎልበት ነው። ቴክኖሎጂካል ሲንጉላሪቲ ማለት አንድ ራሱን የቻለ ሳይንስ ሲሆን ዋነኛ ትኩረቱ ሱፐር (የላቀ) ኢንተለጀንት ማሽን መፍጠር ወይም ሱፐር አርተፊሻል ኢንተለጀንት መፍጠሪያ ዘመን (ጊዜ) ነው።

☑️ የላቁ አርተፊሻል ኢንተለጀንት ማሽኖች እንደ ሠው በቀላሉ የማይደክማቸው፣ የማይሰላቹ በመሆናቸውና በብቃትም ሆነ በቅልጥፍና ከሰው በጣም የተሻሉ ስለሆኑ ብዙን ሥራ በአጭር ጊዜና በጥራት በመስራት፤ የሠው ልጅን ድካም በመቀነስ ረገድ ትልቅ እገዛ ያደርጋሉ።

☑️ ቴክኖሎጂካል ሲንጉላሪቲ #በህክምና ዘርፍ መጠነ-ሰፊ የሆነ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
ለምሳሌ፦ ነርሶችን በመተካት ህሙማን በመንከባከብ፣ ህሙማን ላይ ችግር ሲፈጠር በፍጥነት በማሳወቅ ወይም ሪፖርት በማድረግ ህሙማንን ከጉዳት ይከላከላሉ።

#በግብርናው ዘርፍም ቢሆን የእርሻ ምርታማነት በማሳደግ ድህነትንና ርሃብን ለማጥፋት በሚደረግ ጥረት ላይ ትልቅ ጠቀሜታ ይሰጣል። ለምሳሌ፦ ሱፐር ኢንተለጀንት ማሽኖች ከሰው በብዙ እጠፍ የተሻሉ ኢንተለጀንት ይሆናሉ፤ እናም ከሠው በተሻለ ኢንተለጀንት ማሽኖች በመፍጠር ምርታማነትን ያሳድጋል።

ከላይ የተጠቀሱት ጥቅሞች እንዳሉ ሆነው ብዙ የሚነሱ ስጋቶች አሉ። ከነዚህ መካከል እነዚህ ማሽኖች ሱፐር ኢንተለጀንት ከመሆናቸው የተነሳ የሠውን ልጅ መቆጣጠር የማይችለው ኢንተለጀንት ቴክኖሎጂ (ማሽን) መፍጠር ስለሚችሉና እነዚህም ማሽኖች ‘ሰው አያስፈልግም’ ወደ ሚል ድምዳሜ ሊደርሱ ይችላሉ::

@seen311
@computer_mobile_maintenanc_ethio

Read more 👇👇👇👇👇

https://www.educba.com/artificial-intelligence-vs-human-intelligence/
#pdf_reader_background_and_text color

🔰አብዛኛውን ጊዜ በኮምፒውተር soft copy pdf reader'ን ተጠቅመን ስናነብ white background እና black text ሆኖ ነው የምናገኘው። ነገር ግን ለአንዳንዶቻችን ይህ ለአይናችን ምቾት ላይሰጠን ይችላል:: ከታች ያለውን ቅደም ተከተል በመጠቀም ወደ የምንፈልገው መቀየር እንችላለን።

1. open pdf files using PDF reader

2. 🔝 Click on 'Edit'

3. click on 'Preference'

4. select 'Accessible'

5. tick on 'Replace document color'

6. tick on 'In Custom color'
'Page background'
'Document text'
እነዚህ ሁለቱ ላይ የምንፈልገውን እንመርጣለን

7. Click 'ok'
ለውጡ ወዲያው ይመጣል::
👍ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት❗️

@seen311
@computer_mobile_maintenanc_ethio
#mobile_hardware_microphone

📱ስልክ ደውለው....ስልክ የተደወለለትም ሰው ስልኩን አንስቶ በተደጋጋሚ ጊዜ
ሄሎ ...ሄሎ ...ይልዎታል እርሶም መልዕክትዎን ለማድረስ
ተቻኩለው አይሰማህም እንዴ ሀሎ...የሚል መልዕክት
ሲያቀብልዎት የእርሱ ድምፅ ግን ጥርት ብሎ እየተሰማዎት ነው።ንግግርዎንም ሳይጨርሱ ስልኩ ተዘጋብዎት እንደገናም ደወሉ የወዳጅዎ ድምፅ አሁንም እየተሰማዎት ነው ነገር ግን የእርስዎ ድምፅ ለእርሱ ሊደርስ አልቻለም ሌሎችም
ጋር ደወሉ ተመሳሳይ ችግር ገጠመዎት ....."ለምንድነው
የምናገረውን የማይሰሙኝ ሞባይሌ ምን ሆነ" ብለው ግራ ተጋብተው ይሆናል።

እርስዎ በሞባይልዎ ሲናገሩ ድምፅዎን ወደ ኤሌክትሪካል መልዕክት የሚቀይረውና የሚያስተላልፈው የሞባይሉ ክፍል
#Microphone እየሰራ አይደለም ማለት ነው። እናም ይህንን ችግር
ለመቅረፍ በራስዎ ማድረግ የሚገባዎት ወይም የሚሞክሯቸው ነገሮች ምን ምን ናቸው

1. ሞባይልዎን #አጥፍተው_በማብራት መልሰው በመደወል ማረጋገጥ

2. የሞባይል #ኔትዎርኩ ያለበት ባር ምልክት መቀነሱንና መጥፋቱ ማየት: የኔትወርክ መጥፋትና መቀነስ ለድምፅ መቆራረጥና
አለመሰማት ምክንያት ሰለሚሆን

3. የሞባይሉን #ድምፅ_መቅጃ ወይም ቪዲዮ መቅረጫ በመክፈት እና ሪከርድ በማድረግ ድምፅዎን ቀርፀው መልሰው ማዳመጥ እና ማረጋገጥ

4. ሞባይልዎ ስማርት ስልክ ከሆነ እና ሴቲንግ ላይ የአፕዴት ምልክት ከተመለከቱ የሞባይል ስልክዎን #አፕዴት ማድረግ

5 . እርስዎ ሲናገሩ ድምፅዎ ወደ ሞባይሉ የሚገባበት ክፍል
የሚገኘው ቻርጅ መሰኪያው(USB) አጠገብ በትንሹ የተበሳ የሚመስል ቀዳዳ ይገኛል: እሱ አካባቢ በተለያየ ነገር ተደፍኖ ከሆነ #ማፅዳት

6. መደወያውን በመጫን *#0283# ቁጥርን ሲያስገቡ ይህ ፅሁፍ ይመጣልዎታል
.Start=RVC-1stmic
.Start=SPK-1ndmic
.Start=Ep
.Stop
የተፃፉትን በመንካትና ድምፅዎን በማውጣት ማይክራፎኑ ወደ
ስፒከር መልሶ እንደሚያሰማዎት መፈተሽ

7. #Phone_doctor_plus የሚል አፕሊኬሽን በመጫን
የሞባይል ስልክዎን መፈተሽና ማስተካከል

8. የመጨረሻው አማራጭ ስልክዎ ላይ የሚገኙትን ሰነዶች ወደ ሌላ በማዘዎወር #ፎርማት በማድረግ
መሞከር ነው::

⚙️ይህን ሁሉ አድርገው ካልተስተካከለ ለባለሙያ ያሳዩት

👍ከወደዱት ለወዳጅዎ #ያጋሩት❗️

@seen311
@computer_mobile_maintenanc_ethio

Read more👇👇👇👇👇
https://joyofandroid.com/fix-microphone-problem-on-android/
2
#mobile_share_me_account

🖐 Use another phone no Voice, Internet & Message #package 🖐

እንዴት አድርገን እኛ በራሳችን ስልክ ኢንተርኔት:ስንደውልና መልዕክት ስንልክ #ከሌላ_ሰው_እንዲቆጥር ማድረግ እንደምንችል ያውቃሉ

እኛ እንድንጠቀምበት የምንፈልገው ስልክ ላይ 👇👇

1 👉 ወደ *999# ይደውሉ

2 👉 ቁጥር 4 ላይ 'ለተጨማሪ አገልግሎት' የሚለውን ምረጡ

3 👉 'ከአካውንትዎ ያጋሩኝ' ለመመዝገብ subscribe ካደረጋቹ በኋላ ተመልሳቹ ወደ *999*4# መደወል

4 👉 'ተጋሪ ለማካተት' ካልን በኋላ የተጋሪ ቁጥር እናስገባለን ለምሳሌ 0911**** የናንተን ቁጥር ማስገባት።

5 👉 1,2 ወይም 3 እንደፍላጎታችሁ

6 👉 1 ወይም 2 መምረጥና የሚጠይቀውን መሙላት

👍ከዚያም 'ተጋሪው ከእርሶ አካውንት አባል ነው' የሚል ጽሁፍ ይመጣል ። ከላይ የወሰንለት እስኪያልቅ ስልካችን ላይ ሒሳብ ቢኖርም ባይኖርም ከእኛ ሳንቲም ሳይቆርጥ መጠቀም እንችላለን።

ስለዚህ ይህን አገልግሎት በተለይ አሁን ላይ ኢትዮቴሌኮም ላበረከተው ተጨማሪ ስጦታ package ከሚገዙ ቤተሰቦቻችን በመጋራት መጠቀም እንችላለን❗️❗️
ከወደዱት ለወዳጅዎ #ያጋሩ!

@seen311
@computer_mobile_maintenanc_ethio
#phone_side_effect📱

**ሁሉም ሊያነበው የሚገባ

⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️
📱ስልካችንን ስንጠቀም
#ማድረግ_የሌለብን ነገሮች
⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️

⚠️ #በዝናብ ሰዓት Networking የሆኑ ነገሮችን ማጥፋት
✔️Airplane Mode ላይ ማድረግ ምክንያቱም ራዲየሽኑ መብረቅ ይስባል።
✔️ wi-fi, Bluetooth, Main Network ማጥፋት።

⚠️ #FM(ኤፍ.ኤም) በEarphone አለማዳመጥ
✔️ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ስማርት ስልኮች FM Antenna ስለሌላቸው ኢርፎኑን እንደ አንቴና ነው የሚጠቀሙት - ስለዚህ በኢርፎን ስናዳማጥ Eectromagnetic ራዲየሽኑ ጭንቅላታችን ላይ ጉዳት ያደርሳል።

⚠️ ስልክን #Charge_እያደረጉ ማንኛውንም ነገር አለመጠቀም
✔️ በተለይም አለመደዋወል - Calling Wifi,data አለመጠቀም::

⚠️ #በEarphone ሙዚቃ ስናዳምጥ Equalizer በመጠቀም ድምፁን Bass ላይ ማድረግ
✔️ምክንያቱም በNormal ድምፅ ስንጠቀም ለጆሯችን ቀጭን ድምፅ ስለሚያወጣ ያሳምመናል።

⚠️ ትልልቅ #Magnet (Magnetic field) ያላቸው ነገሮች አቅራቢያ ስልካችሁን አታስቀምጡ።

⚠️ የስልክ #ስክሪን Blue Light የሚባል አደገኛ ጨረር ይለቃል::
✔️ በተቻለ መጠን የስልካችንን Brightness መቀነስ ወይም Blue Light Filter App መጠቀም።

⚠️ #የባትሪ_ቻርጅ በጣም Low ሲሆን ወይም ሲቀንስ ስልኩን ያለመጠቀም ልማድ ይኑርዎ
✔️ ምክንያቱም ቻርጅ ሲቀንስ የሚረጨው የጨረር መጠን ይጨምራል።

⚠️ #በስልክ_ሲያወሩ ወደ ጆሮዎ እና ጭንቅላትዎ እጅግ በጣም አያስጠጉ
✔️ ቢያንስ ከ5 Centimetre በላይ ራቅ በማድረግ Electromagnetic Radiation ከተባለው አደገኛ ጨረር ራስዎን ይጠብቁ፡፡

⚠️ የሞባይል #ስልክ ታቅፈው አይተኙ
✔️ በእንቅልፍ ወቅት ባትሪውን ያጥፉ ወይም ከአልጋዎ 1.8 ሜትር በማራቅ ማታ ሲደወል ከሚለቀቀው Electromagnetic ራስዎን ይከላከሉ፡፡

⚠️ #ነፍሰጡር_እናቶች ሞባይል ሲይዙና ሲጠቀሙ ይጠንቀቁ
✔️ የጽንሱ ሕዋሳት ለElectromagnetic radiation እጅግ በጣም አለርጂክ ናቸው::
✔️ ስለዚህ አቀማመጡንም ሆነ አጠቃቀሙን ከጽንሱ ራቅ ባለ ሥፍራ ይሁን::
✔️ አላስፈላጊ አጠቃቀምን ለምሳሌ ረጅም ሰዓት ማውራት እና ቶሎ ቶሎ መደዋወል መቀነስ ያስፈልጋል፡፡

⚠️ #ብረት_ነክ ነገሮች ባሉበት ሥፍራ ሞባይል ብዙ ባይጠቀሙ ይመከራል
✔️ ብረት የኤሌክትሮማግኔቲክ ራድየሽኑን ወይም የጨረሩን ጉልበት ያጠነክረዋል::
✔️ ስለዚህ መኪና ውስጥ፣ አውሮፕላን ውስጥ፣ አሳንሱር(lift) ውስጥ፣ ባቡር ውስጥ፣ ብረት አጥር ወይም በር አካባቢ፣ የብረታብረት ወርክሾፕ ውስጥ፣ ጋራዥ ውስጥ ወዘተ አስቸኳይ ወይም አጣዳፊ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በተቻለ መጠን ሞባይል አይጠቀሙ::
✔️ የሚጠቀሙም ከሆነ ለአጭር ደቂቃ ይሁን፡፡

⚠️⚠️ በተለይ ደግሞ ዕድሜያቸው #ከ15_ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ሞባይልን ባይጠቀሙ ወይም ባያዘወትሩ ይሻላል❗️
✔️ምክንያቱም ጨረሩ የጭንቅላት ሴሎቻቸውን እጅግ በጣም ይጎዳዋል፤ ለካንሰርም ያጋልጣቸዋል፡፡

📌በበለጸጉት አገሮች ከ15 ዓመት በታች ባሉ ልጆች ውስጥ ለሚከሰተው ሞት በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ምክንያት #የጭንቅላት_እጢ ነው።
📌 ወላጆች ይህንን እውነታ በመገንዘብ አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር ሞባይል መጠቀምን በመደበኛነት ልጆች አዘውትረው እንዳይለምዱት ማድረግ ይገባቸዋል፡፡

⚠️⚠️ አዲስ የተወለዱ ጨቅላ #ሕፃናት ዕድሜያቸው ከ2 ዓመት በታች የሆኑት ሁሉ የጭንቅላታቸው ራስ ቅል በጣም ስስ ነው:
📌 ስለዚህ ጨረሩ ሙሉ ለሙሉ በስሱ አጥንት በኩል ወደ አንጎላቸው ሰርፆ ስለሚገባ ጥንቃቄ አድርጉ‼️
📌ሕፃናት አጠገብ ሁነው ሞባይል አዘውትረው የሚነጋገሩ ከሆነ ለአደጋ ስለሚያጋልጣቸው አጠቃቀሙንና አቀማመጡን ከእነርሱ ራቅ ባለ ሁኔታ ላይ ያድርጉት‼️

🔴Smartphone አብዝተን ስንጠቀም የሚመጣው በሽታ
👉Premature Death
👉Diabetes
👉Heart disease
👉የተለያዩ የካንሰር በሽታዎች
👉Discomfort
👉Musculoskeletal Symptoms

⁉️ቴክኖሎጂ የራሱ የሆነ ዘርፈ ብዙ #ጠቀሜታ እንዳለው ሁሉ የራሱም የሆነ ከፍተኛ #ጉዳት አለው:: ስለዚህ በተቻለን መጠን የሞባይል ስልክ አጠቃቀማችንን ማስተካከል አለብን።

‼️ይህን መልዕክት ለወዳጅ ዘመድዎ #በማጋራት ከሚደርስ ጉዳት ይታደጉ‼️

ይቀላቀሉን❗️👇👇👇👇👇
@computer_mobile_maintenanc_ethio


Read more 👇👇👇👇
https://www.google.com/amp/s/m.wikihow.com/Protect-Yourself-when-Using-a-Cell-Phone%3Famp=1
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼
🌼 A NEW YEAR
🌼 A New Challenge
🌼 A New Goal
🌼 A New Optimism
🌼 A New Approach
🌼 A New Mission
🌼 A New Resolution
♥️Wishing You♥️

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
HAPPY NEW YEAR
መልካም አዲስ አመት 2012
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

Join 👇 🌼🌼🌼🌼🌼 @computer_mobile_maintenanc_ethio
🌼🌼🌼🌼🌼
#new_year_promise #2012

ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች የአዲሱ ዓመት አቀባበል እንዴት ነው❗️በእኛ በኩል መልካሙን ሁሉ ተመኘን!
በዚህ ቻናል 2012ን
🌼 ካለፈው ዓመት ጠንካራ ጎኖችን
🌼 ከእናንተ ገንቢ አስተያየቶችን
🌼 ከእኛም አስተማሪና ጠቃሚ የምንላቸውን ዝግጅቶች በተከታታይ የምናቀርብ መሆኑን ቃል እንገባለን‼️
👍 ከቻናሉ ዓላማ ውጭ ሌላ ነገር አንለቅም(ለቤተሰቦቻችን በጣም አስፈላጊ የሆኑትን አይጨምርም)

@computer_mobile_maintenanc_ethio

ንቁ ተሳትፎና አስተያየታችሁ አይለየን:: ቻናሉን ለወዳጆቻችሁ አጋሩ:: ታዲያ ከታች አበበዋን በመጫን አብሮነታችሁን ግለጹልን!!
COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE
#mobile_share_me_account 🖐 Use another phone no Voice, Internet & Message #package 🖐 እንዴት አድርገን እኛ በራሳችን ስልክ ኢንተርኔት:ስንደውልና መልዕክት ስንልክ #ከሌላ_ሰው_እንዲቆጥር ማድረግ እንደምንችል ያውቃሉ እኛ እንድንጠቀምበት የምንፈልገው ስልክ ላይ 👇👇 1 👉 ወደ *999# ይደውሉ 2 👉 ቁጥር 4 ላይ…
#share_me_account

ከዚህ በፊት 'ከአካውንትዎ ያጋሩኝ' እንዴት ማስጀመርና መጠቀም እንደምንችል አቅርበን ነበር።
በውስጥ መስመር '... አገልግሎቱን እንዴት እናቋርጣለን?' የሚሉ ጥያቄዎች እየደረሱን ነው። ሌሎቻችሁንም ካስቸገራችሁ @seen3bot ላይ ጠይቁ እናስተናግዳለን።

@computer_mobile_maintenanc_ethio
#pc_mobile_filesharing

💻📲 💻📲 💻📲
አንድሮይድ ስልካችን እና ላፕቶፓችን እንዴት #Xender ተጠቅመን በማገናኘት መረጃዎችን መላክ እንደምንችል ያውቃሉ?

አንዳንዴ ከላፕቶፓችን ወደ ሞባይል ወይም ከሞባይል ወደ ከላፕቶፓችን መረጃዎችን ለመላክ USB ኬብል ላናገኝ እንችላለን። በዚህ ጊዜ የስልካችንን Xender: የኮምፒዩተራችንን wifi እና browser(pc app: chrome,opera,..)ተጠቅመን ማገናኘት እንችላለን።

አሰራሩም:
1️.📱Update የሆንዉን Xender ስልካችን ላይ እንጭናለን

2️.📱Xender እንከፍታለን

3️.📱Connect to PC የሚለዉን እንጫናለን
connect to pc የሚለው ከሌለ የ Xender profile picture ላይ በመጫን more የሚለውን በመንካት ማገኘት

4️.📱WI-Fi Hotspot የሚለዉን እንጫንና Create hotspot እንለዋለን

5️.💻 ወደ ላፕቶፓችን እንሄድና WI Fi ከፍተን ስልካችን ላይ በሚነግረን የ Xender ስም አይተን Connect እንላለን። Xender_AP6911 ብዙ ጊዜ ይሄ ነው የሚሆነው ሌላም ሊሆን ይችላል።

6️. 💻Connect መሆኑን ካረጋገጥን በኋላ ማንኛዉንም ኢንተርኔት የምንጠቀምበተን ብሮውዘር ከፍተን ስልካችን ላይ የሚያሳየንን አይፒ(IP) “ http://192.168.43.1:334/
55/ ” አስገብተን Connect እንላለን። ሌላም IP ሊሆን
ይችላል።

7️.📱 ስልካችን ላይ Accpet እንላለን አበቃ።
ከዚያ ላፕቶፓችን ላይ ከስልካችን ላይ ያሉን መተግበሪያዎች ጨምሮ ሁሉንም ፋይሎችን እንደ ፎቶ ቪዲዮ ልክ ኢንተርኔት እምንጠቀም እስኪመስለን
እናገኛቸዋለን፡፡ ከፈለግን ላፕቶፓችን ላይ Backup መውሰድ ፡ ኮፒ ማድረግ ወደ ስልካችን መጫን እንችላለን።

ከስልክ ወደ ኮምፒውተር መረጃ ለመላክ 📱➡️💻
👉 ኮምፒውተሩ ላይ connect ካደረግንበት browser ስንገባ የስልካችንን መረጃዎች እናገኛለን። ከዚያም የምንፈልገውን ፋይል ስንመርጥ ከላይ የ download ምልክትን መጫን ወይም drag በማድረግ መውሰድ
ከኮምፒውተር ወደ ስልክ መረጃ ለመላክ 💻 ➡️📱
👉 መረጃውን ኮምፒውተር ላይ drag በማድረግ ስልካችንን connected ካደረግንበት browser በመውድን move የሚል ሲመጣ መልቀቅ(drop)

#ማሳሰቢያ ፡- ይህን ስንሰራ ሞባይል ዳታ መዝጋት ይኖርብናል ፡ ምክንያቱም ወደ ላፕቶፓችን ሼር ስለሚሆን ከስልካችንን ካርድ ስለሚቆርጥ ነው፡፡
👍ከወደዱት ለወዳጅዎ #ያጋሩት

@seen3bot
@computer_mobile_maintenanc_ethio
Join 👆👆👆👆👆👆👆
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#baidu_browser_crashing
how can you solve it? answer @Computer_Mobile3
COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE
#baidu_browser_crashing how can you solve it? answer @Computer_Mobile3
#Baidu_browser_crashing

Here is simple Answer
1. On search bar write 'baidu browser'
2. Right click on it
3. Open file location
4. Find the file name 'bdstatreport' & delete it
5. Solved! Then check it

Have you any other solution?

@computer_mobile_maintenanc_ethio