COMPUTER and MOBILE MAINTENANCE
7.1K subscribers
71 photos
7 videos
53 files
103 links
Welcome To Computer & Mobile Maintenance Channel.
It Gives You Some Hints To Repair(Improve Performance Of) Your Computer & Mobile By Yourself. ለጠጋኞችም የሚጠቅም ምርጥ ቻናል ነው!
JOIN @Computer_Mobile21
Contact @seen311 or @seen3bot

Group👉 @Computer_Mobile3
Download Telegram
@computer_mobile_maintenanc_ethio

#mobile_internet
በቀላል መንገድ #mobile_internet_setting እንዴት
ማስተካከል እንደምንችል ያውቃሉ?

1. መጀመሪያ #setting ውስጥ መግባት

2. #more_network ውስጥ መግባት

3. #mobile_network የሚለውን መምረጥ

4. #acess_point_names የሚለውን መምረጥ

5. ከዛ የስልካችንን የግራ ዳር 3 ነጥቦች ወይም ከላይ የ+ ምልክት ካለ መንካት

6. ከላይ በተከታታይ የሚመጡልንን ማለትም
name እና APN ሁለቱንም በተከታታይ etc.com ብለን
ሁለቱንም መሙላት ከዛ save አድርገን መውጣት።

@computer_mobile_maintenanc_ethio
@computer_mobile_maintenanc_ethio

#mobile_charging
ሞባይል ስልክ ቻርጅ አላደርግ ቢል በራሳችን እንዴት እንፈትሻለን?

👉ለሰዓታት ሞባይል ስልኩን አጥፍቶ ቻርጀሩ ሳይሰካ ማቆየትና
ከቆይታም በኋላ መሞከር

👉በሌላ ማለትም በተመሳሳይ ቻርጀር ሰክቶ መፈተሽ

👉የሞባይል ስልኩ ባትሪ ተነቃይ ከሆነ ባትሪውን በመንቀል
የባትሪ መገናኛ ቦታዋች ንፁህን እንደሆኑ ማረጋገጥና ንፁህ
ካልሆነ ማፅዳት

👉ሞባይል ስልኩን አጥፍቶ በማብራትና በድጋሜ ቻርጀሩን
በመሰካት ማረጋገጥ

👉የሌላ ሞባይል ስልክ ባትሪ በመቀየርና ቻርጀር በመሰካት
መሞከር በተጨማሪም ባትሪው አለመበላሸቱን ወይም
አለማበጡን ማየት

👉የሞባይል ስልኩ ቻርጅ መገናኛ ቦታ በተለያዪ ነገሮች ሊደፈን
ስለሚችል ሞባይል ስልኩን በማጥፋት(ባትሪ በመንቀል)
ማፅዳት በተጨማሪም ቻርጅ መሰኪያ ቦታው እንዳልሰፋ,
እንዳልተጣመመ ,እንዳልተሰበረና እንዳልተበላሸ ማረጋገጥ

👉የሞባይል ስልኩ Software system አፕዴት የሚፈልግ
(የሚጠይቅ) ከሆነ አፕዴት ማድረግ

👍ከላይ የተጠቀሱት የመመርያ ፅሁፎች ሞባይል ስልክ ቻርጅ
እንዳያደርግ ከሚከለክሉት ነገሮች ውስጥ ጥቂቶቹ ሲሆኑ ይህንን
በመከተል የሞባይል ስልኩ ባለቤት በራሱ ሊፈትሻቸው
የሚችሉትን ነገሮችን ብቻ ነው::

Contact @seen311

@computer_mobile_maintenanc_ethio
@computer_mobile_maintenanc_ethio

#mobile_internet_data_Saving
ሞባይል ዳታ በሚከፈትበት ጊዜ ካርድ ወይም የተሞላውን የዳታ
ጥቅል በቶሎ የሚጨርስበት ምክንያትቶችና መፍትሔዎች:

ምክንያቶች :-
1.#የሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሳይዘጋ ሲቀር
2.#ኢንተርኔት ክፍት ሆኖ ከተለያዩ ደህረ ገፆች ላይ ቀጥታ
ቪዲዮች ሲታዩ
3.#System settings እና Applications በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ
4.#በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቃሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ
5.#በሞባይል ስልኩ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር

መፍትሔዎች :-
👉ሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሲቆይ እንደ ሶሻል ሚዲያና
ኦንላይን የሚሰሩ አፕሊኬሽኖች ከተጠቃሚው እይታ ውጪ
ስራቸውን ያከናውናሉ። በዚህ ጊዜ በሞባይሉ ላይ የተሞላው
ክሬዲት ሰዓት ይቀንሳል ወይም ያልቃል ስለዚህም ኢንተርኔት
ተጠቅመው ከጨረሱ በኋላ የሞባይሉን ዳታ ያጥፉ።

👉በሞባይል ዳታ ኢንተርኔት ከፍቶ ከተለያዪ ድህ ገፆች ላይ
በቀጥታ ቪዲዮ መመልከት የተሞላውን ካርድ መጠን በጊዜ
ከሚያሳጥሩት ነገሮች ወስጥ አንደኛው ሲሆን ለዚህም ዋነኛው
ምክንያት በኢንተርኔት ቪዲዮ ቀጥታ መመልከት የሚቆጥረው
የዳታ መጠን ከፍተኛ ስለሆነ ነው ስለዚህ ቪዲዮ ማየቱ ግዴታ
ከሆነ በ Vidmate እና በሌሉች ቪዲዮ ዳውሎደር
አፕሊኬሽኖች የቪዲዮ ይዘት በመቀነስ ጭኖ መመልከቱ ወጪን
ይቆጥባል።

👉System settings እና Application በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ የተሞላውን ዳታ(ካርድ) ይወስዳሉ ታዲያ ይህን ለማስቀረት Free wifi ከተገኘ አፕዴት ማድረግ ይህ ማድረግ የማይቻል ከሆነ system settings አፕዴት እንዳያደርግ ማስቆም:
👍Settings ----About----Software Update---
Automatic update የሚለውን ማጥፋት
Applications አፕዴት እንዳያደርጉ ከተፈለገ ደግሞ
-Google Play መክፈት.
- hamburger የሚመስለውን በለ ሶስት ሆሪዞንታል ምልክት
ያለበትንም አናት ላይ በስተግራ በኩል Settings በመንካት
Auto-update apps.- disable automatic app
updates, የሚለውን በመክፈት እና በመምረጥ መዝጋት
ይቻላል

👉በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቀሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ ከእይታ ውጪ በመሆን የክሬዲት መጠን ይቀንሳሉ ታዲያ ይህን ለመከላከል:
👍Settings----
data usage ---Restricted Background data
የሚለውን መክፈት... ከዚህ ይበልጥ ደግሞ Mobile data
saver አፕሊኬሽኖች በመጫን መጠቀም

👉በሞባይል ሰልክ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር የተሞላውን ሞባይል
ዳታ ከመቅስፈት እድሜው እንዲያጥር ያደርጋል ብሎም ቫይረሱ በራሱ ጊዜ የሞባይሉን ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማዘዝ ያለማንም ትዕዛዝ ዳታ ይከፍታል ዳውንሎድ ያደርጋል አላስፈላጊ ነገሮችና ማስታወቂያዋች ይለቃል ከዚህም የተነሳ በፍጥነት የሞባይል ካርድ( ዳታ ጥቅል) ይጨርሳል ይህ ነገር በሞባይሉ ላይ ቢከሰት አንቲ ቫይረስ በመጫ ሰካን ማድረግ ይህ መፍትሔ
የማይሆን ከሆነ ለባለሙያ ማሳየቱ ተገቢ ነው::

ለአስተያየትና ጥያቄ @seen311

@computer_mobile_maintenanc_ethio
@computer_mobile_maintenanc_ethio

#techno_news
#ሁዋዌ_አንድሮይድን የሚተካ #ሆንግ_ሜንግ የተሰኘ አዲስ
መተግበሪያ ያለውን ስማርት ስልክ ሙከራ አደረገ።

👉ሁዋዌ ቴክኖሎጂስ በራሱ ባለሙያዎች የተሠራ ሆንግ ሜንግ
የተሰኘ አንድሮይድን የሚተካ አዲስ መተግበሪያ ያለው ስማርት
ስልክ ሙከራ አደረገ
አዲሱ ስማርት ስልክ በተያዘው 2019 የፈረንጆች ዓመት
መጨረሻ ላይ ለገበያ ሊቀርብ ይችላል ሲል ግሎባል ታይምስ
የተሰኘው የሀገሪቱ መንግሥት ሚዲያ ዘግቧል።

👉የአሜሪካ መንግሥት ቻይና የጎግል አንድሮይድ መተግበሪያ
እንዳትጠቀም ማዕቀብ መጣሉን ተከትሎ፣ ሆንግ ሜንግ
መተግበሪያ ላይ የተመሠረተው ስማርት ስልክ ይፋ መሆን
ለሁዋዌ ትልቅ እምርታ ነው ተብሏል።

👉አዲሱ ስማርት ስልክ #288 የአሜሪካ ዶላር ያወጣል ተብሏል፡፡
ይህም በገበያ ላይ ከሚገኙት ስማርት ስልኮች አንጻር ዋጋው
አነስተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡-ሮይተርስ

@computer_mobile_maintenanc_ethio
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
@computer_mobile_maintenanc_ethio

#telegram_bot
ምርጥ የቴሌግራም ቦቶች

👉 @ChatIncognitoBot -ይሄን ቦት ተጠቅማቹ Randomly ቻት ማድረግ ትችላላቹህ።

👉 @UnitConversionBot - ይህን ቦት ተጠቅማቹ ማንኛውንም የልኬት አሀድ መቀየር ትችላላቹ።
ምሳሌ: start ብላችሁ '125km to m' ጻፉና ላኩለት መልሱን እራሱ ይነግራችኋል።

👉 @iFlipTextBot - የፈለጋቹትን text ስትልኩለት ከታች ወደ ላይ ይገለብጠዋል።

👉@liverobot - premier leauge እና laliga የጨዋታ መርሃ ግብር ለማየት ይጠቅማቹሃል።

👉 @GeezNumberBot - ማንኛውንም ቁጥር ወደ ግዕዝ ቁጥር ለመቀየር ከፈለጉ።
ምሳሌ: start ብላችሁ '50' ጻፉና ላኩለት መልሱን እራሱ ያመጣል።

👉 @FBvidzBot - ከፌስቡክ ላይ ቪድዮ ማውርድ ከፈለጋቹ ይህን ቦት ተጠቀሙ።ከናንተ ሚጠበቀው የቪዲዮውን ሊንክ ለቦቱ መላክ ብቻ ነው።

👉 @MyAndroidNewsBot - ስለ አንድሮይድ ስልክዎ አዳዲስ እና ትኩስ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ ይህን ቦት ምርጫዎ ያድርጉ።

👉 @MyGenderBot - ይሄ ቦት ስምን በመጠቀም ጾታን ለመለየት ያገለግላል።

👉 @nosticker_bot - ግሩፓቹ ላይ እስቲከር እየተላከ ከተቸገራቹ ይሄን ቦት ተጠቀሙ።እስቲከሩ ሲላክ ወድያው ከግሩፑ ያጠፋዋል።

👉 @bukgrouphelpbot - ሰው ወደ ግሩፓቹ ሲገባ የጆይን ሚሴጅ እንዳይገባ ከፈለጉ ይህን ቦት ይጠቀሙ።

👉 @RemoveHiBot - ግሩፓቹ ላይ Hi/Hello የመሳሰሉ ሚሴጆችን እንዳይላኩ ከፈለጋቹ ለዚህ ቦት አድሚን ስጡት።
👉 @Anonymous_telegram_bot - ማንነታቹ ሳይታወቅ ግሩፕ ላይ ማውራት እንዲሁም ፎቶ መላክ ትችላላቹ።

👉 @instaroonx_bot - Instagram ላይ ፎቶ ማውርድ ከፈለጋቹ ይህን ቦት ተጠቀሙ።ከናንተ ሚጠበቀው የፎቶውን ሊንክ ለቦቱ መላክ ብቻ ነው።

ለአስተያየትና ጥያቄ @seen311

@computer_mobile_maintenanc_ethio
#telegram_bot

#አዲስ_ቦት ከፍተው መልዕክት አልቀበልለዎትና አልክለዎት ካለ መፍትሔው ይሄው!

👍ወደሌላ ቦት ጋር ማገናኘት ለምሳሌ
ወደ @LimitatiBot ጋ ወይም @livegrambot ጋ ማገናኘት።

👉ወደ @livegrambot ለማገናኘት በዚህ መልኩ በቀላሉ ማስተካከል ይችላሉ።

⇓⇓
በመጀመሪያ @BotFather ላይ ገብተው
/mybot የሚለውን ok ይበሉ ከዛም የእርሰዎ ቦት ላይ ክሊክ ያድርጉ።
ከዛ Api token የሚለውን ይጫኑ በመቀጠል የሆነ ኮድ ይላክሎዎታል። ያንን የተላከውን
☟☟
554887452:AAG-A8KB5t8yQlSLPQLbMcR3PEPQpjEY
👆👆
የዚህ አይነት ጽሁፍ ኮፒ አድርገው ይያዙና እዚህ

👉 @LivegramBot 👈 bot ላይ ይግቡና start ብለው / 👈 ሲጽፉ /Addbot የሚለውን ክሊክ ብለው ይላኩ ከዛ

Agree continue የሚል ሲመጣልዎት ክሊክ ያድርጉ።
ከዛም የቡትዎን Api token paste አድርገው ይላኩለት።

ከዛ እራሱ ይጨርሰዋል። ቀጥታ ስራውን ጀምሯል ማለት ነው።

በመጨረሻም @BotFather ውስጥ በመግባት

editname,
about,
discription መሙላት ይችላሉ።
ባይሞሉም ግን ቀጥታ የሚላክለዎት መልክት ይደርሰወታል።

👍ያስታውሱ: ለሚልኩለዎት ሰዎች መልስ ለመስጠት ሲፈልጉ ከያንዳንዱ ሰው መልዕክት ላይ reply እያደረጉ መሆን አለበት።
ካልሆነ ግን መልክቱ አይሄድለትም ።

Contact @seen311

@computer_mobile_maintenanc_ethio
#computer_hardware

#ኮምፒውተር 💻 በሚያሰማቸው #የድምፃች_ቁጥር (beep sound number ) 🔉 ምኑ እንደተበላሸ ማወቅ እንችላለን!

1 Beep 🔔(once beep )
👍Refresh Failure Reseat

Replace memory, troubleshoot motherboard.

2 Beeps 🔔 (twice pip)
👍Parity Error

Reseat/replace memory, troubleshoot motherboard.

3 Beeps 🔔
👍Memory Error (first 64KB)

Reseat/replace memory.

4 Beeps 🔔
👍Timer Failure

Troubleshoot motherboard.

5 Beeps 🔔
👍Processor Failure

Troubleshoot CPU, motherboard.

6 Beeps 🔔
👍Keyboard Controller Failure

Troubleshoot keyboard, motherboard.

7 Beeps 🔔
👍Virtual Mode Exception Error

Troubleshoot CPU, motherboard.

8 Beeps 🔔
👍 Display Memory Failure

Trouleshoot graphics card, motherboard.

9 Beeps 🔔
👍 ROM BIOS Check sum Failure

Replace ROM BIOS, troubleshoot motherboard.

10 Beeps 🔔
👍 CMOS Shutdown Register Failure

Troubleshoot motherboard.

11 Beeps 🔔 (11 times beep)
👍L2 Cache Failure

Troubleshoot L2 cache, motherboard.

Contact @seen311

@computer_mobile_maintenanc_ethio
#computer_windows

ኮምፒውተራችንን #Rufes_software ተጠቅመን እንዴት #Format አድርገን Window መጫን እንችላለን?

አስፈላጊ ነገሮች
1. #Flash_disk: 4GB ወይም ከዚያ በላይ
2. #operating_system(Os) setup: windows xp 7, 8 or 10 iso IMG💿
3.Format የሚደረገው #ኮምፒውተር

ማሳሰቢያ:
👍ይህን ስራ ለማጠናቀቅ ወደ 40 ደቂቃ ሊቆይ ይችላል::

የአሰራር ቅደም ተከተል
1. በመጀመሪያ Rufus Software ከሌላችሁ Download አድርጉ....

2. በመቀጠል ሶፍትዌሩን ሳትጭኑ ራይት ክሊክን በመጫን ''run as admin"የሚለውን ይምረጡ...

3. ከዛ የተዘጋጀውን Flash Disk ኮምፒተሩ(rufes ካለበት) ላይ እንሰካለን። ፕሮግራሙ ከተከፈተ በኋላ ፍላሽ ዲስኩን device የሚለውን menu ተጭነን እንመርጠዋለን...

4. ከዚህ በኋላ iso image የሚለው ቦታ ሄደን የተዘጋጀውን የ windows soft ኮፒ አስገብተን drive letter እንመርጣለን...

5. ይህን ስናደርግ ፕሮግራሙ ራሱ ሁሉን ነገር ስለሚያዘጋጅ ሌላ የምናስተካክለው ነገር የለም ማለት ነው...

6. ከዛ start የሚለውን በተን ስንጫን ፍላሽ ላይ ያለ ማንኛውም ዳታ ይጠፋል ብሎ ማስጠንቀቂያ ይሰጠናል...

7. የምንፈልግው መረጃ ፍላሽ ላይ ካለ ባክአፕ ማድረግ አለብን።
እሱን ካረጋገጥን በኋላ ok እንለዋለን...

8. በመጨረሻ ፕሮግራሙ የ window setup ን ወደ ፍላሽ ዲስኩ ኮፒ በማድረግ ስራውን መስራት ይጀምራል....

9. ፕሮግራሙ ኮፒ አድርጎ ሲጨርስ exit አድርጎ መውጣት....

👍አሁን ፍላሽ ዲስኩን ተጠቅመን እንዴት ፎርማት እንደምንችል እናያለን

1. Format የሚደረገውን ኮምፒውተር shut down ያድርጉ...

2. ያዘጋጀነውን ፍላሽ ዲስክ አስገብተው turn on ያድርጉ.....

3 : F2 ወይም F12 ን (እንደ ኮምፒውተሩ ሞዴል ይለያያል) ይጫኑ እና ቀጣይ ትዕዛዙን ይከተሉ...

4. " install windows " የሚለው ሲመጣልዎ የሚፈልጉትን ቋንቋ እና ሌሎች ዝርዝሮችን ይሙሉ ከዛም next ን ክሊክ ያድርጉ....

5. "Please read the license terms" የሚለው ሲመጣልዎ
"I accept the license terms" የሚለውን ክሊክ ያድርጉ...

6. "Which type of installation do you want?" ሲልዎት Custom የሚለውን ይምረጡ...

7. "Where do you want to install Windows?" የሚለው ፔጅ ላይ "Drive options" የሚለውን ክሊክ...

8. ፎርማት ማድረግ የሚፈልጉትን "partition" ይምረጡና "format" ላይ ክሊክ ያድርጉ...

9. ፎርማት አድርገው ሲጨርሱ "next" ላይ ክሊክ ያድርጉ...

10. ከዛ በመቀጠል ትዕዛዙን (instruction) በመከተል window install ያድርጉ...እዚህ ላይ ስለሚዘገይ በትዕግስት ይጠብቁ...

11. Window install አድርጎ ሲጨርስ የሚፈልጉትን application software ይጫኑበት::

Contact @seen311

👇👇👇 join us
@computer_mobile_maintenanc_ethio
1
@computer_mobile_maintenanc_ethio

#window_7_installation

🖋ዛሬ ትላንት ካቀረብንላችሁ ርዕስ ጋር የሚገናኝና በፎቶ የተደገፈ የ windows 7 installation ይዘን መጥተናል!!
👇ሙሉ አጫጫኑን ለማየት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!

https://www.google.com/amp/s/m.wikihow.com/Install-Windows-7-(Beginners)%3Famp=1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#driverpack_solution

After installing #operating_systems on computers, it is difficult for you to find all the #right_driver for the computer,
#DriverPack_Solution will solve this problem for you!!

#DriverPack_Solution is the world’s most powerful driver updating solution, it gives you the the easiest way to updates all your drivers in a single click. This software, offering automation solutions for driver installation in online and offline mode, the tool automatically searches for and finds the proper drivers for your computer and then install them for you in just a few easy steps. In addition, DriverPack also brings some additional applications that usually are needed such as archive manager, internet browser, media player and some other tools.

👍Next we will come back with the installation guides of driverpack solution!
Contact @seen311

@computer_mobile_maintenanc_ethio
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DriverPack_Solution

How to install driverpack Solution?

👉first,download full file of driverpack solution Version if you don't have it
👉 Next, open the full driverpack solution files & install the file name 'driverpack solution'

👉 then wait untill it identifies all the missing drivers automatically & install
👉 use the following link for detail

http://googleweblight.com/i?u=http://www.blog.creativform.com/auto-install-drivers-without-internet-connection-driverpack-solution/&hl=en-ET

@seen311
@computer_mobile_maintenanc_ethio
#mobile_virus

ሞባይላችን #በቫይረስ_መጠቃቱን እንዴት ልናውቅ እንችላለን?

1. #ፍጥነቱ_እየቀነሰ ከመጣ:
ቫይረሱ በሞባይላችን ካለ የሞባይላችንን የመስራት ፍጥነት
ይቀንሰዋል።ይህም አፕልኬሽን ስንጭን ዝቅተኛ መሆን፣ስልካችንን ስናበራ ለመነሳት ረዥም ስዓት መውሰድ ።

2.የሞባይላችን #ባትሪ_በቶሎ_ካለቀ
ቫይረሱ በሞባይላችን ካለ የባትሪያችንን ሃይል በጣም ስለሚጠቀም ባትሪያ
ችን ከተለመደው በተለየ ሁኔታ ቶሎ ያልቃል።ነገር ግን ባትሪያችን ብዙ ግዜ ካገለገለ ቶሎ የሚያልቅበት ምክንያትም አለ።

3. #የማናቃቸው_አፕልኬሽኖች መገኘት:
እኛ ሳንጭናቸው አፕልኬሽኖችን በ ሞባይላችን ላይ
ተጭነው ካገኘን ሞባይላችን በቫይረስ መጠቃቱን ያመለክታል።

4. #ዳታ_ስንጠቀም :
እንተርኔት ዳታ በፍጥነት ማለቅ ከጀመረ ዳታችን እየቀነሰው ያለ
ቫይረስ ሊሆን ይችላል።

5. #አፕልኬሽኖቻችን_ክራሽ ሲያደርጉ:
አፕልኬሽን ስንጠቀም ክራሽ እያደረገ ሲያስቸግረን ቫይረስ ሊሆን ይችላል።

6. ስልኩ ጠፍቶ #ሲበራ_ረዘም_ያለ_ጊዜ ከወሰደ:

7. በቀላሉ #የሚሞቅ ከሆነ:

8. ስልኩ በራሱ #ጠፍቶ_የሚበራ ከሆነ:

👉እነዚህን ምልክቶች ሞባይላችን ላይ ካስተዋልን ስልካችን በቫይረስ ተጠቅቷል ማለት ነዉ::

@seen311
@computer_mobile_maintenanc_ethio
#የሽልማት_ውድድር

🙏የኮምፒውተር እና ሞባይል ጥገና ቻናል ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ!!!

#ለነገ_እሁድ(12/12/2011) #ምሽት 2:30 ለየት ያለና #ጠቃሚ ውድድር እዚህ ቻናል ላይ ተዘጋጅቷል።ውድድሩ ምን እንደሆነ #ዛሬ_ምሽት 2:30 ላይ ይገለፃል። የመጀመሪያ 3 ምርጥ #አሸናፊዎች ተሸላሚ ይሆናሉ!

መረጃውን ለሌሎችም ያካፍሉ👇
@computer_mobile_maintenanc_ethio