Computer science sec 3/12
178 subscribers
346 photos
4 videos
679 files
97 links
Channel for section 3 student
comment
@Susu41 @Eyuel_N
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#ExitExam

ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ምን አሉ ?

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተናን በተመለከተ ለፋና ቴሌቪዥን ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸው ምን አሉ ?

- የፈተናው አይነት " የምርጫ ጥያቄ " መሆኑን ገልፀዋል።

- የፈተናው ጥያቄ ብዛት በተመለከተ ጊዜው ሲደርስ እንደሚገለፅ፤ የጥየቄው ብዛት ግን ከ50 በላይ እንደሆነ ፤ በአብዛኛው ፕሮግራም 100 ጥያቄ እንደሚኖር አሳውቀዋል።

- በአብዛኛው ፕሮግራም 100 ጥያቄ ነው ፈተናው ፤ በተወሰኑ መስኮች ምርጫውን ለመሙላት ብዙ ሂሳብ ስለሚሰሩ የጥያቄ ቁጥሩ ከ100 ሊያንስ ይችላል።

- ተማሪዎች ፈተናውን እንደተፈተኑ ውጤታቸውን ወዲያው መላክ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ቢሮርም የመጀመሪያ ቀን የተፈተኑ ተማሪዎች ውጤት ቢገለፅ ሌሎች ላይ ከሚያሳድረው ጫና አንፃር ወይም ፈተናው ቀለል / ከባድ ነው ብሎ እንዳይዘናጋ / እንዳይጨነቅ ወዲያው አይገለፅም። የፈተናው ውጤት የሚገለፀው የመጨረሻው ፈተና ከተሰጠ ከአንድ ቀን በኃላ ነው።

- ውጤት አልፏል ወድቋል ብቻ ሳይሆን ተማሪው ያመጣው ውጤት ይገለፃል።

- የጤና ተማሪዎች ፈተና ሰኔ 30 ይጀምራል እስከ ሐምሌ 8 ድረስ ይዘልቃል። የጤና ተማሪዎች ቀድመው የሚፈተኑበት ምክንያት ቀኑን ሙሉ ፈተናውን ስለሚወስዱ ነው። ጥዋት ላይ ከሙያቸው ጋር የተያያዘውን ይፈታናሉ ፤ ከሰዓት ላይ የመውጫውን ፈተና ይወስዳሉ / በተቃራኒው / ።

- ፈተናው በከፍተኛ ጥንቃቄ ነው የተዘጋጀው ፤ በውስን ኃላፊዎች ብቻ እንዲታወቅ ተደርጓል፤ ስለማይታተም፣ እጅም ስለሌለበት ደህንነቱ አያሰጋንም።

- ፈተናውን ከመስጫው ሰከንድ በፊት ማየት የሚችል ሰው አይኖርም። ፈተናው ካለቀበት ሰከንድ በኃላ መስራት የሚችል ሰው አይኖርም። ይህ በማዕከል ነው ቁጥጥር የሚደረገው።

- የማለፊያው ነጥብ 50 % እና በላይ ሲሆን ይህን ያላለፉ (ኮርስ ያልጨረሱ) ከ5 / ከ6 ወር በኃላ ጥር እና የካቲት ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና መውሰድ ይችለሉ። በዚህም ከለተሳካ ከቀጣይ አመት ተፈታኞች ጋር መውሰድ ይቻላል። በዓመት ሁለት ጊዜ ለመስጠት ታቅዷል።

- አብዛኛው ተማሪ በመጀመሪያው ዙር ያልፋል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል፤ ካልሆነ ግን በሁለተኛው ዙር ተፈትኖ ያልፋል። ሁለቴ ተፈትኖ ማለፍ ያልቻለ እስከሚያልፍ / 50 % እና ከዚያ በላይ ማምጣቱ እስኪረጋገጥ ፈተናውን መውሰድ ይችላል።

- ፈተናው ተማሪዎች አልተሳካላቸውም ብሎ የማሸማቀቅ ዓለማ ስለሌለው እስኪያልፉ ድረስ መፈተን ይችላሉ።

- ምናልባት ያላለፉ ተማሪዎች ዳግም ፈተና ለመውሰድ መጀመሪያ ሲማሩበት ወደነበረበት ተቋም መሄድ አይጠበቅባቸውም ፤ ባሉበት አካባቢ ባሉ ተቋማት ፈተናውን እንደሚወስዱ የሚደረግበት ሁኔታ ይኖራል።

- ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎች በምረቃ ፕሮግራም ላይ ይሳተፋሉ ? ትምህርት ሚኒስቴር የምረቃ ፕሮግራም በተመለከተ በፖሊሲው ላይ እንደማይፅፍ ገልፀዋል። ጉዳዩ የተቋማት ነው ብለዋል። ሚኒስቴሩ በፖሊሲ የሚያስገድደው ግን የመውጫ ፈተናው የስርዓተ ትምህርቱ አካል ስለሆነ ይህን ያላለፈ ዲግሪ/ጊዜያዊ ጭምር፣  ትራንስክሪብት አይሰጠውም። የምረቃ ፕሮግራም ከማዕከል አይመራም ይህ የተቋማቱ ጉዳይ ነው። እኛ የምንከታተለው ፈተናውን ሳያልፉ ዲግሪ እንዳይሰጣቸው ነው።

- የምረቃ ጉዳይ እና በዕለቱ በምረቃ ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች ጉዳይ የሴኔት ነው ትምህርት ሚኒስቴር አይመለከተውም። ነገር ግን የመውጫ ፈተናው እየተሰጠ/ ሳይሰጥ በፊት ምረቃ ማድረግ በፍፁም አይቻልም።

- የመውጫ ፈተና ያላለፈ ተማሪ በፍፁም ዲግሪ፣ ቴምፖራሪ ዲግሪ፣ ሰርተፊኬት እንደማይሰጠው አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopia
👍2
As per the email received and reported today from MoE, out of the total 367 student accounts, only 136 have been successfully activated. For the remaining 231 students whose accounts are still pending activation, I want to emphasize the importance of this process. We kindly remind you to complete the activation process.
#From Department Head

Guys take ur user name and password from the department head and activate ur account
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለመውጫ ፈተና ወደ መተግበሪያው መግቢያና አፈታተኑን የሚያሳይ አጋዥ ተንቀሳቃሽ ምስል(Video)
4.11 Min 
3.8 MB                          


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
7:30 operating system
9:30 networking class
Find the questions written in the blackboard for the IP 168.50.10.0/20

For tomorrow
Photo
Tomorrow class 2:30-9:30
,Nega compiler result metachu eyu afternoon lay
Forwarded from Getch Tilahun
ውድ የመንግስት ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንቶች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሃላፊዎችና/ ባለቤቶች 
ጤና ይስጥልኝ፡፡

ከፊታችን ባሉ ሁለት ፈተናዎች ማለትም የሬሜዲያልና የመውጫ ፈተና በተመለከተ እስካሁን ያለው አፈፃፀም(ምንም እንኳ ብዙ መልዕክት በመላክ ብናሰለቻችሁም) በጥሩ ሁኔታ እየሀደ ይገኛል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ፈተናዎች መስጫ ጊዜ በመቃረቡ ቀበቶ ማጥበቂያው  ወቅት ላይ ደርሰናል፡፡ እነኚህን ጉዳዮችን የሚመለከታቸው የእናንተ መዋቅር አውቀው እንዲዘጋጁ ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡

1.ለመውጫ ፈተና የሙከራ ፈተና በኮምፒውተር መፈተንን እንዲለማመዱ ነገ(ሰኔ 23) ይኖራል፡፡ ፕሮግራሙን ዶ/ር  ኤባ ና ዶ/ር ዘላለም ባሳወቁት መሰረት፤

2.ለመውጫ ፈተና የሞዴል ፈተና ከዋናው ፈተና ጋር ተመሳሳይ በሆነ መርሃግብር፣ የመፈተኛ አውድ፣ ፈተና ጊዜ እርዝማኔ ፣ ተቀራራቢ የፈተና ጥያቄ መልክ በመያዝ ከፊታችን ሰኞ(26/10) እስከ ረቡዕ/ሃሙስ ይሰጣል፡፡ መንግስት ዩኒቨርስቲ ውስጥ እየተማሩ ያሉ  እጩ ተፈታኞች  በየተቋሞቻቸው እንደዚሁም የግል ተቋማት ተማሪዎች በራሳቸው ተቋማትና  በሚችሉት ሌሎች አማራጮች የሚፈተኑ ይሆናል፡፡ መርሃግብሩን ነገ የምንልክ ይሆናል፡፡

3.ሰኞ(በ26) የሚጀመረውን ሬሜዲያል ፕሮግራም ለሚከታተሉ ተማሪዎች የሚሰጠውን በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና(ዋጋው 70 ፐርሰንት) ጥያቄውን በየእለቱ ጠዋት ጠዋት  የምንልክ ሲሆን  ፈተናው በተመሳሳይ ጊዜ ከሰዓት 8 ፡00 ጀምሮ ይሰጣል፡፡ ሰለሆነም ሁሉም ተቋማት ለዚህ ሥራ የተመደበ  ማለትም ፈተና በሃላፊነት በኢሜል ደርሶት እንዲባዛ የሚያደርግ ወይም ራቅ ብለው ለሚገኙ ካምፓሶች ለሚመለከታቸው ልኮ እንዲያባዙት የሚያደርግ  የሚመለከተው ሀላፊ ኢሜል  መላካችሁን በድጋሚ እንድታረጋግጡ ይሁን፡፡ 
ብሩክ ምሽት ይሁንላችሁ፡፡
አርብ 23/10/2015 የትምህርት ሚኒስቴር የመለማመጃ ምዴል ፈተና ፕሮግራም(scedule)

የነገው የመውጫ ፈተና መተግበርያ ( system) ተማሪዎች እንዲለማመዱ እንዲሁም የይለፍ ቃላቸው ( password) ስላልቀየሩ ከመተግበሪያው እንዲተዋወቁ መለማመጃ ጥያቄዎች (mok Question) ናቸው ተማሪዎች እንዲለማመዱ እንዲሁም የተቋማትን የመፈተን አቅም ለመገምገም የታሰበ ነው።
ጥያቄዎች ት/ት ክፍል መሰረት ያደረጉ ሳይሆን ቀላል የእንግሊዘኛ ጥያቄዎች ናቸው።
ዋናው የሞዴል ፈተና በቀጣይ ቀናት ይሰጣል። የግል ት/ቤቶች ወደ ኋላ ስለቀሩ ነው እንጂ ቀደም ብሎ እንዲሰጥ ጠይቀን ነበር። አሁንም እየጠየቅን ነው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዝግጁ ቢሆንም የግል ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ለተማሪዎች የይለፍ ቃል አድርሰው አልጨረሱም። ባይጨርሱም ግን በአጭር ጊዜ እንዲሰጥ ጠይቀናል።

ሀገር አቀፍ ተማሪዎች ህብረት

@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
👍1
@7:30 #compiler wetat yasayal
Class yelem....