በንጽጽር ሰዎች የተሰራጩ ስህተቶችን ማረም
547 subscribers
59 photos
4 videos
35 links
Download Telegram
ከ40 ቀን ቡኋላ አሏህ ካለ ጥሩ ነገር እፖስትላቹሀለሁ እስከዚያ ቻናሉን ሼር አድርጉት አሏህ የምንጠቀም ያድርገን😊

August 12
👍11😁2👏1
የኪታብ  ሽያጭ

የኪታቡ ስም   ፈትሁል ባሪ
ኪታቡ አዲስ ነው አልተነካካም

አሁን ላይ ገበያው ላይ 21k ከመሆኑ ጋር
በ17k በአሪፍ ዋጋ ይውሰዱ

የሚፈልግ 
@Samirrrrrrrrrrrrrrrr ያናግረኝ
😢73
አቶ ተድላን ድሮ ሲሰልም ነበረ ዋይዋይ እንዳትሉ ያልኩት፥ከዚያም በመሀልም ዲን ላይ ሲራገጥ ተው ስለው ምቀኛ ተባልኩ

ዛሬ ሁሉም ማየት ያለበትን እያየ ይመስለኛል
👍142
አንዱ ሚስት ሊያገባ ስራህ ምንድነው ሲባል አነፃፃሪ ነኝ አለ



ስሙ ሙራድ ይባላል
😁43😭1
እዚህ ቻናል ላይ አነፃፃሪ ሰዎች በደስ አለኝ እና መሰለኝ የሰሩትን ተሻጋሪ ዲናዊ ስህተት ከፊሉን በቮይስ ተብራርቱዋል ምትፈልጉ በውስጥ ጠይቁኝ


@Samirrrrrrrrrrrrrrrr
😁3🥴1
Sαlαh Responds ࿈
የክርስቲያን ሰባኪዎች በተደጋጋሚ ከሚያነሷቸው ትችቶች ውስጥ አንዱ [📚Qur'an 66:1] ላይ ያለውን ጉዳይ ነው። يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ لَكَ ۖ تَبْتَغِي مَرْضَاتَ أَزْوَاجِكَ ۚ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ አንተ ነቢዩ ሆይ! አላህ ለአንተ የፈቀደልህን ነገር ሚስቶችህን ማስወደድን የምትፈልግ…
ማርያ አል-ቂብጢያ ሚስት ወይስ ቁባት?


ወንድም ሳላህ “ማርያ አልቂብጢያ" የመልዕክተኛው ሚስት ነች የሚል ጽፎ ነበር። ይህ ጽሁፋ ሙሉውን በስህተት የተሞላ ነው። እና ነብዩ ላይም መዋሸት ውስጥ ሊካተት የሚችል ነው። ነብዩ ያላደረጉትን ለነብዩ ለመከላከል ብሎ እንኳን አደረጉ ብሎ መናገር አደገኛ የሆነ የሰውዬውን ሀይማኖት የሚጎዳ ነገር ነው።

በእስልምና ለአንድ ወንድ ሚስትም በእጅ ስር ያሉ ሴት ባሮችም ለግኑኝነት የተፈቀዱ መሆኑ የማያሻማ እና ግልጽ ነው። 
አላህ እንዲህ ይላል፦
وَٱلَّذِينَ هُمْ لِفُرُوجِهِمْ حَٰفِظُونَ إِلَّا عَلَىٰٓ أَزْوَٰجِهِمْ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَٰنُهُمْ فَإِنَّهُمْ غَيْرُ مَلُومِينَ
እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት (አገኙ)፡፡በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዟቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡ (Al-Mu'minun 23:5:6)


ጌታችን አላህ ለመልእክተኛውም ይህን ነገር በግልጽ መፍቀዱ ተቀምጧል፦

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ إِنَّآ أَحۡلَلۡنَا لَكَ أَزۡوَٰجَكَ ٱلَّٰتِىٓ ءَاتَيۡتَ أُجُورَهُنَّ وَمَا مَلَكَتۡ يَمِينُكَ
አላህ ባንተ ላይ ከመለሰልህም እነዚያን እጅህ የጨበጠቻቸውን ምርኮኞች ፈቀድንልህ (ሱረቱል አህዛብ 33:50)



እስከዚህ ድረስ ከተግባባን ማርያ አል-ቂብጢያ የነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሚስት ሳትሆን በቀኝ እጅ ስር የነበረች ሴት ነች። ስለዚህ ነብዩ ማርያን ሳየገቧት ሚስት ናት እያሉ መናገር ነብዩ ላይ መዋሸት ነው። ነብዩ ላይ መዋሸት ደግሞ ትልቅ ጥፋት ነው ። መልእክተኛው እንዲህ ይላሉ፦

مَن كَذَبَ عليَّ مُتَعَمِّدًا فليَتَبَوَّأْ مَقعَدَه مِنَ النَّارِ
(በኔ ላይ ሆነ ብሎ የዋሸ መቀመጫውን ከእሳት ያስቀምጥ) (  ሰሂህ አል-ቡኻሪይ book 23: hadith 49)

ወደ ጉዳዩ ዘልዬ ከመግባቴ በፊት  ቃላቶችን በጊዜ ሂደት እየተለወጡ እና ኖርማል የነበሩ ነገራት እየተዛቡ ስለመጡ ቅድምያ ቃላት ላይ ግንዛቤ መስጠት ግድ ይላል። ባርያ(አል-አማ) እና ቁባት(ሱረያ) መሀል ልዩነት ምንድነው?

ሴት ባሪያ(الأمة) ፦ ስንል በአሳዳሪው እጅ ላይ ሚገኙ ሁሉንም ሴት ባሪያዎች አካቶ ይይዛል ፤ ይህ ማለት ሴት ህፃናቶችን እንዲሁም ባል ያላቸውንም ባሪያ ሴቶች ጭምር ማለት ነው። ሙጀረድ አል-አማ ብቻ  የሆነች ሴት ልትወረስም ልትሸጥም ትችላለች።
 
ነገር ግን ...

  ቁባት(سرية ) ፦ ስንል በአሳዳሪዋ ንብረትነት ውስጥ ሆና  ከሌላው ምትለየው ለአሳዳሪዋ በሚልከል የሚን (ልክ  እንደ ኒካህ ትስስር ) ለጂማዕ የተፈቀደች ሰዪዷ በፈለገ ሰአት ሚመጣት ሚመመለከታት አይማኑኩም ተብለው ከተጠቀሱት የምትመደብ ናት ።

ከሷ ልጅ ከወለደ እሷን መሸጥም ለሌላ አካል ስጦታ መስጠትም አይችልም ። አሳዳሪዋ ሲሞት ነፃ ትወጣለች እንጂ አትወረስም። አጠቃላይ በኒካህ ስምምነት ሳይሆን በንብረትነት እንደ ሚስት ናት(ሚስት ናት ሳይሆን ከሚስት ጋ አንዳድ ሚመሳሰሉበት ሁክም አላቸው) ።

ስለዚህ ባሪያ(الأمة) ከቁባት (سرية )ሰፋ ያለና ጠቅላይ ስለሆነ ትስስራቸው ኡሙም ወኹሱስ ሙጥለቅ ይሆናል (i.e ሁሉም ሱረያ አል-አማ ነው ሁሉም አል-አማ ግን ሱረያ አይደለም) ማለት ነው።


ሐጀራ ለኢብራሒም (ዓለይሂ ሰላም) በሱ እጅ ስር የነበረች ሱረያ እንደነበረች ሁሉ ማርያ አል-ቂብጥያ ለመልእክተኛው ሱረያ ነበረች ።ይህ እንግዲህ በሲራ በኩል ላለፈ በሙሉ የታወቀ እውነታ ነው።
قال الإمام النسائي: أخبرني إبراهيم بن يونس بن محمد نا أبي نا حماد بن سلمة عن ثابت عن أنس أن​رسول الله ﷺ كانت له أمة يطؤها فلم تزل به عائشة وحفصة حتى حرمها فأنزل الله عز وجل: ﴿يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَآ أَحَلَّ ٱللَّهُ لَكَ تَبْتَغِي مَرْضَاتَ أَزْوَٰجِكَ﴾ إلى آخر الآية.
አነስ (ረዲየላሁ ዓንሁ) “መልእክተኛ የሚገናኛት ባርያ ሴት  ነበረቻቸው አዒሻ እና ሀፍሳ ከእራሱ ላይ እርም እስኪያደርጋት ድረስ አልተዉትም አላህም  “አንተ ነቢዩ ሆይ! አላህ ለአንተ የፈቀደልህን ነገር ሚስቶችህን ማስወደድን የምትፈልግ ስትኾን (ባንተ ላይ) ለምን እርም ታደርጋለህ?”
        (አ'ነሳኢይ :3959)

እዚህ ሰሂህ ሀዲስ ላይ አል-አማ ተብላ የተገለፀቹ ማርያ አል-ቂብጥያ እንደሆነች ሳይታለም የተፈታ ነው። ስለዚህ ሚስት ሳትሆን ቁባት እንደነበረች ያሳየናል።


የሰሃባዎችን ታሪክ ላይ የፃፋ ሰዎች በሙሉ በዚህ ርእስ ላይ በማውቀው የእውቀት ደረጃ አልተለያዩም (አል-ከማሉ ሊላህ!)።

አል-ኢማም ዓሊይ ቢን ሙሐመድ አል-ጀዘሪይ (ኢብኑል አሲር) በመባል የሚታወቀው ዓሊም “ኡስዱል ጋባ ፊ መዕሪፈቲ ሰሃባ" ላይ እንዲህ ብሏል፦
مارية القبطية:- مولاة رسول الله ﷺ وسريته  وهي أم ولده إبراهيم بن النبي  أهداها له المقوقس صاحب الإسكندرية...

“ማሪያ አልቂብጢያ የነብዩ ባሪያና ቁባት ነበረች ። እሷም የነብዩ ልጅ የሆነው  ኢብራሂም እናት ስትሆን የግብፁ መሪ ሙቀውቂስ ነው በስጦታ መልክ የሰጣቸው”

እንዲሁም ኢማሙ ነወዊ “ተህዚብ ሲይረቱ ነበውያ" ላይ እንደመጣው እንዲህ ይላሉ፦
وكانت له سُرِّيَّتان: مارية وريحانة بنت زيد، وقيل: بنت شمعون، ثم أعتقها

ለርሱ (ለነብዩﷺ) ማሪያና ረይሀና ቢንት ዘይድ (ቢንት ሸምዖንም ተብሏል ) ሚባሉ ሁለት ቁባቶች ነበሩት ከዚያም ረይሀናን ከባርነት ነፃ አወጧት::

(N:B ተህዚይብ ሲይረቱ'አነበውያ ከተህዚቡ ሉጋት ወል-አስማእ ተወስዶ የታተመ ነው)


ኢማሙ ነወዊ መልእክተኛው ሪይሃናን ነፃ እንዳወጡዋት በግልጽ አስቀምጠዋል። ማርያ በተመለከተ ግን በህይወት ጊዚያቸው ነፃ አወጧት ሚል ስላልመጠ ዝም ብለዋል። ወንድማችን ታድያ አገቧት ሚለው ምንድነው? “ነፃ ሳያወጧት" አገቧት ማለት ይቻላል እንዴ?


ወንድማችን ማርያ የሙቀውቂስ ሃድያ መሆኗን አስፍራል ከዛን ደግሞ አግብቷታል ይለናል። በዚህ መሀል ግን ነፃ እንዳወጧት አልጠቀሰም ። ሰይድ የሆነ አካል ሱረያውን ማግባት ከፈለገ ቅድምያ ነፃ ሊያወጣት ይገባል። ነብዩ ማርያን በህይወት ጊዜያቸው ነፃ አውጥተዋታልን ?

መልሱ አላወጧትም ነው። በእርግጥ ከኢብን አባስ እንደሚወራው ነብዩ ኢብራሂምን የወለደች ጊዜ ኢብራሂምን መውለዷ ነፃ አወጣት እንዳሉ መጥቷል ።

ነገር ግን ኢብን አብዱል በር ኢስቲዓብ ላይ እንዲህ ይለናል ፦
روي من حديث ابن عباس عن النبي ﷺ أنه لما ولدت مارية القبطية الرسول الله ﷺ ابنه إبراهيم قال : «أعتقها ولدها». وإسناده لا تقوم به حجة لضعفه
.“ ማሪያ   ኢብራሂምን በወለደች ጊዜ የአላህ መልእክተኛ ልጇ ነፃ አወጣት ማለታቸው ኢብኑ አባስ ከነብዩ መዘገቡ ተወስቷል። ስነዱ ደካማ በመሆኑ ማስረጃ አይቆምበትም።”

ስለዚህ ማርያ ነፃ መውጧት የሚያመላክት ምንም ዓይነት አስረጂ የለም። ታድያ ቤት በኩል ሚስት አደረጋቿት??


( ይቀጥላል)

https://t.me/comparativeerror
6👍2😭1
. ማየት ማመን ነው በሚለው

https://t.me/comparativeerror
👍41
ክርስቲያኖች መጥተው ቢያርሟቸው የሚገቡበት ይጠፋቸው ለመመለስ ለማስተካከል እንቧ ከረዩ ይሉ ነበረ፥ነገሩ የአሸናፊነትና የተሸናፊነት ስለሆነባቸው።
😁4😭1
Forwarded from Murad|⛉ (Nebil)
ለመመዝገብ፦@dillara126

በየቲክቶክ ፔቻጁህና በየ ፕሮፋይላቹህ በየቻናሎቻቹህ እስከ ቀጣይ እሁድ ፕሮሞት በማድረግ ተባበሩን።
😁3👍2🥰2
አል-ቀዋዒዱል ሙስላ ፊ ሲፋቲላሂ ወአስማኢሂል ሁስና። (1)
5
አ'ሸማኢል አል-ሙሀመዲያ (2)
3
አ'ሱለሙል አል-ሙነውረቅ ፊ ዒልም አል-መንጢቅ (3)
🔥1
ፈድል ዒልመ ሰለፍ ዓላ ዒልመ አል-ኸለፍ (4)
🤔1
አል-ባዒሱ አል-ሀሲይስ ሸርህ ኢኽቲሳር ዑሉሙል ሀድስ(5)