በንጽጽር ሰዎች የተሰራጩ ስህተቶችን ማረም
541 subscribers
49 photos
4 videos
34 links
Download Telegram
እርምት

ወንድም አቡበከር ድብቅ ብዥታዎች በሚለው መጽሀፉ ሙስጠላህ በተመለከተ ያስቀመጣቸው ጥሩ ነጥቦች አሉ። እንደ ማንኛውም ሰው የተፈጸሙ አንዳድ ስህተቶችም በተጨባጭ አሉ። እኝህን ማረሙ የአርትዖት ሰሪዎች ስራ ቢሆንም ዝም ስለተባሉ እኔ ላርማቸው ወድጅያለሁ።
ከነዚህም ውስጥ ወንድም አቡኪ ድብቅ ብዥታዎች ገጽ 19 ላይ እንዲህ ይላል “እነዚህ የጠቅስናቸው ሙርሰሎች በሙሉ ደዒፍ ናቸው። ምክንያቱም በታቢዕዩ እና በነብዩ መካከከል ያለ መካከለኛ (ሰሀባ) ባለመኖሩ!!”
ይህ ገለጻ ሙርሰልን ለመጣል ትክክለኛ ምክንያት ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም እንዲህ ከሆነ ሙርሰሉ ሰሃባም ተቀባይነት የለውም። ሰሃባ ኢርሳል ሲያደርግ በእርሱና በነብዩ መሐከል ያለውን ሰሀባ ጥሎ ነው። ታድያ ይህ ውድቅ ነውን ስንል?
ወንድማችን ራሱ ሙርሰሉ ሰሃባ ተቀባይነት እንዳለው ቅድምያ ተናግሮ ነበር (ፈአህሰነ ወአጃደ) ። እንዲህ ይላል፦“አው የሰሀቦች ኢርሳል ተቀባይነት አለው ምክንያቱም ሰሀቦች በአብዛኛው የሚያስተላልፉት ከሰሀቦች ነው። ሰሀቦች ደግሞ ታማኞች መሆናቸው እሙን ነው”
(ድብቅ ብዥታዎች ገጽ 18)


ሰሃቦች ከመልእክተኛው ቀጥታ ያልሰሙትን ሲያስተላልፉ የነገራቸውን ሰሃባ ጥለው ነው ይህን ተቀባይነት አለው ካለ ሙርሰል ደካማ የሆነው “በታቢዕዩ እና በነብዩ መካከከል ያለ መካከለኛ (ሰሀባ) ባለመኖሩ" ማለቱ ትርጉም አይሰጥም።

ጤነኛ አንባቢ ሙርሰሉ ሰሀባ ላይም እኮ “በሰሀቢዩና በነብዩ መካከል ያለ መካከለኛ ሰሀባ የለም” ብሎ ሊጠይቅ ይችላል! ስለዚህ ወንድማችን እዚህ ጋር ሳያውቀው ገድፏል ይታረማል!

           {ሙርሰል ተቀባይነት የሌለው ለምንድነው?}

ሙርሰል ማለት ታቢዕይ (የሰሀቦች ተከታይ) ወደ ነብዩ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም)  ያልሰማውን ሲያስጠጋ የሚሰጠው ስያሜ ነው። ይህ ዓይነቱ ዘገባ ተቀባይነት አለው ወይስ የለውም የሚለው በዑለማዎች መካከል ልዩነት ያስተናገደ ነጥብ ነው። ነገር ግን ትክክለኛው አቋም የሙርሰል መሰረቱ ደዒፍ ነው የሚለው አቋም ሲሆን ለዚህም ደግሞ ጤናማ የሆነ ለትችት ክፍት ያልሆኑ ምክንያቶችን ደርድረዋል።

ዋነኛው ታቢዕይ ከመልእክተኛው ሲያወራ ይህን ዘገባ ቀጥታ ከሰሀባ ወስዶት ሊሆን ይችላል ወይም ከታቢዕይ ሊሆን ይችላል የሚል ይሁንታ በመኖሩ ነው። ከታቢዕይ ሊሆን ይችላል የሚለው ይሁንታን ከከፈትን ይህ ታቢዕይ ሲቃ ነው ወይስ ደዒፍ የሚለው ይሁንታ በቅድምያነት ይከፈታል ማለት ነው።
ይህ ደግሞ ሙርሰል መርዱድ ውስጥ ለማካተት ዋነኛው ነጥብ ነው።

ስለዚህ ሙርሰል ደካማ የሚሆነው “መሀከል ላይ የተጣለው አካል ማን እንደሆነ ስለማይታወቅ" ነው። ሰሀባ ብቻ እንደተጣለ ቢረጋገጥ ኖሮ ሙርሰል ደካማ አይሆንም ነበር። ሰሀባውን አለማወቃችን ሐዲሱ ላይ የሚያመጣው ተፅእኖ የለም።

ኢማሙ ቲርሚዚይ እንዲህ ይላል፦

: ومَنْ ضَعَّفَ المرسلَ فإنه ضَعَّفَهُ من قِبَلِ أَنَّ هؤلاء الأئمةَ قد حَدَّثوا عن الثقاتِ وغيرِ الثقاتِ ، فإذا روى أحدهم حديثاً وأرسَلَهُ لعلهُ أخذه عن غير ثقةٍ .وقد تكلَّمَ الحسنُ البصريُّ في مَعْبَدٍ الجُهَنِيِّ ، ثم روى عنه ! .
“ሙርሰልን ደካማ ያደረጉት ደካማ ያደረጉበት ምክንያት እነዚህ አኢማዎች ከሲቃም ሲቃም ካልሆነም አካል ስላወሩ ነው። አንዱ 'ታቢዕይ' ሀዲስን አውርቶ ሰነዱን ካልጠቀሰው ከሲቃ ካልሆነ አካል ይዞት ሊሆን ይችላል (የሚል ይሁንታ አለ።) ሀሰን  አል-በስሪይ መዕበድ አል-ጁሐኒይ ከመተቸቱ ጋር አስተላልፎለታል” (ዒለሉ ሰጊር )

አል-ሃፊዙ ኢብን አብዱልበር እንዲህ ይላል፦

وحجتهم في رد المراسيل ما أجمع عليه العلماء من الحاجة إلى عدالة المخبر وأنه لا بد من علم ذلك، فإذا حكى التابعي عمن لم يلقه، لم يكن بد من معرفة الواسطة، إذ قد صح أن التابعين أو كثيراً منهم، رووا عن الضعيف وغير الضعيف، فهذه النكتة عندهم في رد المرسل، لأن مرسله يمكن أن يكون سمعه ممن يجوز قبول نقله، وممن لا يجوز، ولا بد من معرفة عدالة الناقل، فبطل لذلك الخبر المرسل للجهل بالواسطة.
ሙርሰልን በመመለስ ላይ ማስረጃቸው ዑለማዎች የተናጋሪውን ዐዳለነት ማወቅ ግድ ነው በሚለው ስምምነታቸው ላይ የቆመ ነው። ታቢዕይ ካልተገናኘው አካል ካስተላለፈ መሐከል ላይ ያለውን ማወቅ ግድ ማለቱ ቅሮት የሌለው ነው። ምክንያቱም ታቢዕዮች ወይም አብዛኞቹ ታቢዕዮች ከደካማም ከታማኝም አስተላልፈዋል። ሙርሰልን ለመጣል ያመጡት ይህችን ነጥብ ነው። ምክንያቱም ሰነዱን የጣለው አካል ሊተላለፍለት ከሚገባ ይዞት ሊሆን ይችላል ላይሆንም ይችላል የዘጋቢውን ዓዳላ ማወቅ ደግሞ ቅሮት የሌለው ግዴታ ነው። ለዚህም ሲባል ሙርሰል መሐከል ላይ የተጣለው ስላልታወቀ ውድቅ ይደረጋል” (ሙቀዲመቱ ተምሂድ)

አል-ሃፊዙ ኢብን ሐጀር እንዲህ ይላል፦

”(المرسل) وإنما ذُكِرَ في قِسْمِ المردود للجهل بحال المحذوف؛ لأنه يُحتمل أن يكون صحابيًا، ويُحتمل أن يكون تابعيًا.
​وعلى الثاني يُحتمل أن يكون ضعيفًا، ويُحتمل أن يكون ثقةً، وعلى الثاني يُحتمل أن يكون حَمَلَ عن صحابي، ويُحتمل أن يكون حَمَلَ عن تابعي آخر، وعلى الثاني فيعود الاحتمالُ السابقُ، ويتعدد. أمّا بالتجويز العقلي فإلى ما لا نهاية له، وأمّا بالاستقراء فإلى ستةٍ أو سبعةٍ،“
«ሙርሰል በደካማ ክፍል ውስጥ የተመደበው የታጠለው አካል ስለማይታወቅ ነው። ምክንያቱም ሰሀቢይ ሊሆን ይችላል ታቢዕይም ሊሆን ይችላል ታቢእይ ይሆናል ካልን ይህ ታቢእይ ደካማ ሊሆን ይችላል ሲቃ ሊሆን ይችላል ይህ ታቢእይ ሲቃ ይሆናል ካልን ራሱ አሁንም ከሰሀቢይ ይዞት ሊሆን ይችላል ወይም ከሌላ ከታቢእይ ይዞት ሊሆን ይችላል። ከታቢእይ ይዞት ሊሆን ይችላል ካልን ያሳለፍነው ይሁንታ ተመልሶ ይመጣል። ዓቅል በሚፈቅደው በዚህ መልኩ ገደብ እስከሌለው ድረስ መቀጠል ይቻላል በተጨባጭ በመገኘቱ ግን ወደ ስድስት እና ሰባት ታቢዕዮች 'ይኬዳል'።” (ኑዝሀቱ ነዘር)


አል-ሃፊዙ ስዩጢይ እንዲህ ይላል፦
”​( ثم المرسل حديث ضعيف ) ، لا يحتج به ،.......... والنظر للجهل بحال المحذوف ، لأنه يحتمل أن يكون غير صحابي ،وإذا كان كذلك ،فيحتمل أن يكون ضعيفاً “

«(ሙርሰል ደካማ ሀዲስ ነው) ማስረጃ አይደረግበትም... የተጣለው አካል ማን እንደሆነ ማወቅ አለመቻላችንን ከማየት አንጻር ምክንያቱም የተጣለው ከሰሃባ ውጭ የሆነ አካል ሊሆን ይችላል ይህ ከሆነ ደግሞ የተጣለው ደካማ ዘጋቢ ሊሆን ይችላል» (ተድሪቡ ራዊ )


ስለዚህ ሙርሰል ሐዲስ ውድቅ ሚሆነው ሰሀባው ስለተጣለ ሳይሆን ሰሀባ ብቻ ነው ወይ የተጣለው? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ስለማይቻል ነው። ታቢዕይ ከታቢዕይ የሚያወራበት እድል በጣም የሰፋ ስለሆነ ታቢዕይ ቀጥታ ከረሱል ሲያወራ ሰሃባ ብቻ ነው የተጣለው ብሎ መደምደም የሚቻል ስላልሆነ ነው ደካማ የሆነው።
https://t.me/comparativeerror
12👏93😁2🔥1
የቲርሚዚይ
የኢብን ዐብዱል በር
የኢብን ሐጀር
የስዩጢይ ንግግሮች!
43
Sαlαh Responds ࿈
ነገረ-ተሕሪም የሱረቱል ተሕሪም (ምዕራፍ 66) ሰበብ አን-ኑዙል (Historical background) ሁለት መሆናቸው ይታወቃል፣ አንደኛው በቡኻሪ መጽሐፍ 68 ሐዲስ 17 ላይ የተጠቀሰው ሲሆን ነቢዩ ከዘይነብ ቤት ማርን በልተው ሌላኛው ሚስታቸው ስትቀና (የሴት ነገር ታውቁ የለ Hhh) እርሷን ላለማስከፋት ብለው ጣፋጩን ማር በራሳቸው ላይ እርም ሲያደርጉ አላህ «ለአንተ የፈቀደልህን ነገር ሚስቶችህን ማስወደድን…
ለነገረ-ተሕሪም የተሰጠ ማስተካከያ


ሱረቱ ተሕሪም የወረደበት ምክንያት ላይ ወንድማችን ሳላህ አንዱን ምክንያት አስበልጦ ሌላኛው ጥሎ ነበር። አንዱን ጥሎ ሌላኛውን ማስበለጡ በራሱ ራሱን የቻለ ስህተት ቢሆንም ይህን ስህተት የፈፀመበት አግባብ ደግሞ ከስረ መሰረቱ የተበላሸ ነው።

ወንድማችን ሳላህ እንዲህ ይላል፦

“ታድያስ ከሁለቱ ሰበብ አን-ኑዙሎች የትኛው ነው ትክክል ? መቼም ሁለቱም በአንዴ ልክ ሊሆኑ አይችልም ! ስለዚህ የቁርኣኑ አንቀጽ የወረደው ለማሩ ጉዳይ ነው ወይስ ለማሪያ?..... ”

Yh ንግግሩ ላይ “መቼም ሁለቱም በአንዴ ልክ ሊሆኑ አይችልም” ሚለው ትልቅ የመነሻ ስህተት ነው። አንድ የቁርዓን አንቀፅ ከአንድ በላይ አስባበ ኑዙል ሊኖረው ይችላል።

ለአንድ የቁርዓን አንቀጽ ከአንድ በላይ ሰበቦች (ምክንያቶች) ከተለያዩ ሰሀቦች ሲጠቀስ ቅድምያ ጀምዕ (መሰብሰብ) እንጂ ወደ ተርጂህ (አንዱን ለመጣልና ሌላኛውን ለማስበለጥ አይሮጥም) ። ከሚሰበሰብበት መንገዶች ውስጥም ሁለቱን እዚህ ጋር ማስቀመጥ ወደድኩ።


የመጀመርያው የተለያዩ ሰበቦች ለቁርዓኑ አንቀጽ መውረድ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ የሚለው ይሁንታ ነው።ማለትም ከአንድ በላይ ክስተቶች ቢኖሩና አንደኛው ሰሀቢይ ይህ አንቀጽ ለዚህ ምክንያት ነው የወረደው ቢል ሌላኛው ደግሞ ሌላ ምክንያት ቢጠቅስ በነዚህ ምክንያቶች መኃል ሰፊ የጊዜ መራራቅ እስከሌለ ድረስ የቁርዓኑ አንቀጽ በሁለቱም ምክንያት ላይ ወርዷል ሊባል ይችላል።

አል-ሃፊዙ ስዩጢይ  እንዲህ ይላሉ፦

الحال الخامس : أنْ يُمكِنَ نزولُها عَقِبَ السَّبَبَيْن أو الأسبابِ المذكورةِ بأن لا تكون معلومة التباعد، كما في الآيات السابقة، فيُحْمَلَ على ذلك.
​«(አምስተኛው ሁኔታ : በሁለቱ ወይም በተወሱት ሰበቦች ምክንያት መጨረሻ ላይ መውረዱ ሊያስመች ነው። ግና በምክንያቶቹ መሀል ረጅም የጊዜ ርቀት አለመኖሩ ሊታወቅም ነው። ልክ እንዳለፉት አናቅጽቶች ፣ (ካልታወቀ) በዚህ ላይ ይያዛል»(ኢትቃን)

ለምሳሌ አያቱ ሊዓን “የመረጋገም አንቀጽ" (ሱረቱ ኑር ከ 6-9) ያለው ኢማሙል ቡኻሪይ በዘገበው ሀዲስ በሂላል ኢብን ኡመያ ምክንያት ነው የወረደው የሚል ሲሆን  ሁለቱ ሸይኾች (ቡኻሪና ሙስሊም በጋራ ባወጡት ) ደግሞ ከሰሕል ኢብን ሰዕድ ላይ ተንተርሰው በዑወይሚር አል-ዓጅላኒ ምክንያት ነው የወረደው የሚል ነው።

እንደወንድማችን አካሄድ መሰረት “መቼም ሁለቱም በአንዴ ልክ ሊሆኑ አይችልም” ብለን አንዱን ወደ መጣል ሊገባ ነበር ነገር ግን ጀምዕ ማድረግ እየተቻለ ወደ ተርጂህ መሮጥ ጥንቁቅነትን የተላበሰ አካሄድ አይደለም።

ኢማሙ ስዩጢይ ከኢብን ሐጀር ይዞ ይህን የአያቱ ሊዓንን ሰበቦች በተመለከተ ንግግራቸውን ነቅል (Qoute) ያደርግልናል፦

قال الحافظ ابن حجر: اختلف الأئمة في هذه المواضع فمنهم من رجح أنها نزلت في شأن عويمر ومنهم من رجح أنها نزلت في شأن هلال ومنهم من جمع بينهما بأن أول ​من وقع له ذلك هلال وصادف مجيء عويمر أيضاً فنزلت في شأنهما معاً وإلى هذا جنح النووي وسبقه الخطيب فقال لعلهما اتفق لهما ذلك في وقت واحد.

«አኢማዎች እዚህ ቦታ ላይ ተለያዩ
ከነሱ ውስጥ በዑወይሚር ምክንያት ነው የወረደው የሚለውን ያስበለጡ አሉ። ከነሱ ውስጥም በሒላል ምክንያት ነው የወረደው ሚለውን ያስበለጡ አሉ። ከአኢማዎች ውስጥም  መጀመርያ ጉዳዩ ያጋጠመው ሂላል ቢሆንም ከዚያን የዑወይሚር መምጣት ጋርም ገጠመ ስለዚህ በሁለቱም ጉዳይ ላይ አንቀጹ ወረደ በሚል ሁለቱንም የሰበሰበ አለ ነወዊይ ወደዚህ አቋም ተዘንብሏ  በዚህ ላይም ኸጢብ  ቀድሞታል እንዲህ አለ፦ “ምናልባትም በአንድ ጊዜ ላይ ገጥሞላቸው ይሆናል”» (ሉባቡ ኑቁል ፊ አስባቢ ኑዙል)


ስለዚህ ለአንድ የቁርዓን አንቀጽ ከአንድ በላይ ምክንያቶች ሊመጡለት በሚችልበት ሁኔታ “መቼም ሁለቱም በአንዴ ልክ ሊሆኑ አይችልም” ማለት “አንድ የቁርዓን አንቀጽ አንድ ሰበብ ብቻ ነው ሚኖረው" ከሚል  የተሳሳተ ቃዒዳ መነሳት ነው።

በአያቱ ሊዓን ዙርያ ኢብን ሐጀር እንዲህ ይላሉ
«لا مانع من تعدد الأسباب»
«ለአንቀጹ መውረድ ምክንያቶቹ መብዛታቸው ላይ ከልካይ የለም» (አል-ኢትቃን ፊ ዑሉሚል ቁርዓን)

ሁለተኛው አፕሮች በመጀመርያው መልኩ መሰብሰብ ካልተቻለ የቁርዓኑ አንቀጽ ተደጋግሞ ወርዷል ማለት ይቻላል። አንድ የቁርዓን አንቀጽ በተደጋጋሚ ለተለያዩ ምክንያቶችም የሚወርደበት ሁኔታ እንዳለ ግልጽ ነው።

አል-ሀፊዙ ስዩጢይ እንዲህ ይላሉ፦

الحال السادس : ألا يُمكِنَ ذلك، فيُحمَلُ على تَعَدُّدِ النزول وتكرُّرِه،
“ስድስተኛው ሁኔታ: በተለያዩ ሰበቦች ወርዷል ሚለው ላይቻል ነው ይህን ጊዜ ተደጋግሞ ወርዷል ተብሎ
ይያዛል” (አል-ኢትቃን ፊዑሉሚል ቁርዓን)


ለምሳሌ ይህን የቁርዓን አንቀጽን ያዙ
مَا كَانَ لِلنَّبِىِّ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَن يَسۡتَغۡفِرُواْ لِلۡمُشۡرِكِينَ
(ሱረቱ ተውባ:113)

ሁለቱ ሸይኾች (ቡኻሪና ሙስሊም) መልእክተኛው ለአቡ ጧሊብ ማሀርታን ጠይቆ እንደወረደ የሚያመላክት ዘገባ አስፍረዋል።
አል-ኢማሙ ቲርሚዝይ ሀሰን ባደረገው ሀዲስ ዓሊይ (ረዐ) አንድ ሰውን “ አባትህ ሙሽሪክ ሆኖ እስቲግፋር ትጠይቅለታለህ ወይ?” ብሎ  ሲጠይቀው ሰውዬው “ኢብራሂም አባቱ ሙሽሪክ ሆኖ ጠይቋል" ብሎ ሲመልስለት ዓሊይ ጉዳይን መልዕክተኛውን ሲጠይቃቸው ነው ይህ አንቀጽ የወረዳው የሚል አስፍሯል።
አል-ኢማሙል ሃኪም በዘገበው ደግሞ መልእክተኛው ለእናታቸው ኢስቲግፋርን መጠየቅ ፈልገው አንቀጹ እሳቸውን በመከልከል ነው የወረደው ሚልን ዘግቧል
የቱ ነው ትክክል? ወንድማችን ሳላህ እንደሚለው ከሆነ “መቼም ሁለቱም በአንዴ ልክ ሊሆኑ አይችልም” ብለን  አንዱን ማስበለጥ ግድ ይል ነበር
ነገር ግን እንዲህ የሚባል መርሆ የለም
ዑለማዎች ይህንን አንቀጽ በተደጋጋሚ ወርዷል በሚል ልዩነቱን አስታርቀዋል። ይህ የተለመደ ነው። አንድ የቁርዓን አንቀጽ  ተደጋግሞ ሊወርድ ይችላል

አል-ኢማሙ ዘርከሺይ እንዲህ ይላል፦

وقد ينزل الشيء مرتين تعظيمًا لشأنه وتذكيرًا به عند حدوث سببه، خوف نسيانه وهذا كما قيل في الفاتحة نزلت مرتين مرة بمكة وأخرى بالمدينة”

“ አንድን አንቀጽ ለማላቅ እና ምክንያቱ የተገኘ ጊዜ እንዳይረሳ ተፈርቶ ለማስታወስ ሁለቴ ሊወርድ ይችላል ልክ ፋቲሃ  አንዴ በመካ ሌላ ጊዜ በመዲና ወርዷል እንደተባለው ነው።"


ኢማሙ ዘርከሺይ ለዚህ ማሳያ የተለያዩ ምሳሌዎችን ከጠቀሱ ብኃላ ሲጠቀልሉ  እንዲህ ይላሉ......

«وما يذكره المفسرون من أسباب متعددة لنزول الآية قد يكون من هذا الباب،»
«ሙፈሲሮች ለአንድ አንቀጽ ለመውረዱ የተለያዩ ምክንያቶችን የሚጠቅሱበት ምክንያት ከዚህ ርእስ ስር ሊሆን ይችላል(ተደጋግሞ የወረደ ሚለው ርእስ)»
(አል-ቡርሐን ፊ ዑሉሚል ቁርዓን)



ስለዚህ ወንድማችን የሰራው ስህተት ተዋራሽና ተደራሽ ስለሆነ ጽሁፍን ማስተካከል የሱ ፋንታ ሲሆን መናገር የኛ ነው።ስፔስፊካሊ ሱረቱ ተህሪም ላይ እርምቱ ይቀጥላል...

https://t.me/comparativeerror
14👍3👏3
የስዩጢይ
የኢብን ሐጀር
የዘርከሺይ ንግግሮች
3
አል-ሃፊዙ ስዩጢይ እንዲህ ይላል፦ “አንደኛው አንድ ሰበብን ከጠቀሰ ሌላኛው ሌላ ሰበብን ከጠቀሰ እነዚህ ምክንያቶች ተከትሎ የወረደ ይሆናል አያቱ ሊዓን ላይ እንደሚመጣው ወይም ደግሞ ተደጋግሞ ወርዶ ሊሆን ይችላል አያቱ ሩህ እና የነሕል መጨረሽያው ላይ
እንደሚመጣው .......”
(ሉባቡ ኑቁል ፊ አስባቢ ኑዙል)

ወንድማችን እንዲህ ይላል፦

“ታድያስ ከሁለቱ ሰበብ አን-ኑዙሎች የትኛው ነው ትክክል ? መቼም ሁለቱም በአንዴ ልክ ሊሆኑ አይችልም ! ስለዚህ የቁርኣኑ አንቀጽ የወረደው ለማሩ ጉዳይ ነው ወይስ ለማሪያ?..... ”


(ስህተት ነው ይታረም።)

https://t.me/comparativeerror
👍9👏21🥰1😁1
መጽሀፍ ጽፈህ የታወቀ ፍንትው ያለ ዲናዊ ነጥብ (ለምሳሌ ሙስጠላህ ምናምን ላይ) Reference ኢንጊሊዘኛ መጽሀፍ ምታስቀምጡ ሰዎች ፈጣሪ እያያቹ ነው🤧
ጻፍ ብሎ ያስገደደህ ሰው አለ እንዴ?


አረ ጃሂል ናቸው ብላቹ አቀልዱብን የሆነ ቀን እንነቃለን ባረከላሁ ፊኩም!!!

https://t.me/comparativeerror
😁42👎2💯1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሼኽ ያዕኒ  አረብኛ ላይ የፈፀማቸው አስገድዶ መድፈር እንዳለ ሆኖ ኢትቃን ባላደረገው ነገር እንዳደረገው ማስመሰል ለምን አስፈለገ? ሁሉም አድማጭ ጃሂል ነው እንዴ ሚመስለን ? አረ ሚያውቁ ይታዘቡናል አረ እንፈር ባረከላሁ ፊኩም። ሼኽ አድበስብ አዋቂ ለመባል የሚጫወታት ስነልቦና ገጠመም አልገጠመ የመትን አረብኛ  ቃላትን መወርወር ነው ሰብሃነክ 😭😁

በእርግጥ ቋንቋ በፕራክቲስ ነው ሚመጣው ይህ ማለት ግን ሕዝብ ላይ ነው እንዴ ምንለማመደው??? በአማርኛ አውራ ያልከው ወንድሜ ግን በአረብኛ እያወራህ መስሎህ ነው ወይ😭

በዚች ሙሉ ባልሆነ በሁለት ደቂቃ ቅጂ ውስጥ ያዕኒ ከ 30 ጊዜ በላይ ተጠቅሞታል። ሕዝብ ላይ መለማመድ ነውር ነው ሀቂቃ ለወደፊቱ ይታረም ምክንያቱም አድማጭን ከመናቅ የመጣ ድፍረት ስለሆነ:)

ለማንኛውም ኡስታዝ ያዕኒ ወሼኽ አድበስብስ ተማሩ ሲላቹ አንተም ተማር በሉት ለአለህ ብላቹ


( ወንድም ሉቅማን ግን ትችላለህ አላህ ይጨምርልህ ሀቂቀተን እንዲህ ዓይነት ነገር መለጠፍ አልፈልግም ነበር ግን ቆማጣን ቆማጣ ካልተባለ ካልፈተፈትኩ ይላል።)

https://t.me/comparativeerror
😁32👎32👍1🔥1
ነገረ ሼኽ አድበስብስ


የ ሼኽ አድበስብ ጉዳይ ከአቅም በላይ ሆኗል። እልህ ምላጭ ያስውጣል በሚል ውይይቱ ላይ የፈፀማቸው አስቀያሚ ዲናዊ ጥፋቶች እና ማጭበርበሮች ዝም ልል ፈልጌ ነበር ከመመለስ ይልቅ ወደ እልህ እንዳይገባ በማሰብ

እያደረ በመጣ ቁጥር ይቆጨዋል ወይም ወደ አላህ ይመለሳል በሚል ዝምታን ልመርጥ ነበር ነገር ግን ይህ ሰው ወደ አላህ ከመመለስ ይልቅ ውይይቱን እንዳሻነፈና እንደረታ እያሰበ ነው (ወይም ሰዎች እንዲያስቡ እያደረገ ነው) ስለዚህም ምን ያህል እንደገደፈ ለሰው መግለጽ ግዴታዬ ሆኖብኛል።


በዚህም የተነሳ አንድ በአንድ ማረም የምቀጥል ይሆናል የመጀመርያው እርምት ሸይኽ አብዱልዓዚዝ አ'ረይስ ላይ ያጭበረበረበው በጽሁፍ ከዛን በድምጽ ከድምጹ ጋር አስቀምጣለሁ ።

https://t.me/comparativeerror
👍104👏3😁3🔥2
አረይስ ላይ ቅጥፈት


ተመልከቱ ይህን ተልቢስ (ማወጫበር😁)
😁3
በድግሜ አረይስ ላይ ሲያወጫብር
😁1
መረጃ ብሎ ቆርጦ ያቀረበው ይህ ነው
👍2👎2
አተርፍ ባይ አጉዳይ የሆኑት ሽይኽ አድበስብስ፦ ( part 1)

ጄክ ሸይኹና በሚለው አ'ሸይኽ ዐብዱል ዓዚዝ አ'ረይስ ላይ ሆን ብሎ ቀጥፏል!


ወንድማችን ሙራድ፦  “አልፋዝ ሙጅመላን " (ስፔስፊካሊ ጂስምን) ዓለል ኢጥላቅ ነፍይ ማድረግ ይቻላል ያለ ዓሊም ጥቀስ ሲለው ወንድም 'ጄክ' ዐብዱል አዚዝ አረይስ ብሎ 'ማስረጃ' ብጤ አቅርቦ ነበር 

ያቀረበው ማስረጃ ይህ ነው፦

”فإذا قيل لك: هل نُثبت لله يداً جارحة؟ فلا يصح أن نستفصل فيه؛ لأن معنى جارحة أي مخلوقة،.......ولا يُقال إنه لفظٌ مجمل ويُستفصل فيه، بل يُنفى عن الله، ذكر ذلك شيخ الإسلام ابن تيمية
“ለአላህ የሰውነት አካል(ጃሪሃ) የሆነ እጅ እናጸድቃለን ብትባል? ኢስቲፍሳል (የዝርዝር ማብራርያ) ማስቀመጡ ትክክል አይሆንም። ምክንያቱ የጃሪሃ ትርጉም ፍጡር ማለት ነው። ....... (ጃሪሃ ሚለው) ጥቅል ቃል ነው ተብሎ ወደ ዝርዝር አይገባም ይልቁንም ከአላህ በጥቅሉ ውድቅ ይደረጋል ልክ ኢብን ተይሚያህ እንዳወሳው” (ዐብዱል አዚዝ አረይስ)

ይህ እንግዲህ በምን መልኩ ለሱ ማስረጃ መሆን እንደቻለ በሰዓቱ ግራ የሚያጋባ ነበር።

የውይይቱ መነሻ ለፍዝ ሙጅመል ስለሆነው ጂስም እንጂ ጃሪሃ የሚለው አልነበረም።

በሁለቱ ቃላቶች መካከል ራሱን የቻለ ልዩነቶች አሉ። ነገር ግን አዋቂ ለመባል በየርዕሱ ሲዘል የነበረው ጄክ ይህን እንደማስረጃ አቅርቧል! ይህን ማስረጃ ማቅረቡ ስህተት ነው ብቻ ተብሎ የሚታለፍ ሳይሆን ወደ መነሻው (አ'ሸይኽ አረ'ይስ ንግግር ስንመለስ ጄክ ሆነ ብሎ የሚያምታታ ሙለቢስ መሆኑ ግልጽ ይሆናል)

    እንዴት ማለት ደግ?

ጄክ የጠቀሰው ማስረጃ ሼኽ ዐብዱልአዚዝ አረ'ይስ ሳፋሪኒይ ላይ ከሰጡት ማብራርያ (اللآلى المضيئة عل العقيدة السفارني) ነው። እሱ የተጠቀመው ማስረጃ ገጽ 46 ላይ የተቀመጠውን ንግግር ሲሆን ገጽ 44 ላይ ያለውን ለምን ዘለለው?

በሚያጅብ ሁኔታ ሸይኽ አረ'ይስ  “ሳፋሪይኒይ" ከአላህ ጂስም ፣ ዓረድን እንዲሁም ጀውሀር ነፍይ (በጥቅሉ ውድቅ ) ማድረጉ ተሳስተዋል ብለው ቅድምያውኑ አስቀምጠዋል። ውይይቱም ደግሞ ጁስምን ዓለል ኢጥላቅ ነፍይ ማድረግ ይቻላል ወይ የሚል መሆን ልብ ይባል!


አል-ዓላመቱ ሳፋሪኒይ እንዲህ ይላል፦


​وَلَيْسَ رَبُّنَا بِجَوْهَرٍ وَلاَ ۞۞۞ عَرَضٍ وَلاَ جِسْمٍ تَعَالَى ذُو الْعُلاَ

ሼይኽ ዓብዱልአዚዝ ይህንን ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፦

”​سيأتي الكلام على الجوهر والعرض والجسم في آخر المنظومة، لكن النفي هذا لا يصح عند أهل السنة؛ لأن عند أهل السنة قاعدة: الألفاظ المجملة لا تُنفى ولا تُثبت ولابد من التفصيل فيها، فإذا قيل: الله جسم، فهذا لفظٌ مجمل، فلابد من الاستفصال فيه، فلا يُنفى ولا يُثبت، ومثل ذلك العرض والجوهر ...إلخ، والسفاريني أخطأ لما نفى الجميع بلا استفصال، وهذه الملاحظة الثامنة.“
( ስለ ጀውሀር፣ ስለ ዓረድ ፣ ስለ ጂስም በግጥሙ መጨረሻ ላይ ይመጣል። ነገር ግን ይህን ከአላህ ውድቅ ማድረግ አህሉ ሱና  ጋር ትክክል አይደለም ። ምክንያቱም አህሉ ሱና ጋር መርህ አለ እርሱም “ ጥቅል የሆኑ ቃላቶች አይፀድቁምም ፤ ውድቅም አይደረጉም።  አላህ ጂስም ነው ወይ ከተባለ ይህ ቃል ጥቅል ነው ። ማብራርያ መጠየቁ ቅሮት የለውም ኢስባትም ነፍይም አይደረግም ዓረድም ጀውሀርም ልክ እንደዚሁ ......  ሳፋሪኒይ እነዚህን ቃላት ባጠቃላይ ሳያብራራው ውድቅ ያደረገ ጊዜ ተሳስቷል ይህ ስምንተኛ  ሙላሃዛ (ትኩረት ሚሰጠው ) ነው።

​ልብ በሉ ይህ የሸይኽ ዐብዱልዓዚዝ ንግግር ከአጀንዳው ጋር ቀጥታ የተገናኘ ነው። ሳፋሪኒይ ጂስምን ከአላህ ነፍይ ማድረጉ ስህተት ነው እያለ ነው። ከአላህ ጂስምን ኢጥላቀን ነፍይ ማድረግ ይቻላል ያለ ዓሊም አምጣ ሲባል “ ወላ ዩቃሉ አነሁ ለፍዙን ሙጅመል ወዩስተፍሰሉ ፊሂ በል ዩንፋ ዓኒ ላህ" በሚል ስለ ጃሪሃ ያስቀመጡትን እንደ መረጃ አምጥቷል ይህ ምን ዓይነት ስራ ነው ቢላህ ዓለይኩም?


ምን ዓይነት ማድበስበስ እና ማወጫበር ነው?  ሼኹ ጃሪሃ ለፍዝ ሙጅመል አይደለም ምንም አይነት እስቲፍሳል አያስፈልገውም ኢጥላቀን ነፍይ ማድረግ ይቻላል በሚል ተንቢህ የሰጡበትን ጂስም ዓለል ኢጥላቅ ነፍይ ማድረግ ይቻላል ብለዋል ብለህ ይህን ማስረጃ ማምጣትህ ትልቅ ስህተት ከመሆኑ ጋር ስለጂስም የተናገሩበት አውድ ላይ ሆነህ ግን “ጂስም ነፍይ ማድረግ ስህተት ነው የሚለውን ቆርጠህ" ጂስም በጥቅሉ ውድቅ ማድረግ ይቻላል ብለዋል በሚል ይህን ማምጣት ግን ማጭበርበርና ማድበስበስ አይደለም ወይ? ( በዲን ስም ማወጫበር ሱብሃነከ ረቢ!! )


የጃህሚያ ፣ የአሽዓሪያ መደበቅያ ለሆነ አቋም ሸይኽ አ'ረይስ ላይ መቅጠፍ ወላሂ ከባድ ወንጀል ነው። ሼኹ ላይ ዋሽተሃል አውፍ እንዲሉህ ጠይቃቸው


በዚህ ውይይት ሌሎች ማወጫበሮች ጊዜ ሳገኝ እቀጥላለሁ። ይህ ዲን ነው ወላህ!!

https://t.me/comparativeerror
🔥116😁3
ይህን አድበስባሽ ሸይኽ ተመልኩቱት ለአላህ ብላቹ

ጂስም ሙጥለቅን ነፍይ ይደረጋል ያለ ጥቀስ ሲባል ገጽ 46 ላይ ያለው “ጂራሃ ሙጥለቀን ነፍይ ይደረጋል ሚለውን ማስረጃ አመጣ" ነገር ግን ገጽ 44 ላይ ጂስም ሙጥለቀን ነፍይ እንደማይደረግ ሼኹ ተናግሮ ነበር!!!


ይህ ጊሽ(ማታለል) ነው ወላሂ !! አማ እልህ ነው ምናምን ሚነዛውን ተከታዮችን አዕምሮዋቸውንና ጆሮዋቸውን ለመድፈን ሚነዛውን ልከውልኝ ነበር ። ሼኽ አድበስብስ ወላሂ ይህ እልህ አይደለም ይህ ዲን ነው። መሳሳትህ አልፎ የዐለማእን ንግግር ሆነ ብሎ ለማምታት መጠቀም "ዓቃቢ" ነኝ ከሚል አይጥበቅም።
😁4🔥31