የኢብን ተይሚያህ ኑሱሶች !
ደብሮኝ እንጂ ከኢብኑ ተይሚህ ብቻ ብዙ ማዝነብ ይቻላል አንቡትና ጄክ ያለውም ደግሞ ተመልከቱ።

❤8🔥2
ሼይኽ ሳሊህ አ'ሲንዲይ ሚሉትን ተመልከት! (ከዛን ጄክ ሚለውን ተመልከቱ)
ጄክ
“አላሁ መውጁዱን ቢላ መካን” ይባላል
“አላህ ጂስም አይደለም” ይባላል
ወንድሜ መስአላው ላይ ስተሃል ተመለስ ወደ ሀቁ!
https://t.me/Hardsalafi
ጄክ
“አላሁ መውጁዱን ቢላ መካን” ይባላል
“አላህ ጂስም አይደለም” ይባላል
ወንድሜ መስአላው ላይ ስተሃል ተመለስ ወደ ሀቁ!
https://t.me/Hardsalafi
👍7😁2❤1
Forwarded from ᒪEYᒪᗩ тяυтн_ѕєитιиєℓ (Amir zeynu)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መተራረም ከዲን ነው የሰዎችን ዓይብ መከታተል ግን ኬት ነው?
ንጽጽር ላይ ዲናዊ መስአላ ሲገድፋ አንዱ አንዱን
ለምን አያርመውም? ሲባል አንዱ የአንዱን የግል ነውር አፈንፍኖ ስለደረሰበት ነው ብሏል ኢንጀነር። ማታም የተፈጠረው ይህ ነው። ወንድማችን በጠዋፍ መኀከል መሰል የሰማትን ወሬ አፈንፍኖ ለስህተቱ መደበቅያ አድርጎታል። እኔንን ዝም እንድል ሊያደርገኝ ፈልጎ ነበር። በሁለት ሳምንት ውስጥ እንድከፍልና አይለመደኝም የሚል ይቅርታ ድምጽ ለአበዳሪዋ እንድልክ ፈልጎ ነበር አለበለዝያ እነደሚፖስተው ነገረኝ ። (በሱ ሀሳብ ፋይል ልይዝብኝ) እኔ ደግሞ እንዲ ያሸረገደ ሜንታሊቲ ሊኖረኝ ስለማይችል ለአበዳሪዋ ራሱ ብርሽን ምሰጥሽ በኢጎ የተወጠረ ማንነቱ እኔን በማስጠንቀቅ ፖስቶ ገሀድ ሲወጣ ነው ብዬ ቁዳሁለት። ድምጹን ቅድምያ ልኬላቹ ነበር ሰው ከሰማው ቡኃላ ደልቼዋለሁ የፈለገው ወንድማችን ቤት ሄዶ ያዳምጠው። ቅድምያ የላኩትን ነው የላከው።
ያኢኽዋኒ ፊላህ በአላህ ሲትር ምኖር ሰው ነኝ። መዝገቤ በሙሉ በድብቅ ነውሮች እና ወንጀሎች የቶሞሉ ናቸው። ዲን ላይ ተሻጋሪ ስህተት ነው ብዬ በተሳሳታቹ ቁጥር ሳርማቹ ይቅማል ያጭሳል በሚል ተደብቄ የምሰራውን ወንጀል መዘገብ ከሆነ መልሳቹ አላህ ወንጀሌን ሊያብስልኝ ፈልጎ እንደሆነ መረዳት አያቅተኝም። ሸክረን ለኩም ወጀዛኩሙለሁ ኸይረን።
ሌላ ምታረመው ዑምራ በሴት ብር አልሄድኩም ብሏል ከሆነ እሰየው አብዛኛው ስለሄደ እንደዛ መስሎኝ ነው። ብሯን ወዲያው ሲለጥፈው በመክፈሌ ፈርቶ ነው ብሏል ።ካለጠፈው አልከፍልም የሚል ሸርጥ ያስቀመጥኩት እኔ😁
ወዲየውኑ አየር ላይ በመከፈሉ ስለደበረው ብዙ የዘረፈው ሐብት አለው ብሎ ደንግጧል ተው ይህን ያህል ሚያስለጥጥ ነገር የለም ለጉዳዩ ማጠራቀም ከጀመርኩ ቆይቷል አንተ ሳታውቅ በፊት ሀቋ ሀቅ ነው ይመለሳል።

👍8🥰6👎1
Forwarded from ᒪEYᒪᗩ тяυтн_ѕєитιиєℓ (Amir zeynu)
ከጉዳዩ ጋር በተያየዘ አኺሩል ቀውል .....
ረድ የጀመርከው ይህ ሲታወቅ ነው አሉ ለወንድማችን ሆነ ለሌላው አላህ ምትፈሩ ከሆነና እርግጠኛ ከሆናቹ ለአደባባይ ሙበሐላ ( መረጋገም) እጠራቹሁለሁ። ወላሂ ይህን ጉዳይ አላየሁትምም ልብም አላልኩትምም ነበር)
የሰማሁትም ከአበዳሪዋ ሀይዋኑን ናጢቅ ላይ ቢያስትካካከው ካልኩ ብቻ ቡኃላ ነው።
ምኑ ከምኑ ነው ያገናኙት በረቢ¡ (ሲደግፈኝ ነበር የሚለው ድምጽ መስአላው አልገባኝም ነበር ካልኩት ፎቶ እየለጠፈ ረድ ያደርጋል ዓቅል ግን አለን?)
የአኺ ማታውን ሙሉ ማይረባ ነገር ስትቸከችክ ነው ያደርከው ከዛ ይልቅ ናጢቅ ሚለውን በሶስት ፊደል "አሳቢ" ብለህ ብትለውጠው አይቀልም?.
Silent ታዛቢዎችም ይኖራሉ!!)

👍21❤9🥴3
Audio
ሼኽ ፈውዛን “አላህ መውጁዱን ቢላ መካን" የሚለው ዑሉውን ማስተባበል ነው ይሉናል። ወንድም ጄክ ደግሞ ኢጥላቀን “አላህ መውጁዱ ቢላ መካን" ይባላል ይላል።
ሼኽ ፈውዛንን ወይስ ጄክን?
ይህንን ንግግሩን ከቻናሉ ደልቶታል መሰለኝ ላገኘው አልቻልኩም ነገር ግን አላህን ፈርተህ የማይባል እንዳልክ እውቅ። ዑለማዎች ሻዝ የሚሆኑባቸውን ቀውል እየተከታተልክ አዲስ ነገር ያመጠን ማስመሰል አግባብ አይደለም።
“አላሁ መወጀዱን ቢላ መካን”
የሙብተዲዓዎች ሺዓር(መገለጫ) ነው።የአላህን ከአርሽ በላይ መሆኑ የሚክዱ ጠማሞች የዕለተ ዕለት መፈክርን እንዲህ በልቁ ማለት ይቻላል እንዴት ትላለህ?
ሀቅን ከውሸት መደብለቅ ያለው ንግግር ነው። ሀቅን ፍንትው አድርጎ ማስቀመጥ እንጂ ማድበስበስ አያስፈልግም። የአህባሽና የአሽዓሪያ ተፅእኖ ስር ወድቀህ ነው? ወይስ ነጥብህ ምንድነው?
https://t.me/comparativeerror

❤17👍9👎6👏2
ወደ ሀቅ መመለስ በባጢል ላይ ከመዘውተር አስር እጥፍ የተሻለ ነው። ጄክ ላለመታረም እርስ በእርሱ እየተጋጨ ነው።
jake፦ “ሚን ባቢል ኢኽባር አላህ ላይ ስንጠቀም ከሁሉም አቅጣጫ መጥፎ ትርጉም ሚያስይዝ መሆን የለበትም”
ይለንና
Jake መልሶ፦ “አላህ ያለ ቦታ ነው ተብሎ ኢጥላቀን መናገር ይቻላል" ይልሃል)
አላህ ያለ ቦታ ነው ሚለው ቃል ከሁሉም አቅጠጫ ንጹህ ነውን? ( ንጹህ ስላልሆነስ አይደል ተፍሲል እያደረክ ያለከው።) ስለዚህ ለምን "አላህ ሙውጁዱ ቢላ መካን" ኢጥላቀን ማለት እንደማይቻል አታስቀምጥም? መሳሳትህ ግልጽ ነው አትገትር አላህን ፍራ!!

👍17❤2😐2😁1
ዓጀበን ሊአምሪከ !!
ሸይኽ አድበስብስ “ዛት ሚል ለአላህ አልመጣም” አለ
ኡስታዝ ወሂድ ፦ “ አረ በሐዲስ መጥቷል"
ሲለው
ሸይኽ አድበስብስ፦ “ሐዲሱ ደዒፍ ነው” አለ
ኡስታዝ ወሂድ፦ “ ቡኻሪይ ላይ አለ" ሲለው
ሸይኽ አድበስብስ ፦ “አረይስ ይጠቅሱታል..." ይላል አረ ጌታዬ
ሸይኽ አድበስብስ እውነትን ከማድበስበስ ውጭ አላወቁም ነበር፣ ተሳስቻለሁ ከአፋ አይወጣም።
ያሃ ሁሉ ከተራገጠ እና ከተሳደበ ቡኃላ ውይይት ጠራኝ ይህም ከተልቢሱ ነው።ውይይት ከፈለክ ከመሳደብህ በፊት አጠራኝም ነበር🤧
ማድበስበስ ማለባበስ መሸፋፈን ላይ expert ነው።

👍10😁6👎2❤1
እርምት
ወንድም አቡበከር ድብቅ ብዥታዎች በሚለው መጽሀፉ ሙስጠላህ በተመለከተ ያስቀመጣቸው ጥሩ ነጥቦች አሉ። እንደ ማንኛውም ሰው የተፈጸሙ አንዳድ ስህተቶችም በተጨባጭ አሉ። እኝህን ማረሙ የአርትዖት ሰሪዎች ስራ ቢሆንም ዝም ስለተባሉ እኔ ላርማቸው ወድጅያለሁ።
ከነዚህም ውስጥ ወንድም አቡኪ ድብቅ ብዥታዎች ገጽ 19 ላይ እንዲህ ይላል “እነዚህ የጠቅስናቸው ሙርሰሎች በሙሉ ደዒፍ ናቸው። ምክንያቱም በታቢዕዩ እና በነብዩ መካከከል ያለ መካከለኛ (ሰሀባ) ባለመኖሩ!!”
ይህ ገለጻ ሙርሰልን ለመጣል ትክክለኛ ምክንያት ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም እንዲህ ከሆነ ሙርሰሉ ሰሃባም ተቀባይነት የለውም። ሰሃባ ኢርሳል ሲያደርግ በእርሱና በነብዩ መሐከል ያለውን ሰሀባ ጥሎ ነው። ታድያ ይህ ውድቅ ነውን ስንል?
ወንድማችን ራሱ ሙርሰሉ ሰሃባ ተቀባይነት እንዳለው ቅድምያ ተናግሮ ነበር (ፈአህሰነ ወአጃደ) ። እንዲህ ይላል፦“አው የሰሀቦች ኢርሳል ተቀባይነት አለው ምክንያቱም ሰሀቦች በአብዛኛው የሚያስተላልፉት ከሰሀቦች ነው። ሰሀቦች ደግሞ ታማኞች መሆናቸው እሙን ነው”
(ድብቅ ብዥታዎች ገጽ 18)
ሰሃቦች ከመልእክተኛው ቀጥታ ያልሰሙትን ሲያስተላልፉ የነገራቸውን ሰሃባ ጥለው ነው ይህን ተቀባይነት አለው ካለ ሙርሰል ደካማ የሆነው “በታቢዕዩ እና በነብዩ መካከከል ያለ መካከለኛ (ሰሀባ) ባለመኖሩ" ማለቱ ትርጉም አይሰጥም።
ጤነኛ አንባቢ ሙርሰሉ ሰሀባ ላይም እኮ “በሰሀቢዩና በነብዩ መካከል ያለ መካከለኛ ሰሀባ የለም” ብሎ ሊጠይቅ ይችላል! ስለዚህ ወንድማችን እዚህ ጋር ሳያውቀው ገድፏል ይታረማል!
{ሙርሰል ተቀባይነት የሌለው ለምንድነው?}
ሙርሰል ማለት ታቢዕይ (የሰሀቦች ተከታይ) ወደ ነብዩ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ያልሰማውን ሲያስጠጋ የሚሰጠው ስያሜ ነው። ይህ ዓይነቱ ዘገባ ተቀባይነት አለው ወይስ የለውም የሚለው በዑለማዎች መካከል ልዩነት ያስተናገደ ነጥብ ነው። ነገር ግን ትክክለኛው አቋም የሙርሰል መሰረቱ ደዒፍ ነው የሚለው አቋም ሲሆን ለዚህም ደግሞ ጤናማ የሆነ ለትችት ክፍት ያልሆኑ ምክንያቶችን ደርድረዋል።
ዋነኛው ታቢዕይ ከመልእክተኛው ሲያወራ ይህን ዘገባ ቀጥታ ከሰሀባ ወስዶት ሊሆን ይችላል ወይም ከታቢዕይ ሊሆን ይችላል የሚል ይሁንታ በመኖሩ ነው። ከታቢዕይ ሊሆን ይችላል የሚለው ይሁንታን ከከፈትን ይህ ታቢዕይ ሲቃ ነው ወይስ ደዒፍ የሚለው ይሁንታ በቅድምያነት ይከፈታል ማለት ነው።
ይህ ደግሞ ሙርሰል መርዱድ ውስጥ ለማካተት ዋነኛው ነጥብ ነው።
ስለዚህ ሙርሰል ደካማ የሚሆነው “መሀከል ላይ የተጣለው አካል ማን እንደሆነ ስለማይታወቅ" ነው። ሰሀባ ብቻ እንደተጣለ ቢረጋገጥ ኖሮ ሙርሰል ደካማ አይሆንም ነበር። ሰሀባውን አለማወቃችን ሐዲሱ ላይ የሚያመጣው ተፅእኖ የለም።
ኢማሙ ቲርሚዚይ እንዲህ ይላል፦
አል-ሃፊዙ ኢብን አብዱልበር እንዲህ ይላል፦
አል-ሃፊዙ ስዩጢይ እንዲህ ይላል፦
ስለዚህ ሙርሰል ሐዲስ ውድቅ ሚሆነው ሰሀባው ስለተጣለ ሳይሆን ሰሀባ ብቻ ነው ወይ የተጣለው? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ስለማይቻል ነው። ታቢዕይ ከታቢዕይ የሚያወራበት እድል በጣም የሰፋ ስለሆነ ታቢዕይ ቀጥታ ከረሱል ሲያወራ ሰሃባ ብቻ ነው የተጣለው ብሎ መደምደም የሚቻል ስላልሆነ ነው ደካማ የሆነው።

: ومَنْ ضَعَّفَ المرسلَ فإنه ضَعَّفَهُ من قِبَلِ أَنَّ هؤلاء الأئمةَ قد حَدَّثوا عن الثقاتِ وغيرِ الثقاتِ ، فإذا روى أحدهم حديثاً وأرسَلَهُ لعلهُ أخذه عن غير ثقةٍ .وقد تكلَّمَ الحسنُ البصريُّ في مَعْبَدٍ الجُهَنِيِّ ، ثم روى عنه ! .
“ሙርሰልን ደካማ ያደረጉት ደካማ ያደረጉበት ምክንያት እነዚህ አኢማዎች ከሲቃም ሲቃም ካልሆነም አካል ስላወሩ ነው። አንዱ 'ታቢዕይ' ሀዲስን አውርቶ ሰነዱን ካልጠቀሰው ከሲቃ ካልሆነ አካል ይዞት ሊሆን ይችላል (የሚል ይሁንታ አለ።) ሀሰን አል-በስሪይ መዕበድ አል-ጁሐኒይ ከመተቸቱ ጋር አስተላልፎለታል” (ዒለሉ ሰጊር )
አል-ሃፊዙ ኢብን አብዱልበር እንዲህ ይላል፦
وحجتهم في رد المراسيل ما أجمع عليه العلماء من الحاجة إلى عدالة المخبر وأنه لا بد من علم ذلك، فإذا حكى التابعي عمن لم يلقه، لم يكن بد من معرفة الواسطة، إذ قد صح أن التابعين أو كثيراً منهم، رووا عن الضعيف وغير الضعيف، فهذه النكتة عندهم في رد المرسل، لأن مرسله يمكن أن يكون سمعه ممن يجوز قبول نقله، وممن لا يجوز، ولا بد من معرفة عدالة الناقل، فبطل لذلك الخبر المرسل للجهل بالواسطة.አል-ሃፊዙ ኢብን ሐጀር እንዲህ ይላል፦
ሙርሰልን በመመለስ ላይ ማስረጃቸው ዑለማዎች የተናጋሪውን ዐዳለነት ማወቅ ግድ ነው በሚለው ስምምነታቸው ላይ የቆመ ነው። ታቢዕይ ካልተገናኘው አካል ካስተላለፈ መሐከል ላይ ያለውን ማወቅ ግድ ማለቱ ቅሮት የሌለው ነው። ምክንያቱም ታቢዕዮች ወይም አብዛኞቹ ታቢዕዮች ከደካማም ከታማኝም አስተላልፈዋል። ሙርሰልን ለመጣል ያመጡት ይህችን ነጥብ ነው። ምክንያቱም ሰነዱን የጣለው አካል ሊተላለፍለት ከሚገባ ይዞት ሊሆን ይችላል ላይሆንም ይችላል የዘጋቢውን ዓዳላ ማወቅ ደግሞ ቅሮት የሌለው ግዴታ ነው። ለዚህም ሲባል ሙርሰል መሐከል ላይ የተጣለው ስላልታወቀ ውድቅ ይደረጋል” (ሙቀዲመቱ ተምሂድ)
”(المرسل) وإنما ذُكِرَ في قِسْمِ المردود للجهل بحال المحذوف؛ لأنه يُحتمل أن يكون صحابيًا، ويُحتمل أن يكون تابعيًا.
وعلى الثاني يُحتمل أن يكون ضعيفًا، ويُحتمل أن يكون ثقةً، وعلى الثاني يُحتمل أن يكون حَمَلَ عن صحابي، ويُحتمل أن يكون حَمَلَ عن تابعي آخر، وعلى الثاني فيعود الاحتمالُ السابقُ، ويتعدد. أمّا بالتجويز العقلي فإلى ما لا نهاية له، وأمّا بالاستقراء فإلى ستةٍ أو سبعةٍ،“
«ሙርሰል በደካማ ክፍል ውስጥ የተመደበው የታጠለው አካል ስለማይታወቅ ነው። ምክንያቱም ሰሀቢይ ሊሆን ይችላል ታቢዕይም ሊሆን ይችላል ታቢእይ ይሆናል ካልን ይህ ታቢእይ ደካማ ሊሆን ይችላል ሲቃ ሊሆን ይችላል ይህ ታቢእይ ሲቃ ይሆናል ካልን ራሱ አሁንም ከሰሀቢይ ይዞት ሊሆን ይችላል ወይም ከሌላ ከታቢእይ ይዞት ሊሆን ይችላል። ከታቢእይ ይዞት ሊሆን ይችላል ካልን ያሳለፍነው ይሁንታ ተመልሶ ይመጣል። ዓቅል በሚፈቅደው በዚህ መልኩ ገደብ እስከሌለው ድረስ መቀጠል ይቻላል በተጨባጭ በመገኘቱ ግን ወደ ስድስት እና ሰባት ታቢዕዮች 'ይኬዳል'።” (ኑዝሀቱ ነዘር)
አል-ሃፊዙ ስዩጢይ እንዲህ ይላል፦
”( ثم المرسل حديث ضعيف ) ، لا يحتج به ،.......... والنظر للجهل بحال المحذوف ، لأنه يحتمل أن يكون غير صحابي ،وإذا كان كذلك ،فيحتمل أن يكون ضعيفاً “
«(ሙርሰል ደካማ ሀዲስ ነው) ማስረጃ አይደረግበትም... የተጣለው አካል ማን እንደሆነ ማወቅ አለመቻላችንን ከማየት አንጻር ምክንያቱም የተጣለው ከሰሃባ ውጭ የሆነ አካል ሊሆን ይችላል ይህ ከሆነ ደግሞ የተጣለው ደካማ ዘጋቢ ሊሆን ይችላል» (ተድሪቡ ራዊ )
ስለዚህ ሙርሰል ሐዲስ ውድቅ ሚሆነው ሰሀባው ስለተጣለ ሳይሆን ሰሀባ ብቻ ነው ወይ የተጣለው? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ስለማይቻል ነው። ታቢዕይ ከታቢዕይ የሚያወራበት እድል በጣም የሰፋ ስለሆነ ታቢዕይ ቀጥታ ከረሱል ሲያወራ ሰሃባ ብቻ ነው የተጣለው ብሎ መደምደም የሚቻል ስላልሆነ ነው ደካማ የሆነው።
https://t.me/comparativeerror
❤12👏9⚡3😁2🔥1
Sαlαh Responds ࿈
ነገረ-ተሕሪም የሱረቱል ተሕሪም (ምዕራፍ 66) ሰበብ አን-ኑዙል (Historical background) ሁለት መሆናቸው ይታወቃል፣ አንደኛው በቡኻሪ መጽሐፍ 68 ሐዲስ 17 ላይ የተጠቀሰው ሲሆን ነቢዩ ከዘይነብ ቤት ማርን በልተው ሌላኛው ሚስታቸው ስትቀና (የሴት ነገር ታውቁ የለ Hhh) እርሷን ላለማስከፋት ብለው ጣፋጩን ማር በራሳቸው ላይ እርም ሲያደርጉ አላህ «ለአንተ የፈቀደልህን ነገር ሚስቶችህን ማስወደድን…
ለነገረ-ተሕሪም የተሰጠ ማስተካከያ
ሱረቱ ተሕሪም የወረደበት ምክንያት ላይ ወንድማችን ሳላህ አንዱን ምክንያት አስበልጦ ሌላኛው ጥሎ ነበር። አንዱን ጥሎ ሌላኛውን ማስበለጡ በራሱ ራሱን የቻለ ስህተት ቢሆንም ይህን ስህተት የፈፀመበት አግባብ ደግሞ ከስረ መሰረቱ የተበላሸ ነው።
ወንድማችን ሳላህ እንዲህ ይላል፦
“ታድያስ ከሁለቱ ሰበብ አን-ኑዙሎች የትኛው ነው ትክክል ? መቼም ሁለቱም በአንዴ ልክ ሊሆኑ አይችልም ! ስለዚህ የቁርኣኑ አንቀጽ የወረደው ለማሩ ጉዳይ ነው ወይስ ለማሪያ?..... ”
Yh ንግግሩ ላይ “መቼም ሁለቱም በአንዴ ልክ ሊሆኑ አይችልም” ሚለው ትልቅ የመነሻ ስህተት ነው። አንድ የቁርዓን አንቀፅ ከአንድ በላይ አስባበ ኑዙል ሊኖረው ይችላል።
ለአንድ የቁርዓን አንቀጽ ከአንድ በላይ ሰበቦች (ምክንያቶች) ከተለያዩ ሰሀቦች ሲጠቀስ ቅድምያ ጀምዕ (መሰብሰብ) እንጂ ወደ ተርጂህ (አንዱን ለመጣልና ሌላኛውን ለማስበለጥ አይሮጥም) ። ከሚሰበሰብበት መንገዶች ውስጥም ሁለቱን እዚህ ጋር ማስቀመጥ ወደድኩ።
የመጀመርያው የተለያዩ ሰበቦች ለቁርዓኑ አንቀጽ መውረድ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ የሚለው ይሁንታ ነው።ማለትም ከአንድ በላይ ክስተቶች ቢኖሩና አንደኛው ሰሀቢይ ይህ አንቀጽ ለዚህ ምክንያት ነው የወረደው ቢል ሌላኛው ደግሞ ሌላ ምክንያት ቢጠቅስ በነዚህ ምክንያቶች መኃል ሰፊ የጊዜ መራራቅ እስከሌለ ድረስ የቁርዓኑ አንቀጽ በሁለቱም ምክንያት ላይ ወርዷል ሊባል ይችላል።
አል-ሃፊዙ ስዩጢይ እንዲህ ይላሉ፦
ለምሳሌ አያቱ ሊዓን “የመረጋገም አንቀጽ" (ሱረቱ ኑር ከ 6-9) ያለው ኢማሙል ቡኻሪይ በዘገበው ሀዲስ በሂላል ኢብን ኡመያ ምክንያት ነው የወረደው የሚል ሲሆን ሁለቱ ሸይኾች (ቡኻሪና ሙስሊም በጋራ ባወጡት ) ደግሞ ከሰሕል ኢብን ሰዕድ ላይ ተንተርሰው በዑወይሚር አል-ዓጅላኒ ምክንያት ነው የወረደው የሚል ነው።
እንደወንድማችን አካሄድ መሰረት “መቼም ሁለቱም በአንዴ ልክ ሊሆኑ አይችልም” ብለን አንዱን ወደ መጣል ሊገባ ነበር ነገር ግን ጀምዕ ማድረግ እየተቻለ ወደ ተርጂህ መሮጥ ጥንቁቅነትን የተላበሰ አካሄድ አይደለም።
ኢማሙ ስዩጢይ ከኢብን ሐጀር ይዞ ይህን የአያቱ ሊዓንን ሰበቦች በተመለከተ ንግግራቸውን ነቅል (Qoute) ያደርግልናል፦
ስለዚህ ለአንድ የቁርዓን አንቀጽ ከአንድ በላይ ምክንያቶች ሊመጡለት በሚችልበት ሁኔታ “መቼም ሁለቱም በአንዴ ልክ ሊሆኑ አይችልም” ማለት “አንድ የቁርዓን አንቀጽ አንድ ሰበብ ብቻ ነው ሚኖረው" ከሚል የተሳሳተ ቃዒዳ መነሳት ነው።
በአያቱ ሊዓን ዙርያ ኢብን ሐጀር እንዲህ ይላሉ
ሁለተኛው አፕሮች በመጀመርያው መልኩ መሰብሰብ ካልተቻለ የቁርዓኑ አንቀጽ ተደጋግሞ ወርዷል ማለት ይቻላል። አንድ የቁርዓን አንቀጽ በተደጋጋሚ ለተለያዩ ምክንያቶችም የሚወርደበት ሁኔታ እንዳለ ግልጽ ነው።
አል-ሀፊዙ ስዩጢይ እንዲህ ይላሉ፦
ለምሳሌ ይህን የቁርዓን አንቀጽን ያዙ
مَا كَانَ لِلنَّبِىِّ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَن يَسۡتَغۡفِرُواْ لِلۡمُشۡرِكِينَ
(ሱረቱ ተውባ:113)
ሁለቱ ሸይኾች (ቡኻሪና ሙስሊም) መልእክተኛው ለአቡ ጧሊብ ማሀርታን ጠይቆ እንደወረደ የሚያመላክት ዘገባ አስፍረዋል።
አል-ኢማሙ ቲርሚዝይ ሀሰን ባደረገው ሀዲስ ዓሊይ (ረዐ) አንድ ሰውን “ አባትህ ሙሽሪክ ሆኖ እስቲግፋር ትጠይቅለታለህ ወይ?” ብሎ ሲጠይቀው ሰውዬው “ኢብራሂም አባቱ ሙሽሪክ ሆኖ ጠይቋል" ብሎ ሲመልስለት ዓሊይ ጉዳይን መልዕክተኛውን ሲጠይቃቸው ነው ይህ አንቀጽ የወረዳው የሚል አስፍሯል።
አል-ኢማሙል ሃኪም በዘገበው ደግሞ መልእክተኛው ለእናታቸው ኢስቲግፋርን መጠየቅ ፈልገው አንቀጹ እሳቸውን በመከልከል ነው የወረደው ሚልን ዘግቧል
የቱ ነው ትክክል? ወንድማችን ሳላህ እንደሚለው ከሆነ “መቼም ሁለቱም በአንዴ ልክ ሊሆኑ አይችልም” ብለን አንዱን ማስበለጥ ግድ ይል ነበር
ነገር ግን እንዲህ የሚባል መርሆ የለም
ዑለማዎች ይህንን አንቀጽ በተደጋጋሚ ወርዷል በሚል ልዩነቱን አስታርቀዋል። ይህ የተለመደ ነው። አንድ የቁርዓን አንቀጽ ተደጋግሞ ሊወርድ ይችላል
አል-ኢማሙ ዘርከሺይ እንዲህ ይላል፦
ኢማሙ ዘርከሺይ ለዚህ ማሳያ የተለያዩ ምሳሌዎችን ከጠቀሱ ብኃላ ሲጠቀልሉ እንዲህ ይላሉ......
ስለዚህ ወንድማችን የሰራው ስህተት ተዋራሽና ተደራሽ ስለሆነ ጽሁፍን ማስተካከል የሱ ፋንታ ሲሆን መናገር የኛ ነው።ስፔስፊካሊ ሱረቱ ተህሪም ላይ እርምቱ ይቀጥላል...

الحال الخامس : أنْ يُمكِنَ نزولُها عَقِبَ السَّبَبَيْن أو الأسبابِ المذكورةِ بأن لا تكون معلومة التباعد، كما في الآيات السابقة، فيُحْمَلَ على ذلك.«(አምስተኛው ሁኔታ : በሁለቱ ወይም በተወሱት ሰበቦች ምክንያት መጨረሻ ላይ መውረዱ ሊያስመች ነው። ግና በምክንያቶቹ መሀል ረጅም የጊዜ ርቀት አለመኖሩ ሊታወቅም ነው። ልክ እንዳለፉት አናቅጽቶች ፣ (ካልታወቀ) በዚህ ላይ ይያዛል»(ኢትቃን)
ለምሳሌ አያቱ ሊዓን “የመረጋገም አንቀጽ" (ሱረቱ ኑር ከ 6-9) ያለው ኢማሙል ቡኻሪይ በዘገበው ሀዲስ በሂላል ኢብን ኡመያ ምክንያት ነው የወረደው የሚል ሲሆን ሁለቱ ሸይኾች (ቡኻሪና ሙስሊም በጋራ ባወጡት ) ደግሞ ከሰሕል ኢብን ሰዕድ ላይ ተንተርሰው በዑወይሚር አል-ዓጅላኒ ምክንያት ነው የወረደው የሚል ነው።
እንደወንድማችን አካሄድ መሰረት “መቼም ሁለቱም በአንዴ ልክ ሊሆኑ አይችልም” ብለን አንዱን ወደ መጣል ሊገባ ነበር ነገር ግን ጀምዕ ማድረግ እየተቻለ ወደ ተርጂህ መሮጥ ጥንቁቅነትን የተላበሰ አካሄድ አይደለም።
ኢማሙ ስዩጢይ ከኢብን ሐጀር ይዞ ይህን የአያቱ ሊዓንን ሰበቦች በተመለከተ ንግግራቸውን ነቅል (Qoute) ያደርግልናል፦
قال الحافظ ابن حجر: اختلف الأئمة في هذه المواضع فمنهم من رجح أنها نزلت في شأن عويمر ومنهم من رجح أنها نزلت في شأن هلال ومنهم من جمع بينهما بأن أول من وقع له ذلك هلال وصادف مجيء عويمر أيضاً فنزلت في شأنهما معاً وإلى هذا جنح النووي وسبقه الخطيب فقال لعلهما اتفق لهما ذلك في وقت واحد.
«አኢማዎች እዚህ ቦታ ላይ ተለያዩ
ከነሱ ውስጥ በዑወይሚር ምክንያት ነው የወረደው የሚለውን ያስበለጡ አሉ። ከነሱ ውስጥም በሒላል ምክንያት ነው የወረደው ሚለውን ያስበለጡ አሉ። ከአኢማዎች ውስጥም መጀመርያ ጉዳዩ ያጋጠመው ሂላል ቢሆንም ከዚያን የዑወይሚር መምጣት ጋርም ገጠመ ስለዚህ በሁለቱም ጉዳይ ላይ አንቀጹ ወረደ በሚል ሁለቱንም የሰበሰበ አለ ነወዊይ ወደዚህ አቋም ተዘንብሏ በዚህ ላይም ኸጢብ ቀድሞታል እንዲህ አለ፦ “ምናልባትም በአንድ ጊዜ ላይ ገጥሞላቸው ይሆናል”» (ሉባቡ ኑቁል ፊ አስባቢ ኑዙል)
ስለዚህ ለአንድ የቁርዓን አንቀጽ ከአንድ በላይ ምክንያቶች ሊመጡለት በሚችልበት ሁኔታ “መቼም ሁለቱም በአንዴ ልክ ሊሆኑ አይችልም” ማለት “አንድ የቁርዓን አንቀጽ አንድ ሰበብ ብቻ ነው ሚኖረው" ከሚል የተሳሳተ ቃዒዳ መነሳት ነው።
በአያቱ ሊዓን ዙርያ ኢብን ሐጀር እንዲህ ይላሉ
«لا مانع من تعدد الأسباب»
«ለአንቀጹ መውረድ ምክንያቶቹ መብዛታቸው ላይ ከልካይ የለም» (አል-ኢትቃን ፊ ዑሉሚል ቁርዓን)
ሁለተኛው አፕሮች በመጀመርያው መልኩ መሰብሰብ ካልተቻለ የቁርዓኑ አንቀጽ ተደጋግሞ ወርዷል ማለት ይቻላል። አንድ የቁርዓን አንቀጽ በተደጋጋሚ ለተለያዩ ምክንያቶችም የሚወርደበት ሁኔታ እንዳለ ግልጽ ነው።
አል-ሀፊዙ ስዩጢይ እንዲህ ይላሉ፦
الحال السادس : ألا يُمكِنَ ذلك، فيُحمَلُ على تَعَدُّدِ النزول وتكرُّرِه،
“ስድስተኛው ሁኔታ: በተለያዩ ሰበቦች ወርዷል ሚለው ላይቻል ነው ይህን ጊዜ ተደጋግሞ ወርዷል ተብሎ
ይያዛል” (አል-ኢትቃን ፊዑሉሚል ቁርዓን)
ለምሳሌ ይህን የቁርዓን አንቀጽን ያዙ
مَا كَانَ لِلنَّبِىِّ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَن يَسۡتَغۡفِرُواْ لِلۡمُشۡرِكِينَ
(ሱረቱ ተውባ:113)
ሁለቱ ሸይኾች (ቡኻሪና ሙስሊም) መልእክተኛው ለአቡ ጧሊብ ማሀርታን ጠይቆ እንደወረደ የሚያመላክት ዘገባ አስፍረዋል።
አል-ኢማሙ ቲርሚዝይ ሀሰን ባደረገው ሀዲስ ዓሊይ (ረዐ) አንድ ሰውን “ አባትህ ሙሽሪክ ሆኖ እስቲግፋር ትጠይቅለታለህ ወይ?” ብሎ ሲጠይቀው ሰውዬው “ኢብራሂም አባቱ ሙሽሪክ ሆኖ ጠይቋል" ብሎ ሲመልስለት ዓሊይ ጉዳይን መልዕክተኛውን ሲጠይቃቸው ነው ይህ አንቀጽ የወረዳው የሚል አስፍሯል።
አል-ኢማሙል ሃኪም በዘገበው ደግሞ መልእክተኛው ለእናታቸው ኢስቲግፋርን መጠየቅ ፈልገው አንቀጹ እሳቸውን በመከልከል ነው የወረደው ሚልን ዘግቧል
የቱ ነው ትክክል? ወንድማችን ሳላህ እንደሚለው ከሆነ “መቼም ሁለቱም በአንዴ ልክ ሊሆኑ አይችልም” ብለን አንዱን ማስበለጥ ግድ ይል ነበር
ነገር ግን እንዲህ የሚባል መርሆ የለም
ዑለማዎች ይህንን አንቀጽ በተደጋጋሚ ወርዷል በሚል ልዩነቱን አስታርቀዋል። ይህ የተለመደ ነው። አንድ የቁርዓን አንቀጽ ተደጋግሞ ሊወርድ ይችላል
አል-ኢማሙ ዘርከሺይ እንዲህ ይላል፦
“وقد ينزل الشيء مرتين تعظيمًا لشأنه وتذكيرًا به عند حدوث سببه، خوف نسيانه وهذا كما قيل في الفاتحة نزلت مرتين مرة بمكة وأخرى بالمدينة”
“ አንድን አንቀጽ ለማላቅ እና ምክንያቱ የተገኘ ጊዜ እንዳይረሳ ተፈርቶ ለማስታወስ ሁለቴ ሊወርድ ይችላል ልክ ፋቲሃ አንዴ በመካ ሌላ ጊዜ በመዲና ወርዷል እንደተባለው ነው።"
ኢማሙ ዘርከሺይ ለዚህ ማሳያ የተለያዩ ምሳሌዎችን ከጠቀሱ ብኃላ ሲጠቀልሉ እንዲህ ይላሉ......
«وما يذكره المفسرون من أسباب متعددة لنزول الآية قد يكون من هذا الباب،»
«ሙፈሲሮች ለአንድ አንቀጽ ለመውረዱ የተለያዩ ምክንያቶችን የሚጠቅሱበት ምክንያት ከዚህ ርእስ ስር ሊሆን ይችላል(ተደጋግሞ የወረደ ሚለው ርእስ)»
(አል-ቡርሐን ፊ ዑሉሚል ቁርዓን)

❤14👍3👏3