በንጽጽር ሰዎች የተሰራጩ ስህተቶችን ማረም
542 subscribers
52 photos
4 videos
1 file
34 links
Download Telegram
ምከራከራቸው “ለተከራካሪው ወይ ሹብሐ ልፈጥርበት" ነው 🤔

ይህ ሰው ግን ኖርማል ነው ? የትኛው ሀይማኖተኛ ሰው ነው ከሰው ጋር ምከራከረው ሹብሐ ለመፍጠር ነው ብሎ ኒያውን በግልጽ ሚያውጀው? )


ይህ የሰለፎች አደብ ነው? ኬት ነው የተማርከው? وقال الشافعي -رحمه الله
"ما ناظرتُ أحدًا إلا وددتُ أن يظهر الله الحق على لسانه"


ኢማሙ ሻፊዕይ እንዲህ ይላሉ ፦ “ አንድ ሰውንም አልተከራከርኩም አላህ ሐቅን በምላሱ ላይ ግልጽ እንዲያደርገው እየወደድኩ ቢሆን እንጂ”

ይህ ሰው ደግሞ ፦

“ሹብሐ ልፈጥርባቸው ነው ምወያያቸው?" (ድንቄም ሰለፍይ)

ሹብሐ ተፈጥሮብን ከእስልምና እንድንወጣ ፈልገህ ነው ወይስ ምንድነው? አጂብ እኮ ነው ሱብሃነላህ!! እንዲህ ዓይነት ሰው አይቼ አላውቅም እኔ በረቢ

ሹብሐ መፍጠርህ እውቀት ከሆነ ካፊሮችም ሹብሐ እየፈጠሩ አይደል እንዴ ለምን አብራቹ አሰሩም ?

መራድ እኮ የተወያየው አላህ ብሎለት ወደ ሀቅ እንዲመለስ ነበር እንጂ ሹብሐ ሊፈጥርበት አይደለም ሹብሐት በፈጠረ ከሆነ 9ኝነው 12 ሙጀለድ አረድ ዓለ ሹብሐት ሚል መጽሀፍ አለ አይደል እንዴ ሹብሃ ሹብሃው ይነበብልህ?

( እኔ እንዳልኳቹ ነው ሰውዬው ባወራ ቁጥር ይሳሳታል ስለዚህ አታስወሩት ለአላህ ብላቹ )


(ለዛሬ በቃኝ) መልካም ቀን))😁

https://t.me/comparativeerror
😁142
ጀዛከላሁ ኸይረን ጀዛ ሀቢብ አኹና!!



** ላይ የተደረገ ረድ ነው ይደመጥ !! ማን ሃቅን እንደጣሰ ተመልከቱ እናንተ ጆሮዋቹኝ የደፈናቹ ዓይናቹን የጨፈናቹ ሰዎች!!!


እናንተ እኮ አታፍሩም እኮ መልሳቹ “ሰውን ሳይሆን ሀቅን መከተል ነው ትላላቹ"
🔥73👍3😁1
በንጽጽር ሰዎች የተሰራጩ ስህተቶችን ማረም
Voice message
ይህ ትልቅ ጥመት ነው! (የዘንደቃ በር ነው!!)

“ቢድዕይ የሆኑ አልፋዝ ሙጀመላ ሰሃቦች ታቢዕዮች ... ተፍሲል አድርግ ያሉት የት ነው?”

“የለም ሲባል ደግሞ”


ሰለፎችን አትከተሉም ወይ ይላል?” No comment ወላህ! በዚህ በሄደው መልኩ ከተሄደ ብዙ ሚክደው የአህሉ ሱና ወልጀማዓ አቋሞች ይኖራሉ!! የሙራድን ”ስለዚህ....” ምትለውን መልስ ልብ በሉ!! (አጂብና ትክክለኛ መልስ ነው “የለም ስለዚህ?” አላህ ጂስም አይደለም ማለት ይቻላል ነው ሚለን?)


(ለዚህ ትልቅ ጥመት ወላሂ ቃል የለኝም!!! ለዚህስ የአካሄድ ስህተቱ ይመለስ ይሆን?)

https://t.me/comparativeerror
👍8😁1😢1
Forwarded from Murad|⛉ (Nebil)
2026-08-02
Murad|⛉
ንፅፅር እና እኛ?
4🥱1
የተረገሙ ናቸው😅
ደጃል 🤔

Live እየገባ ሚለውን ተመልከቱ)
😁121
Forwarded from AMIR ZEYNU
ኢብሊስ በለው😅😅

አረ ኡስታዝ ሱብሃነላህ!
😁6
Forwarded from AMIR ZEYNU
ደጃጂላ ናቸው 😅😁
🤣7
Forwarded from Murad|⛉ (Nebil)
ጁምሁሩል ኡለማዕ የሚለውን እርሱ ኢጅማዕ አድርጎ በማውሳቱ ከላይ በምታዩት መልኩ እንዲያስተካክል ነግሬው ነበረ፥ይህ ሰው መልዕክተኛው አለይሂሰላም ላይ ዋሸ፥አሸይኽ አረይስ ላይም ዋሸ፥አሁን ደግሞ በሁሉም ኢስላም ሊቃውንት ኢጅማዕ አድርገዋል በማለት ኢብኑ ተይሚያን እያስዋሸና ኡለማዎች በጁምሁር ተስማምተዋል የሚለውን ኢጅማዕ በማለት ያድበሰብሳል።

ለዚህ ሰውዬ ነው
Forwarded from Murad|⛉ (Nebil)
Murad|⛉
ጁምሁሩል ኡለማዕ የሚለውን እርሱ ኢጅማዕ አድርጎ በማውሳቱ ከላይ በምታዩት መልኩ እንዲያስተካክል ነግሬው ነበረ፥ይህ ሰው መልዕክተኛው አለይሂሰላም ላይ ዋሸ፥አሸይኽ አረይስ ላይም ዋሸ፥አሁን ደግሞ በሁሉም ኢስላም ሊቃውንት ኢጅማዕ አድርገዋል በማለት ኢብኑ ተይሚያን እያስዋሸና ኡለማዎች በጁምሁር ተስማምተዋል የሚለውን ኢጅማዕ በማለት ያድበሰብሳል። ዛሬ ለተማሪዎቹ ተሸሽጎ ኢጅማዕ ነው ሙራድ አልተረዳውም እንጂ…
ጁምሁሩል ኡለማዕ የሚለውን እርሱ ኢጅማዕ አድርጎ በማውሳቱ ከላይ በምታዩት መልኩ እንዲያስተካክል ነግሬው ነበረ፥ይህ ሰው መልዕክተኛው  አለይሂሰላም ላይ  ዋሸ፥አሸይኽ አረይስ ላይም ዋሸ፥አሁን ደግሞ በሁሉም ኢስላም ሊቃውንት ኢጅማዕ አድርገዋል በማለት ኢብኑ ተይሚያን እያስዋሸና ኡለማዎች በጁምሁር ተስማምተዋል የሚለውን ኢጅማዕ በማለት ያድበሰብሳል። ዛሬ ለተማሪዎቹ ተሸሽጎ ኢጅማዕ ነው ሙራድ አልተረዳውም እንጂ እያላቸው እንደነበረ ተነገረኝ እና ልመልስበት ስል መጣሁ።

የኢብኑ ተይሚያ ንግግር በቃ ግልፅ ነው ኢጅማዕን ሳይሆን ጁምሁሮችን ነው የጠቀሱት ለዚህም ነው የጁምሁሮቹን(የአብዛሀኛዎቹን) አቋም ከገለፁ ቢኋላ፥የአቀሎችን አቋም የገለፁት ለምሳሌ ኢማም አህመድን ጠቅሰዋል። so ሙሉ ፅሁፋቸው ከላይ አለ  አንብቡ፥ ወሏሂ እሳቸው  በዚህ ንግግራቸው ኢጅማዕን አልጠቀሱም፥ወሏሂ በሳቸው ላይ ተዋሽቶባቸዋል፥ሼኽ አድበስብስ ይህ አውድ ተነቦ በየትኛውም መልክ ኢጅማዕን አያመጣልህም፥ስርቆትም ውሸትም ላይ ጎበዝ መሆን እንዴት ቻልክበት ግን ቢላሂ አለይክ።

ለዚህ ሰው ነውዴ የምትከላከሉለት? ዲንን ለስሜቱ የሚጠመዝዝ የጠመመ ሰውን ይህንን ነው የምትከላከሉለት?በኡለማዎች ሆን ብሎ ከሚቀጥፍ ሰው ነው ትምህርትን የምትማሩት?

አሏህን የሚፈራ ሳይሆን ሰውን የሚፈራ ትውልድ ነው ወሏሂ ይህንን ሁሉ እያያቹህ ዝም ያላቹህ ኡስታዞች፥ከጎኑ ያላቹህ ሰወች ከርሱ አትተናነሱም፥ ኡለማኦች ላይ እየቀጠፈ መልዕክተኛው ላይ እየቀጠፈ እርሱን ሰወች እንዲገጠነቀቁ መንገር ወይም እንዲያርፍ እና አርፎ እንዲማር መንገር ግዴታቹህ ነው ወሏሂ አሏህ ይጠይቃቹሀል። ይህ ዲን ነው ስለተግባባነው ብቻ አንድን ሰው ሲዋሽ ሲያጠፋ ዝም እንለዋለን ማለት አይደለም።

ጅህልናህ ያገጠጠ እንደሆነ ሁሉም አይቷል፥ በቡዙዎች እውቀትን በቀመሱ ሰወች ፊት የተዋረድክ ነህ አንተ።

ያሳዝናል አሏሁል ሙስተኣን በማንም ዱርዬ ዲናችን ይደፈር!!
🔥5
መንጋው የንጽጽር ወንድሞቻችን ላይ ተነስቷል ለምን ሲባል? “ለእገሊት እንዴት ብር ያሰባስባሉ” በሚል ይህ መንጋ ከዚህ በፊት እገሌ ያለ እውቀት በዲን ላይ ተናገረ ይታረም ሲባል “ምቀኝነት ነው” "እልህ ነው” ወዘተ ብሎ ሲያለቃቅስ የነበረ ነው)

አረ መለክያቹንና መመዘኛቹን አስተካክሉ ባረካላሁ ፊኩም ። ይህን ያህል ለፋሉስ እሪሪሪሪሪ ብላቹ ጠባቂዎቻቹሀን ልትውጧቸው ነው እንዴ መንጋው ደምስሩ ሚቆመው በብር ሲሆን እንደሆነ እያየን ነው)

(ብር ማሰባሰባቸው ትክክል ነው ምናምን ለማለት አይደለም መንጋው ግን ይህን የመቃወም አቅም የላቸውም ዲን ላይ ተሳሳተዋል ሲባሉ ምቀኞች ናቹ እያሉ ነበር አሁን ምቀኛ ተባልን ብለው ለምን ያለቅሳሉ?)

https://t.me/comparativeerror
😁62🤷‍♀1🥴1
Sαlαh Responds ࿈
ነገረ-ተሕሪም የሱረቱል ተሕሪም (ምዕራፍ 66) ሰበብ አን-ኑዙል (Historical background) ሁለት መሆናቸው ይታወቃል፣ አንደኛው በቡኻሪ መጽሐፍ 68 ሐዲስ 17 ላይ የተጠቀሰው ሲሆን ነቢዩ ከዘይነብ ቤት ማርን በልተው ሌላኛው ሚስታቸው ስትቀና (የሴት ነገር ታውቁ የለ Hhh) እርሷን ላለማስከፋት ብለው ጣፋጩን ማር በራሳቸው ላይ እርም ሲያደርጉ አላህ «ለአንተ የፈቀደልህን ነገር ሚስቶችህን ማስወደድን…
ለ ነገረ ተህሪም የተሰጠ ማስተካከያ ²

ወንድም ሳላህ የሱረቱ ተሕሪም ማብራርያ ላይ የሰራውን መርሃዊ ግድፈት ጠቅሰን ነበር። አሁን ደግሞ ቀጥታ ከተሕሪሙ ጋር የተያያዘ ነገር እንጠቅሳለን ።ሱረቱ ተሕሪም የወረደው በዓሰሉ “መልእክተኛው ራሳቸው ማርን እርም በማድረጋቸው"? ነው ወይስ ማርያ አል-ቂብጥያ (ረዲየላሁ ዓንሃ) የተስኝፕች አገልጋያቸውን ራሳቸው ላይ እርም በማድረጋቸው ነው?

እንደ ወንድም ሳላህ እና ሌሎች አንዳድ የንጽጽር ልጆች አካሄድ ሱረቱ ተሕሪም የወረደው “በማሩ" ብቻ  ነው የሚል አካሄድን ይሄዳሉ ነገር ግን በማርያ ምክንያትም እንደወረደ የሚያመላክቱ ሰሂህ ሃዲሶች አሉ።

ስለዚህ በማርያ ነው የወረደው የሚል ሰሂህ ሀዲስ ካለ በማርም ነው የወረደው ሚል ሌላ ሰሂህ ሀዲስ ካለ ሁለቱም ምክንያቶች ቁርዓን ለመውረድ ምክንያት መሆን እየቻሉ አንዱን መጣል ጥንቁቅነት የተሞላበት አካሄድ አይደለም።


ሱረቱ ተህሪም ስለ ማርያ የመጡ መሆኑን ሚጠቁሙ ዘገባዎች ውስጥ ኢማሙ ነሳኢይ ከአነስ (ረዲየላሁ ዓንሁ) የዘገበው ነው።


قال الإمام النسائي: أخبرني إبراهيم بن يونس بن محمد نا أبي نا حماد بن سلمة عن ثابت عن أنس أن​رسول الله ﷺ كانت له أمة يطؤها فلم تزل به عائشة وحفصة حتى حرمها فأنزل الله عز وجل: ﴿يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَآ أَحَلَّ ٱللَّهُ لَكَ تَبْتَغِي مَرْضَاتَ أَزْوَٰجِكَ﴾ إلى آخر الآية.
አነስ (ረዲየላሁ ዓንሁ) “መልእክተኛ የሚገናኛት ባርያ ሴት  ነበረቻቸው አዒሻ እና ሀፍሳ ከእራሱ ላይ እርም እስኪያደርጋት ድረስ አልተዉትም አላህም  “አንተ ነቢዩ ሆይ! አላህ ለአንተ የፈቀደልህን ነገር ሚስቶችህን ማስወደድን የምትፈልግ ስትኾን (ባንተ ላይ) ለምን እርም ታደርጋለህ?”


ይህን የኢማሙ ነሰኢይ ሀዲስ በተመለከተ አል-ኢማሙል ሃኪም ሙስተድረክ ላይ ጥራዝ 2 ገጽ 493 ላይ “ሰሂሁን ዓላ ሸርጢ ሙስሊም" (የሙስሊምን መስፈርት ያሟላ ሰሂህ) ነው ብሎ አስቀምጦታል።

ነገር ግን ይህ ሰነድ ላይ ሙሐመድ ቢን ቡከይር አል-ሀድረሚይ አለበት እርሱ ደግሞ የሙስሊም ሪጃል አይደለም። ስለዚህም የሙስሊምን መስፈርትን ያሟላ ሰሂህ ነው የሚለው የሃኪም ንግግር ተመላሽ ቢሆንም ሀዲሱን ኢብኑል ሐጀር ፈትሁል ባሪ ጥራዝ 11 ገጽ 292 ላይ ኢስናዱ ሰሂህ ነው ብሎ ተናግሯል።

ታላቁ ሼኽ ሙቅቢል አል-ዋዲኢም ሀዲሱን በሙስሊም መስፈርት ሰሂህ ነው ባይባልም ሰሂህ ብቻ ግን ይባላል በሚል “አሰሂህ አል'ሙስነዳ ፊ አ'ስባቢ ኑዙል" ላይ ተናግረዋል።

ጉዳዩ በማርያ ላይ እንደመጣ የሚያመላክት ሰሂህ ሀዲስ ይህ ብቻ አይደለም። ሌላም ከኢብን አባስ የመጣ ዘገባ ይኖራል።
وفي مجمع الزوائد ج ٧ ص ١٢٦ عن ابن عباس: ﴿يَٰأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَا أَحَلَّ ٱللَّلهُ لَكَ﴾ قال: نزلت هذه في سريته.

በሙጅመዑ ዘዋኢድ ጥራዝ 7 ጉጽ 126 ከኢብን አባስ ተይዞ «አንተ ነቢዩ ሆይ! አላህ ለአንተ የፈቀደልህን ነገር ሚስቶችህን ለምን እርም ታደርጋለህ?» ሚለው በባርያቸው ላይ ነው የወረደችው" ብሏል።

ይህን ሀዲስ አል-በዛር በሁለት ሰነዶች ዘግቦታል ። የበዛር ሪጃሎች ከቢሽር ኢብን አደም ውጭ ያሉት በሙሉ የሰሂህ ኪታብ ሪጃሎች ናቸው ቢሽር ኢብን አደምም ቢሆን ሲቃ(ታማኝ) ነው። ስለዚህ ሰነዱ ሰሂህ ሲሆን አል-ኢማሙ ስዩጢይም ይህን ጠቅሰዋል።

ታድያ በዚህ መልኩ ሱረቱ ተሕሪም መልእክተኛው አገልጋያቸውን እራሳቸው ላይ እርም በማድረጋቸው እንደወረደ ሚያሳይ ሰሂህ ማስረጃዎች ባሉበት ለካፊሮች ተራ ውዥንብሮች ሲባል ለመጣል መሮጡ ትክክለኛ አካሄድ አይደለም።

አስለን መልእክተኛው ከማርያ አል-ቂብጥያ ጋር ግኑኝነት አላቸው ለዛም ነው ኢብራሒም የሚባል ልጅ ከማርያ አል-ቂብጥያ (ረዲየላሁ ዓንሃ) ያላቸው ። ይህ ደግሞ አላህ ለባሮቹ የፈቀደው እንጂ በአይነ ቁራኛ የሚታይ አልነበረም ገና ለገና ካፊሮች ጥያቄ አነሱ ተብሎ የሐዲስ መዛግብት መጣል ጤናማ አካሄድ ሊሆን አይችልም።

ታድያ የማሩስ ጉዳይ ከተባለ ?  በማሩ እነደወረደ የሚያሳዩ ማስረጃዎች ሰሂህ መሆናቸው ልብ ሊባል ይገባል። ስለዚህ ሱረቱ ተሕሪም በሁለትም አጀንዳዎች ላይ የወረደ ሱራ ይሆናል ማለት ነው።

አል-ሐፊዝ ኢብን ሐጀር ፈትሁል ባሪ ላይ እንዲህ ይላሉ
يحتمل أن تكون الآية نزلت في السببين معاً . اه


.“አንድ ላይ በሁለቱም ምክንያቶች የወረደች መሆኑን ያስመቻል” (ሊሆን ይቻላል) ” (ፈትሁል ባሪ)

በሁለቱም ሰበቦች ሲሉ በማርያም ፣ በማሩም ጉዳይ ማለት ነው።

ኢማሙ ሸውካኒ እንዲህ ይላሉ ፦
فهذان سببان صحيحان لنزول الآية ، والجمع ممكن بوقوع القصتين : قصة العسل وقصة مارية ، وإن القرآن نزل فيهما جميعاً
“እነዚህ ሁለቱ ምክንያቶች አንቀጹ ለመውርደ የመጡ ሰሂህ ዘገባዎች ናቸው።  የማሩንም የማርያንም ታሪክ ቁርዓኑ በሁለቱም ጉዳይ አንድ ላይ ነው የወረደው በሚል ታሪኮች መሰብስሰብ ይቻላል። ”(ፈትሁል ቀዲር )


ዶ/ር ዐብዱል አዚዝ ኢብን ሰዒድ ኡብን ጋኢብ “ኑዝሀቱል ዑቁል ፊ ሰሂህ አስባቢ ኑዙል" በተሰኘው ድርሳናቸው ላይ እንዲህ ይላሉ፦


وكِلا الأمرين - العسل والأَمَة - سببان لنزول هذه السورة، وقد جَمَعَ بينهما أهل العلم، بجواز تَعَدُّد النزول وبجواز تَعَدُّد الأسباب للنازل الواحد، وأنه لا مانع من ذلك؛ خاصة مع صحة الروايتين."
 
"ሁለቱም ጉዳዮች -ማሩም የማርያም- ለዚህ አንቀጽ ለመውረድ ሰበብ ናቸው። በሁለቱ መሐል የእውቀት ባለቤቶች አንቀጹ ተደጋግሞ ሊወርድ ይችላል እናም አንዴ እንኳን ቢወርድ የምክንያት መብዛት ሊኖረው ይቻላል በሚል ሰብስበውታል ለዚህም ከልካይ ነገር የለም። በተለይም ደግሞ ሀለቱም ዘገባዎች ሰሂህ ከመሆናቸው ጋር"

والله اعلم
ለዛሬ በዚህ ይብቃን!

https://t.me/comparativeerror
👍83
እግረ መንገዴን ይሄ ቻናል መስጂድ አይደለም ባረከላሁ ፊኩም እና እንዳድይደብራቹ))
😁8🤔2
አረ ለአላህ ብላቹ Ai አትጠቀም ሚለው ከነገረ ተህሪም ጋር አይያዝም ሳላህ በአንድም አርቲክሉ Ai ተጠቅሞ አያውቅም ምንድነው ምትሉኝ።


Ai አትጠቀም ያልኩት በጥቅሉ ነው ግዴታ ስሙን መጥቀስ አይጠበቅብኝም ግን በጥቅሉ ዲን ነክ ነገር ላይ Ai ተጠቅሞ መጻፍ አያስፈልግም። Ai አትጠቀም ማለት ሰውዬውን መናቅ ነው?
👍7