በንጽጽር ሰዎች የተሰራጩ ስህተቶችን ማረም
545 subscribers
59 photos
4 videos
35 links
Download Telegram
....
◎ ሰው ተናጋሪ እንስሳ መባሉ ስህተት ነውን? ብዥታ ፡ ሰለፊዮች ሰውን "ተናጋሪ እንስሳ በማለት ትገልፃላችሁ ሰውን እንዴት እንስሳ ትላላችሁ?!" መልስ ፡ الإنسان حيوان ناطق ተናጋሪ እንስሳ ነው ይባላል። الحيوان ፡ كل ذي روح . الواحد والجميع فيه سواء . አል-ሀይዋን የአማርኛ የአቻ ቃሉ እንስሳ የሚለው ሲሆን ሁሉም ነፍስ (ሩህ) ያለው እንስሳ ይባላል። 📚 ኪታቡል…
ለወንድም ጄክ የተሻለውን ማመላከት በማስበው  ...

እንደሚታወቀ ተዕሪፍ(ገለፃ) ፦ በ ሀድ (መግባት ያለበትን በማስገባት መውጣት ያለበትን በማስወጣት) ፣ በምሳሌ ፣ በስሜት ሕዋስ ፣ በክፍልፋይ  ሊፈጸም ይችላል።


መንጢቅዮች ሀድን ግልጽ ሲያደርጉ እንደ ምሳሌ 

ኢንሳን(ሰው) ማለት፦
الإنسان حيوان ناطق
በሚል ይገልፃሉ።

حيوان
ሲባል ህይወት ያለው ለማለት እንጂ እንስሳ በሚል አጠቃቀም በጭራሽ አልተፈለገበትም። ሀይዋን ሚለው ቃል በመንጥቅዮች መሰረት  ጂንስ(الجنس) ይባላል ( የተለያዩ መግባት ያለባቸውን ሚያስገባ ነው)

ሀይዋን ሚለው ቃል ሕይወት ያላቸውን ሰውን ፣ እንስሳንም ፣ 'እጽዋትንም' የሚያካትት ቃል ነው። ለምሳሌ በቁርዓን ላይ

وَإِنَّ ٱلدَّارَ ٱلۡأٓخِرَةَ لَهِىَ ٱلۡحَيَوَانُۚ
በእርግጥ የዘላለም ሕይወት አገር ናት፡፡ (አል-ዓንከቡት:64)


በቁርዓኑ ላይ የገባው ቃል አል-ሐይዋን የሚል ሲሆን ሕይወት በሚል ነው የተተረጎመው።
ልክ እንደዛው አል-ኢንሳኑ ሐይዋን ሲባል ሰው ሕይወት ያለው በሚል ነው መተርጎም ያለበት እንጂ እንስሳ በሚል አይደለም። እንስሳ ብለን ከተረጎምነው ጂንስ መሆኑ ቀርቶ ትክክለኛ ሀድም መሆን አይችልም። የሰው ልጅ እንስሳ አይደለም። ነገር ግን ሐይዋን ሚለው ሰውንም ፣ እንስሳንም ፣ እንፅዋትንም የሚያካትት የሆነ ጂንስ ነው።


ناطق
ሚለው ቃል ፋሲል ነው። መውጣት ያለበትን የሚያወጣ ቃል ነው።ሐይዋን ስንል ጂንስ ስለሆነ የተለያየ ነገር ገብቶ የነበር ሲሆን ናጢቅ ስንል ፈስል ሆኖ መውጣት ያለበትን ያወጣል። እንስሳና እፅዋት ናጢቅ በሚለው የሚወጡ ይሆናል። መንጥቅዮች ናጢቅ ሲሉ የፈለጉበት ዓቂል(አሳቢ) ሚል እንጂ ተናጋሪ የሚለውን አይደለም። 

ስለዚህ ስለፍዮች
አል-ኢንሳኑ ሐይዋኑን ናጢቅ ሲሉ

(ሰው ፦ ህይወት ያለው አሰላሳይ የሆነ ) ማለት ይሆናል እንጂ ተናጋሪ እንስሳ ነው በሚል አይደለም። ስለዚህ ከመሰረቱ ችግርም ሆነ ምንም ዓይነት ሹብሃ የለም።

ይህ እንደ ሹብሃ ላነሳው አካል ቅድምያውኑ ለተዕሪፉ ግንዛቤ እንደሌለው ማሳያ ነው። ወንድም ጄክ ጉዳዩ በዚህ መልኩ ብያየው ቢስተተካከል ብዬ አስባለሁ ወላሁ አዕለም።

(Basic sample እንዲሆኑ መረጃ ሚሆኑ ነገር ልክያለሁ )

(እንጽዋት = በቀደምት የመንጢቅ መጽሀፍት ላይ አናገኘውም)
18🔥5🥰3👍2😁1👌1
ትንሽ ላልኩት ማስረጃ ብጤዎች ናቸው።
👍13🤔1
የጁምሁሩ አቋም ማስረጃ ነውን? (ሶስቱ መዝሀቦች የተስማሙበት)


መልስ ፦ አይደለም ኢብኑል ቀይም።

አልፋሩሲያ አል- ሙሀመድያ ላይ።
1
ዑለማኡል መናጢቃ ኑጥቅ ሲሉ ምንድነው ሚፈለግበት?

መልስ ፦ ማሰብ/ማሰላሰል እንጂ መናገር አይደለም።


(ሙዘኪራ ፊ ዒልሚል መንጢቅ የሺንቂጢይ)
4🔥3
ÀƁÙBEĶEŔ ابوبكر(izharull haq)
ግብረ አውናን "ግብር" ማለት ስራ ነው አውናን ደሞ የግለሰብ ስም በአጠቃላይ ግብረ አውናን ሲባል የ አውናን ስራ ,ተግባር ማለት ነው::አውናን ማን ነው? ዘፍጥረት 38፥2 እዚያም ሳለ፣ ይሁዳ የከነዓናዊውን የሴዋን ሴት ልጅ አየ፤ እርሷንም አግብቶ አብሯት ተኛ፤ ዘፍጥረት 38፥4 እንደ ገናም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙን አውናን አለችው። ከዚ መረዳት እንደምንችለው አውናን የ የሁዳ ልጅ ነው…
ይታረም አልያም ራስን ማጥፋት ነው።

ወንድም አቡኪ በዚህ ጽሁፍ ላይ ራስን በራስ ማርካት(masturbation) ከግብረ አውናን ጋር ደብልቋል ። ይህ ብዙኃኑ ጋር የተለመደ ስህተት ቢሆንም ሊታረም ሚገባ ነው አለዚያ ራስ ላይ መተኮስ ነው።


ሁሌም አንድ ነገር ላይ ብያኔ ለማስቀመጥ ነገርየውን ቅድምያ መገንዘብ አስፈላጊ ነው። ቃሉ የሚወክለውን ሀሳብ ሳናውቅ ብያኔ መናገር ግልፅ የሆነ ጥፋት ነው። ግብረ አውናን ሊተካ ሚችለው ኢስላማዊ ሀሳብ ዐዝል እንጂ ኢስቲምናእ (ራስን በራስ ማርካት) አይደለም።

ቅድምያ ዐዝል ምን ማለት ነው? የቃሉ ፍች ላይ ከሁለት ታላላቅ ሻፊዕይ ዑለማዎች ፍች እንነሳ

★ኢማሙ ነውዊ
هو أن يجامع فإذا قارب الإنزال نزع وأنزل خارج الفرج، وهو مكروه عندنا في كل حال، وفي كل امرأة سواء رضيت أم لا، لأنه طريق إلى قطع النسل
“ተረክቦን እየፈፀመ ዘር ፈዛሽን ሊያፈስ ሲል ከብልት አውጥቶ ማፍሰስ ነው። በየትኛውም ሁኔታ እንዲሁም በየትኛውም ሴትም ፈቀደችም አልፈቀደችም እኛ ዘንድ የተጠላ ነው። ምክንያቱም ዘር መቁረጥ ስለሆነ” ይላሉ

(https://www.islamweb.net/ar/library/content/53/4282/%D8%A8%D8%A7%D8%A8-%D8%AD%D9%83%D9%85-%D8%A7%D9%84%D8%B9%D8%B2%D9%84)

★ኢብን ሐጀር
 النزع بعد الإيلاج لينزل خارج الفرج
“ከብልት ውጭ የዘር ፈሳሽን ለማፍሰስ ከመክተት ቡኃላ ማውጣት ነው።”
ይላሉ
https://www.islamweb.net/ar/library/content/52/9521/%D8%A8%D8%A7%D8%A8-%D8%A7%D9%84%D8%B9%D8%B2%D9%84

በአጭሩ ዐዝል ከሚስት ጋር ተራክቦ በሚፈፀምበት ጊዜ የዘር ፈሳሽን ከሚስት ብልት ውጭ በማፍሰስ ከእርግዝና መከላከያ መንገድ ውስጥ የሚካተት ነው በኢንግሊዘኛው "withdrawal" ወይም "pulling out" ወይም coitus interruptis በመባል ይታወቃል።


Withdrawal፦ is when the penis is removed from the vagina before ejaculation so that ejaculation takes place outside and away from the vagina
ትርጉም፦ (ብልትን ከሴት ብልት ላይ የዘር ፈሳሽን ከማፍሰስ በፊት ከሴቷ ብልት ርቆና ውጭ ሆኖ እንዲፈስ ማውጣት ነው)

https://www.optionsforsexualhealth.org/facts/birth-control/methods/withdrawal/#1550008055237-2baa16bd-7e5d4323-f0d5

ዐዝል(withdrawal) ወሊድ መቆጣጠርያ (contraception) ከሚባሉት የሚለየው ምንም ነገር የለም። ዐዝል ራስን በራስ ማርካት ነው የሚል ሰው ጉዳዩ በቅጡ ተሰውር እንዳላደረገ ያሳያል።

Birth control is any medicine, device or method people use to prevent pregnancy
(ወሊድ መቆጣጠርያ ማለት ሰዎች እርግዝናን ለመከላከል የሚጠቀሙት የትኛውም ህክምና ፣ ዕቃ ፣ ወይም ዘዴ ነው)
https://my.clevelandclinic.org/health/articles/11427-birth-control-options

በዚህ መሰረት ዐዝል(withdrawal) አንዱ የወሊድ መቆጣጠርያ መንገድ መሆኑን እንረዳለን ማለት ነው።


በምንም አግባብ አውናን የፈጸመው ተግባር ዐዝል እንጂ ማስቱርቤሽን ሊባል አይችልም ። ዕዝል ደግሞ በሸርዓችን መክሩህ እንጂ ሐራም አይደለም።

ነወዊ የዐዝልን ብያኔ አጠር አድርጎ አስቀምጦታል፦
"وهو مكروه عندنا في كل حال وكل امرأة سواء رضيت أم لا لأنه طريق إلى قطع النسل ، ولهذا جاء في الحديث الآخر تسميته الوأد الخفي ؛ لأنه قطع طريق الولادة كما يقتل المولود بالوأد ."

በየትኛውም ሁኔታ እንዲሁም በየትኛውም ሴትም ወደደችም አልወደደችም መፈፀሙ እኛ ዘንድ የተጠላ ነው። ምክንያቱም ዘር መቁረጥ ስለሆነ ለዚህም ነው በሀዲስ ላይ " ሕያው ህፃናትን በድብቅ መቅበር" በሚል የተሰየመው ምክንያቱም የመውለድን መንገድ መቁረጥ ነው ልክ የተወለደውን በመቅበር እንደሚገደለው” ይላል” https://www.islamweb.net/ar/library/content/53/4282/%D8%A8%D8%A7%D8%A8-%D8%AD%D9%83%D9%85-%D8%A7%D9%84%D8%B9%D8%B2%D9%84

ዐዝል የተጠላ እንጂ ሐራም አይደለም። ማስቱርቤሽን(ኢስቲምናእ/ ራስን በራስ ማርካት) ግን ሐራም ነው።

قال ابن حجر الهيتمي في تحفة المحتاج، في تعريف الاستمناء: وهو استخراج المني بغير جماع، حراما كان كإخراجه بيده، أو مباحا كإخراجه بيد حليلته. اهــ.
{የዘር ፈሳሽን ያለ ግኑኝነት(ወሲብ)ማፍሰስ ሲሆን እርም የሆነው በራስ እጅ ማፍሰስም ሆነ ፍቁድ የሆነው በባለቤት እጅ ማፍሰስ (እስቲምናእ ይባላል)"}ከዚህ በመነሳት እስቲምናእ(ራስን በራስ ማርካት) "ያለ ተራክቦ የዘር ፈሳሽን ማፍሰስን" ሚወክል ቃል ነው።

ወንድሜ የሳተው ግብረ አውናን (onanism ) ቡኃላ ላይ አቻ በሆነው ራስን በራስ በማርካት በሚለው አንግል ብቻ አይቶ ማብጠልጠሉ ነው። ስለዚሂ በተጨባጭ ወደ ባይብል ሄደን ግብረ አውናን ብናይ ዐዝል ሆኖ እንጂ ማስቱርቤሽን ሆኖ አናገኘውም።
ግብረ አውናን ማስቱሩቤሽን መስሎን ከተቸን ሳናውቀው በእስልምና የተፈቀደውንም ዐዝልንም እየተቸን ነው። (ይታረም አልያ ራስ ላይ መቶከስ ነው!)


https://t.me/comparativeerror
👍189🔥9😁1
ኢብኑ ተይሚያህ ሚለው ሌላ ጄክ ሚለው ሌላ!


ወንድማችን ጄክ ጂስም ሚለውን ቃል ልቅ በሆነ ሁኔታ ነፍይ ማድረግ እንደሚቻል ይናገራል። ነገር ግን ከአህሉ ሱና ዑለማዎች አፍ ምንሰማው ቃሉ እንደማይፀድቅም ውድቅ እንደማይደረግ ሲሆን መዕናው ደግሞ ተፍሲል እንዲሚያስፈልገው ነው።

ጂስም የሚለውን ቃል ከአላህ ነፍይ (መንሳት) ሆነ ማፅደቁ (ኢስባት) ማድረጉ ማደናገር (ኢልቲባስ) እና ኢጅማል (ጥቅልነት) ያለው ሲሆን ከጥመት ባለቤቶች አቅጣጫ የመጣ በአላህ ዲን ውስጥ የተፈጠረ ቢድዓ ነው። 


ሸይኹል ኢስላም ኢብን  ተይሚያህ እንዲህ ይላል፦

.
ان القول بأن الله ليس بجسم ولا جوهر ولا متحيز ولا داخل العالم ولا خارجه ونحو ذلك ليس هو قول أحد من سلف الأمة ولا أئمتها ، ولا له أصل في شيء من كتب الله المنزلة ولا آثار أنبيائه ؛ بل متواتر عن السلف والأئمة إنكار هذا الكلام وتبديع أهله ، كما قال ابو العباس بن سريج : توحيد اهل العلم وجماعة المسلمين : أشهد أن لا إله إلا الله وان محمداً رسول الله ، وتوحيد أهل الباطل الخوض في الأعراض والأجسام ، وإنما بعث النبي ﷺ بإنكار ذلك .

“አላህ ጂስም አይደለም ፣ ጀውሀር አይደለም፣ ሙተሀይዝ አይደለም ፣ዓለም ውስጥ አይደለም ፣ ከዓለም ውጭ አይደለም ወዘተ... የሚለው ንግግር የአንዳቸውም የዚህ ኡማ ቀደምቶችና ኢማሞች ንግግር አይደለም። ከአላህ ከወረዱ መጽሀፍትም ሆነ ከነብያት ትውፊቶች ውስጥም ማስረጃ የለውም። ይልቁንም ከሰለፎችና ከኢማሞቻችን በብዛት የተዘገበው ይህን ንግግር ማውገዝና ባለቤቱን ተብዲዕ ማድረግ ነው(ከሱና ማስወጣት) ኡቡ አል-ዓበስ ኢብን ሱረይጅ እንዳለው የእውቀት ባለቤቶችና የሙስሊሞች ስብስብ  ተውሂድ ከአላህ ውጭ በእውነት ሊገዘቱ የሚገባ አምላክ የለም ሲሆን የባጢል ሰዎች ተውሂድ ደግሞ አዕራድ ፣ አጅሳም እያሉ መዋዠቅና ነብዩ የተላኩት ይህን በማውገዝ ነው (ብሎ ማመን ነው)"። (ተልቢሱል ጀሕሚያ)


ጂስም ሚለውን ቃል ከአላህ ውድቅ ለማድረግ ከቁርዓንም ከሱናም ከኢጅማዕም ከአንዳቻውም ሰለፎች ማስረጃ እንደሌለ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ይናገራሉ።

وإذا كان كذلك فنفي التجسيم لا يمكن أن يكون بنص ولا إجماع ؛ بل ولا بأثر عن أحد من سلف الأمة وأئمتها ، وليس مع نفاته إلا مجرد ما يذكرونه من الأقيسة العقلية .

ነገሩ እንዲህ ከሆነ ተጅሲም ነፍይ ማድረግ በነስም በኢጅማዕም የሚሆን አይደለም። በል እንዲያውም ከዚህ ኡማ ቀደምቶችና ኢማሞች ንግግርም አይደለም። ጂስም ነፍይ ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር አእምሮአዊ የሆኑ ልኬቶች እንጂ ምንም የለም። (ተልቢሱል ጀሕሚያ)

በፈክሩዲን አ'ሯዚይ አሳሱ ተቅዲስ ላይ ጂስምን ውድቅ ለማድረግ የተጠቀሱ  ተራ አእምሮአዊ ማስረጃዎችን ኢብኑ ተይሚያህ አንድ በአንድ ተልቢሱል ጀሕምያ ላይ መልስ ሰጥቶበታል።

ወንድማችን ጄኽ ጂስም ሚለውን ቃል ኢጥላቀን ውድቅ ማድረግ ይቻላል ሲለን ኢብን ተይሚያ ግን ውድቁ ማድረጉ መጤ ፈጠራ ነው ይለናል።

ኢማሙ አህመድ ከ ጀሕምዩ ሙሐመድ ኢብን ዒሳ ቡርጉስ ጋር  ስለ አላህ ንግግር እየተወያዩ ለአላህ ንግግር ማፅደቅ ጂስምን ማፅደቅ ያስፈርዳል ሲባል አላህ ጂስም አይደለምም ወደ ሚል አጀንዳ አልገቡም።

ኢብን ተይሚያህ እንዲህ ይላል፦

فأجابه الإمام أحمد بأن هذا اللفظ لا يُدرى مقصود المتكلم به، وليس له أصل في الكتاب والسنة والإجماع، فليس لأحد أن يلزم الناس أن ينطقوا به، ولا بمدلوله، وأخبره أني أقول: هو أحد، صمد، لم يلد ولم يولد، ولم يكن له كفواً أحد؛ فبين أني لا أقول: هو جسم ولا ليس بجسم، لأن كلا الأمرين بدعة محدثة في الإسلام،

ኢማሙ አህመድ በቃሉ ተናጋሪው ምን እንደፈለገበት ግልጽ እንዳልሆነ፤ በቁርዓንም በሱናም በኢጅማዕም መሰረት እንደሌለው ፤ሰዎችንም ቃሉ በሚጦቅምበት እንኳን እንዲናገሩ ማስገድድ እንደማይችሉ መልስ ሰጠው። አላህ አንድ ነው። የሁሉ መጠግያ ነው። አልወለደውም አልተወለደምም ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም እንደሚልም ነገረው።እርሱ ጂስምም ነውም አይደለምም እንደማይል ግልጽ አደረገ ምክንያቱም ሁለቱም ነጥቦች በኢስላም የተፈጠሩ ቢድዓ ናቸው።  ( ዳሩ ተዓሩድ አል-ዓቅል ወነቅል)

ጂስም ሚለውን ቃል መጀመርያ ከአላህ ነፍይ (ውድቅ) ያደረገው ጀሕም ኢብን ሰፍዋን ነው። መጀመርያ ለአላህ ያፀደቀውም ሒሻም ኢብን ሐከም አ'ሯፊድይ ነው። ሰለፎች ኢስባትም ነፍይም ከማድረግ የተቆጥቡ ሲሆን ወንድማችን ግን ነፍይ ይደረጋል ሲል ምን ላይ ተመስርቶ ነው???

ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ይላል፦
والسلف والأئمة لم يثبتوا هذه الأسماء لله ولا نفوها عنه ؛ لما في كل من الاثبات والنفي من الابتداع في الدين من اجمال واشتراك ، ويثبت به باطل وينفى به حق، مع أن السلف والأئمة لم يختلفوا أن نفاة الجسم أعظم ضلالا وابتداعا من مثبتيه

“ሰለፎች እና ኢማሞችችን እነዚህን ስያሜዎች ለአላህ አላፀደቁም። ከእርሱም ውድቅም አላደረጉም።  ማፅደቁም ሆነ መንሳቱእ ጥቅልነት  ያለው ዲን ውስጥ የተፈጠረ መጤ ስለሆነ። ማፅደቁ ውድቅ የሆነ ነገር ይፀድቅበታል መንሳቱ እውነት ውድቅ ይደርግበታል። ሰለፎችና አኢማዎች ጂስምን ውድቅ የሚያደርጉ ጂስምን ከሚያፀድቁ የበለጠ ጠማማ እና አዲስን ነገር ፈጣሪ መሆናቸው ላይ ካለመለያየታቸው ጋር!...”(ተልቢሱል ጀህሚያ)

ስለዚህ የቱ ጋር ነው “አላህ ጂስም አይደለም” ብሎ ኢጥላቀን መናገር ይቻላል የተባለው። ይህ ቃል ሙጅመል አይደለምን? የሙብተዲዓዎችንስ ሺዓር ማሰራጨት አይደለምን? የአላህ ባሕሪያትስ በዚህ መጤ ቃል ምክንያት ውድቅ አልተደረገምን? ወንድማችንም ማይባል ብለሀል አስተካክል!

https://t.me/comparativeerror
🔥9👏96
የኢብን ተይሚያህ ኑሱሶች !


ደብሮኝ እንጂ ከኢብኑ ተይሚህ ብቻ ብዙ ማዝነብ ይቻላል አንቡትና ጄክ ያለውም ደግሞ ተመልከቱ።
8🔥2
ሼይኽ ሳሊህ አ'ሲንዲይ ሚሉትን ተመልከት! (ከዛን ጄክ ሚለውን ተመልከቱ)

ጄክ

“አላሁ መውጁዱን ቢላ መካን” ይባላል

“አላህ ጂስም አይደለም” ይባላል

ወንድሜ መስአላው ላይ ስተሃል ተመለስ ወደ ሀቁ!

https://t.me/Hardsalafi
👍7😁21
Forwarded from ᒪEYᒪᗩ тяυтн_ѕєитιиєℓ (Amir zeynu)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መተራረም ከዲን ነው የሰዎችን ዓይብ መከታተል ግን ኬት ነው?

ንጽጽር ላይ ዲናዊ መስአላ ሲገድፋ አንዱ አንዱን
ለምን  አያርመውም? ሲባል አንዱ የአንዱን የግል ነውር አፈንፍኖ ስለደረሰበት ነው ብሏል ኢንጀነር። ማታም የተፈጠረው ይህ ነው። ወንድማችን በጠዋፍ መኀከል መሰል የሰማትን ወሬ አፈንፍኖ ለስህተቱ መደበቅያ አድርጎታል። እኔንን ዝም እንድል ሊያደርገኝ ፈልጎ ነበር። በሁለት ሳምንት ውስጥ እንድከፍልና አይለመደኝም የሚል ይቅርታ ድምጽ ለአበዳሪዋ እንድልክ ፈልጎ ነበር አለበለዝያ እነደሚፖስተው ነገረኝ ። (በሱ ሀሳብ ፋይል ልይዝብኝ) እኔ ደግሞ እንዲ ያሸረገደ ሜንታሊቲ ሊኖረኝ ስለማይችል ለአበዳሪዋ ራሱ ብርሽን ምሰጥሽ በኢጎ የተወጠረ ማንነቱ እኔን በማስጠንቀቅ ፖስቶ ገሀድ ሲወጣ ነው ብዬ ቁዳሁለት። ድምጹን ቅድምያ ልኬላቹ ነበር ሰው ከሰማው ቡኃላ ደልቼዋለሁ የፈለገው ወንድማችን ቤት ሄዶ ያዳምጠው። ቅድምያ የላኩትን ነው የላከው።


ያኢኽዋኒ ፊላህ በአላህ ሲትር ምኖር ሰው ነኝ። መዝገቤ በሙሉ በድብቅ ነውሮች እና ወንጀሎች የቶሞሉ ናቸው። ዲን ላይ ተሻጋሪ ስህተት ነው ብዬ በተሳሳታቹ ቁጥር ሳርማቹ ይቅማል ያጭሳል በሚል ተደብቄ የምሰራውን ወንጀል መዘገብ  ከሆነ መልሳቹ አላህ ወንጀሌን ሊያብስልኝ ፈልጎ እንደሆነ መረዳት አያቅተኝም። ሸክረን ለኩም ወጀዛኩሙለሁ ኸይረን።

ሌላ ምታረመው ዑምራ በሴት ብር አልሄድኩም ብሏል ከሆነ እሰየው አብዛኛው ስለሄደ እንደዛ መስሎኝ ነው። ብሯን ወዲያው ሲለጥፈው በመክፈሌ  ፈርቶ ነው ብሏል ።ካለጠፈው አልከፍልም የሚል ሸርጥ ያስቀመጥኩት እኔ😁

ወዲየውኑ አየር ላይ በመከፈሉ ስለደበረው ብዙ የዘረፈው ሐብት አለው ብሎ ደንግጧል ተው ይህን ያህል ሚያስለጥጥ ነገር የለም ለጉዳዩ ማጠራቀም ከጀመርኩ ቆይቷል አንተ ሳታውቅ በፊት ሀቋ ሀቅ ነው ይመለሳል።
👍8🥰6👎1
Forwarded from ᒪEYᒪᗩ тяυтн_ѕєитιиєℓ (Amir zeynu)
ከጉዳዩ ጋር በተያየዘ አኺሩል ቀውል .....

ረድ የጀመርከው ይህ ሲታወቅ ነው አሉ ለወንድማችን ሆነ ለሌላው አላህ ምትፈሩ ከሆነና እርግጠኛ ከሆናቹ ለአደባባይ ሙበሐላ ( መረጋገም) እጠራቹሁለሁ። ወላሂ ይህን ጉዳይ አላየሁትምም ልብም አላልኩትምም ነበር)

የሰማሁትም ከአበዳሪዋ ሀይዋኑን ናጢቅ ላይ ቢያስትካካከው ካልኩ ብቻ ቡኃላ ነው።
ምኑ ከምኑ ነው ያገናኙት በረቢ¡ (ሲደግፈኝ ነበር የሚለው ድምጽ መስአላው አልገባኝም ነበር ካልኩት ፎቶ እየለጠፈ ረድ ያደርጋል ዓቅል ግን አለን?)

የአኺ ማታውን ሙሉ ማይረባ ነገር ስትቸከችክ ነው ያደርከው ከዛ ይልቅ ናጢቅ ሚለውን በሶስት ፊደል "አሳቢ" ብለህ ብትለውጠው አይቀልም?.


Silent ታዛቢዎችም ይኖራሉ!!)

https://t.me/Hardsalafi
👍219🥴3
Audio
ሼኽ ፈውዛን “አላህ መውጁዱን ቢላ መካን" የሚለው ዑሉውን ማስተባበል ነው ይሉናል። ወንድም ጄክ ደግሞ ኢጥላቀን “አላህ መውጁዱ ቢላ መካን" ይባላል ይላል።
ሼኽ ፈውዛንን ወይስ ጄክን?

ይህንን ንግግሩን ከቻናሉ ደልቶታል መሰለኝ ላገኘው አልቻልኩም ነገር ግን አላህን ፈርተህ የማይባል እንዳልክ እውቅ። ዑለማዎች ሻዝ የሚሆኑባቸውን ቀውል እየተከታተልክ አዲስ ነገር ያመጠን ማስመሰል አግባብ አይደለም።

“አላሁ መወጀዱን ቢላ መካን”
የሙብተዲዓዎች ሺዓር(መገለጫ) ነው።የአላህን ከአርሽ በላይ መሆኑ የሚክዱ ጠማሞች የዕለተ ዕለት መፈክርን እንዲህ በልቁ ማለት ይቻላል እንዴት ትላለህ?

ሀቅን ከውሸት መደብለቅ ያለው ንግግር ነው። ሀቅን ፍንትው አድርጎ ማስቀመጥ እንጂ ማድበስበስ አያስፈልግም። የአህባሽና የአሽዓሪያ ተፅእኖ ስር ወድቀህ ነው? ወይስ ነጥብህ ምንድነው?

https://t.me/comparativeerror
17👍9👎6👏2
ወደ ሀቅ መመለስ በባጢል ላይ ከመዘውተር አስር እጥፍ የተሻለ ነው። ጄክ ላለመታረም እርስ በእርሱ እየተጋጨ ነው።

jake፦ “ሚን ባቢል ኢኽባር አላህ ላይ ስንጠቀም ከሁሉም አቅጣጫ መጥፎ ትርጉም ሚያስይዝ መሆን የለበትም”
ይለንና

Jake መልሶ፦ “አላህ ያለ ቦታ ነው ተብሎ ኢጥላቀን መናገር ይቻላል" ይልሃል)


አላህ ያለ ቦታ ነው ሚለው ቃል ከሁሉም አቅጠጫ ንጹህ ነውን? ( ንጹህ ስላልሆነስ አይደል ተፍሲል እያደረክ ያለከው።) ስለዚህ ለምን "አላህ ሙውጁዱ ቢላ መካን" ኢጥላቀን ማለት እንደማይቻል አታስቀምጥም? መሳሳትህ ግልጽ ነው አትገትር አላህን ፍራ!!

https://t.me/comparativeerror
👍172😐2😁1
ዓጀበን ሊአምሪከ !!

ሸይኽ አድበስብስ “ዛት ሚል ለአላህ አልመጣም” አለ

ኡስታዝ ወሂድ ፦ “ አረ በሐዲስ መጥቷል"
ሲለው

ሸይኽ አድበስብስ፦ “ሐዲሱ ደዒፍ ነው” አለ

ኡስታዝ ወሂድ፦ “ ቡኻሪይ ላይ አለ" ሲለው

ሸይኽ አድበስብስ ፦ “አረይስ ይጠቅሱታል..." ይላል አረ ጌታዬ


ሸይኽ አድበስብስ እውነትን ከማድበስበስ ውጭ አላወቁም ነበር፣ ተሳስቻለሁ ከአፋ አይወጣም።

ያሃ ሁሉ ከተራገጠ እና ከተሳደበ ቡኃላ ውይይት ጠራኝ ይህም ከተልቢሱ ነው።ውይይት ከፈለክ ከመሳደብህ በፊት አጠራኝም ነበር🤧

ማድበስበስ ማለባበስ መሸፋፈን ላይ expert ነው።


https://t.me/comparativeerror
👍10😁6👎21
እርምት

ወንድም አቡበከር ድብቅ ብዥታዎች በሚለው መጽሀፉ ሙስጠላህ በተመለከተ ያስቀመጣቸው ጥሩ ነጥቦች አሉ። እንደ ማንኛውም ሰው የተፈጸሙ አንዳድ ስህተቶችም በተጨባጭ አሉ። እኝህን ማረሙ የአርትዖት ሰሪዎች ስራ ቢሆንም ዝም ስለተባሉ እኔ ላርማቸው ወድጅያለሁ።
ከነዚህም ውስጥ ወንድም አቡኪ ድብቅ ብዥታዎች ገጽ 19 ላይ እንዲህ ይላል “እነዚህ የጠቅስናቸው ሙርሰሎች በሙሉ ደዒፍ ናቸው። ምክንያቱም በታቢዕዩ እና በነብዩ መካከከል ያለ መካከለኛ (ሰሀባ) ባለመኖሩ!!”
ይህ ገለጻ ሙርሰልን ለመጣል ትክክለኛ ምክንያት ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም እንዲህ ከሆነ ሙርሰሉ ሰሃባም ተቀባይነት የለውም። ሰሃባ ኢርሳል ሲያደርግ በእርሱና በነብዩ መሐከል ያለውን ሰሀባ ጥሎ ነው። ታድያ ይህ ውድቅ ነውን ስንል?
ወንድማችን ራሱ ሙርሰሉ ሰሃባ ተቀባይነት እንዳለው ቅድምያ ተናግሮ ነበር (ፈአህሰነ ወአጃደ) ። እንዲህ ይላል፦“አው የሰሀቦች ኢርሳል ተቀባይነት አለው ምክንያቱም ሰሀቦች በአብዛኛው የሚያስተላልፉት ከሰሀቦች ነው። ሰሀቦች ደግሞ ታማኞች መሆናቸው እሙን ነው”
(ድብቅ ብዥታዎች ገጽ 18)


ሰሃቦች ከመልእክተኛው ቀጥታ ያልሰሙትን ሲያስተላልፉ የነገራቸውን ሰሃባ ጥለው ነው ይህን ተቀባይነት አለው ካለ ሙርሰል ደካማ የሆነው “በታቢዕዩ እና በነብዩ መካከከል ያለ መካከለኛ (ሰሀባ) ባለመኖሩ" ማለቱ ትርጉም አይሰጥም።

ጤነኛ አንባቢ ሙርሰሉ ሰሀባ ላይም እኮ “በሰሀቢዩና በነብዩ መካከል ያለ መካከለኛ ሰሀባ የለም” ብሎ ሊጠይቅ ይችላል! ስለዚህ ወንድማችን እዚህ ጋር ሳያውቀው ገድፏል ይታረማል!

           {ሙርሰል ተቀባይነት የሌለው ለምንድነው?}

ሙርሰል ማለት ታቢዕይ (የሰሀቦች ተከታይ) ወደ ነብዩ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም)  ያልሰማውን ሲያስጠጋ የሚሰጠው ስያሜ ነው። ይህ ዓይነቱ ዘገባ ተቀባይነት አለው ወይስ የለውም የሚለው በዑለማዎች መካከል ልዩነት ያስተናገደ ነጥብ ነው። ነገር ግን ትክክለኛው አቋም የሙርሰል መሰረቱ ደዒፍ ነው የሚለው አቋም ሲሆን ለዚህም ደግሞ ጤናማ የሆነ ለትችት ክፍት ያልሆኑ ምክንያቶችን ደርድረዋል።

ዋነኛው ታቢዕይ ከመልእክተኛው ሲያወራ ይህን ዘገባ ቀጥታ ከሰሀባ ወስዶት ሊሆን ይችላል ወይም ከታቢዕይ ሊሆን ይችላል የሚል ይሁንታ በመኖሩ ነው። ከታቢዕይ ሊሆን ይችላል የሚለው ይሁንታን ከከፈትን ይህ ታቢዕይ ሲቃ ነው ወይስ ደዒፍ የሚለው ይሁንታ በቅድምያነት ይከፈታል ማለት ነው።
ይህ ደግሞ ሙርሰል መርዱድ ውስጥ ለማካተት ዋነኛው ነጥብ ነው።

ስለዚህ ሙርሰል ደካማ የሚሆነው “መሀከል ላይ የተጣለው አካል ማን እንደሆነ ስለማይታወቅ" ነው። ሰሀባ ብቻ እንደተጣለ ቢረጋገጥ ኖሮ ሙርሰል ደካማ አይሆንም ነበር። ሰሀባውን አለማወቃችን ሐዲሱ ላይ የሚያመጣው ተፅእኖ የለም።

ኢማሙ ቲርሚዚይ እንዲህ ይላል፦

: ومَنْ ضَعَّفَ المرسلَ فإنه ضَعَّفَهُ من قِبَلِ أَنَّ هؤلاء الأئمةَ قد حَدَّثوا عن الثقاتِ وغيرِ الثقاتِ ، فإذا روى أحدهم حديثاً وأرسَلَهُ لعلهُ أخذه عن غير ثقةٍ .وقد تكلَّمَ الحسنُ البصريُّ في مَعْبَدٍ الجُهَنِيِّ ، ثم روى عنه ! .
“ሙርሰልን ደካማ ያደረጉት ደካማ ያደረጉበት ምክንያት እነዚህ አኢማዎች ከሲቃም ሲቃም ካልሆነም አካል ስላወሩ ነው። አንዱ 'ታቢዕይ' ሀዲስን አውርቶ ሰነዱን ካልጠቀሰው ከሲቃ ካልሆነ አካል ይዞት ሊሆን ይችላል (የሚል ይሁንታ አለ።) ሀሰን  አል-በስሪይ መዕበድ አል-ጁሐኒይ ከመተቸቱ ጋር አስተላልፎለታል” (ዒለሉ ሰጊር )

አል-ሃፊዙ ኢብን አብዱልበር እንዲህ ይላል፦

وحجتهم في رد المراسيل ما أجمع عليه العلماء من الحاجة إلى عدالة المخبر وأنه لا بد من علم ذلك، فإذا حكى التابعي عمن لم يلقه، لم يكن بد من معرفة الواسطة، إذ قد صح أن التابعين أو كثيراً منهم، رووا عن الضعيف وغير الضعيف، فهذه النكتة عندهم في رد المرسل، لأن مرسله يمكن أن يكون سمعه ممن يجوز قبول نقله، وممن لا يجوز، ولا بد من معرفة عدالة الناقل، فبطل لذلك الخبر المرسل للجهل بالواسطة.
ሙርሰልን በመመለስ ላይ ማስረጃቸው ዑለማዎች የተናጋሪውን ዐዳለነት ማወቅ ግድ ነው በሚለው ስምምነታቸው ላይ የቆመ ነው። ታቢዕይ ካልተገናኘው አካል ካስተላለፈ መሐከል ላይ ያለውን ማወቅ ግድ ማለቱ ቅሮት የሌለው ነው። ምክንያቱም ታቢዕዮች ወይም አብዛኞቹ ታቢዕዮች ከደካማም ከታማኝም አስተላልፈዋል። ሙርሰልን ለመጣል ያመጡት ይህችን ነጥብ ነው። ምክንያቱም ሰነዱን የጣለው አካል ሊተላለፍለት ከሚገባ ይዞት ሊሆን ይችላል ላይሆንም ይችላል የዘጋቢውን ዓዳላ ማወቅ ደግሞ ቅሮት የሌለው ግዴታ ነው። ለዚህም ሲባል ሙርሰል መሐከል ላይ የተጣለው ስላልታወቀ ውድቅ ይደረጋል” (ሙቀዲመቱ ተምሂድ)

አል-ሃፊዙ ኢብን ሐጀር እንዲህ ይላል፦

”(المرسل) وإنما ذُكِرَ في قِسْمِ المردود للجهل بحال المحذوف؛ لأنه يُحتمل أن يكون صحابيًا، ويُحتمل أن يكون تابعيًا.
​وعلى الثاني يُحتمل أن يكون ضعيفًا، ويُحتمل أن يكون ثقةً، وعلى الثاني يُحتمل أن يكون حَمَلَ عن صحابي، ويُحتمل أن يكون حَمَلَ عن تابعي آخر، وعلى الثاني فيعود الاحتمالُ السابقُ، ويتعدد. أمّا بالتجويز العقلي فإلى ما لا نهاية له، وأمّا بالاستقراء فإلى ستةٍ أو سبعةٍ،“
«ሙርሰል በደካማ ክፍል ውስጥ የተመደበው የታጠለው አካል ስለማይታወቅ ነው። ምክንያቱም ሰሀቢይ ሊሆን ይችላል ታቢዕይም ሊሆን ይችላል ታቢእይ ይሆናል ካልን ይህ ታቢእይ ደካማ ሊሆን ይችላል ሲቃ ሊሆን ይችላል ይህ ታቢእይ ሲቃ ይሆናል ካልን ራሱ አሁንም ከሰሀቢይ ይዞት ሊሆን ይችላል ወይም ከሌላ ከታቢእይ ይዞት ሊሆን ይችላል። ከታቢእይ ይዞት ሊሆን ይችላል ካልን ያሳለፍነው ይሁንታ ተመልሶ ይመጣል። ዓቅል በሚፈቅደው በዚህ መልኩ ገደብ እስከሌለው ድረስ መቀጠል ይቻላል በተጨባጭ በመገኘቱ ግን ወደ ስድስት እና ሰባት ታቢዕዮች 'ይኬዳል'።” (ኑዝሀቱ ነዘር)


አል-ሃፊዙ ስዩጢይ እንዲህ ይላል፦
”​( ثم المرسل حديث ضعيف ) ، لا يحتج به ،.......... والنظر للجهل بحال المحذوف ، لأنه يحتمل أن يكون غير صحابي ،وإذا كان كذلك ،فيحتمل أن يكون ضعيفاً “

«(ሙርሰል ደካማ ሀዲስ ነው) ማስረጃ አይደረግበትም... የተጣለው አካል ማን እንደሆነ ማወቅ አለመቻላችንን ከማየት አንጻር ምክንያቱም የተጣለው ከሰሃባ ውጭ የሆነ አካል ሊሆን ይችላል ይህ ከሆነ ደግሞ የተጣለው ደካማ ዘጋቢ ሊሆን ይችላል» (ተድሪቡ ራዊ )


ስለዚህ ሙርሰል ሐዲስ ውድቅ ሚሆነው ሰሀባው ስለተጣለ ሳይሆን ሰሀባ ብቻ ነው ወይ የተጣለው? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ስለማይቻል ነው። ታቢዕይ ከታቢዕይ የሚያወራበት እድል በጣም የሰፋ ስለሆነ ታቢዕይ ቀጥታ ከረሱል ሲያወራ ሰሃባ ብቻ ነው የተጣለው ብሎ መደምደም የሚቻል ስላልሆነ ነው ደካማ የሆነው።
https://t.me/comparativeerror
12👏93😁2🔥1