Gurage Zone Government Communication Affairs
1.59K subscribers
25.9K photos
22 videos
4 files
861 links
Gurage Zone Government Communication Affairs
Download Telegram
ህዳር 11/2016
==========
"ብዝሃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን 18ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ቀን አስመልክቶ የጉራጌ ዞን የመንግስት ሰራተኞች ውይይት አካሄዱ።

ኢትዮጵያ የብሔር ብሔርሰቦች ሀገር በመሆኗ ህዝቦቿ የመቻቻልና የመከባበር ባህላቸውን የበለጠ ማጠናከር ይገባል ተባለ ።

የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሀዲሞ ሀሰን በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት ሁሉም ማህበረሰብ ከተሳሳቱ የሀሰት ትርክቶች በመራቅ አንድነትና ብዛሃነትን የሚያጠናክሩ ሁነቶች ላይ በማተኮር አብሮ የመኖር እሴቱን ማጎልበት እንደሚገባ ገልጸዋል ።

ገንቢ የሆኑ ሀሳቦችን በማዳመጥ እርስ በእርስ ከሚያጋጩን ድርጊቶችና ሃሳቦች በመቆጠብና በመቻቻል በብሔር ሽፋን የሚነዙ የጥፋት እቅዶችን በማምከን የሚፈጠሩ ችግሮችንም ለመፍታት የመፍትሔ አካል በመሆን ለሀገራዊ አንድነት መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ቀን "ብዝሃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት"በሚል መሪ ቃል ለ18ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከበር መሆኑን የተናገሩት አቶ ሀዲሞ ሀሰን ኢትዮጵያ ብዝሃነትን ማስተናገድ የማይከብዳት ሀገር እንደሆነችና በተለይ የሁሉ ችግሮቻችን መፍትሔ የሆነውን የወንድማማችነትና የእህትማማችነት መርህ ተከትልን በጋራ መኖርና መልማት ይጠበቅብናል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የብሔር ብሔርሰቦች ሀገር በመሆኗ ህዝቦቿ መብታቸው ተከብሮ እና ተከባብረው እንዲኖሩ በማህበረሰቡ ዘንድ የግንዛቤ ስራ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል ።

የኔ ብቻ ከሚለው አመለካከት በመውጣት የኛ የሚለውን በመያዝ በመቻቻልና በመከባበር ሁሉም ማህበረሰብ በጋራ የሚኖርባት ሀገር መገንባት እንደሚገባ ገልጸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።