ህዳር05/2016ዓ.ም
================
ከጉራጌ ዞን አስተዳደር የተሰጠ የሀዘን መግለጫ
============================
ታላቁ አባታችን ሀጅ ሚፍታ ተረዳ በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ በርጨርና ሞቸያ ልዩ ስሙ ይነቆ በሚባል የገጠር መንደር በ1939 ዓ.ም ተወለዱ።
ሀጅ ሚፍታ ተረዳ የጉራጌ የባህል ሸንጎ አባል፣ የቂጫ ከ3ቱ ዋና ሽማግሌዎች እንዱ የነበሩ ሲሆን የጉመር ወረዳ በመወከል የክልል ምክር ቤት አባል በመሆን ህዝባቸውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ለ15 ዓመታት ያህል በትጋት ያገለገሉ የልማት አርበኛና ሞዴል አርሶ አደር ነበሩ።
አባታችን ሀጅ ሚፍታህ ተረጋ ባደረባቸው ድንገተኛ ህመም በአዲስ አበባ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ህዳር 04/2016 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት አርፈዋል።
አባታችን ሀጅ ሚፍታህ ተረጋ የጉራጌ አንድነት ለማጠናከር፣ ህብረተሰቡ በልማትና በዲሞክራሲ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን፣ በየአካባቢው ጨለማን ተገን በማድረግ ለህግ እንዳይመች መረጃ አጥፍቶ ለሚፈጸሙ ወንጀሎች በባህላዊ የሽምግልና ስርዓት ተጎጂ የሆነው ህብረተሰብ ፍትህ እንዲያገኝ በማድረግ እድሜያቸውን ሙሉ ለጉራጌ ህብረተሰብ ሲያደርጉት የነበረው አበርክትዎ ከፍተኛ እንደነበር የገለጹት አቶ ላጫ ጋሩማ ለቤተሰባቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ፣ ለመላው ለጉራጌ ብሔረሰብ መጽናናት እየተመኘሁ ፈጣሪ ነፍሳቸው በሰላም ከደጋጎቹ ጋር በአፀደ ገነት ያኑርልን በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሀጅ ሚፍታ ተረዳ ባለትዳር እና የ7 ወንዶችና የ2 ሴት ልጆች አባት ሲሆኑ ሁሉንም ልጆቻቸውን አስተምረው ለቁም ነገር አብቅተዋል።
ሀጅ ሚፍት ተረዳ በሰሜኑ የሀገራችን ጦርነት ወቅት የጉራጌን ህዝብ በመወከል ለሰራዊቱ ድጋፍ በአካል ግንባር ድረስ በመሄድ አበረታትው የተመለሱ ሀገር ባለውለታ ነበሩ።
እድሜ ልካቸውን የጉራጌ ህዝብ ሲያገለግሉ የነበሩት ሀጅ ሚፍት ተረዳ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ከዚህ አለም በሞት በመለየታቸው ጥልቅ ሀዘን የተሰማቸው መሆኑን የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ገለፁ።

ህዳር 5/2016ዓ.ም
በያበሩስ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተስተጓጉሎ የነበረው የመማር ማስተማር ሂደት ለማስቀጠል ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ተጠየቀ።
ይህ የተጠየቀው በሰሞኑ በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ያበሩስ ትምህርት ቤት በጸጥታ ችግር ምክንያት የተቋረጠው የትምህርት ሂደት ለማስቀጠል ከወላጆች፣ ከመምህራንና ከሌሎችም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በወልቂጤ ከተማ በተደረገ ውይይት ላይ ነው።
የጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ረዳት ኮሚሽነር ታገሰ አርፊጮ በመድረኩ ተገኝተው እንዳሉት ያበሩስ ትምህርት ቤት ብቁ ዜጋ በማፍራት ለሀገር ያበረከተ ትምህርት ቤት ነው።
ትምህርት ቤቱ ወደ ቀድሞ የመማር ማስተማር ሂደት ለመመለስ የማህበረሰቡ ቁርጠኝነት ትልቅ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ችግር የፈጠሩ አካላት በህግ ይጠየቃሉ ብለዋል።
በሁለት ሴት ተማሪዎች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት የትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር ስራ እንዲስተጓገል ማድረጉን ጠቅሰው በዚህ ተግባር የተሳተፉ አካላት በገለልተኛ አካላት ምርመራ እየተጣራ መሆኑን ገልጸዋል።
የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲቀጥልና ተማሪዎች ትምህርታቸውን ተረጋግተው እንዲማሩ የጸጥታ ሀይሉ ትምህርት ቤቱን በመጠበቁ ረገድ ሀላፊነት እንደሚወስድ አበክረው ተናግረዋል።
ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ሲልኩ ጤናማ አዕምሮ፣ አመለካከትና አስተሳሰብ እንዲኖራቸው ብሎም ብቁና በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ወላጆች ለልጆቻቸው መምከርና መገሰጽ ይኖርባቸዋል።
የኮማንድ ፖስቱ ምክትል ሰብሳቢ ኮማንደር ታምራት ታንቱ በበኩላቸው የመማር ማስተማር ሂደቱ ለማስቀጠል ወላጆች ልጆቻቸውን የፓለቲካ አስተሳሰብ እንዳይዙ መምከር፣ መገሰጽና ክትትል ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል።
ተማሪዎች ወደ ግቢ ሲገቡ በጸጥታ ሀይሉ ተፈትሸው እንዲገቡ እንደሚደረግ ገልጸው ለዚህም ትምህርት ቤቱ ሁሉም ተማሪዎች መታወቂያ እንዲኖራቸው መስራት እንዳለበትም አሳስበዋል።
ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው መቅረት የለባቸውም ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ የትምህርት ቤቱ ዙሪያ በጸጥታ ሀይሉ በአግባቡ ጥበቃ እንደሚደረግለት ገልጸው ከዚህም ባለፈ ወላጆች የትኛውም ችግሮች ሲፈጠሩ ከጸጥታ ሀይሉ ጎን በመቆም መረጃ በመስጠት እንዲተባበሩ ጠይቀዋል።
የሰላም ባለቤት ሁሉም ነው ያሉት ኮማንደሩ ለዚህም ለሰላሙ ሁሉም ዘብ ሊቆም ይገባል ነው ያሉት።
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሙባሪክ አህመድ እንዳሉት ትምህርት ቤቱ ወደ ቀድሞ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲመለስ ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል ብለዋል።
የትምህርት ስርአቱ እንዲስተጓገል ያደረጉ አካላት በህግ አግባብ መጠየቅ አለባቸው ብለዋል።
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መንዚላት አህመድ ወላጆች የባከኑ የትምህርት ጊዜ ቆም ብሎ በማሰብ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት መላክ እንዳለባቸው ጠቁመው ከዚህም ባለፈ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ተማሪዎች እንዲሆኑ ወላጆች ሀላፊነት መውሰድ አለባቸው ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ ወላጆች እንዳሉት ትምህርት ቤቱ ወደ ቀድሞ የመማር ማስተማር ሂደቱ ለመመለስ ወላጆች ልጆቻቸውን በመምከርና በመገሰጽ እንዲልኩ አንስተዋል።
በትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲቋረጥ በማድረግ የተሳተፉ አካላት ላይ እርምጃ እንዲወሰድም ይጠይቀዋል።
ትምህርት ቤት የእውቀት መገበያያ እንጂ የፖለቲካ ማራመጃ አይደለም ያሉት ተሳታፊዎቹ ለዚህም ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱ ለማስቀጠል ሁሉም ኃላፊነት እንዳለበት መናገራቸውን የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።