ጥቅምት 29/2016 ዓ.ም
በዞኑ ዘንድሮ የምርት ዘመን ከ5 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ምርት እንደሚሰበሰብ የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ ገለጸ።
በወረዳው በመኸር ወቅት የለማው ሰብሎችን ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ እንዳይበላሽ ለመሰብሰብ መዘጋጀታቸውን የጌታ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ።
የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አክሊሉ ካሳ በ2014/15 የምርት ዘመን በዞኑ 87ሺህ 560 ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች በስንዴ፣ በገብስ፣ በባቄላ፣ በአተር፣ በጤፍና በሌሎችም ሰብሎች በዘር መሸፈን መቻሉን ገልጸዋል።
በመኸር እርሻ ወቅት እንደ ሀገር የማዳበሪያ እጥረት ችግር እንደነበረና በዞኑም እጥረት ነበር ያሉት አቶ አክሊሉ ከምርጥ ዘር አቅርቦት ጋር ተያይዞ በቂ አቅርቦት ማቅረብ ተችሏል ብለዋል።
በዘንድሮ በምርት ዘመን ከለማው ማሳ 5ነጥብ 5 ሚሊዮን ምርት ይጠበቃልም ብለዋል።
በዞኑ አብዛኛው አካባቢ ምርት መድረሱን ተከትሎ አርሶ አደሩ ሳይዘናጋ የደረሱ ሰብሎችን ለመሰብሰብ ደቦ፣ ጌዝና ተማሪዎች በማስተባበር መሰብሰብ እንዳለበትና መንግስትም ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበት ብለዋል።
የዞኑ አርሶ አደሮች የመኸር ምርት ከመሰብሰብ ጎን ለጎን የበጋ መስኖ ስራዎችን አጠናክሮ መስራት እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
የጌታ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙዘፋ የሱፍ እንዳሉት በወረዳው በዘንድሮ የምርት ዘመን ከ4 ሺህ3 መቶ ሄክታር መሬት በላይ ማሳ በተለያዩ ሰብሎች በመሸፈን በዚህም ከ1መቶ 48 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።
በወረዳው በመኸር እርሻ ወቅት ስንዴ፣ ገብስ፣ ባቄላ፣ አተር፣ድንችና ሌሎችም የጓሮ አትክልት መልማቱን ገልጸዋል።
በወረዳው በመኸር ወቅት ከማሳ ቅድመ ዝግጅት ጀምሮ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ያነሱት አቶ ሙዘፋ በዚህም ለአርሶ አደሩና ለባለሙያዎች የክህሎት ስልጠና በመስጠት ወደ ተግባር መግባቱን አንስተዋል።
በመኸር ወቅት በወረዳው የማዳበሪያ እጥረት እንደነበረ ያነሱት ኃላፊው ይህም ችግር ለመቀነስ ወደ ወረዳው የገባው ማዳበሪያ በፍትሃዊነት ማሰራጨት ተችሏል ብለዋል። በዚህም 2ሺህ 6 መቶ NPS ተሰራጭተዋል።
የምርምር ማዕከላት አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን በምርጥ ዘር በመደገፍና በወረዳው በተለያዩ ሰብሎች ላይ ምርምር በማድረግ እንዲሰሩ ጠይቀዋል።
በወረዳው ያሉ አርሶ አደሮች በየአካባቢያቸው የደረሱ ሰብሎችን ሳይዘናጉ በአግባቡ መሰብሰብ እንዳለባቸው ያነሱት ኃላፊው ለዚህም የወረዳው መንግስት የምርት አሰባሰብ ግብረ ሃይል በማቋቋም ወደ ስራ መግባቱን ገልጸዋል።
አርሶ አደር አሊ ከማል፣ አርሶ አደር ሸምሱ ከማል እና አርሶ አደር ኑሩ ሀሰን በጌታ ወረዳ የሰነንና ቆረፍቻ ቀበሌ አርሶ አደሮች ናቸው።
አርሶ አደሮቹ በጋራ በሰጡት አስተያየት በኩታ ገጠም 10 በመሆን ስንዴ፣ ገብስ ማልማታቸውን ተናግረው በዚህም በማሳ ዝግጅት፣ በአረም ቁጥጥር ወቅት በጋራ ሲሰሩ እንደነበር አስታውሰዋል።
እርሻው ደጋግመው በማረሳቸው፣ የአረም ቁጥጥር በወቅቱ በማረማቸውና አስፈላጊውን እንክብካቤ በማድረጋቸው ሰብሉ በጥሩ ቁመና ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
ሰብሉ እየደረሰ መሆኑን ተከትሎ ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ ምርቱ እንዳይበላሽ የቤተሰባቸውን ጉልበት በመጠቀም በደቦ ለመሰብሰብ ዝግጅት ማድረጋቸውንም ተናግረዋል።
የመኸር እርሻ ባነሱበት ቦታ ድንች ለመትከል እቅድ እንዳላቸውም ጠቁመዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።