የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት
990 subscribers
12.1K photos
14 videos
598 links
Download Telegram
በገጠር የኢንዱስትራላይዜሽን ፕሮግራም በማጠናከር የግብርና ምርቶችን ማቀነባበር የሚያስችል ስርዓት መፍጠር ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ልማት ማጠናከር ያለመ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በውይይት መድረኩ ማጠቃለያ በሰጡት የስራ መመሪያ እንደገለጹት የገጠር የኢንዱስትራላይዜሽን ፕሮግራም በማጠናከር የግብርና ምርቶችን ማቀነባበር የሚያስችል ስርዓት መፍጠር ይገባል ብለዋል።

ከኢንቬስትመንት ጋር በተያያዘ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ በአዲስ አበባ ጽ/ቤት በመክፈት ስራ ይጀመራል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም ከፍተኛ ልምድ ያላቸውን አካላት በመመደብ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ይሰጠዋል ሲሉም ጠቁመዋል።

በክልሉ የኢንዱስትሪ መንደር ለማቋቋም በትኩረት እንደሚሰራም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

ክልሉ ሲቋቋም በርካታ ፈተናዎች እንዳጋጠሙት የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ የነባር እዳ ክፍያ እና ሌሎች ተግዳሮቶችን በመሻገር በአሁኑ ሰዓት በሰባት ማዕከላት የክልል ቢሮዎች ግንባታ እየተካሔደ ስለመሆኑም አመላክተዋል።

የኑሮ ውድነቱን ለማርገብ ለህብረተሰቡ የፍጆታ እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ዝግጅት እየተደረገ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል።

አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተር ፕራይዞች ለባለ ሀብቱ፣ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ እንዲሁም ለዜጎች የስራ እድል ፈጠራ መሰረት መሆኑን ተናግረዋል።

ለኢንተር ፕራይዞች የገበያ ትስስር ፣ የማምረቻ ቦታዎችን ማዘጋጀት፣የሊዝ ፋይናንስ እንዲጠቀሙ ማድረግ እንዲሁም ህጋዊ አሰራርን ተከትሎ እቃዎችን ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ እድል መፍጠር የሚያስችል አሰራር ማጠናከር እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

የስራ ባህልን በማሻሻል ከድህነት መውጣት ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም በቤተሰብ እና በማህበረሰብ ደረጃ የጋራ ጥረት ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል።

ያሉትን ጸጋዎች በመጠቀም ለገቢ እና ለስራ እድል ተጠቃሚነት መዋል አለበት ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

የወጪ ምርቶች ላይ እሴት በመጨመር የገቢ መጠንን ማሳደግ ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ተኪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በስፋት እና በጥራት ማምረት ይገባል ብለዋል።

የሌማት ትሩፋት ስራዎችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ተግባራዊ በማድረግ የገቢ አቅምን ማጎልበት ላይ የተቀናጀ ጥረት ይጠይቃል ሲሉም አብራርተዋል።
መረጃው የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ነው።
መጋቢት 29/2017 ዓ.ም
የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች እና በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በጤናው ልማት ዘርፍ የተያዙ ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ርብርብ ላይ የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ ተገለፀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ይህ የተገለጸው የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት የ2017 ዓ.ም የጤና ኤክስቴንሽን ፌስቲቫል በዛሬው ዕለት በተካሄደበት ወቅት ነው።

በዚህ ወቅትም የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን የመክፈቻ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አክለውም ሃገራችን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የምትታወቅበት የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ተቀርጾ ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት ከ20 ዓመታት በላይ ማስቆጠሩን ጠቅሰው በዘርፉም ከፍተኛ ለውጥ መመዝገቡን ገልጸዋል።
ከተመዘገቡት ለውጦች መካከልም የእናቶችና ህፃናት ሞት መቀነስ፣ ተላላፊ በሽታዎች መቀነስ፣ የግልና አካባቢ ንጽሕና መጠበቅና ምቹ መኖሪያ መንደር መፍጠር በዋናነት ተጠቃሾች መሆናቸውን አቶ ሚፍታ ጠቁመው በአንጻሩ እየተስተዋለ ያለውን የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም መቀዛቀዝ የመጡ ለውጦችን ወደ ሆላ እንዳይቀለብሱ ስጋት የፈጠረ በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካል ፕሮግራሙ እንዲነቃቃ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ዋና ኃላፊ አቶ መሃመድ አሚን ጀማል በበኩላቸው የባለድርሻ አካላትና የባለሙያውን የጋራ አረዳድ ኑሮ የህብረተሰቡን ጤና ማሻሻልና ፍትሃዊነቱ የተረጋገጠ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ የመድረኩ ዋነኛ ዓላማ መሆኑን ተከትሎ ተሳታፊዎች ይህንን ዓላማ ለማሳካት የጋራ ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መሃመድ አሚን ጀማል ለመድረኩ የተዘጋጀ ሠነድ አቅርበው ውይይት ተደርጓል።

በውይይት መድረኩ ላይ ከተነሱት ዋና ዋና ሃሳብና አስተያየቶች መካከል በየደረጃው ያሉ አመራሮች ለጤና ኤክስቴንሽን ተግባር ስኬታማነት አበክረው መስራት እንዳለባቸው ፣ ለጤና ኤክስቴንሽን መኖሪያ ቤትና ጤና ኬላ ማደስ እንደሚያስፈልግ፣ የበታች አመራሩ የሰበሰበውን የማዓጤመ ገንዘብ ገቢ ማድረግ እንዳለበት፣ የግልና አካባቢ ንጽህና አጠባበቅ ላይ እንደሚሰሩ ተሳታፊዎቹ አንስተዋል የሚሉት ተጠቃሾች ናቸው።

የውይይት መድረኩን የመሩት የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ የርእዮት አለም ዘርፍ ኃላፊ እና ረዳት የመንግስት ተጠሪ የሆኑት አቶ ሚፍታ አረቦ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የብልጽግና መንግስት ለጤናው መስክ በሰጠው ልዩ ትኩረት ሊታይና ሊቆጠሩ የሚችሉ ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገብ መቻሉን ጠቁመው አዲሱን የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ በማህበረሰቡ ዘንድ ግንዛቤ በመፍጠር ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባና የሴቶች ልማት ህብረት ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ሚፍታ አረቦ የጤና ኤክስቴንሽን ተግባራትን በአደረጃጀት እና በቅንጅት በመምራት ከመቀዛቀዝ ወጥቶ ወደ ቀድሞ አተገባበር ብሎም ለተሻለ ለውጥ መንቀሳቀስ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መሃመድ አሚን ጀማል በበኩላቸው መንግስት በሽታ መከላከልንና አክሞ የማዳን ፖሊሲ በመቅረጽ ወደ ተግባር በመግባት በረካታ ተግባርት መሰራቱን ጥቅሠው ጽዱ መንደር እና ጽዱ ኢትዮጵያን መፍጠር ብሎም የመዓጤመ አባላት መዋጮ ብር 100% ገቢ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በፌስቲቫሉ ላይ የወረዳ አመራሮች የቀበሌ ሊቀ- መናብርትና ስራ እና የጤና ኤክስቴንሽኖች እንዲሁም የጽህፈት ቤቱ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
ዘገባው የወረዳው የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው።