Code IT | Remote Work
1.94K subscribers
405 photos
72 videos
12 files
200 links
Exploring code, AI, remote work & building in public. Join the lab and grow with us!
Download Telegram
የምስራች 🎉

የአባይ ውሃ ለሦስተኛ ጊዜ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል፡፡

#GERD
ለአይነ ስውራን የቀረበ ዘመናዊ መሪ ወይም ኬን
****
ተመራማሪዎች የእይታ ችግር ያለባቸውን ሰዎች በእንቅስቃሴ የሚያግዝ ዘመናዊ ዘንግ ወይም ኬን ሰርተው አቀረቡ፡፡ በተለምዶ ነጩ ምርኩዝ በመባል የሚታወቀው ይህ አይነስውራን ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚጠቀሙበት ዘንግ ተጠቃሚዎቹ የሚኖራቸውን እንቅስቃሴ የተሸለ ቀላል እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ መደበኛው ዘንግ ከመሬት ጋር ሲጋጭ የሚኖረውን ድምጽ በመከተል አንድ አይነስውር በቀላሉ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ይችላል፡፡

ሳንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ይህንን መደበኛ ዘንግ እጅግ በማሻሻል አይነ ስውራን ከደህንነት ስጋት ነጻ ሆነው እንደፈለጉ እንዲንቀሳቀሱ በሚያስችል መልክ የሮቦት ቴክኖሎጂ አክሎበት ማቅረቡ ተነግሯል፡፡ ከራስ ነድ መኪኖች ቴክኖሎጂ ጋር ተጣምሮ የተሰራው ይህ ዘንግ በ400 ዶላር የቀረበ ሲሆን ተጠቃሚዎች እንደሚኖሩበትና እንደሚንቀሳቀሱበት አካባቢ ምቹ የሆነ ድጋፍን የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡

ስማርት ዘንጉ በመንገድ ላይ ወይም በየትኛውም አካባቢ የሚኖሩ እንቅፋቶችን በመለየት በቤት ውስጥም ሆነ ከቤት ውጭ ለመንቀሳቀስ ምቹ የሆኑ ቦታወችን በመምረጥ መጓዝ የሚያስችል ነው፡፡ በዘርፉ ሌሎች ሴንሰር የተገጠመላቸው መሪ ዘንጎች ያሉ ቢሆንም ከአጠቃላይ ክብደታቸው እና ከሚያወጡት ዋጋ አንጻር ተፈላጊነታቸው አነስተኛ ነው፡፡ በሌላ በኩል ከቴክኖሎጂ አንጻር እጥረት ያለባቸው በመሆኑ ማለትም ሴንሰሩ ከተጠቃሚው ፊት ለፊት ያለን ነገር ብቻ የሚያሳውቅ በመሆኑ ይህ ተሻሽሎ የቀረበው መሪ ዘንግ እጅግ ተመራጭ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡

#Daily_Tech_News
▬▭▬▭▬▭▬▭
Follow us: YouTube,  Telegram,  Tiktok
@innovate_aastu
@innovate_aastu
የአንደኛ አመት ተማሪዎች ፣ የመጀመሪያውን Semester ስለጨረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እያልን😊
የእረፍት ግዜያችሁን ከኛ ጋር እንድታሳልፉ በየቀኑ የሚለቀቁ የ Programming እንድሁም Soft skill ትቶሪያሎች እዚህ ላይ ለመልቀቅ አስበናል። የቱ ብጀመር ትመርጣላችሁ?
Anonymous Poll
31%
C++ for beginners
10%
Java for beginners
26%
Python for beginners
14%
Web Development
19%
Mobile App Development
Audio
My favorite one😘
🎷 🎹 🎸
#Bydawitgetachew #jazz

@innovate_aastu
#MelkamFetena 🎉
ለሁላችሁም የ AASTU ሁለተኛ ዓመት ተማሪዎች፣ መልካም ፈተና። 😊

AASTU STUDENTS APP

@innovate_aastu
@innovate_aastu
⬇️ @faresbelaynehg ⬇️
በግቢ ህይወቴ ያጋጠመኝ ነገር እና እስካሁን የተሸወድንበት
ጉዳይ ላካፍችሁ..
.😞😞😞

አሁን ላካፍላችሁ ያሰብኩት ሀሳብ ዩኒቨርሲቲ ስለሚሰጠን የሴመስተሮች ክፍያችን ስለ GPA (GRADE) ነው።
አንድ ሰራተኛ ስለሚሰራበት መ/ቤት ከመስሪያ ቤቱ ደሞዙ በየወሩ እንደሚከፈለው እኛን ደግሞ በየ ሴመስተሩ ግሬድ ይከፍለናል፣ አንድ ሴመስተር ስንማር የሚንወስዳቸው ኮርሶች፣ ለዛው ሴመስተር ነው የሚንማረው ፤ በስተመጨረሻ አስማሪዎቹ በእንኳን በራሳቸው ባላወጡት ፈተና እየተፈተንን አንድ ሴመስተር ሙሉ ግዜያችንን ፈጅተን የሚናገኘው የመጨረሻው ስጦታ GRADE REPORT ነው። ውስጤ አንድ ጥያቄ የሚጠይቀኝ ነገር ብኖር ያገኘሁት ግሬድ እና አንድ ሴመስተር ውስጥ ያለው ግዜ፣ ሚዛን ላይ ብቀመጥ የቱ ይበልጣል ነው፤ ሰው በግሉ ያለው ብቸኛ ሀብት ግዜ ነው። ይህን ግዜያችንን በ 'GPA' መነገድ ትርፍ ነው ክሳራ ይመስልሻሀል/ሻል??
ይሄን ዋጋክ ብለው የሰጡን አንድ ግሬድ እኮ ለቀጣዩ ሴሜስተር መተማመኛ አይደለም ሁብትህ ልሆን አይችልም፣ ም/ቱም በሚቀጥለው ሴመስተር አሁንም ግዜህን ካልሸጥክላቸው "የባለፎ ሴመስተር ትውስታው አሪፍ ነበር፣ ጥሩ ግረድ ነበረው" ብለው ከግምት ይከታሉ? (አይከቱም) ስለዝህ ከአንድ ሰመስተር ልፋታችሁ የማትፈልጉትን ነገር በመማር እና ማትፈልጉትን ነገር በመልፋት ምንም እውቀት ሳትይዙ ለቀጣይ አመታቶቻችሁ የሚሆን ነገር ሳይኖራችሁ ዝሞ ብሎ መባከን፤ እርግጠኛ ባልሆናችሁበት ነገር ዝም ብላቹ ግዜያቹን ማሳለፍ አልሰለቻችሁም?
በየ ሴመስተሩ የሚንፈተናቸው ነገሮች ይሄ ተማሪ ምን ያህል ያውቃል ምን ያህል ያስባል ምን ያህል ችግር ፈች አእምሮ አለው ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ ምን ያህል እንደምናስታውስ ነው የሚገመግሙት፣በጣም የሚገርመው ደግም አንዳንድ አስተማሪዎች ተማሪ እንድያጣ ነው ጥያቄ የሚያወጡት። እንግድህ ብያንስ ላለፉት 14 አመታት የማስታወስ ችሎታችንን ስንፈተን ነበር፣ ከዚህ በኋላ ግን በዩኒቨርስቲ ባለህ ትርፍ ጊዜያት አሁንም ደግሞ የማስታወስ ችሎታህን proof እንድታረግ ነው ሚመጠብቁህ። እንግድህ እኛ ከዚህ በኋላም የማስታወስ ችሎታችንን ለዩኒቨርስቲው ፣ ለቤተሰቦቻን እናረጋግጥ?
የሚገርመው ለራሳችን እንኳን አይደለም የማስታወስ ችሎታችንን የሚናሳየው፣ ም/ቱም ውስጣችን የቱ እንደሚበልጥ ያውቃል! እንግዲያስ የወጣትነት እድመያችንን ይሄን ነገር proof ለማድረግ እየተሯሯጥን ማሳለፍ አለብን እንዴ?
በሀገራችን በየአመቱ የሚመረቁ ወጣቶች productive ያልሆኑ ለምን ይመስላችኋል፨
ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ጠንክሮ ስላልሰሩ?
እንደዚያ ከሆነ በየአመቱ ከ40 በላይ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ ነጥቦ በማምጣት በማዕረግ እና በዋንጫ የተሸለሙ ልጆች የት ነው ያሉት?
እስቡት ከአምስት አመት በፊት ከ ዩኒቨርስቲው በከፍተኛ በማዕረግ የተመረቁ ልጆች ምን ፈጠሩ?፣ ለሀገራችንስ ምን አስተረፉ?
ካለፉትአራት አመት ጀምሮ እስካሁን ድረስ በዋንጫ እና በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቁ ልጆች ምን ያህሎቹ በሀገሪቱ ውስጥ የተመረቁበት ዘርፍ የሚታይ ነገር አበረከቱ።
በየ ጊቢዎቹ እየተፈበረኩ ያሉ ልጆች ምን የሚገባ ነገር አሳዩ?
እኛ አሁን መንቃት ያለብን አይመስላችሁም?
በአለማችን ታሪክ ወደኋላ ብንመለከት እንኳን ለአለም ብርሀን የሆኑ ፣ አዳድስ ነገር የሰሩ፣ ችግሮችን የፈቱ፣ በኛ እድሜ ላይ የነበገሩ ናቸው። በኛ ኦድሜ ነው ስጠይቁ ስመራመሩ ፣ ስከራከሩ፣ ስፈጥሩ የነበረው።
አንዳንዶች በኛ እድሜ ነው ልጆች አፍርተው ቤተሰብ የሚያስተዳድሩት።
እኛስ አሁን እንኳን አድስ ነገር መፍጠር ይቅርና፣ የተፈጠረውን ራሱ በአግባቡ ማወቅ አልቻልንም።
እንኳን ህይወት እንዴት እንደምትሰራ መጠየቅ ይቅርና ክፍል ውስ ያልገባንን ነገር መጠየቅ ራሱ እስካለመቻል ደርሰናል።
እንኳን ቤተሰብ ማስተዳደር ይቅርና አሁን በቤተሰቦቻን ከዚህ በኋላ ራስህን ቻል ብሉ ህይወት እንደት መኖር እንዳለብን ራሱ አናውቅም።
የእውነት አሁን በዚህ እድሜያችን እንዲህ መሆን ነበረብን? ምን እየሆነ ነው? ስርአቱ ምንያረገን ነው?
አሁን ከአመታት በኋላ ምን አውቃለሁ ብለን ልናወራ ነው። ከጊቢ ስንወጣ ነው ተመራመሪ እና ጠያቂ ሚንሆነው?
እውነት ለመናገር ከተመረቅን ከአንድ አመት በኋላ ስለሰራነው መመረቂያ ፕሮጀክት ብንጠየቅ ራሱ አናውቅም።
ሁላችንም አንድ በእርግጠኝነት ሚናውቀው ነገር የለም፣ ስለ አንድ ነገር እርግጠኛ መሆን አልቻልንም፣ ስለምንማረው ነገር እርግጠኛ አይለንም፣ ስለምናምን ነው ነገር እርግጠኛ አይለንም። ወጣት ነህ በዚህ እድመህ ነው ለመጪዎቹ አመታት የሚትከተለውን መንገድ የሚትወስንበት የቀጣዮች እድሜህን ንድፍ የሚትነድፍበት፣ የሚንከተለው እምነት ላይ እርግጠኛ ምንሆንበት ጊዜ ነው።

የዩኒቨርስቲ አስተማሪዎቻችን ራሱ በሚያስተምሩን ነገር ላይ እርግጠኛ አይደሉም፣ ከየት እንደመጣ ምን እያስተማሩን እንዳለ፣ እርግጠኛ አይደሉም። እስካሁን ያስተማሩን ነገር ስህተት ነው ብባል እና አድስ ነገር ብመጣ እሱንም ልያስተምሩን ሳያንገራግሩ ይመጣሉ። አሁን እኛ እነሱ የተከተሉትን መንገድ ተከትለን የእውነት ፍሬ የሚናፈራ ይመስልሃል? ከኛ በኋላ እየመጡ ላሉት ትውልዶ ለወንድሞቻችን ለእህቶቻችን ለዘመዶቻችን ለነገ ልጆቻችን የምንተረፍ እርግጠኛ የሆንበት ነገር ለማሳለፍ እየሄድን ይመስልሀል?
በርግጠኝነት አብዛኛውን ክሳራ እየነገድን ነው ፣ ቆም ብለህ ማሰብ አለብህ/ቢ?
ከአመታት በፊት ከዩኒቨርስቲ የተመረቁትን እንዳንኛው ሰው ናቸው ፣ እንዳንተኛው ማሰብ ይችላሉ፣ አሁን ግን ያሉበት ደረጃ በቂ ነው ብላችሀ ታስባላቹ ? አይደለም። በጊቢ ውስጥ የለፉትን ያህል አላወቁ፤ ጊቢ ውስጥ የተሰቃዩትን ያህል ውጤታማ አልሆኑም፣ ይህ በነሱ የሚናየው ውጤት እነሱ የተከተሉት መንገድ የት እንደምናደርስ ነው፣ የነሱን ፈለግ ከተከተልን ማንም አያድነንም።
እስከመች ሰውን ለማስደሰት፣ እስከመች ቤተሰብ ለማስደሰት፣ ሰዎች ጋር ክብር ለማግኘት እንልፋ፣ እስከ መች ስለ ትውስታ ስለምንፈተነው ነገር አስተማሪው ራሱ ላላወጣው ጥያቄ እንጨነቅ፣ እስከ መች ግሬድ ለመሸለም እንሯሯጥ።
እኛ አሁን እንግዲህ ከ12 አመት በላይ ለፋን እኮ።አሁን ትምህርት ቆሟል፣ ከዚህ በኋላ ትምህርት ቀርቷል ብባል ምን ልንሰራ ነው። ምን እናውቃለን? ተግባራው የሚሆን ነገር ምን መስራት እንችላለን፣ ወፍ እራስህን እያታለልክ አይመስልህም/ሽም። ዝሞ ብለህ ሰዎች ስላደረጉ ፣ስዎች ስለፈለጉ፣ ያዋጣል ያበላል ስላሉ ፣ ይሻላል ስላሉ፣ በህይወታችን ስንት ነገር እያረግን ነው?!
በውጣችን አምነን የሚናገረገው ነገር ውስን ነው፣ አሁን ከዚህ በኋላ ማን ልያድነን ነው። እንግድህ ከዝህ በኋላ ቤተሰቦቻችንን እንጠብ? ዘመዶቻችንን እንጠብቅ? መንግስት ሌላ ምርምር ሰርቶ እስኪያሻሽል እንጠብቅ?
አይሆንም የራሳችንን ነገር መፈለግ ይሻላል።
እኔ መፍተሄ ናቸው ያልኳቸው፣ ሶስት ሀሳብ ላንሳላችሁ።
Continue Reading


▬▭▬▭▬▭▬▭▬▬▭▬▭▬
Join ● React ● Share
@faresbelaynehg
@faresbelaynehg
▬▭▬▭▬▭▬▭▬▬▭▬▭▬
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
AI Fashion designer 😱
#ai #tech
▬▭▬▭▬▭▬▭
Follow us: YouTube, Telegram, Tiktok
@innovate_aastu
@innovate_aastu