Code IT | Remote Work
1.94K subscribers
405 photos
72 videos
12 files
200 links
Exploring code, AI, remote work & building in public. Join the lab and grow with us!
Download Telegram
አነጋጋሪው መሳርያ የታጠቀ ሮቦት

በያዝነው አመት ለእይታ የቀረበውና ጀርባው ላይ አልሞ ተኳሽ መሳርያ የተገጠመለት ባለ አራት እግር ሮቦት አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ በጎስት ሮቦቲክስ አማካኝነት የተሰራው ይህ ታጣቂ ሮቦት በዚህ ሳምንት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በተካሄደው በአሜሪካን ጦር ኃይል ሕብረት አመታዊ ስብሰባ ላይ ነበር ለእይታ የበቃው፡፡ ሮቦቱ በጀርባው ስዎርድ ዲፌንስ በተባለው ተቋም የተሰራውና በሀገሪቱ ልዩ ኃይሎች ጥቅም ላይ የሚውለው ባለ 6.5 ሚ.ሜ አልሞ ተኳሽ መሳርያ የታጠቀ ሲሆን እስከ 1200 ሜትር ድረስ አርቆ መመልከት የሚችልና በቀንም ሆነ ምሽት የሚሰራ ካሜራም ተገጥሞለታል፡፡

▬▭▬▭▬▭▬▭
Follow us: YouTube, Telegram, Tiktok
@innovate_aastu
@innovate_aastu
Back to Moon\ ጉዞ ወደ ጨረቃ
=================
ናሳ መጪውን ሰው አልባ የአርጤምስ I የጨረቃ ተልእኮ በተመለከተ እሮብ፣ ኦገስት 3 እና አርብ ኦገስት 5 አጭር መግለጫዎችን ያቀርባል።
ኤጀንሲው በአሁኑ ጊዜ ከሰኞ ኦገስት 29 ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የኦሪዮን መንኮራኩር በጨረቃ ዙሪያ እና ወደ ምድር ለመላክ የስፔስ ላውንች ሲስተም ሮኬት ለማስወንጨፍ ኢላማ አድርጓል።
ተልእኮው ሰው በረር ለሆነው ለአርጤምስ 2ተኛ ፈር ቀዳጅና የኦራየን መንኮራኩርን ሆነ የመወንጨፊያ ሮኬቱን ለመፈተሽ በስድስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ይካሄዳል።

NASA will host a pair of briefings on Wednesday, Aug. 3, and Friday, Aug. 5, to preview the upcoming Artemis I lunar mission. The agency is currently targeting no earlier than Monday, Aug. 29, for the launch of the Space Launch System rocket to send the Orion spacecraft around the Moon and back to Earth. The mission will take place over the course of about six weeks to check out systems before crew fly aboard on Artemis II.
https://www.nasa.gov/press-release/nasa-to-host-briefings-to-preview-artemis-i-moon-mission

▬▭▬▭▬▭▬▭
Follow us: YouTube, Telegram, Tiktok
@innovate_aastu
@innovate_aastu
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
An incredible high-quality image was taken recently by NASA on Mars.

The image is so cristal you can analyze every rock, and even the hole drill that curiosity did on the red planet. The footage you are about to see is a combination of 122 images to create a mesmerizing experience.
The red planet is amazing.

Source: https://www.nasa.gov/?fbclid=IwAR2WDmBQoCHNBgtIqIaZF0ZW4VVyhm0-JeihbxqpzPz9SxiiWd7c2EyInzM
▬▭▬▭▬▭▬▭
Follow us: YouTube, Telegram, Tiktok
@innovate_aastu
@innovate_aastu
ኬንያ የኮምፒውተር ቋንቋን (Coding) በትምህርት ሥርዓቷ ውስጥ በማካተት ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች።

ኬንያ በአንደኛ ደረጃ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቿ የኮምፒውተር ቋንቋ (Coding) በስርዓተ ትምህርቶቿ ውስጥ በማካተት የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሀገር ሆናለች። ከዚህ ውሳኔ ሀገሪቱ ብዙ ተጠቃሚ እንደምትሆን በርካቶች እየመሰከሩ ነው።

በተጨማሪም ሀገሪቱ ብሄራዊ የሳይበር ደህንነት ስትራቴጂ 2022 ያዘጋጀች ሲሆን እስከ 2032 ይቆያል የተባለው የኬንያ ብሄራዊ ዲጂታል ማስተር ፕላንም ተመርቋል።

ይህን አስመልክቶ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የስልጣን ዘመናቸው የሚያበቃው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ብሄራዊ ዲጂታል ማስተር ፕላኑ የስራ እድል ፈጠራን እንደሚያሳድግ፤ የአይሲቲ ሴክተሩ የሁሉንም የኢኮኖሚ ዘርፍ እድገት እንደሚያሳድግ ጥርጥር የለውም ሲሉ ተናግረዋል።

የዲጂታል ማስተር ፕላኑ በመላ ሀገሪቱ ከ20,000 በላይ መንደሮች የዲጂታል ማዕከላትን የማቋቋም ግብ ያስቀመጠ ሲሆን 40,000 ወጣቶችን በመቅጠርም ፍላጎት ያላቸውን ዜጎች እንዲያሰለጥኑ እንደሚደረግም ይገልጻል።

ኬንያ በአህጉሪቱ ለዲጂታል ፈጠራዎችና ለዘርፉ ዋነኛ ቦታ መሆኗን ለማስመስከር ጥረቷን ቀጥላለች። ይህንን በሥርዓተ ትምህርቷ መደገፏም የዚህ ትልቅ ማሳያ ነው። በዚህ ዓመት ብቻ ማይክሮሶፍት፣ ቪዛ እና ጎግል በሀገሪቱ ዋና ከተማ የመጀመሪያ የልማት ማዕከላቸውን ከፍተዋል።

@innovate_aastu
ውቅያኖስ ጠላቂው ሮቦት
በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተሰራው ኦሽን ዋን ኬ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሰው መሰል ሮቦት የሰጠሙ የመርከብ ፍርስራሽ እና ሌሎች አካላትን ለማሰስ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡
ሮቦቱ አምስት መቶ ሜትር ድረስ በመጥለቅ በውሃ አካላቱ ግርጌ ላይ የሚገኙ በሰዎች ተደራሽ ለመሆን እጅግ አዳጋች የሆኑ የሰጠሙ ቁሶችን ሁኔታ ለመቃኘት እያገለገለ ነው፡፡
የሮቦቱ የዕይታ አድማስ በ3ዲ የተዋቀረ እና ባለሙሉ ቀለም ምስሎችን ያላንዳች ችግር ማስተላለፍ የሚችል ስለመሆኑም ሲ.ኤን.ኤን አስነብቧል፡፡
በውሃ አካላቱ ወለል ላይ ሆነው ሮቦቱን የሚቆጣጠሩ ሰዎች ሮቦቱ የሚነካውን እያንዳንዱን ቁስ እና የውሀውን ግፊት ሳይቀር እራሳቸው ውሃ ውስጥ ያሉ እስኪመስላቸው ድረስ በሮቦቱ መቆጣጠሪያ ሥርዓት አማካኝነት እንደሚደርሳቸው ተመላክቷል፡፡
ከመስከረም ጀምሮ በነበረው የሮቦቱ ቆይታ በተለያየ ጊዜ የሰጠሙ መርከቦች እና አውሮፕላኖችን ለመቃኘት እንዳገለገለ ተገልጿል፡፡
ኦሽን ዋን ኬ ለሰው ልጆች እጅግ አደገኛ የሆኑ ጥልቅ የውሃ ውስጥ ፍለጋዎች በሮቦቶች የሚከወኑበትን አዲስ መንገድ እንድናይ የሚረዳ የመጪው ጊዜ ተስፋ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

#እለታዊ_ቴክ_ዜናዎች
@innovate_aastu
የምስራች 🎉

የአባይ ውሃ ለሦስተኛ ጊዜ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል፡፡

#GERD
ለአይነ ስውራን የቀረበ ዘመናዊ መሪ ወይም ኬን
****
ተመራማሪዎች የእይታ ችግር ያለባቸውን ሰዎች በእንቅስቃሴ የሚያግዝ ዘመናዊ ዘንግ ወይም ኬን ሰርተው አቀረቡ፡፡ በተለምዶ ነጩ ምርኩዝ በመባል የሚታወቀው ይህ አይነስውራን ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚጠቀሙበት ዘንግ ተጠቃሚዎቹ የሚኖራቸውን እንቅስቃሴ የተሸለ ቀላል እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ መደበኛው ዘንግ ከመሬት ጋር ሲጋጭ የሚኖረውን ድምጽ በመከተል አንድ አይነስውር በቀላሉ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ይችላል፡፡

ሳንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ይህንን መደበኛ ዘንግ እጅግ በማሻሻል አይነ ስውራን ከደህንነት ስጋት ነጻ ሆነው እንደፈለጉ እንዲንቀሳቀሱ በሚያስችል መልክ የሮቦት ቴክኖሎጂ አክሎበት ማቅረቡ ተነግሯል፡፡ ከራስ ነድ መኪኖች ቴክኖሎጂ ጋር ተጣምሮ የተሰራው ይህ ዘንግ በ400 ዶላር የቀረበ ሲሆን ተጠቃሚዎች እንደሚኖሩበትና እንደሚንቀሳቀሱበት አካባቢ ምቹ የሆነ ድጋፍን የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡

ስማርት ዘንጉ በመንገድ ላይ ወይም በየትኛውም አካባቢ የሚኖሩ እንቅፋቶችን በመለየት በቤት ውስጥም ሆነ ከቤት ውጭ ለመንቀሳቀስ ምቹ የሆኑ ቦታወችን በመምረጥ መጓዝ የሚያስችል ነው፡፡ በዘርፉ ሌሎች ሴንሰር የተገጠመላቸው መሪ ዘንጎች ያሉ ቢሆንም ከአጠቃላይ ክብደታቸው እና ከሚያወጡት ዋጋ አንጻር ተፈላጊነታቸው አነስተኛ ነው፡፡ በሌላ በኩል ከቴክኖሎጂ አንጻር እጥረት ያለባቸው በመሆኑ ማለትም ሴንሰሩ ከተጠቃሚው ፊት ለፊት ያለን ነገር ብቻ የሚያሳውቅ በመሆኑ ይህ ተሻሽሎ የቀረበው መሪ ዘንግ እጅግ ተመራጭ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡

#Daily_Tech_News
▬▭▬▭▬▭▬▭
Follow us: YouTube,  Telegram,  Tiktok
@innovate_aastu
@innovate_aastu
የአንደኛ አመት ተማሪዎች ፣ የመጀመሪያውን Semester ስለጨረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እያልን😊
የእረፍት ግዜያችሁን ከኛ ጋር እንድታሳልፉ በየቀኑ የሚለቀቁ የ Programming እንድሁም Soft skill ትቶሪያሎች እዚህ ላይ ለመልቀቅ አስበናል። የቱ ብጀመር ትመርጣላችሁ?
Anonymous Poll
31%
C++ for beginners
10%
Java for beginners
26%
Python for beginners
14%
Web Development
19%
Mobile App Development