Ermi dev 🧑‍💻
150 subscribers
117 photos
13 videos
3 files
39 links
This is my channel and I’m Ermi.
A freshman at AAU, really into aerospace and software engineering.

I use this space to share my ideas, the challenges I run into, and my journey as I try to grow in both fields.

DM: @ermijemmy
Download Telegram
በነገው እለት ምድር ለፀሐይ በጣም ቅርብ የምትሆን ሲሆን መሬት ቅርብ የምትሆንበት አካባቢ perihelion ይባላል፡፡

ከላይ የምትመለከቱት ፎቶም ምድር perihelion አካባቢ በምትሆንበት ጊዜ ፀሐይ ስትጠልቅ የሚያሳይ ነው፡፡
ኢትዮጵያ አራት ወቅታት ሲኖራት ፀደይ፣በጋ፣በልግ እና ክረምት ይባላሉ፡፡
በነገው እለት የኢትዮጵያ በጋ ይጀምራል፡፡ ከሦስት ወራት በኋላም ቦታውን ለበልግ ይለቃል።
የሰሞኑ የመሬት መንቀጥቀጥ || ERMI ||
ሰሞኑን ሀገራችን ኢትዮጵያ በዛ ያሉ የመሬት መንቀጥቀጦች እያስተናገደች ትገኛለች።
በቁጥራዊ መረጃም ይህ ጽሑፍ ከተጻፈበት ሰዓት ጀምሮ
ባለፉት 24 ሰዓታት 4
ባለፉት 7 ቀናት 55
ባለፉት 30 ቀናት 67 እና
ባለፉት 365 ቀናት 86 የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዝግበዋል። ከነዚህ ሁሉ ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ ዛሬ ማለትም ታኅሣሥ 26 ከሌሊቱ 10 ሰዓት ገደማ በሬክተር ስኬል 5.8 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ በአማራ ክልል አቦምሳ በሚባለው ቦታ ተመዝግቧል።

በዚህ ጽሑፍ የመሬት መንቀጥቀጡን ምክንያት፣ የት የት አካባቢ እንደሚከሰት፣ ምን ሊፈጠር እንደሚችል እና ምን አይነት ጥንቃቄዎች መውሰድ እንዳለብን እንመለከታለን።

ምክንያት
እንደ ሥነ ምድር ተመራማሪዎች ገለጻ በመሬት ወለሎች እርስ በእርስ መጓተት ምክንያት መሥራቅ አፍሪካን (ኢትዮጵያን ጨምሮ) ከተቀረው የአፍሪካ ክፍል የሚለይ ትልቅ የመሬት መሰንጠቅ ይኖራል። ይህ የመሬት መሰንጠቅ ከደቡብ ቱርክ አንሥቶ እስከ ሞዛምቢክ (ደቡብ ምሥራቅ አፍሪካ) ድረስ የሚሄድ ነው። አሁን የምናያቸው የመሬት መንቀጥቀጦች እና የእሳተ ገሞራ ፍንዳታዎች የዚህ ስንጠቃ አካል ናቸው።(በኢትዮጵያ እየተከሰቱ የሚገኙትንም ጨምሮ)

በኢትዮጵያ የመሬት መንቀጥቀጡ የት የት ቦታዎች ሊከሰት ይችላል?
አሁን ባለው መረጃ ከላይ በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ቢጫ ያለባቸው አካባቢዎች (ዞን 0) ብዙም የመሬት መንቀጥቀጡ የማይደርስባቸው ቦታዎች ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ ጋምቤላ፣ መተከል፣ ነቀምት፣ ጊምቢ፣ ጅማ ይካተታሉ።

አነስ ያለ እና መጠነኛ የመሬት መንቀጥቀጥ የሚስተዋልባቸው ቦታዎች ደግሞ ፈዛዛ አረንጓዴ ያለባቸው ቦታዎች ሲሆኑ (ዞን 1) ከነዚህ ውስጥም ሐዋሳ፣ አርባ ምንጭ፣ ዲላ፣ ሻሸመኔ፣ ጎሬ ይገኙበታል።
መጠነኛ የመሬት መንቀጥቀጥ የሚስተዋልባቸው አካባቢዎች ደግሞ (ዞን 2) በፈዛዛ ሐምራዊ የተቀለሙት ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ አዲስ አበባ፣ ባሕር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደሴ፣ መቀሌ ይገኙበታል።

ከበድ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ የሚስተዋልባቸው አካባቢዎች ደግሞ በቀይ ያሉት ሲሆኑ (ዞን 3) ከነዚህም ድሬዳዋ፣ ጂጂጋ፣ ሐረር፣ ጎዴ፣ ደገሀቡር ይካተቱበታል።

በመሬት መንቀጥቀጡ ምን ሊከሰት ይችላል?
• ብዙ ሰዎች ከመኖርያ ቦታቸው ሊፈናቀሉ ይችላሉ። በዚህም የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች ሊፈጠሩ ይችላሉ። ለምሳሌ ያህልም በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ከ100 በላይ ቤቶች የወደሙ ሲሆን ከ2560 ሰዎች በላይ ከመኖርያ ቦታቸው ተፈናቅለዋል እንዲሁም የቤት እንስሳዎች ሞተዋል።

• የተለያዩ መሠረተ ልማቶች መንገዶች፣ ግድቦች፣ የኃይል ማመንጫዎች ሊጎዱ ወይም ከበድ ያለ ውድመት ሊያስተናግዱ ይችላሉ።

• የተለያዩ የብዝኃ ሕይወት መገኛዎች ፓርኮች፣ የዱር እንስሳዎች፣ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች ሊወድሙ እና ቱሪዝሙን ሊያዳክሙት ይችላሉ።

አያድርገውና የመሬት መንቀጥቀጥ ቢከሰት እና እዛ አካባቢ ብንሆን ምን እናድርግ?
በመጀመርያ:
• አለመደናገጥ፣ ራስን ማረጋጋት፣ ያለንበትን ቦታ መቃኘት

ቤት ውስጥ ከሆንን:
•ባሉበት መቆም
•በጉልበት እና በእጅ ወደታች መቆም
•በር መቃን ሥር አለመሆን (በር መቃን ሥር ሁኑ የሚለው የተሳሳተ ዕይታ ነው።)
•ሊጎዱ የሚችሉ አካላቶቻችን መሸፈን
•ከቤት አለመውጣት
•ከመስኮቶች እና ሊወረወሩ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ
•አልጋ ላይ ከሆንን ባለንበት መተኛት እና ጭንቅላታችንን በትራስ መሸፈን

ውጪ ከሆንን:
•ከፎቆች፣ ዛፎች፣ የመንገድ ላይ መብራቶች፣ ፖሎች፣ ድልድዮች መራቅ እና ባዶ ሜዳ ወዳለበት መሄድ
•መኪና ውስጥ ካለን አለመውጣት
•ሰው በበዛበት አካባቢ ከሆንን
አለመደናገጥ፣ አለመሯሯጥ ቤት ውስጥ የምናደርጋቸውን ነገሮች እዚህም ማድረግ

ሁላችንም ትክክለኛ መረጃ እንለዋወጥ፤ ሐሰተኛ መረጃ መልቀቅ የብዙ ሰው ሕይወት ይነካልና ያንን ከማድረግ እንቆጠብ፤ በጸሎት እንበርታ።

Ermi ነበርኩኝ 🫡
👍6
Hey #Mondayers

Remember
Your week starts at sunday afternoon.
Make sure to do these things this afternoon :
• prepare for tomorrow
• have little usage of digital devices
• organize your materials for the week
• reflect on the past week and try not to repeat your mistakes
• don't procrastinate your sleeping time
• stay positive
👍8
በቅርቡ በሃገራችን ሰማይ ሥር ስለታየው ነገር (ያው እንደዜጋ) መጻፍ ነበረብኝ።
መረጃና ጽሑፍ እየሰበሰብኩ ነው።

ባጭሩ ግን ነገርየው የspace debris አካል እንደሆነና በspace ውስጥ ከሚገኝ አገልግሎቱን ጨርሶ ወደ ቦታው ከተመለሰ የቻይና መንኮራኩር እንደወደቀ ይነገራል።

ይህ አካልም የወደቀበት ቦታ ላይ (Kenya) ሰው አለመጉዳቱን ነገር ግን ብዙ አጋዘኖች እንደወደሙ ቃጠሎም እንደተነሣ ይነገራል።

በነገራችን ላይ space ላይ በአሁን ጊዜ እንደምናስበው ንጹሕ ቦታ ላይኖር ይችላል። በተለያዩ ሰው ሰራሽ ሳተላይቶች፣ በአረጁ ሳተላይቶች እና በሳተላይት ስብርባሪዎች የተሞላ ነው። (እንደሰማውት😁) እና በዚህ ነገር ሰሞኑን ጽሑፍ የምለቅ ይሆናል።
👍3
Hey #Mondayers

Remember
Your week starts at sunday afternoon.
Make sure to do these things this afternoon :
• prepare for tomorrow
• have little usage of digital devices
• organize your materials for the week
• reflect on the past week and try not to repeat your mistakes
• don't procrastinate your sleeping time
• stay positive
🙏1
ኮሜት አትላስ አምና የተገኘች ተወርዋሪ ኮከብ ስትሆን በዚህ ወቅት ለፀሐይ በጣም ቅርብ ስለምትሆን በሙሉ አቅሟ ትበራለች። በብርሃኗ ምክንያትም (ሳናያት በፀሐይ ተቃጥላ ካልጠፋች እና ሙሉ ጨረቃ ካልከለለችን) በዐይናችን ልናያት እንችላለን። ነገና ከነገ በስቲያ ትታያለች፡
ደማቋ ማርስ በጨረቃ ጀርባ የምታልፍ ይሆናል።

ይህ ምንን ያመለክታል?
ማርስን ከጨረቃ ጀርባ መመልከታችን ከሁለት ቀናት በኋላ መሬት በፀሐይ እና በማርስ መካከል በትክክል እንደምትቀመጥ ምልክት ይሆነናል። ይህ event lunar occultation በመባል ይታወቃል።
🔥1
ኹለት የጨረቃ መንኮራኩሮች በተመሳሳይ ጊዜ በአንድ ሮኬት በ SpaceX ወደ ጨረቃ ተልከዋል።

ዛሬ የተላኩት ኹለት መንኮራኩሮች ሥሪታቸው አንደኛው የአሜሪካኑ ድርጅት Firefly Aerospace ሲሆን አንዱ ደግሞ የጃፓኑ ድርጅት Ispace ነው።

የ Firefly ድርጅት መንኮራኩር እንዲህ አይነት ጉዞ የመጀመርያው ሲሆን የሚሄደውም የናሳን ካርጎ ወደ ጨረቃ ለማድረስ ነው።

የጃፓኑ Ispace ደግሞ ዘንድሮ ኹለተኛ ጊዜው ሲሆን አምና የሞከረው መንኮራኩሯ ጨረቃ ላይ ስትደርስ ከሽፋለች።

ኹለቱም መንኮራኩራቸውን ያስወነጨፉት በ SpaceX በኩል ነው።
🔥2
ተጨማሪ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Blastoff! SpaceX launches Starship on Flight 7 — catches booster, loses ship
Hey 👋 buddies,
Here is ERMI from experience. The only thing I would give to my younger self, if I were older than I am at the current time, is: "Please focus on your social media usage."

Today, I saw the Netflix documentary "The Social Dilemma," which briefly tells you about the effects of social media directly from the developers. Yes, you read that correctly—I said from the developers themselves.

From the developers who made Facebook Facebook. Those who created the like button, who were the suggestion experts for Facebook, and who held positions such as: Head of User Experience at Mozilla, investor in Facebook, engineer at Facebook, Director of Monetization at Facebook, President of Pinterest...

These guys told us how the algorithm works to make us stick to our technological devices day and night. They also explained how this phenomenon is leading us to inevitably bad destinations. And what about AI? I can't finish—just watch the documentary.

They told us what they could share, from the basic intentions of social media to its current consequences, as well as its future threats.

Friends, please be cautious about your social media usage.
🤔1🙏1
In God's will, I will write couple of articles in Amharic about social media, for teens. I will discuss why it was created, its purpose, how we are using it now, what the consequences will be if we continue to use it the way we do now, and how is the appropriate usage.....

Stay tuned!
እስኪ ከሰሞኑ YouTube ስትገቡ ራሱ shorts ውስጥ የሚወስዳችሁ 👍 አድርጉ🤔
👍2
በነገው እለት ሰባት ፕላኔቶች በተመሳሳይ ሰዓት በሰማይ ላይ የሚታዩ ይሆናል። (Saturn,Uranus እና Neptuneን ለማየት ማጉያ መነፅር ያስፈልጋል።)

አንዳንድ የሥነ ከዋክብት ባለሙያዎች የፕላኔቶች ሰልፍ ብለው ጠርተውታል።
Mercury, Venus, Mars እና Jupiter ያለ መነፅር በዓይን መታየት ይችላሉ።

ነገ ማታ 12 ሰዓት ይሄን ለመመልከት እንጦጦ አብሮኝ የሚሄድ ካለ በውስጥ አናግሩኝ፡፡ @I_am_Ermi
👍3