Ermi dev 🧑‍💻
150 subscribers
117 photos
13 videos
3 files
39 links
This is my channel and I’m Ermi.
A freshman at AAU, really into aerospace and software engineering.

I use this space to share my ideas, the challenges I run into, and my journey as I try to grow in both fields.

DM: @ermijemmy
Download Telegram
ሀ ብዬ ልጀምር
ለ ብዬ ልቀጥል
ሐ ብዬ ልሠልሰው


ረቱን ልወቀው እውቀት ብርሃን ነው
ሰ ብዬ እሳቱን ልለኩሰው
ሸማኔውም ይሸምን
ቀለማትም ይውጡ ኢትዮጵያም ይመርባት


ቸገረ ሀገር ስም የተፃፈው ስሟ በኔ ይቀየርላት
ኃይል ማለት
ነው ሕብረት በፍቅር የተቃ

አብሮ የሠራም
ከበረበት
ኧረ የስኬት
ወግ አየ
ዐይኔም የቀና መንገድን ያ
ዘ ከሰነፎቹ ጋርስ መቼ ቃ



ጀን
ገበሬ ሲከምር ከላይ
ጠፈር አደረሰው
ጨረቃ ላይ
ጰ ስታምር ኢትዮጵያ ውስጥ እይዋት
ጸን እንደ
ፀሐይዋ
ፈክታ አገኘኋት
ቨ እና
ፐን ስደርስባቸው
ሀገርስ ማለት ፊደላት ናቸው!
2👌2
Ermi dev 🧑‍💻
Photo
ስታነቡ በኔ ስም ቦታ የናንተን እንድትጠቀሙ እመክራለሁ!!
Ermi dev 🧑‍💻 pinned «ኤርሚ ተስፋን አይጥልም ያዝ ነው የስኬት ምሥጢሩ መንገድን አንድ ነው መጽናት ራስን ለማንሣት ቁልፍ ነው ያኔ ተራራው ይናዳል ዝርግ ነው!! Never give up⚡️»
Right now, especially for us Ethiopians and teens, these courses are necessary for real:
1. Digital literacy
2. Digital detox

If you get any opportunities to learn them, don't hesitate!!
ያሳዘነኝ ባንተ መመስገኔ ህዝብ ወደደው አልወደደው፣ እልልልልልል ሊደመጥ የሚገባው አስተማሪ መልእክት
እኔን ያሳዘነኝ ባንተ መመስገኔ ነው!

ጥሩ እይታ ናት አድምጧት!
ጸሐፊ ➟ ዳንኤል ክብረት
1
The biggest company -> you
The biggest lose -> different inner and social personality
The biggest time -> solitude
The biggest success -> being mindful
The biggest trust -> being a person who do what he told to himself
The biggest knowledge -> self awareness
The biggest win -> discipline
The longest way -> positivity
The longest journey -> life
Doing nothing all year vs doing something
(1)³⁶⁵ = 1
(1.01)³⁶⁵ = 37.7

Just do at least a little thing before going to bed
Hey #Mondayers

Remember
Your week starts at sunday afternoon.
Make sure to do these things this afternoon:
• prepare for tomorrow
• have little usage of digital devices
• organize your materials for the week
• reflect on the past week and try not to repeat your mistakes
• don't procrastinate your sleeping time
• stay positive
Hey #Mondayers

Remember
Your week starts at sunday afternoon.
Make sure to do these things this afternoon :
• prepare for tomorrow
• have little usage of digital devices
• organize your materials for the week
• reflect on the past week and try not to repeat your mistakes
• don't procrastinate your sleeping time
• stay positive
🥰2👍1
Ermi dev 🧑‍💻
we shall explore more and more together!!
እዚህ ጋር እንደጠቀስኩት 👆👇
በ 2025 ዋና ዋና የሰማይ ላይ ክንውኖች (አዘጋጅ --> እኔው (Ermi))😎

1. ታኅሣሥ 26: መሬት ለፀሐይ በሙሉ አቅሟ ቅርብ ትሆናለች።

2. ታኅሣሥ 26: የኢትዮጵያ በጋ ይገባል።(በጥንታዊው ሳይንስ መሠረት)

3. ጥር 5: አትላስ የተባለችው ተወርዋሪ ኮከብ በዐይን ልትታይ ትችላለች።

4. ጥር 5 እና 6: ደማቋ ማርስ በጨረቃ ጀርባ የምታልፍ ይሆናል።

5. ጥር 10-15: ኹለት የጨረቃ መንኮራኩሮች በተመሳሳይ ጊዜ በአንድ ሮኬት በ SpaceX ወደ ጨረቃ ይላካሉ።

6. ጥር 24 አካባቢ: የ SpaceX መንኮራኩር እና የናሳ orbiter በ SpaceX በአንድ ላይ የሚወነጨፉ ይሆናል።

7. የካቲት 15: አካባቢ ናሳ ሰማይን በ102 አይነት ቀለማት ለማጥናት SPHEREx የተባለ mission launch ያደርጋል።

8.  የካቲት 21: ሰባት ፕላኔቶች በተመሳሳይ ሰዓት በሰማይ ላይ የሚታዩ ይሆናል። (Saturn,Uranus እና Neptuneን ለማየት ማጉያ መነፅር ያስፈልጋል።)

9. መጋቢት 4 እና 5: በሰሜን ንፍቀ ክበብ የጨረቃ ግርዶሽ ይፈጠራል።

10. መጋቢት 11: የመጋቢት እኩሌ ሲሆን የቀኑና የምሽቱ ርዝማኔ እኩል የሚሆንበት ነው። (ከዚያ ቀኑ እያጠረ ሌሊቱ እየረዘመ ይሄዳል።)

11. መጋቢት 20: በሰሜን አሜሪካ፣ ካናዳ እና አውሮፓ ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ ይፈጠራል።

12. መጋቢት ወር ሳያልቅ: ናሳ እና የህንድ ስፔስ ኤጀንሲ የመሬትን ውጫዊ አካል ለማጥናት NISAR የተባለውን መንኮራኩር ያመጥቃሉ።

13. ሚያዝያ 13 እና 14: Lyrids የተባለው የተወርዋሪ ከዋክብት ጥርቅም በደንብ ይታያል።

14. ሚያዝያ 25-26: Eta Aquarids የተባለው የተወርዋሪ ከዋክብት ጥርቅም በደንብ ይታያል።

15. ሰኔ 13 ሳይንሳዊው(ዘመናዊ) የኢትዮጵያ ክረምት ይገባል።
👍2
16. ሰኔ 26 ሳይንሳዊው (ጥንታዊ) የኢትዮጵያ ክረምት ይገባል።

17. ሰኔ 26: መሬት ከፀሐይ በሙሉ አቅሟ ሩቅ የምትሆንበት ቀን ነው። ከዚህ በኋላ ብትቀርብ ነው እንጂ አትርቅም።

18. ሰኔ 27:  Vera C. Rubin የተባለው ኦብዘርቫቶሪ የመጀመርያውን የምሽት ምልከታ ያነሣል ተብሎ ይጠበቃል።

19. ሐምሌ 22-23: ሁለት የተወርዋሪ ከዋክብት ስብስቦች በደንብ የሚታዩ ይሆናል።

20. ነሐሴ 6-7: ፔርሴይድ የተባለው የተወርዋሪ ከዋክብት ስብስቦች በደንብ ይታያል።

21. ጳጉሜ 2-3: ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ በኤዢያ፣አውሮጳ፣አውስትራሊያ እና አፍሪካ የሚከሰት ይሆናል።

22. መስከረም 12: 2018; ሳይንሳዊው (ዘመናዊ) ፀደይ ይገባል።

23. መስከረም 26:2018; ሳይንሳዊው(ጥንታዊ) ፀደይ ይገባል።

24. ጥቅምት 12-13:2018; Orionids የተባለው የተወርዋሪ ከዋክብት ሕብረት በደንብ ይታያል።

25. ኅዳር 7-8:2018; Leonids የተባለው የተወርዋሪ ከዋክብት ጥርቅም በደንብ ይታያል።

26.ታኅሣሥ 3-4:2018; Geminids የተባለው የተወርዋሪ ከዋክብት ጥርቅም በደንብ ይታያል።

27. ታኅሣሥ 5:2018; ሳይንሳዊው (ዘመናዊ) የኢትዮጵያ በልግ ይገባል።

28. Ursids የተባለው የተወርዋሪ ከዋክብት ጥርቅም በደንብ ይታያል።

29. ታኅሣሥ 26:2018; ሳይንሳዊው (ጥንታዊው) የኢትዮጵያ በልግ ይገባል።
👍3
ከላይ የለቀቅኩት እንዳለ ሁኖ
ክስተቱ ሊፈጠር ቀን ሲቀረው የተወሰነ መረጃ ስለክስተቱ የምለቅ ይሆናል።🤓
በነገው እለት ምድር ለፀሐይ በጣም ቅርብ የምትሆን ሲሆን መሬት ቅርብ የምትሆንበት አካባቢ perihelion ይባላል፡፡

ከላይ የምትመለከቱት ፎቶም ምድር perihelion አካባቢ በምትሆንበት ጊዜ ፀሐይ ስትጠልቅ የሚያሳይ ነው፡፡
ኢትዮጵያ አራት ወቅታት ሲኖራት ፀደይ፣በጋ፣በልግ እና ክረምት ይባላሉ፡፡
በነገው እለት የኢትዮጵያ በጋ ይጀምራል፡፡ ከሦስት ወራት በኋላም ቦታውን ለበልግ ይለቃል።
የሰሞኑ የመሬት መንቀጥቀጥ || ERMI ||
ሰሞኑን ሀገራችን ኢትዮጵያ በዛ ያሉ የመሬት መንቀጥቀጦች እያስተናገደች ትገኛለች።
በቁጥራዊ መረጃም ይህ ጽሑፍ ከተጻፈበት ሰዓት ጀምሮ
ባለፉት 24 ሰዓታት 4
ባለፉት 7 ቀናት 55
ባለፉት 30 ቀናት 67 እና
ባለፉት 365 ቀናት 86 የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዝግበዋል። ከነዚህ ሁሉ ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ ዛሬ ማለትም ታኅሣሥ 26 ከሌሊቱ 10 ሰዓት ገደማ በሬክተር ስኬል 5.8 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ በአማራ ክልል አቦምሳ በሚባለው ቦታ ተመዝግቧል።

በዚህ ጽሑፍ የመሬት መንቀጥቀጡን ምክንያት፣ የት የት አካባቢ እንደሚከሰት፣ ምን ሊፈጠር እንደሚችል እና ምን አይነት ጥንቃቄዎች መውሰድ እንዳለብን እንመለከታለን።

ምክንያት
እንደ ሥነ ምድር ተመራማሪዎች ገለጻ በመሬት ወለሎች እርስ በእርስ መጓተት ምክንያት መሥራቅ አፍሪካን (ኢትዮጵያን ጨምሮ) ከተቀረው የአፍሪካ ክፍል የሚለይ ትልቅ የመሬት መሰንጠቅ ይኖራል። ይህ የመሬት መሰንጠቅ ከደቡብ ቱርክ አንሥቶ እስከ ሞዛምቢክ (ደቡብ ምሥራቅ አፍሪካ) ድረስ የሚሄድ ነው። አሁን የምናያቸው የመሬት መንቀጥቀጦች እና የእሳተ ገሞራ ፍንዳታዎች የዚህ ስንጠቃ አካል ናቸው።(በኢትዮጵያ እየተከሰቱ የሚገኙትንም ጨምሮ)

በኢትዮጵያ የመሬት መንቀጥቀጡ የት የት ቦታዎች ሊከሰት ይችላል?
አሁን ባለው መረጃ ከላይ በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ቢጫ ያለባቸው አካባቢዎች (ዞን 0) ብዙም የመሬት መንቀጥቀጡ የማይደርስባቸው ቦታዎች ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ ጋምቤላ፣ መተከል፣ ነቀምት፣ ጊምቢ፣ ጅማ ይካተታሉ።

አነስ ያለ እና መጠነኛ የመሬት መንቀጥቀጥ የሚስተዋልባቸው ቦታዎች ደግሞ ፈዛዛ አረንጓዴ ያለባቸው ቦታዎች ሲሆኑ (ዞን 1) ከነዚህ ውስጥም ሐዋሳ፣ አርባ ምንጭ፣ ዲላ፣ ሻሸመኔ፣ ጎሬ ይገኙበታል።
መጠነኛ የመሬት መንቀጥቀጥ የሚስተዋልባቸው አካባቢዎች ደግሞ (ዞን 2) በፈዛዛ ሐምራዊ የተቀለሙት ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ አዲስ አበባ፣ ባሕር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደሴ፣ መቀሌ ይገኙበታል።

ከበድ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ የሚስተዋልባቸው አካባቢዎች ደግሞ በቀይ ያሉት ሲሆኑ (ዞን 3) ከነዚህም ድሬዳዋ፣ ጂጂጋ፣ ሐረር፣ ጎዴ፣ ደገሀቡር ይካተቱበታል።

በመሬት መንቀጥቀጡ ምን ሊከሰት ይችላል?
• ብዙ ሰዎች ከመኖርያ ቦታቸው ሊፈናቀሉ ይችላሉ። በዚህም የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች ሊፈጠሩ ይችላሉ። ለምሳሌ ያህልም በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ከ100 በላይ ቤቶች የወደሙ ሲሆን ከ2560 ሰዎች በላይ ከመኖርያ ቦታቸው ተፈናቅለዋል እንዲሁም የቤት እንስሳዎች ሞተዋል።

• የተለያዩ መሠረተ ልማቶች መንገዶች፣ ግድቦች፣ የኃይል ማመንጫዎች ሊጎዱ ወይም ከበድ ያለ ውድመት ሊያስተናግዱ ይችላሉ።

• የተለያዩ የብዝኃ ሕይወት መገኛዎች ፓርኮች፣ የዱር እንስሳዎች፣ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች ሊወድሙ እና ቱሪዝሙን ሊያዳክሙት ይችላሉ።

አያድርገውና የመሬት መንቀጥቀጥ ቢከሰት እና እዛ አካባቢ ብንሆን ምን እናድርግ?
በመጀመርያ:
• አለመደናገጥ፣ ራስን ማረጋጋት፣ ያለንበትን ቦታ መቃኘት

ቤት ውስጥ ከሆንን:
•ባሉበት መቆም
•በጉልበት እና በእጅ ወደታች መቆም
•በር መቃን ሥር አለመሆን (በር መቃን ሥር ሁኑ የሚለው የተሳሳተ ዕይታ ነው።)
•ሊጎዱ የሚችሉ አካላቶቻችን መሸፈን
•ከቤት አለመውጣት
•ከመስኮቶች እና ሊወረወሩ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ
•አልጋ ላይ ከሆንን ባለንበት መተኛት እና ጭንቅላታችንን በትራስ መሸፈን

ውጪ ከሆንን:
•ከፎቆች፣ ዛፎች፣ የመንገድ ላይ መብራቶች፣ ፖሎች፣ ድልድዮች መራቅ እና ባዶ ሜዳ ወዳለበት መሄድ
•መኪና ውስጥ ካለን አለመውጣት
•ሰው በበዛበት አካባቢ ከሆንን
አለመደናገጥ፣ አለመሯሯጥ ቤት ውስጥ የምናደርጋቸውን ነገሮች እዚህም ማድረግ

ሁላችንም ትክክለኛ መረጃ እንለዋወጥ፤ ሐሰተኛ መረጃ መልቀቅ የብዙ ሰው ሕይወት ይነካልና ያንን ከማድረግ እንቆጠብ፤ በጸሎት እንበርታ።

Ermi ነበርኩኝ 🫡
👍6