የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.25K subscribers
2.41K photos
5 videos
1 file
57 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ በኮሪደር ልማት የሳይክል መንገድ ላይ የጭነት መኪና ያሽከረከረ ግለሰብ የገንዘብ ቅጣት ቀጣ

01/03/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 5 አራዳ ፓርክ ውስጥ በኮሪደር የለማ የሳይክል መንገድ ላይ በጭነት መኪና በመንቀሳቀስ የደንቤ ጥሰት የፈጸመ አሽከርካሪ በደንብ ቁጥር 167/2016 መሰረት ሹፌሩ 5000 ብር ሲቀጣ ባለቤቱ 50,000 ብር በድምሩ 55,000 ብር በመቅጣት ያቆሸሹትን አካባቢ እንዲያፀዱ ተደርጓል።

ባለስልጣኑ የህብረተሰቡ የጋራ ሀብት የሆኑ የኮርደር ልማትና በሌሎች አካባቢ የማገኙ መሠረተ ልማቶችን፣ለህዝብ የተሰሩ አረንጓዴ ስፍራዎች እና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን ደህንነት በመጠበቅ በሀላፊነት እንዲገለገል መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማዋ ደንብ የሚተላለፉ የግልና የመንግስት ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል ።

ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።