በአዋኪ ድርጊቶች እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ዙሪያ የህዝብ ውይይት መድረክ ተካሄደ
30/01/2018 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በኮልፌ ፣ በአራዳ እና በቦሌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በአዋኪ ድርጊቶችን መከላከል ላይ፣ በደንብ ቁጥር 150/2015 እና በፀረ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ዙሪያ በህዝብ ንቅናቄ መድረክ በማዘጋጀት ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠር ተፈጥሯል ::
በግንዛቤ መድረኮቹ አዋኪ ድርጊቶችን መከላከል እና በስነምግባር እና ብልሹ አሰራር መከላከል በሚል ርዕስ ለህብረተሰቡ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል ።
በመድረኩ ከአዋኪ ድርጊት ጋር በተያያዘ በተለያዩ መንገዶች ግንዛቤ ተፈጥሯል በተለይም ደግሞ በት/ቤቶች ላይ ለተማሪዎች በቅ/መከላከል ባለሙያዎቻችን አማካኝነት በየጊዜው ግንዛቤ የመፍጠር ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል ።
ህብረተሰቡ በአሁኑ ሰዓት ህገ ወጥነትን ለመከላከል እያደረገ ያለውን ስራ በማጠናከርና ተባባሪ በመሆን ሊሰሩ እንደሚገባና ከመሰል አዋኪ ተግባራት ልጆቻቸውና ራሳቸውን በማራቅ ለሌሎች አርዓያ መሆን እንደሚገባቸው በመድረኮቹ ተገልጿል ።
የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ደንቡና መመሪያውን ተፈፃሚ እንዲሆን እና በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ በማድረግ ለብልሹ አሰራር እና ፀረ ሙስና ተጋላጭነት መቆጣጠር መቻል ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑ ተገልጿል::
በመድረኩ አዋኪ ድርጊትን በመከላከል ህብረተሰቡም ከደንብ ማስከበር ጋር በመቀናጀት የግንዛቤ ስራዎችን አጠናክረው መስራትና እርምጃ እንዲወሰድ የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው ተነግሯል ።
ወጣቱን ከአዋኪ ድርጊቶችን እና ብልሹ አሰራሮችን እንዴት እራሱን መከላከልና መቆጣጠር እንደሚቻል በሰነዱ በዝርዝር ተገልፃል ።
በመጨረሻም ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች በተሰጡ ሀሳብ አስተያየት ጥያቄዎች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ ከመድረኩ ለተነሱት ሀሳብና አስተያየት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡

❤4
ባለስልጣኑ "18ተኛውን የሠንደቅ ዓላማ ቀን በድምቀት አከበረ።
03/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን "ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጲያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ሉአላዊነታችንና ለኢትዮጲያ ሕዳሴ" በሚል መሪ ቃል 18ተኛውን ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀንን የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ ኦፊሰሮችና መላሙ የተቋሙ ሰራተኞች በተገኙበት አከበረ።
ክብረ-በዓሉ በብሄራዊ ህዝብ መዝሙር የተጀመረ ሲሆን የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ የዘንድሮውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን የህዳሴ ግድብ እና ለሎች በርካታ ሜጋ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ወደ ስራ በገቡበት ወቅትና እንዲሁም ተቋማችን ከፍተኛ ውጤት ባስመዘገበበት ማግስት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
ኃላፊው አያይዘውም ሰንደቅ ዓላማችን የክብራችንና የሉአላዊነት መገለጫ አርማችን እንደመሆኑ መጠን ይህንን ቀን ስናከብር አባቶቻችን በደም ጠብቀው ያቆዩልንን ሀገር በስኬት የማንሰራራትና የከፍታ ዘመን የምናስቀጥልበትና በቁርጠኝነት የምንሰራበት ሊሆን እንደሚገባ በአፅንኦት ገልጸዋል።
ዘገባው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።

👍3
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በወርቃማ የሰኞ ማለዳ የአብሮነት መድረክ በከተማ ደረጃ ተሸላሚ ለሆኑ ዳይሬክቶሬቶች እውቅና ሰጠ
ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዘወትር ሰኞ ማለዳ አመራሮችና አጠቃላይ ሰራተኞች የሚሳተፉበት ልምድና ዕውቀት ተሞክሮ የሚጋራበት የወርቃማ ሰኞ የአብሮነት መድረክ አካሂድዋል፡፡
በአብሮነት መድረኩ ላይ ከኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ሰርካለም ንጋቱ "የተግባቦት ክህሎት" በሚል ርዕስ ሰነድ በማቅረብ የህይወት ፣ የዕውቀትና የስራ ተሞክሮአቸውን በመድረኩ አጋርተዋል
በመድረኩ የባለስልጣኑ የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ይልማ የወርቃማ ሰኞ የአብሮነት መድረክ የአንኛ ሩብ አመት አፈፃፀም ሪፖርት ስለመድረኩ አስፈላጊነት ፣ ስለዓላማው ፣ ስላጋጠሙ ተግዳሮቶችና የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ የተዘጋጀ ሰነድ በማቅረብ ከተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችን በማንሳት ውይይት ተካሂዷል።
የባለስልጣኑ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት እና የስ-ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶረት በ2017 ዓ.ም በተደረገ ምዘና በከተማው ውስጥ ካሉ ተቋማት ጋር በመወዳደር ባስመዘገቡት ስኬትና የላቀ አፈፃፀም "ዕውቅና በላቀ ውጤት " በሚል ርዕስ የባለስልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ዳይሬክቶሬቶቹ ለስኬት ብቁ ያደረጉ ዋና ዋና ተግባራትን የሚገልፅ ሰነድ በማቅረብ ለዚህ ስኬት የበቁትን የሁለት ዳይሬክቶረቶች ዕውቅናና የመስጠትና ሰርተፍኬት የማበርከት መርሀ-ግብር ተከናውኗል።
በማጠቃለያው ላይ የባለስልጣኑ አማካሪ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ለሁለቱ ዳይሬክቶሬቶች እንኳን ደስ አላችሁ መልክት በማስተላለፍ የሁለቱ ዳይሬክቶሬቶች እዚህ ደረጃ ላይ መድረስና እውቅና መሰጠቱ ለሌሎች በባለስልጣኑ ስር ለሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች መነሳሳትን የሚፈጥር በመሆኑ ለቀጣይ በላቀ ትጋት ስራዎች ሊሰሩ ይገባል የሚል መልክትን በማስተላለፍ መድረኩ ተጠናቋል።

👍5