ኢትዮ ቴሌኮም የ2018 በጀት ዓመት ስኬቱን በማስመልከት ለደንበኞቹ የነጻ የኢንተርኔት እና የድምጽ አገልግሎቶችን አቅርቧል።
ኢትዮ ቴሌኮም ለደንበኞቹ ያቀረበው አገልግሎት
• 1.5 ጂቢ (GB) የኢንተርኔት ዳታ፣
• 15 ደቂቃ የድምፅ ጥሪ፣ እና
• 30 አጭር የጽሑፍ መልዕክቶች (SMS) ያካተተ ነው።
የቴሌብር ሱፐርአፕ (telebirr SuperApp) ተጠቃሚ ለሆኑ ደንበኞች ተጨማሪ 500 ሜጋ ባይት (MB) ዳታ የተሰጠ ሲሆን፣ ያልተገደበ ጥቅል ተጠቃሚ ለሆኑ ደንበኞች ደግሞ የ10 ደቂቃ ነፃ የዓለም አቀፍ ጥሪ ስጦታ መዘጋጀቱን ገልጿል።
ይህ ነጻ አገልግሎት ከሐምሌ 17 እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ውስጥ፣ ከለሊቱ 6:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ድረስ የሚያገለግል መሆኑን ኩባንያው አስታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ

❤2
Forwarded from Ministry of innovation and technology (MinT)
የስታርትአፕ ዘርፍን በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ለማጎልበት ሲካሄድ የነበረው የ«Cursor AI Hackathon 2026» ውድድር በስኬት ተጠናቀቀ።
==================
በኢትዮጵያ የስታርትአፕ ሥነ-ምህዳርን ለማጎልበትና የወጣቶችን የፈጠራ አቅም በሰው ሰራሽ አስተዋፅኦ (AI) ቴክኖሎጂ ለማበልጸግ ያለመው «Cursor AI Hackathon Ethiopia 2026» ውድድር ከሐምሌ 18 እስከ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. ሲካሄድ ቆይቶ በስኬት ተጠናቀቀ።
በውድድሩ ማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢኖቬሽን ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሰላምይሁን አደፍርስ እንደገለጹት፣ መሰል የቴክኖሎጂ ውድድሮች የወጣቶችን የፈጠራ እውቀቶችን ወደ ተግባራዊ የፈጠራ መር ቢዝነሶች በመቀየር የሀገሪቱን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ እንደሚያፋጥኑ ገልጸዋል።
አክለውም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለዲጂታል ስታርትአፖች የሚያደርገውን ሁለገብ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመጠቆም፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ሀገር በቀል ችግሮችን የሚፈቱ መፍትሔዎችን ማመንጨት የነገዋ ኢትዮጵያን እድገት የሚያረጋግጥ መሠረት መሆኑን አብራርተዋል።
በውድድሩ ላይ የላቀ የቴክኖሎጂ መፍትሔዎችን በማቅረብ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የወጡ አሸናፊ ቡድኖች የተለያዩ ማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ይህ የሃካቶን ውድድር ወጣት የፈጠራ ባለቤቶች በጋራ በመሆን ሀሳቦቻቸውን በተግባር የሚፈትሹበትና ልምድ የሚለዋወጡበት ትልቅ መድረክ ሆኖ ማገልገሉ ተመልክቷል።
በመጨረሻም ውድድሩ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አዘጋጆችና አጋር አካላት ምስጋና የቀረበ ሲሆን፣ በቀጣይም መሰል የፈጠራ መድረኮችን በስፋት በማዘጋጀት ለኢትዮጵያ የስታርትአፕ ዘርፍ እድገት በትኩረት እንደሚሠራ ተገልጿል።

❤1