ዛሬ ማርች-8 ዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን ስናከብር በመላው ዓለም ላሉ ሁሉ በአንድነት ሁላችን ግድ እንደምንል በማሳየት ነው። የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን "ለሁሉም ሴቶች እና ልጃገረዶች መብት ፣ እኩልነት እና ልህቀት" በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ይገኛል።
ጭላንጭል በእዚህ ቀን የአፍሮ ፌሚኒዝም አቀንቃኞችን፣ ደጋፊዎችን ፣ የሚዲያ እና የሲቪል ማህበረሰቡን ፣ ወጣቶች እና የማህበረሰብ መሪዎችን ለጋራ ለውጥ እና ትግል ጥሪዋን ታቀርባለች።ጭላንጭል በወል ጥላቻ እና መድሎ የተገፉ እና ትኩረት የተነፈጋቸው የLBQT ሴቶች መብቶች እና የፆታ እኩልነት እንዲከበሩ መታገል እና የለውጥ እርምጃዎች እንዲወሰዱ መጠየቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ መሆኑን ታምናለች። በእዚህም መሪዎቻችን ለሁሉም ሴቶች መብት መከበር እና ለፆታ እኩልነት የተሻሉ እርምጃዎች እና የፖሊሲ ለውጦች ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ እንጠይቃለን!
በጋራ ድምፃችንን በማጉላት እና በመወያየት የተሻለ እና ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት እንደምንችል እናምናለን!!
ለሴቶች መብት መከበር እና ለተሻለ ማህበራዊ ለውጥ በጋራ እንቁም!!! ብሩህ ተስፋን ለሁለም እናረጋግጥ!
ጭላንጭል

በስነ ቋንቋ ጥናት ቋንቋ ይወለዳል ፣ ያድጋል ፣ ይሞታል። ለእዚህ የቋንቋ ዝግመተ ለውጥ ምክንያት ከሚሆኑ ነገሮች አንዱ የሰው ልጅ ልዩ ልዩ ማንነቶች መኖራቸው እና የሰው ልጅ የተለያዩ የህይወት ተሞክሮዎችን ለማንፀባረቅ ነው። በእዚህም በተለያዩ ዘመናት የስርዓተ-ፆታ ማንነት እና የፆታዊ ተማርኮ ዝንባሌን (Gender identity and sexual orientation) ለመግለፅ የተጠቀምንባቸው ቃላት እና ሃረጋት እያደጉ እና የበለጠ አካታች እየሆኑ ይገኛሉ። በ20ኛው መቶ ክፍለዘመን አጋማሽ ላይ በወንድ ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን (gay) እና በሴት ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን (lesbian) የተጀመረው እንቅስቃሴ በኋላ ላይ ለሁለቱም ፆታ መስህብ ያላቸውን (bisexuals) እና ከአካለ ፆታቸው ባሻገር ፆታዊ ማንነታቸውን የሚገልፁ (transgender) ሰዎችን ለማካተት LGBT የሚለውን መግለጫ ለመጠቀም በቅቷል። ከእዚህ በኋላ በተለይም Q የተጨመረችው በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ጥላ ውስጥ ያሉ እና የራሳቸውን ፆታዊ ዝንባሌ እና መስህብ በመጠየቅ እና በመፈለግ ላይ ያሉትን ሁሉ ለማካተት ነው። አሁን የምንጠቀምበት LGBTQIA+ የሚለው መግለጫ በአካለ ፆታቸው የሁለቱንም ተፈጥሯዊ ፆታዎች አካለ ፆታ የያዙ እና በተለምዶ ፍናፍንት የምንላቸውን (intersex) እና ለፆታዊ ተራክቦ ቁጥብ የሆኑ (asexuals) ሰዎችን ሁሉ ያቀፈ ነው። አካታች ለመሆን የተሻሻለው ይህ ቃል "+" በሚለው ምልክት ውስጥ ሌሎችን በአንድ ላይ ስለሚይዝ ሌላ የተሻለ እና የበለጠ አካታች ሆኖ የተገኘው እና አሁን ላይ ሰፊ ተቀባይነትን እያገኘ ያለው SOGIE የሚለው አፅሮተ መግለጫ ነው። ትርጉሙም የፆታዊ ተማርኮ ዝንባሌ፣ የስርዓተ-ፆታ ማንነት እና መገለጫን ያካተተ ነው። ይህ አገላለፅ በህግ እና በፖሊሲ ውይይቶች ውስጥ ሰፋ ያለ እና ሁሉም የራሱ ፆታዊ ተማርኮ ዝንባሌ እና የስርዓተ ፆታ ማንነት እንዳለው እንዲሁም ስርዓተ ፆታዊ ማንነቱን መግለፅ እንዲችል እውቅና የሚሰጥ ቃል ነው።
እነዚህ የአገላለጽ እድገቶች የመጡት ነገሮች ለማወሳሰብ ታስቦ አይደለም። ይልቁንም ሁሉም ሰው በማንነቱ እውቅና እንዲሰጠው፣ እንዲከበር እና የእኩልነት መብቱ እንዲከበር ከመፈለግ ነው። ቋንቋ እውነትን ከመግለፅ ባለፈ እውነትን ይቀርፃል። ስለዚህ ለተለያዩ ማንነቶች እውቅና በመስጠት የበለጠ አካታች እና ተቀባይነት ያለው ዓለም ለመፍጠር ያግዛል።
EN
Language evolves to reflect the diversity of human experiences, and the terms used to describe gender identity and sexual orientation have expanded over time to be more inclusive. What started as "gay" and "lesbian" activism in the mid-20th century grew into "LGBT" to acknowledge bisexual and transgender people. Later, "Q" was added for queer and questioning individuals, and eventually, "LGBTQIA+" emerged to include intersex, asexual, and other identities. This term has evolved to be more inclusive, but it has since been replaced by SOGIE, which is even broader and more inclusive, as it explicitly encompasses all identities, including those represented by the "+" sign. SOGIE (Sexual Orientation, Gender Identity, and Expression) became a broader term, used in legal and policy discussions to recognize that everyone, regardless of identity, has a sexual orientation and gender expression.
These terms exist not to complicate things, but to ensure visibility, respect, and equal rights for all. Language shapes reality, and by acknowledging diverse identities, we help create a more inclusive and accepting world.

👍6
ከተማ ቀመስ የሆነው የሴቶች እንቅስቃሴ በተለይ በቅርብ ዓመታት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ጎልቶ ታይቷል። ጥቂት የማይባሉ የሴት መብት ተሟጋቾች ድምፅ ይዞ የመጣው ይህ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ በኢትዮጵያ የመደበኛ ሚዲያዎችንም ትኩረት የሳበ እና በማህበረሰቡ ዘንድ ለውይይት አጀንዳ ያቀበለ እንቅስቃሴ ነው። ይሁን እንጂ ይህ እንቅስቃሴ ከተማ ቀመስ በመሆኑ የገጠር ሴቶችን እና በተለየ የብሔር፣ የፆታ ተማርኮ እና መደብ ማንነታቸው ድርብ ጭቆና የሚያስተናግዱ ኢትዮጵያዊ ሴቶችን በብዙ ያገለለ ትግል ነው።
ሙሉ መጣጥፍን ማስፈንጠሪያውን በመጫን ያንብቡ

https://medium.com/@articles_89210/አግላዩ-የኢትዮጵያ-የፌሚኒዝም-እንቅሰቃሴ-ሴታሴት-fd736b7e34e4

❤4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🏳️⚧️ ዛሬ የትራንስጄንደር ማህበረሰብን የምናከብርበት ቀን ነው። የምናከብረው "ማንነትን ማሳወቅን" ብቻ ሳይሆን፣ ዓለም ገና ማዳመጥን እየተማረ ባለበት በዚህ ወቅት፣ በራስ ማንነት ለመኖር የሚያስፈልገውን ድፍረት ጭምር ነው።
❤1
እንደ ውብ የጥለት ክሮች፥ አብረን ስንሆን ይበልጥ ፥ እንደምቃለን፥ እንጠነክራለን ። መልካም የኩራት ወር 🏳️🌈
#pridemonth #QueerJoy #loveislove #lovewins

🥰3❤2
የኩራት የማስታወሻ ላይ ስንብቶች
የሰኔ ወርን ስናገባድድ እና ዓለምአቀፍ የኩራት ሰልፎች ሲጠናቀቁ በየእለት ህይወታችን ልናስታውሳቸው የሚገቡ የኩራት ቁምነገሮች አሉ። ኩራትን ወቅት ጠብቆ ከሚመጣ ክብረበዓል አልፎ እኛ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ከሰኔ እስከ ሰኔ በእለት ህይወታችን ውስጥ ልናስታውሳቸው የሚገቡ ኩራት ስንብቶች አሉት!… ተስፋ ፣ ድፍረት ፣ ትግል ፣ ፍቅር እና ኩራት!
ምንም እንኳን በሀገራችን ጥልቅ በሆነው ማህበራዊ ጭቆና በነፃነት እና በእኩልነት መኖር አዳጋች ቢሆንም በድፍረት ራስን መቀበል ፣ ስለነገ ተስፋ ማድረግን ፣ ደግሞም ለተሻለ ነፃነት መታገልን ከምንም በላይ ራሳችንን እና ማህበረሰባችንን ፍቅር ማስተማር የኩራት ስንብቶች ናቸው። ጭላንጭል ተስፋን እያየን ፣ ለነገ በጋራ እየታገልን በኩራት እንኖራለን!
ቸር የኩራት ዓመት!

❤2🥰1
እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ!!!
በአለፉት ዓመታት በብዙ ፈተናዎች በጋራ እንደማህበረሰብ አብረን ቆመናል። ዝምታ ብቸኛው መፍትሔ በሚመስልባቸው ጊዜያት እንኳን በአገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ለማህበራዊ ፍትህ ድምፅ ሆነናል። በፍርሃት እንድንደበቅ በሚገፋፉ የደቦ ፍርዶች እና የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች በጋራ ጠንካራ ትግሎቹን አድርገናል። ለሀገራችን ሰፊው ህብረተሰብ እምቢተኝነታችንን አሳይተናል! ቀላል አልነበረም ነገር ግን በብዙ ፈተናም በጋራ ወደ አዲሱ ዓመት ተሻግረናል።
በአዲሱ ዓመትም ከሚገጥሙን ፈተናዎች በላይ በአንድነት በጋራ ቆመን ለማህበራዊ ፍትህ እና እኩልነት እንታገል! ጭላንጭል ሁሌም ለመላዉ ማህበረሰባችን ፍቅርን ፣ ሰላምን እና ራስን ሆኖ የመኖር ነፃነትን ትመኛለች። ውድ ዜጎች በአዲሱ ዓመት የልባችሁ መሻት እንዲሆንላችሁ እንዲሁም በፍቅር እና በነፃነት መኖርን ጭላንጭል ትመኝላችኋለች። እንቁ-ለጣታችሁ! ተስፋ ለነጋችሁ!
መልካም አዲስ ዓመት!

❤2