ኪዳነ ምህረት ኢየሱስ በእግዚአብሔር እና ሰው መካከል ያለውን ውል በደሙ የምህረት አደረገው ።
ሃያላን ሰላምን ለማምጣት ጦር ልከዋል ፤ አብ ግን ሰላምን ለማስፈን ልጁን ኢየሱስ ልኳል !!!
ስለ .........?
በሳምንት አንድ ቀን " ስለ" የተባለ የሚዲያ ፕሮግራም ነበር ። ፕሮግራሙ ከስሙ እንደምንረዳው "ስለ" ብዙ ነገሮች ነው ። ምሳሌ .. ስለ ምግብ ፣ስለ ሀገር ፣ስለ ፖለቲካ፣ ስለ ባህል ፣ስለ እንስሳ ፣ስለ እፅዋት ...ስለ ተፈለገው ነገር ይወራል የማይነካ ጉዳይ የለም ።
ወደ ወንጌል ስንቀርብ ስለ ብዙ ነገር መደስኮር አይደለም ።ስለ ብዙ ነገር ማብራራት አይደለም !! ወንጌል ስለ አንድ አካል ነው እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ ስለሆነው ኢየሱስ ነው ። ወንጌል ስለ ልጁ ነው ።
ስለ ልጁ ነው 🤔 ልጁ ማን ነው ??
ሮሜ 1 (Romans)
3-4፤ ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

መፀሀፍ ቅዱስ📖 ስለ ኢየሱስ ነገረን !! ኢየሱስን በማመን 👉 የሚገኘውን መዳን አመላከተን ።
2 ጢሞቴዎስ 3 (2 Timothy)
15፤ ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል።

ማንም ወደ እሱ መጥቶ የህይወት ውሃ እንዲጠጣ እሱ ተጠማ ። በፍቅር ድምፅ ማንም የተጠማ ወደ እኔ መጥቶ ይጠጣ ሲል ተጣራ ግን ኑ ብቻ ብሎ አይደለም የተጣራው ከጥማችን መሃል ገብቶ በእንጨት ላይ ተንጠልጥሎ ተጠማ። ሊያጠጣን ፣ ተጠማ ! አጠጪው ለጠጪዎቹ ተጠማ !!
የተጠማው አጠጪ !!ኢየሱስ
ዮሐንስ 19 (John)
28፤ ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ፡— ተጠማሁ፡ አለ።
ዮሐንስ 7 (John)
37፤ ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ፡— ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ።
38፤ በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ።

ክርስቶስ ተሰቅሎ እንደነበር ካየን ይቅርታ ማረግ አይከብደንም የክርስቶስ ፍቅር እና የቆሰለው ቁስል ይታየናል ። አይናችን ከመስቀሉ ስናሸሽ ይቅርታ ይከብደናል የሚታየን የራሳችን ቁስል ብቻ ሰለሚሆን።
#ሕይወት ተገለጠ
(1ኛ ዩሀንስ መልዕክት)
* የዩሀንስ መልዕክት ተወዳጅ መፀሀፍ ነው ። ይቺ መልዕክት በዩሀንስ ተፅፋለች ።
* ዩሀንስ ማን ነው ??
* ዩሀንስ ኢየሱስን ተገናኝቶ የጌታ ደቀ መዝሙር ከመሆኑ በፊት የመጥምቁ ዩሀንስ ደቀ መዝሙር የነበረ ..ከመጥምቁ ዩሀንስ ስር ይማር የነበረ ሰው ነው ።
ዮሐንስ 1 (John)
35፤ በነገው ደግሞ ዮሐንስ ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት ቆመው ነበር፥
37፤ ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን ተከተሉት።
* አባቱ ዘብዲዎስ ሲባል በሙያው ደግሞ አሳ አጥማጅ የነበረ ነው ። ወንድሙ ደግሞ ያዕቆብ ይባላል ። አሳ ከማጥመድ ነው ኢየሱስን የተከተሉት
ማቴዎስ 4 (Matthew)
21፤ ከዚያም እልፍ ብሎ ሌሎችን ሁለት ወንድማማች የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በታንኳ መረባቸውን ሲያበጁ አየ፤ ጠራቸውም።
22፤ እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት።
* ወንድሙ ያዕቆብ የመጀመሪያው ሰማዕት ሁኖ በሰይፍ የተገደለ የመጀመሪያው ሐዋሪያ ነው
ሐዋ. ሥራ 12 (Acts)
2፤ የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው።
* ያዕቆብ እና ዩሀንስ እነርሱም ደግሞም እናታቸው ኢየሱስ በመንግስቱ በቀኝ እና በግራ ለመቀመጥ ለምነውት አስተምነውት ነበር
ማቴዎስ 20 (Matthew)
20፤ በዚያን ጊዜ የዘብዴዎስ ልጆች እናት ከልጆችዋ ጋር እየሰገደችና አንድ ነገር እየለመነች ወደ እርሱ ቀረበች።
* ያዕቆብ እና ዩሀንስ ቁጣ ይቀድማቸው ስለነበረ እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጠፋን እንዲበላ ኢየሱስን ስለጠየቁ ጌታ የነጎድጓድ ልጆች ብሎ ሰየማቸው ። ነጎድጓድ ማለት ሀይለኛ ስለሆነ ያን ለማሳየት ነው ።
ማርቆስ 3 (Mark)
17፤ የዘብዴዎስንም ልጅ ያዕቆብን የያዕቆብንም ወንድም ዮሐንስን ቦአኔርጌስ ብሎ ሰየማቸው፥ የነጎድጓድ ልጆች ማለት ነው፤
* ኢየሱስ ብዙ ጊዜ ከደቀመዛሙርቱ ሶስቱን ማለት ዩሀንስ ወንድሙን ያዕቆብን፣ጴጥሮስን በተለየ መልኩ ልዩ ልዩ ልምምዱን ያሳያቸው ነበር ።
ማቴዎስ 17 (Matthew)
1፤ ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።
* ዩሀንስ በተለይ በበርካታ ዘንድ የፍቅር ሐዋሪያ ፣የፍቅር ፀሀፊ እየተባለ ይጠራል ። የፍቅር ሐዋሪያ ያሰኘው በፃፈው ወንጌል እና መልዕክቱ ውስጥ በርከት ባለ መልኩ ስለ ፍቅር በመፃፉ ነው ። ቀድሞ የነጎድጓድ ልጅ የተባለበት እውነታ ባለፈ መልኩ አሁን የፍቅር ሐዋሪያ ይሉታል ።
* ዩሀንስ ኢየሱስ ይከተል በነበረበት ጊዜ ከሁሉም በዕድሜ ትንሹ እሱ ነበር በተለይ ወደ ሃያዎቹ ሊገባ ያለ ወጣት መሆን ያትታሉ ብዙዎች ።ይሔም ብቻ ሳይሆን ከሁሉም ሐዋሪያት በመጨረሻ የሞተው ዩሀንስ ነው ።
* ዩሀንስ በፃፈው ወንጌል ላይ 5 ጊዜ ራሱን ጌታ የሚወደደው ደቀ መዝሙር ይል ነበር ። ጌታ ዩሀንስ ይወደው እንደነበረ ራሱ ፅፎልናል ።
ዮሐንስ 21 (John)
7፤ ኢየሱስ ይወደው የነበረውም ደቀ መዝሙር ጴጥሮስን፡— ጌታ እኮ ነው፡ አለው። ስለዚህ ስምዖን ጴጥሮስ ጌታ መሆኑን በሰማ ጊዜ ዕራቁቱን ነበረና ልብሱን ታጥቆ ወደ ባሕር ራሱን ጣለ።
* ዩሀንስ ወደ ኢየሱስ ደረት ወደ እቅፍ ይቀርብ ነበር ። በዚህ ምክኒያት የእቅፍ ወዳጅ (bosom friend ) እያሉ የሚጠሩትም አሉ ።
ዮሐንስ 13 (John)
23፤ ኢየሱስም ይወደው የነበረ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ በኢየሱስ ደረት ላይ ተጠጋ፤
* ኢየሱስ በመስቀል ላይ እያለ እናቱን አደራ ያለው ለዩሀንስ ነበር ።
ዮሐንስ 19 (John)
26፤ ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን፡— አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ፡ አላት።
* ይሔን መልዕክት ዩሀንስ በፃፈ ጊዜ አርጅቶ ነበር እራሱንም ሽማግሌው እኔ እያለ ይናገራል ለሚፅፍላቸው ደግሞ ልጆች
1 ዮሐንስ 2 (1 John)
1፤ ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
* ፀሀፊው 5 መፅሀፍ አበርክቶልናል ( ዩሀንስ ወንጌል ..1፣2፣3 ተኛው ዩሀንስ .. ዩሀንስ ራዕይ )
* ዩሀንስ መልዕክት የተፃፈበት ዋና ምክኒያት ኖስቲዝምን አስተምሮ ለመከላከል ነው ።
ኖስቲዝም ???
* ኖስቲዝ በውስጡ ሌሎችን አስተምሮ የያዘ ከግሪክ የተወሰደ ፍልስፍና ነው ።
በተለይ አስተምሮው የሚያጠነጥነው በስጋ ላይ ነው ። ስጋ ርኩስ በመሆኑ ኢየሱስ ስጋ ሳይሆን የበለሰው ስጋ የሚመስል አካልን ነው እንጂ ኢየሱሰ ፍፁም ሰው አልሆነም ይላሉ ኖስቲስት።
* ዩሀንስ ደግሞ ክርስቶስ ሰው ካልሆነ መዳናች እውን እንደማይሆን እምነታችን ከንቱ እንደሚሆን ስለገባው ለዚህ አስሰተምሮ በቂ መልስ ይሰጣል ።
1 ዮሐንስ 2 (1 John)
22፤ ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው? አብንና ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።
1 ዮሐንስ 4 (1 John)
3፤ ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም እንኳ በዓለም አለ።
2 ዮሐንስ 1 (2 John)
7፤ ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ገብተዋልና እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ናቸው፤ ይህ አሳቹና የክርስቶስ ተቃዋሚው ነው።
....ዩሀንስ መልዕክት እምታተችን፣ ተሰፋችን፣ ፍቅራችን የሚቀዳው ባመንነው እውነተኛው የክርስቶስ ማንነት ተመስርተን እንደሆነ ይጠቁማል ።
ወገኔ ክርስቶስ ላይ እንዴት ናችሁ ?? ብዥታ አለባችሁ ??ማንነቱ ላይ ቅዝቅዝ ትላለችሁ??
ትኩረት ለዋናችን!!
* መልዕክቱ የተፃፈው የዘላለም ህይወት የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ተገልጧል እና ያላችሁ ይሔን የዘላለም ህይወት እወቁ ለማለት ነው ።
1 ዮሐንስ 5 (1 John)
13፤ የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።
የዘላለም ህይወት የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ተገለጠ (ሕይወት ተገለጠ)
✍ ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd

እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን (ኤክሌዢያ) ላይ ልጁን ለዘላለም ራስ እና ጌጥ እንዲሆንላት ሹሞታል ።
የእግዚአብሔር ፅድቅ ተገልጦ የእግዚአብሔር ወንጌል ደረሰልን ከዛም የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ሆንን..የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ጋር ቀላቅሎን አካል አደረገን ።