በክርስቶስ ( in christ)
853 subscribers
99 photos
34 videos
40 files
40 links
Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin
Download Telegram
ድካሜን በተረዳሁ ቁጥር በራሴ መፍጨርጨር አቆማለሁ ፀጋው ለመደገፍ  አብዝቼ ወደ ፀጋው ዙፋን እቀርባለሁ !!

(እፉፉ በፀጋ ከራስ መገላገል እንዴት ያለ እፎይታ ነው)


@ownkin
@cgfsd
( ይርባል እንዴ ??)

ሁለት ወዳጆች ጨዋታቸው ይጫወታሉ ። አንድኛዋ ለተወሰነ አመታት እስራኤል ኑሯለች ። ስለ እስራኤል የምታወቀውን ለሌላኛዋ ጓደኛዋ ትነግራታለች ።
   " እስቲ ተይኝ አሁን አሜሪካ ፣ አውስትራሊያ ሀገር ነው ምናምንቴዎች ፤ ሀገር ማለት እስራኤል ነው ። መሬቱን እንደው ብታይ አሸዋ ነው ግን በልምላሜ አረጓዴ ነው። ለካ እውነት  ነው ... በመፀሀፍ ቅዱስ ማር እና ወተት የምታፈሰው የተባለላት ያለ አንዳች አይደለም ። አይምሮአቸውስ ብትይ የተባረከ በእውቀት የተሞሉ ናቸው ።

እንደው በየቤተክርስቲያኑ ምስባክ እንደው ስለጌታችን ታሪክ  ሲወራ በአይምሮዬ ኮለለል እያለ ይታየኛል  የጎበኘሁት ሁሉ  ።
  ጌታችን የተቀበረበት መቃብር ብትይ ፣ ክብሩ ከደቀመዛሙርቱ ጋር የተገለጠበት ደብረ ታቦር ፣ ሊሰቀል ሲል ቀድሞ የፀለየበት ጌተሰማኒ፣ አርባ ቀን አርባ ሌሊት ከፀለየ በኋላ ድንጋዩን ዳቦ አርግ ተብሎ የተፈተነበት ፣የተሰቀለበት ቀራኒዬ ጎልጎታ፣ ደግሞ በምፅአቱ ይመጣበታል የሚባለውንን ተራራ፣ ይሔ ይገርምሻ ስሙ ማን ነበር ??? ይሔ አራጣ ያበድር የነበረው አዎ አዎ አጭሩ ዘኪዬስ እሱ የወጣበት ዛፍ ሁላ ሳትቀር ነው ያየሁት ።
     ሌላኛዋ ጓደኛው በተራዋ ወይ ያንን ማየት የሚችል እንደው የተባረከ ነው!! አለች ፤ በረጅም እየተነፈሰች  እንባ ከአቀረሩ አይኖቿ ጋር ።
  ግን አንድ ጥያቄ ልጠቅሽ ....ግን እዛ ይርብሻል እንዴ?? (ይርባል እንዴ) ??   ማለት በቃ ይሔን እያየሽ አይርብሽም አይደል  ነፍስማ መቼም ይሔ አይታ ትጠግባለች እንጂ አትራብም ።
   የእስራኤሏ ሴትዬ አንገቷን ዝቅ አድርጋ ትዝታ እንደገረፈው ተክዛ አዎ ያጠግባል ብላ ቋጨችው።
.............................

.... ታዲያ እንዴት እንጥገብ??መቼም መንፈሳዊ ነገር ለመጥገብ የግድ ኢየሱሰስ የተወለደበት፣ እና የሞተበትን ብቻ ማየት አይጠበቅብንም ። እርሱ ራሱ የህይወት እንጀራ ነኝ ብሎናል እሱን ከበላን አይርበንም ማንነቱ ጥጋብ ሆኖናል።   

  ጋሽ ሰለሞን አበበ ገብረመድህን በአንድ የፅሀፉ ልጠፋቸው ላይ እንዲህ አሉ
  " መስቀል ላይ የተጋገረ እንጀራ "።
ግሩም አባባል እንደሆነ ተረድቻለሁ ። እግዚአብሔር መቼ የነፍስ ጠኔያችን እና ጉስቁላችን ለማከም፣ለማስታገስ፣ ለማጥገብ ብሎም ለማርካት አንድያውን በዘላለማዊ ፍቅሩ ህይወት እንዲሆንል ጋገረልን ። ከዛም የተጋገረውን በፍቅር ድምፅ ብሉልኝ አለ ። ከዚህ በላይ ምን የሚያጠግብ ህይወት አለ??ምንም !!
   የተጋገረውን እንጀራ እያሰብኩ አጭር ስንኝ ቋጠርኩ
        መስቀል ባሉት ምጣድ
                 ርሃብ ታሰረ
          የህይወት እንጀራው
                  መናው ተጋገረ

ለማስታወስ ያክል እግዚአብሔር እስራኤላዊያን በግብፅ ሳሉ ስለ ፋሲካው በግ በተመለከተ ከአዘዛቸው ትዕዛዝ አንዱ የፋሲካው በግ እንዲበሉ በመጀመሪያ ጥጋብ እንዲሆናቸው ነበር ።ግልፅ ያለ የኢየሱስ ምሳሌ ነው  ፋሲካችን ክርስቶስ ከሆነ ዘንዳ ምን እንበላለን ??ምንም !! እስራኤላዊያን ከግብፅ ወጥቸው ወደ ከነአን ለሚያደርጉት ጉዞ የበሉት የፋሲካ በግ ስንቅ ሆኖቸው ነው ። እኛስ የጀመርነው እውነተኛው መንፈሳዊ ህይወት ኢየሱስን ተመግበን አይደል ። የጀመርነውን ህይወት በድል የሚያስጨርሰን ሚስጥሩ የበላነው እውነተኛው መብል ኢየሱስ ነው ። እግዚአብሔር እንደዚህ የሚል አይመስላችሁም ..ብሉልኝ ይሔው ቢበሉት የማያልቅ ይሔው የሚትረፍረፍ ማዕድ ከሰማይ የሆነ የህይወት እንጀራ ። አባቶች መና በልተው ተራቡ በዛው በምድረበዳ ቀሩ ..እውነተኛ የህይወት እንጀራው ኢየሱስ የበላ ግን የዘላለም ህይወት ይቀናጃል ። ቲሞቲ ከለር የተባሉ ሰው እንዲህ አሉ " ኢየሱስ የህይወት እንጀራ ነኝ ሲል እግዚአብሔር ጋግሮላችኋል እያለ ነው "።

ጌታችን ኢየሱስ እሱ ራሱ የህይወት እንጀራ እንደሆነ ለተከተሉት ሊያሳውቅ በማሰብ 2አሳ እና 5እንጀራን አበዛላቸው ደስም አላቸው በሉ ተነጋገሩ መብዛቱ በራሱ አስደሳችነው አለማለቁም ሌላ አጃይብ ነው ።ግን ከበዛው ምግብ በላይ እሱ ኢየሱስ በእነርሱ ህይወት ሊበዛላቸው የህይወት እንጀራ ሊሆንላቸው እንደመጣ አልተገነዘቡም ነበር ።  2አሳ እና 5 እንጀራው በአንድ ጊዜ ተበልቷል ያው እዛ ቦታ ለነበሩት የህይወት እንጀራ ሁኖ ከመስቀል ላይ የተበላለው ግን ዛሬም ፣ነገም
  የሚበላ ለሁሉም የሚደርስ የተትረፈረፈ ማዕድ ነው ።


    በቀራንዬ ላይ ለእኛ በጉ ታርዷል
    ፈርኦን አይደለም ዲያቢሎስ ተረቷል
    በትረ ሙሴያችንም የጌታ መስቀል ነው
     በእሱ ቀጥቅጠን ነው ሞትን የገደልነው
                  (ዘማሪ ቴዎድሮስ)


ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
አብዝቶ በመስቀሉ ስራ የተመሰጠ(የተደነቀ) በመዳኑ ውስጥ ያለውን ደስታ ያጣጥማል ።

@ownkin
@cgfsd
የመስቀሉን ሊሻን አርገን #የደሙን ሀብል አጥልቀን #በቀዩ ምንጣፍ ላይ በእምነት #ተራምደን ገብተናል ገነት #ድል ነስቶ ድል አልብሶናል #ኢየሱስ ማዕረግ ሁኖናል ።



🎼
@cgfsd
@ownkin
በመዳፍህ መሃል ያሳለፍከኝ #ጌታ ተቸንክረህ ደምተህ ሰው ያረከኝ #ጌታ የቱ ትከሻዬ ፍቅርህን ይችላል ከምገልፀው በላይ #ውለታህ ከብዶኛል ።


🎼
@ownkin
@cgfsd
የሰማይ ድባብ የቤዛነቱ ድባብ ነው ። ለዚህም ነው በሰማይ ታርደሃል እና እየተባለ ቅኔ የሚቀኙለት እዛም ሰማይ የቤዛነቱ ጠረን ይሸታል ፣ የቤዛነቱ መአዛ ያውዳል። ቤተክርስቲያንም የክርስቶስ የቤዛነት ድባብ ጉባኤዋን ያጥናል ፣ በመካከሏ የቤዛነቱ ደስታ ያስተጋባል፣ ቤዛነቱ ያንሰፈስፋታል፣ ቤዛነቱ ቀልቧን ይሰርቃል።


@ownkin
@cgfsd
#የዘላለም ርዕስ #የማያልቅ ምዕራፍ #የማይፈፀም ታሪክ #የማይጨረስ መፀሀፍ #የእሱ መች አልቆብን ሌላ እንጀምራለን #የተሰቀለውን ስንሰብክ እንኖራለን #ዋናው ኢየሱስ ነው  #ዋናው ክርስቶስ ነው #ከሞት ለተቤዥን #በደሙ መፍሰስ #በደሙ መፍሰስ #መቼ አወጅነው እና #የእርሱን ድንቅ ስራ


🎼
@ownkin
@cgfsd
(የነካኝ ምስክርነት)


በክርስቲያን ቤተሰብ በማደጌ ኢየሱስን የማውቀው ልክ  በመስቀል ላይ የተሰቀለ  የሚል ብቻ እውቀት ነበር ። በኋላ ግን ከዛ ያለፈ እንደሆነ አስገራሚ ማንነት እንዳለው ስረዳ አብዝቼ አብዝቼ ኢየሱስ የሚለው ስም አንስቼ ማንነቱ አስቤ አልጠግብ አልኩ ።ስለ ኢየሱስ ሳይሆን ራሱን ኢየሱስ ማወቅ ጀመርኩ ።

ኢየሱስ አስገራሚ ማንነት አለው 😍



@ownkin
@cgfsd
ውዳችን ኢየሱስ ወከባ አያስቆመውም .... ለአየር መተንፈስ በሚከብደው  በግፊያ መሀል ግን ለነካው ይቆማል ።
             
      ምስክር : የደሟ ምንጭ የቆመላት


@ownkin
  @cgfsd
#ኢየሱስ -በምድር በነበረበት ዘመን አለመኖሬ ኢየሱስ እንዲያመልጠኝ አላደረገኝም....በምድር አይኑር እንጂ እሱ ወዳለበት መንፈስ ቅዱስ አድርሶኛል......እርሱ ካልገለጠልን በቀር ኢየሱስን ማወቅም መንካትም አንችልም 😇😘

Ariel

@ownkin
@cgfsd
ኢየሱስ ከክህደት በኋላ የምትሾም አንተ ነህ !! የወደድካቸውን እስከ መጨረሻው የምትወድ ወዳጅ
(የግንዱ ላይ ሰንባች)



  ኢየሱስ ገበሬው አባቴ ነው በማለት ሊሰራ ስላለው ታላቅ ስራ የአንበሳውን ድረሻ የአባቱ  እንደሆነ አስገንዝቦናል ። በእርግጥም እግዚአብሔር ጥንቅቅ ያለ ገበሬ ነው ። ገበሬ ያነገበው አላማውን እስከ መጨረሻው እንጥፍጣፊ ደረጃ ድረስ ሰንቆ የሚተጋ ነው። ሁሉም ነገር የሚታየው ከግቡ የተነሳ ነው ቢጥል ፣ቢያነሳ፣ ቢቆፍር፣ ቢቧጥጥ የሰነቃትን ተልዕኮ ለማሳካት እንጂ እግረ መንገድ የሆነ ራዕይ የለውም ። በጠዋት ማልዶ ሲነሳ ፀሀይ በምስራቅ በኩል መፈንጠቋ ለእሱ ቅንጦት አይደለም ምርቱን በላቀ ሁኔታ ለመጨመር ሌላ እድል አድርጎ ያየዋል ። ዝናብ ደግሞ እንዲሁ አየር ንብረቱ እየሞቀው ስለረበሸው እንደው ቀዝቀዝ ለማለት አይሻውም ይልቁንም የዘራቸው ዘሮቹ እንዲያቆጠቁጡ ተስፋ ይጥልበታል ። ሀብቱም ፣ ንብረቱም ፣ ጉልበቱም  የሚያፈሰው (ኢንቭስት የሚያደርገው ) መሬቱ ላይ ነው ። ምናልባት በለስ ካልቀናችው ደግሞ ኪሳራውም በእጅጉ አስደንጋጭ ነው የሚሆነው ያለውን በሙሉ የሰጠው ለዚሁ ጉዳይ ነውና ።  የእግዚአብሔር ገበሬነት ግን በእጁጉ ይለያል ብሎም ይማርካል ።  ቆይ ግን እግዚአብሔር ምን ገዶት ገበሬ ሆነ 🤔???

    ህብረት ...ህብረት ...ህብረት ብቻ ነው ። እግዚአብሔር የገበሬን ግብር ይዞ የተጠራው እኛን ሆን ብሎ ለማስገረም አይደለም ህብረት ፈልጎ እንጂ ። አምላካች ህብረት የሚወድ ህብረት የሚያረግ አምላክ ነው ። ለዚህም ነው ገበሬ ብሎ የተጠራው !!  የፈለገው ህብረት ደግሞ በግንድ በቅርንጫፍ በኩል የሆነ ህብረት ነው ።  የሚያስገረም ነው ነገር ቢኖር ገበሬው እግዚአብሔር ለዚህ ህብረት ኢንቭስት ያደረገው ዋጋ ነው ። ኢንቭት ለማድረግ ውሃ አልቋጠረም ፣ አፈር አልጫረም ፣አቧራ አላስነሳም አንድ ልጁ ላይ ጨከነበት ። የተጠቀመው ውሃ የልጁን ደም ፣ የተኮኮተው መሬት የልጁን ስጋ ነበር ። ወደር የማይገኝለት ዘላለማዊ ልጁን ስለ ሌሎች ተብሎ ተማገደ ። እግዚአብሔር የመጨረሻ ኢንቭትመንቱን በልጁ ቤዛነት (ምትክነት ) በኩል አደረገው ።ገበሬው አምላካችን በልጁ በኩል አለምን የሚያርስበት ቀን በጉጉት ለቀደሙት አባቶች አመላከተ ። ዘመቻ ቀራኒዮ ...ዘመቻ ጎልጎታ የኢንቭትመንቱ የመጨረሻ ግብ ነበር ። ምንም እንኳን እንደ ገጠሩ አካባቢዎች ለአጨዳ ቀን ሆ ብሎ ሰው በሆታ ሊሰበስብ አልመጣ ይብሱኑ በአንድነት በጩኸት ስቀለው ስቀለው እያሉ አንድያውን አሳልፎ በሰጠው የገበሬውን ልጅ ላይ ለመግፋት ተሰበሰቡ እንጂ ።  ገበሬው በኩራት ይሔው ኢንቭትመንቴ ይሔው ከመስቀሉ ላይ ፣ ይሔው የተሰቀለው እሱ ላይ የሚበቅሉ ቅርጫፎች ውጤቶቼ ናቸው ።ቅርጫፎቹ የሚያፈሩት ፍሬው ደግሞ የሰራውት ታላቅ የኢንቭትመንት ስራ ማሳያዎች ናቸው ።

የልጁ ደም ከልጁ እና ከገበሬው አባቱ ጋር ህብረት ማድረጊያ ነው ።ህብረቱ  ከተሰቀለው ጋር አብሮ መሰቀል ነው ፣ ህብረቱ ከሞተልን ጋር መሞት ነው ፣ ህብረቱ ከተነሳልን ጋር መነሳት ነው ፣ህብረቱ ለግንዱ መኖር፣ ህብረቱን ግንዱ ለመምሰል መኖር ፣  ህብረቱ ገበሬው በቅርጫፉ በኩል የገለጠልን ፍቅር መቋደስ፣ መተንፈስ ፣ ለሌሎች ማካፍል ፣ በፍቅሩ መፈንደቅ ፣ በፍቅሩ መኩራራት ይሔ ህብረቱ ነው ... ገበሬው ... እኛ ለግንዱ ሰጥቷል ... በግንዱ በኩል የማያስፈልገው አኑሮሯል ። ግንዱ ሁል ጊዜ እንዲህ ይለናል በእኔ ኑሩ !! በእኔ ቆዩ ፣ በእኔ ሰንብቱ ፣ በእኔ ክረሙ ፣ በፍቅሬ ኑሩ እያለ ከእርሱ ጋር ወዳለው ቁርኝት እና መጣበቅ ይጠራናል ።

በግንዱ ክርስቶስ ጋር መቆየት ምርጫ የሌለው የህይወት ስርአታችን ነው ። ከእርሱ ጋር እንድንከርም ተጠርተናል ። የገበሬውን የልብ ትርታ ለመረዳት ካሰነበተን ግንድ ጋር መሰንበት ነው ። ግንድ ለቅርጫፎቹ የሚሆኑትን ሚኒራል ፣ ውሃ የሚያስፈልጉት ሁሉ ወደ ቅርጫፎቹ ሳያጓድል ያደርሳል የእኛም ግንድ ክርስቶስ ለእኛ የሚያስፈልገን ለህብረቱ የሚጠቅመን ማንነቶች ሳያዛንፍ ይሰጠናል ።


ከግንዱ ክርስቶስ ጋር ስለተወዳጀን ነው ፤ የገበሬውን ቤተሰብ የተቀላቀል ነው።
በክርስቶስ ( ግንዱ) እና በእኛ (በቅርንጫፎቹ) መካከል ያለው የወዳጅነት መጣበቅ ምክኒያቱ ክርስቶስ ላይ እንድንቆይ የወደደው ገበሬ ነው ።


ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
ክርስቶስ በቅዱሳት መጻሕፍት በኹሉም ስፍራ አለ! ለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስን አብዝቼ የምወድደው!

Diakon abenezer

@cgfsd
@ownkin
ይሔ ንጉስ ማን ነው ?? በፍቅር ያጌጠው #ልብሱ በደም ቀልቶ ሞትን የረገጠው #በጉልበቱ ፅናት የሚረማመደው #አዎን ኢየሱስ ነው አዎን ጌታዬ ነው

🎼

@ownkin
@cgfsd
(ኢየሱስ ያስቀናል )


የፈንሳዩ የጦር አበጋዝ ናፖሊዮ ቦናባርቴ በርከት ያሉ የውጊያ ድሎች አስመዝግቧል፣ ብዙዎች ማርኳል ነገር ግን ስለ ጌታ ኢየሱስ ማራኪነት ተደንቆ ያለ ጠብመንጃ ሚሊየኖች በፍቅር እንደሚከተሉት በአግራሞት ተናግሯል ። የክርስቶስ ማንነት በእጅጉ የሚገዛው በሰባአዊነቱ የሚጠቀሰው ማህተመ ጋንዲ የኢየሱስ ባህሪ ለዕድሜ ዘመኑ እንደጠቀመው ፣ ስብዕናው ውስጡ እንደሚገዛው አትቷል ።አለም በመዝገቧ ከትባ ያስቀመጠቻቸው ታላላቅ ሰዎች በናዝሬቱ ኢየሱስ የተነሳ እየተገረሙ ወቸው ጉድ በማለት እጃቸውን በአፋቸው አጣምረው ጭነዋል ። በአሜሪካን ለሰው ልጆች እኩልነት ወገቡን አስሮ በቀዳሚነት  ዘብ የቆመው ማርቲን ሉተር ኪንግ  እንዲህ ይላል "ኢየሱስ ለፍቅር ፣ ለእውነት ፣ ለመካምነት ፅንፈኛ ነበር "  በማለት ሀሳቡን አጋርቷል ። በዘመነ አብርሆት ለአለም መንቃት አስተፆ የተጫወተው ፈላስፋው ሩሶ ደግሞ በበኩሉ "ሶቅራጥስ እንደ ፈላስፋ ሞተ ኢየሱስ ግን እንደ እግዚአብሔር ሞተ " በማለት እይታውን አስቀምጧል ።

የቀጠናው አስተዳዳሪ ሔሮዶስ እልፍ እየተከተሉት እንደሆነ በተአምራቱ እና በትምህርቱ አካባቢውን አልፎ ዙሪያ ገባውን  የናዝሬቱ ኢየሱስ እንደሞላ ሲሰማ ስለ ስልጣኑ ስጋት ቢኖረው እሱን ሊሰማ ይናፍቅ ነበር ። መሲሁ ኢየሱስ ላይ ጥርስ የነከሱት የካህናት አለቆች ወታደር አሰማርተው ተጠፍንጎ እንዲመጣ ትዕዛዝ ቢሰጡም የተላኩት ወታደሮች ግን በማንነቱ ፣ በትምህርቱ እና በስራው ተመስጠው የተላኩበትን ረስተው  ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ስለ ንፅህናው ሽንጣቸውን ገትረው ተከራክረዋል ። የሸንጎ አባሉ ፈሪሳዊው ኒቆዲሞስ ኢየሱስን ለማወቅ በሌሊት ያለበት ድረስ አነፍንፎ መቷል ። ኢየሱስ ያስቀናል !! እንስማህ፣ እንይህ፣ እንንካህ ፣እንከተልህ ያስብላል ። 

በጨዋታችን መሃል አንድ የምቀርበው ወዳጄ በቤተክርስቲያን መሃል ስለተንሰራፋው ክርስቶስን ስለማይመስለው ልምምዳችን ሲያስብ እንዲህ ይለኛል " እኔ ግን አይገባኝም ክርስቶስን እንዲህ አለውቀውም  ኧረ እኔ ኢየሱስ እንደዚህ አላውቀውም ..ይገርምሃል ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኝ አድርጌ የተቀበልኩት በመፀሀፍ ቅዱስ የዕለት ተለዕለት  ጥናት ወቅት ነበር ። በተለይም ደግሞ የወንጌል መፀሀፍት ማቴዎስ ፣ ማርቆስ ፣ሉቃስ እና ዩሀንስ ወንጌላት ላይ ያነበብኩት ጌታ ባህሪው፣ ትህትናው ፣ ፍቅሩ ፣ አላማው ፣ ታዛዥነቱ ያስቀናኝ ነበር  " በማለት አውግቶኛል ። በትክክል !! በተጨባጭ !!! ለዚህም ነው  የዕውቀት ቀንዲሉ  ሊቁ አልበርታን አንስታይል እንዲህ ያለው " ማንም የኢየሱስን እውነተኛነትን ሳይሰማ ወንጌልን ማንበብ አይችል " ያለው። ይሔው ነው !! የወንጌል መፀሀፍት ስናነብ የኢየሱስ የማንነት ውበት ይወረናል ፣ የባህሪው ማራኪነት ይማርከናል፣ አስደናቂነቱ ቀልባችንን ይገዛዋል ። የህይወት ታሪክ አይደለም አምላክ በስጋ የኖረው ህይወት እንጂ ። በቃ እንዲህ ነው የክርስትና ወጉ ኢየሱስን ከሰማበት ፣ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ መመረቅ ለሌለው ጊዜ ዘወትር በውስጥ እየተቃጠሉ ፣ እጅ እየነሱ መኖር ።

   ኢየሱስ ያስቀናል


ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
እንጀራ ልንበላ አልተከተልህም ሀብት ብልጥግና ወደ አንተ አልጠራንም #ለምድር በረከት ታይቶ ለሚጠፋው #መች ደምህ ፈሰሰ ለሚያልፍ ተስፋ #የዘላለም ህይወት ማግኘታችን ጉዳይ ሁሌ ብርቃችን ነው #ህይወት ያካፈልከን #ኢየሱስ አንተ ነህ #ሌላ አላየንም በነፍሱ የጨከነ ...


🎼 መስኪ

@ownkin
@cgfsd