በክርስቶስ ( in christ)
863 subscribers
100 photos
34 videos
40 files
40 links
Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin
Download Telegram
የወደድኩት ምስክርነት



"እሰከ ዛሬ ኢየሱስ ኢየሱስ ሲሉ ጥያቄ ይሆንብኝ ነበር ። በጌታ ነኝ ግን አብዛኛው እንደ ታሪክ ነበር የምመለከተው ። ነገር ግን ክርስቶስ የሆነው መሆን የከፈለው ዋጋ በክርስቶስ ያገኘሁትን ማንነነት ሲገባኝ  መፀሀፍ ቅዱስ በናፍቆት ማንበብ ጀመርኩ በጉጉት መፀለይ ቀጠልኩ ..መኖር መኖር ጓጓሁ ፍቅሩ ጨመረብኝ  ። "


   @ownkin
  @cgfsd
ክርስቶስ አልዓዛርን በታላቅ ድምጽ ጮኾ "ወደ ውጭ ና!" ብሎ ከጥልቅ እንቅልፉ እንደቀሰቀሰው ጳውሎስም በመልዕክቱ "አንተ የምትተኛ ንቃ!" በማለት ሰውን ከጥልቅ እንቅልፉ ይቀሰቅሳል።

ሰው የሚነቃው በዝግመተ-ለውጥ ሳይሆን በክርስቶስ ነው፡ ክርስቶስ የሰውን ዘር የማንቂያ ደውል ነው፡ ሰው ከጨለማ ከጥልቁ የሚወጣው በክርስቶስ ብቻ ነው፣ ምክንያቱም አንተ የምትተኛ ንቃ ካለ በኃላ ክርስቶስም #ያበራልሃል ነው የሚለው።

ዮሃንስም በወንጌሉ በአልዓዛር አስታኮ የሰው ዘር ሁሉ እንዳንቀላፋ እየነገረን ነው፡ ለዚህም ነው ጌታችን፦

"ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቶአል፣ ነገር ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ" ያለው።

ሰው ሁሉ ተኝቶአል ነገር ግን ክርስቶስ የማስነሳት አቅም አለው።

ጳውሎስም ምንም እንኳን ለኤፌሶን አማኞች ቢጽፈውም መልዕክቱ ግን ለሰው ሁሉ ነው፡ ምክንያቱም ሰው ያለ ክርስቶስ "እንቅልፋም" ነው፡ ስለዚህም ንቃ! ይላል ጳውሎስ።

ሰውን ዝግመተ-ለውጥ ወይም ቴክኖሎጂና ሳይንስ አያነቃውም ክርስቶስ እንጂ፡ እርሱ ወደ ዓለም የመጣው ብርሃን ነው ምንም እንኳን ሰው ስራው ክፉ መሆኑን አውቆ ቢደበቅም፤ ልክ አዳም በዛፍ እንደተደበቀው።

ክርስቶስ የሰውን ሁሉ ጨለማ ያበራል!!!

Yilu danu

@ownkin.
@cgfsd
እንደራሱ ቁስል ህመሜ የሚያመው
የኔ ሊቀ ካህን ኢየሱስ ብቻ ነው

Kaleab Tsegaye 🙏

@ownkin
@cgfsd
( ጌታዬ ኢየሱስ)


*የማደምቀው ጌታ የለኝም በሞቱ ያደመቀኝ እንጂ
* የምኩለው አዳኝ የለኝም በደሙ የኳለኝ እንጂ
* የማካፍለው አምላክ የለኝም በትንሳኤው ያካፈለኝ እንጂ
* ወድጄ የፈለገኩት መሲህ የለኝም የወደደኝ እንጂ

@ownkin
@cgfsd
በኢየሱስ በማመናችን ምክንያት እግዚአብሔር በእኛ፣ እኛ ደግሞ በእግዚአብሔር መኖር ጀመርን።መለኮት በእኛ ውስጥ ኖረ።እኛ ደግሞ በመለኮት ህልውና ውስጥ ኖርን።
ዋው ይሄ በእውነት ድንቅ ነገር ነው።😍😍🙏🙏🙏

ከገፅ የተወሰደ

@ownkin
@cgfsd
ኢየሱስን ለመናፈቅ ከህልውናው የተሻለ አንድም ነገር የለም ። በህልውናው ውስጥ የክርስቶስን ፍቅር ያንሰፈስፈናል .. በህልውናው ውስጥ ጎልጎታ የትናንት ያክል ቅርብ ያረገዋል ..ቀራኒዮን የዛሬን ያክል ያሳያል ..በህልውናው ውስጥ ኢየሱስ የሚለው ስም ተጠርቶ አይጠገብም ..በህልውናው ውስጥ እኔነት ፀጥ ይላል .. በህልውናው ውስጥ የኢየሱስ መምጣት በጉጉት ያስናፍቃል ያስጠብቃል ..በህልውናው ውስጥ የክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ተነስቶ አይጨረስም ..በህልውናው ውስጥ የክርስቶስ ደም ትርጉም ይሰጣል..በህልውናው ውስጥ የኢየሱስ ልብ ጮኽ ብሎ ይሰማል ..በህልውናው ውስጥ ኢየሱስ ያረካል..በህልውናው ውስጥ ኢየሱስ ብቻ ..በህልውናው ውስጥ የሞተልን፣የተሰቀለልን፣ የተሰቃየልን እርሱ ብቻ ይደምቃል ..


@ownkin
@cgfsd
ዉዴ ለእኔ ያለዉን የፍቅር መግለጫ የጻፈው በስጋና በደሙ ቀራኒዮ ነበር ፍቅሩ ደግሞ ከመቃብር በላይ ነው።

#ኢየሱስ

sharona

@ownkin
@cgfsd
የመስቀሉ ፍቅር ለየት ያረገው ዘላለማዊ መሆኑ ነው ።ዘላለማዊ መሆኑ ደግሞ እያደር የማይቀዘቅዝ፣የማይበርድ ፣የማይሰበር የወደዳቸውን እስከ መጨረሻው የሚያስወድድ ፍቅር ነው ። ለተካፈለው ደግሞ በዘላለለም ውስጥ ሁልጊዜ ዘላለማዊን ፍቅር እያወቁ የሚያስኖር ነው ። የመስቀሉ ፍቅር የአንድ ጊዜ ክስተት አይደለም ዘላለማዊ እንጂ ። ይሔ ዘላለማዊ ፍቅር በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት በደሙ ተፃፈ ፣ በደሙ ተበሰረ ፣ በደሙ ተተረከ፣ በደሙ ታየ ... በደሙ የፍቅሩን ጥንካሬ ፣ብርታት ፣ውበት ፣መልክ ፣ልክ አሳየን ... ለዚህ ነው ደሙ ፍቅሩ ላይ እርግጠኛ ያረገን .. የእኛ ጌታ ውዳችን ኢየሱስ በአንደበቱ ሳይሆን በደሙ የነገረን ፍቅር ሰምተናል ..በእርግጥም ይወደናል ።
(ጠበቃ አለን!!!)

ጠበቃ ብሎ በግሪከኛው ጵራቅሊጦስ ይለዋል ። ጵራቅሊጦስ  ለመንፈስ ቅዱስ የተሰጠ ስም ነበር አፅናናኝ ማለት ነው ።ሌላኛው ትርጉሙ እዚህ ጋር የተጠቀሰው ጵራቅሊጦስ በጥብቅናው  የሚታይ ፣ክስ የሚያስወግድ ጠበቃ  ነው  ። የድሮ የመፀሀፍ ቅዱስ ቅጅ ጠበቃ የሚለውን የሚከራከርልን ይላል ምናልባት እኛን የወከለ ብቁ የሆነ ተከላካይ ነው ።ማስተዋል ያለብን ኢየሱስ ጵራቅሊጦስ ተብሎ የተጠራበትን እውነት እና ምክኒያት ይሆናል።(1ዩሀ2:2-3)

ኢየሱስ ብቸኛ  የማይከራከር ጠበቃ ነው ምክኒያቱም ደግሞ ደሙ የታመነ ምስክር ነው። ደሙ ራሱ ይመሰክራል የታመነ ምስክር በንፁሁ ደም በኩል አቅርቧል  ። የእኛ ጠበቃ አያሳፍርም የታመነ ደም አለው እርሱን ደሙን ጥብቅና ስለቆመላቸው  አሳይቷል ። ጠበቃ የሚያቀርበው አንዳች ማስረጃ የተከሰሰውን አካል ነፃ የሚያወጣ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል የእኛ ጠበቃ ጌታችን ኢየሱስ ያቀረበው ማስረጃ ደሙን ነው ይሔው እኔ ሙቻለሁ ስለ እርሱ በደል ተሰውቻለው ሞታቸውን በሞቴ ወስጃለሁ በቀራኒዮ ላይ አልፊያለሁ እኔ እንደዚህ የሆንኩት የእነርሱን እዳ ለመክፈል ነው እና ይሔው ንፁህ ደሜ እነርሱ ከእኔ እንከን አልባ ንፁህ ደም የተነሳ ንፁህ ናቸው የሚል ማስረጃ አቅርቧል ።

ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን ሲባል የብሉይን ስርአት ማስታወስ አለብን .. ምሳሌ በመፀሀፍ ቅዱስ ውስጥ ሰዎች ሀጢያት ሲያደርጉ ወይም ባያደርጉ የሚከሳቸው ከሳሽ ነበር ። ኢዮብ 1... ኢዩብን ለመጣል በእግዚአብሔር ፊት ሰይጣን ከሳሽ ሆኖ ቀርቧል እዬብን በማጣጣል በእግዚአብሔር ፊት እደ ከሳሽ ቁሟል ።
ሌላው ታላቁ ካህን ኢያሱ (ዘካ3&4) ካህኑ ኢያሱ የለበሰው ልብስ ቆሽሾ ነቀፋ ተገኝቶበት በእግዚአብሔር ፊት ከሳሽ ሁኖ ሰይጣን ቆመ ። አሁን ግን ክሱ ስለተዘጋ ከሳሽ ሁኖ አይቆም ለምን ሲባል አሁን ጠበቃው ነው የቆመው ለከሽ መዝገቡ ተዘግቷል አበቃ ካላስ ጠበቃ አለን ።የወንድሞች ከሳሽ ተጥሏል("ራዕ 11) አሁን ከሳሼን ሳይሆን ጠበቃዬን ነው ማስበው ..እዚህ ጋር ማስተዋል ያለብን ዋና ነገር ጠበቃ አለን በማለት በሀጢያት መመላለስን ሳይሆን ጠበቃ አለን ብለን ጠበቃችን ዋጋ ለከፈለበት ክቡር እና ቅዱስ ደም በፅድቅ መኖር ነው ።

ይሔ ጠበቃ ፃዲቅ ነው ። ስራው ትክክል ነው ጠበቃው ፃዲቅ ነው። 


ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
ሁልጊዜ የማስተውለው አንድ ባለ ጋሪ  ነበር ። የፈረሱን አይኖች አራት በአራት በተከረከመ የጄሪካን ቁራጭ   ወደ ጎን እንዳይመለከት አይኖቹን ይሸፍነዋል ። በመሆኑም ፈረሱ ወደ ግራም ሆነ ወደ ቀኝ አያማትርም የፊት ለፊቱን ብቻ እየተመለከ ይጓዛል ።

  ይሔ እውነት በተለይም ክርስቶስ ኢየሱስን አምኖ ዳግም ለተወለደ ክርስቲያን የግድ ግድ አስፈላጊ ነው  ። ወደ ግራም ወደ ቀኝም በሄድንበት በሙሉ አይናችን እንዳንኳትን ፣ ያየነው ሁሉ እንዳያምረን ፣ በመንገድ ሁሉ እየተደነቅን ፣  እየተገረምን እንዳንቆም በአይኖቻችን ዙሪያ የሚከል አንድ ወሳኝ ጉዳይ ያስፈልጋል ፤ እሱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ነው ። የክርስቶስ መስቀል ወደ ሌላ ቦታ እንዳንመለከት ይከልለናል ፣ ሁሉን ጉዳይ ያቀልብናል ፣ የክርስቶስ ፍቅር ፣ ይቅርታ ፣ ምህረት ፣ መወደድ ፣ ፅድቅ ፣ ቅድስና ሁሉ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል ..ያኔ ሁሉ በአይናችን ፊት ይቀላል ፣ እንደምናምንቴ እንድናይ ያረጋል ። የክርስቶስ መስቀል አለምን ፣ ሰይጣን ፣ ሀጢያት ፣ ሞት እንዳናይ የተለያየንበት የእግዚአብሔር የመንግስት ሚስጥር ፣ ፈቃድ ፣ ዕቅድ ፣ ህብረትን እንድንረዳ እና እንድንመለከት ያግዛል ።




@ownkin
@cgfsd
ፀጋ በህይወታችን ፀጋነቱ የሚታወቀው በእኛ በኩል ያለው ድካም በክርስቶስ ስራ በመሸፈኑ ነው ።
          (የዱባ ጥጋብ)


@ownkin
@cgfsd
ስጋውን ቆርሶ ፣ ደሙን አፍስሶ ድግስ የጠራው ጌታችን ኢየሱስ ብቻ ነው ። 

እኔ የህይወት እንጀራ ነኝ በሞቴ ብሉኝ እያለ በተወጋው እጁ ሞቶ ያጎረሰን ጌታችን ኢየሱስ ❤️ ብቻ ነው ።

     (ኢየሱስ)


@ownkin
@cgfsd
(ደሙ ደምግባቴ)


ጌታ ኢየሱስ በምድር በነበረበት ጊዜ አይተነው እንወደው ዘንድ ደምግባት (ውበት) እንዳልነበረው መፀሀፍ ቅዱሳችን ይናገራል። በሰው አይን ምናልባት ሲታይ እዚህ ግባ የማይባል ሊወደድ የማችል ይሆናል ። ያፈሰሰው ደም ግን በእኛ ዘንድ ደምግባት አለው ደሙ ውበታችን ነው ። ደሙ ደምግባታችን ነው !!

በእርግጥም ያለጥርጥር የጌታችን የኢየሱስ ደም ደምግባታችን ነው ምክኒያቱም ደግሞ ለእኛ በፈሰሰው  የክርስቶስ ደም የተተረጎምን ፣ የህይወት ጣዕም ያገኘን ፣ በደሙ የተኳልን ፣ በደሙ የምንፈነድቅ ፣ በደሙ የፀደቅን ፣ በደሙ ያበራል ፣ በደሙ የተከለልን ፣ በደሙ መኖር መኖር የጓጓን የክርስቶስ ደም ፍሬዎች ስለሆንን ነው ።

ከክርስቶስ ደም በላይ ምን ውበት ፣ምን አይነት ትምክት አለን  በእርግጥም ደሙ ደምግባታችን ነው አዎን ደሙ ውበታችን ነው ።

@ownkin
@cgfsd
አስቀድሞ በዙፋኑ ያየኝን መስቀል ላይ አየሁት

            (ያየኝን አየሁት)


@ownkin
@cgfsd
ስለ ጌታ ሳስብ ስቅለቱ ይቀድመኛል፤ የተሰቀለው ስለው የተገኘሁበትን እውነት እና ፍቅር  ያስታውሰኛል ።

የተሰቀለው


@ownkin
@cgfsd
እግዚአብሔር ራሱ በፈጠረው አለም ምስኪን ሆኖ ገባ። ኅጢአት ወዳንኮታኮተው አለም የህማም ሰው ሆኖ መጣ። ዐመፃው ላዳሸቀውና በጠና ህማም ለሚያቃስተው የሰው ልጅ እግዚአብሔር ራሱን ቆረሰ። በባለሙያ አሰቃዮች እጅ በመገረፍ፣ በመዘለፍ፣ በመዋረድ እና በመስቀል በመቸንከር የዚህን አለም ውድቀት ግፍ በደስታ ተጎነጨ። ደሙን አፈሰሰ። ስጋውን ቆረሰ። በስቃዮና በፍዳው መኸል በእግዚአብሔርም ተተወ። በውድቀቱ ከእግዚአብሔር ለተለየው ፍጥረት እግዚአብሔር እግዚአብሔርን ከፈለለት። እግዚአብሔር ለአለሙ ራሱን ሰጠለት። ከጠና ሕመሙ ፍጥረቱን ይፈውሰ ዘንድ አንድ ውድ ልጅ ተቸረው። ሰውን ከውድቀት ሸለቆ ያወጣው ዘንድ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠው።

ትዝ ይለኛል ያ መድኅኔ
በመስቀል ላይ የሞተው ስለኔ
ትውስ ይለኛል የመስቀል ፍቅሩ
ያደረገልኝ ውለታው ሁሉ

"ጥቂት የደም ጠብታ መላውን ዓለም ዐደሰው። በወተት ውስጥ ኾኖ ወተትን እንደሚያጣብቀው ፈሳሽ ደሙ የሰውን ዘር አንድ ላይ አያያዘው።" —ጐርጐርዮስ ዘኢንዚናንዙ (ኒዛናዙ)

Amanuel asegid

@ownkin
@cgfsd
ኢየሱስ ሆይ ትንሳኤህ ሲገባን ከቀድሞ ይልቅ አብልጠን የመስቀሉን ስራ(ሞትህን) ወደድነው ።

@ownkin
@cgfsd
(  እግዚአብሔር ረክቷል )


እግዚአብሔር ቀድሞ በብሉይ ኪዳን ይቀርብ የነበረው የበግ ደም መስዋዕት ለመቀበሉ ሰዎች ማረጋገጫቸው  መብረቅ ወይም ንፋስ ከመስዋዕቱ መቅረብ በኋላ ሲታዩ በእርግጥ እግዚአብሔር መስዋዕቱን ተቀብሏል ብለው ያምናሉ ።

የእኛ መስዋዕት የበግ ደም አይደለም ንፁህ ፣ቅዱስ ፣ ህያው  የሆነው ራሱን አሳልፎ የሰጠው ኢየሱስ ነው ። የቀረበው መስዋትም በመስቀል ላይ ነበር ። እግዚአብሔር ግን በቀረበው መስዋት ተደስቷል ፣ ረክቷል ያኔ የአቤል መስዋዕት አይቶ የቃየልን ሊያይ እንዳልወደደ ሁሉ እግዚአብሔር በኢየሱስ መስዋትነት ብቻ ረክቷል። ለዛም ነው እንደ ብሉይ ኪዳን ነፋስ ወይም መብረቅ አምጥቶ መስዋቱን ተቀብያለሁ ያላለው !!  መቀበሉን ያረጋገጠል ክርስቶስን ከሙታን በማስነሳት ነበር ። እግዚአብሔር የክርስቶስን መስዋዕት መቀበሉን በዛም መርካቱን መደሰቱን ያወቅነው ክርስቶስን ከሙታን በማስነሳቱ ነው ። ትንሳኤ ማረጋገጫ ነው የእግዚአብሔር ርካታ እና ደስታ ።


@ownkin
@cgfsd
እግዚአብሔር ለእኛ ባደረገው የደም ኪዳን ታማኝ መሆኑን ያረጋገጥነው በክርስቶስ ትንሳኤ ነው ።

@ownkin
@cgfsd
በማይነቃነቅ ተስፋ የተሞላ ሰው ምን ይመስላል ??🤔

👇
  በክርስቶስ ትንሳኤ የታወደ ነዋ ።

    (ትንሳኤው ያውዳል )


@ownkin
@cgfsd