1, እግዚአብሔር ሚሲዬናዊ ነው !!"
" እግዚአብሔር አንድ ልጅ ነው ያለው እርሱንም ሚሲዮናዊ ነው ያረገው "
ዴቪድ ሊቨንግስተን
# ልጁም በአባቱ እንደተላከ ተናግሯል ።
ዩሐ 17:18
# እግዚአብሔር ልጁን እና የልጁን መንፈስ ላከ
ገላ4:4-7
2, መፀሀፍ ቅዱስ ሚሲዮናዊ መፀሀፍ ነው ።
" ቅዱሱ መፀሀፍ ሚሲዬናዊ የሆነ ስራ በማስጀመር ይጀምራል በማጠናቀቅ ያልቃል ።"
አንድ ግለሰብ ስልጠና እያሰለጠነ በነበረበት ወቅት ወደ ስልጣኖቹ እንዲህ ይጠይቃል " መፀሀፍ ቅዱስ ሌላ ስም ቢኖረው ምን ተብሎ የሚጠራ ይመስላችኋል ?? ተጠያቂዎቹም ብዙ ከመለሱ በኋላ ጠያቂው ደግሞ እንዲህ በማለት ይመልሳል ....ሚሲዮናዊ መፀሀፍ ወይም የእግዘብሔርን ተልዕኮ የሚባል ይመስለኛል" ።
3, ሚሲዬናዊ አዳም(ሰው)
* ዘፍ 1:28
ብዙ ተባዙ የሚለው ቃል እግዚአብሔር በሰው በኩል ራሱን ለፍጥረቱ ለማስተዋወቅ የሰጠው ትልቅ ሚሲዬናዊ ተልዕኮ ነበር ።
4, ሚሲዮናዊት እስራኤል
" በሐዋሪያው ጳውሎስ አገላለፅ የእግዚአብሔር እስራኤል "ገላ 6:16
እግዚአብሔር አብርሃምን ጠርቶ ከአብርሃም እስራኤልን አዘጋጀ ከእስራኤልም ኢየሱስ መጣ ኢየሱስም ቤተክርስቲያን ሰራ ።
እግዚአብሔር ለሚሲዬናዊ ተልዕኮው እስራኤልን የአህዛብ ካህን እንዲሆኑ ጠርቷል ። ዘፀ 19:6
* ካህን አስታራቂ ፣መካከለኛ ናቸው ስለዚህ እግዚአብሔር ራሱን ከአህዛብ ጋር ለማስታረቅ እና ለማስተዋወቅ እስራኤልን ካህን እንዲሆኑ ጠርቶ ነበር ።
5, ሚሲዮናዊት ቤተክርስቲያን(አካል)
" ቤተክርስቲያን በክርስቶስ መምጣት ተመርቆ በተከፈተና በዳግመኛ መምጣቱ ፍፃሜውን በሚያገኘው የመጨረሻው ዘመን የወንጌል ባላደራ ሆና ተልካለች "
ሰለሞን አበበ ገብረመድን
ቤተክርስቲያን
ክፋፉ ከሆነው አለም የወጣች ክፉ ወደሆነው አለም በሚሲዮናዊነት የተላከች
* ከቤተክርስቲያን ዋና ዋና ባህሪያት መካከል አንድኛው ሐዋሪያዊነት ነው ።
#ሐዋሪያ ማለት የተላከ ማለት ነው።
*ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ማለት ተጠርታ ከወጣችበት አለም መድሃኒት ይዛ የተላከች ናት ።
( #አንፆካዊነት )
ሐዋ13
*አንፆኪያ አህዛብ የሚኖሩባት ከተማ ስትሆን የመጀመሪያው የአህዛብ ቤተክርስቲያን በዛው ይገኝ ነበር ።
*የእየሩሳሌም ቤተክርስቲያን ለሚሲዮናዊነት ወደ አህዛብ ባላከችበት ጊዜ የአንፆኪያ ቤተክርስቲያን የሚሲዮናዊ በመላክ ወንጌልን ለማድረስ ቀዳሚ ቤተክርስቲያን ናት ።
#የአንፆኪያ ሚሲዬናዊ አላላክ አካሄድ
ሐዋ 13_1:5
1,በእውነተኛ አምልኮ፣በህብረት፣በፆም ፀሎት መትጋት
2, ለመንፈስ ቅዱስ ምሪት መታዘዝ
3, ለሚላኩ ሚሲዮናውያን መፀለይ
4, ሚሲዮናውያን መላክ
#የአንፆኪያ ሚሲዮናውነት ውጤት
* 1ኛ፣2ኛ እና 3ኛ ሐዋሪያዊ ጉዞ
* 3ቱ ሐዋሪያዊ ጉዞ በጳውሎስ በርናባስ እና በሌሎች ወንድሞች መካከል የተደረገ ጉዞ ነው ።
#በእነዚህ ጉዞ ውስጥ
_ 3 አህጉር ወንጌል ደርሷል
_ ለሚሊዮኖች ወንጌል መስማት ምክኒያት ሁኗል
_ በመፅሀፍ ቅዱሳችን አንዳንድ ደብዳቤ ለመፃፍ ምክኒያት ሁኗል ምሳሌ :- ገላቲያ፣ኤፌሶን፣ቆሮንቶስ ፣ተሰሎንቄ በጥቂቱ ተጠቃሽ ናቸው ።
# የአቂላ እና ጵርስቅላ ሞዴል
* አቂላ እና ጵርስቅላና ባል እና ሚስት ሲሆኑ ቀድሞ ከሮም ክርስቲያኖች በስደት የተመለሱ ቅዱሳን ናቸው ።
* በተለይ የሚታወቁት ከሐዋርያው ጳውሎስ ጋር በመሆን ድንኳን እየሱፉ ወንጌል በማድረሳቸው ነው ። በኤፌሶን ላሉት ቤተክርስቲያን በረከት ሁነዋል ፣ አጵሎስ የመሰለ ሰው ለወንጌል ብቁ በሚያረገው መንገድ የእግዚአብሔር መንግስት ገልጠውለታል (ሐዋ18:24)
ድንኳን በመስፋት (professional evagelism) በንቃት ባሉበት ቦታ እና የስራ መስካቸው ወንጌል ለመስራት ተንቀሳቅሰዋል ።
✍ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd

ኢሳይያስ በራዕይ ያየው፤ ደግሞም ከአራቱ ወንጌላት ምስክርነት እንደምንረዳው ያ ስቁይ አገልጋይ በርግጥም መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም። መምህር የነበረ ቢሆንም ከተማሪዎቹ አትለዩትም። ጌታ ቢሆንም ከተከታዮቹ የተለየ መቀመጫ እና ልብሰ ተክህኖ አልነበረውም። ፊቱ እንደ ተከታዮቹ ሁሉ ኑሮ ያደቀቀው አይነት፤ የስራ ጫና ያስረጀው አይነት፤ ኃላፊነት እና የቤተ ሰብ ሸክም ያጠቆረው አይነት፤ ... እና ብዙ። ነገር ግን እንዲህ ያለው ፊት "እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ..." የተባለለት አብ ራሱን ይገልጥ ዘንድ የመረጠው ፊት፤ በክርስቶስም መልክ በፈሰሰው ብርሃን የክብሩን እውቀት ያሳይበት ዘንድ የሾመው አስደናቂ ፊት ነው። በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት እግዚአብሔር አብን እና የተገለጠ ክብሩን እናይበት ዘንድ ችለናል። ክብር ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ ይሁን።
https://t.me/En_Light_enment
https://t.me/En_Light_enment
Telegram
My_Damascus#የእኔደማስቆ
የእግዚአብሔር ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ እንዲገለጥልን ያለ ልክ መንፈስ ቅዱስን መውደድ እና መፈለግ፤ በመንፈስ ቅዱስ የተገለጠልን የእግዚአብሔር ክርስቶስ ህይወታችን እንዲሆን እና ህይወቱን በሙላት በእኛ እንዲገልጥ በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ቅዱሳት መጽሐፍትን መመርመር እና መረዳት፤ የእግዚአብሔርን ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ ለመረዳት ከሚተጉ እና ከተረዱ ቅዱሳን ወንድሞች ጋር ህብረት ማድረግ......
ሐዋ 8:27-35👉......ፈዘዝኩኝ በዚህ ቃል🙆....አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር...ያዉ ሰግዶ ሲመለስ የኢሳይያስን መጽሐፍ ከፍቶ ያነባል የሚያነበዉ ክፍል👉ሐዋርያት 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³² ያነበውም የነበረ የመጽሐፉ ክፍል ይህ ነበረ፤ እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፥ የበግ ጠቦትም በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።
³³ በውርደቱ ፍርዱ ተወገደ፤ ሕይወቱ ከምድር ተወግዳለችና ትውልዱንስ ማን ይናገራል?......ሰዉዬዉ ቀድሞ ከፍቶ እያነበበ እየቆየበት የነበረዉ ክፍል #መንፈስ ቅዱስ እንዲቆይበት የሚፈልገዉ ጉዳይ ነበር.....ለዛም ነዉ ነገር ወደ #መብራራትና ወደ #መገለጥ እንዲመጣለት ፊሊጶስን የሰደደለት.....የኢየሱስ መስቀል፣ ሞትና ትንሳኤ #መንፈስ #ቅዱስ እንዲገባን የሚፈልገዉ ጉዳይ ነዉ....ብዙ ይብራልን🙌
Barbi

ለእግዚአብሔር ፀጋ አደራ መሰጠት
ከአጣልያም፣ እስካሁን ላከናወኑት ሥራ፣ ለእግዚአብሔር ጸጋ በዐደራ ወደ ተሰጡባት ከተማ ወደ አንጾኪያ በመርከብ ተመለሱ።
በዚያም ከደቀ መዛሙርት ጋር ብዙ ጊዜ ተቀመጡ።
ሐዋርያት ሥራ 14:26, 28
ጳውሎስ እና በርናባስ በሐዋሪያት ስራ ምዕራፍ 13 ላይ ለወንጌል ተልዕኮ ተለዩ ። የአንፆኪያ ቤተክርስቲያን ጳውሎስን እና በርናባስን በመፀለይ ወንጌል ወደሚሰሩበት ቦታ ላኳቸው ። እነ ጳውሎስ በፀሎት ተላኩ ።
በጳውሎስ እና በርናባስ መላክ ውስጥ ፀሎት አስፈላጊ ጉዳይ ነበር ። ለእነርሱ መፀለይ ለምን አስፈለገ ? ለእግዚአብሔር ፀጋ አደራ ለመስጠት ነው ። ለምትፀልዩላቸው ሰዎች ይሔን ማወቅ ይኖርባችኋል ስትፀልዩላቸው ለእግዚአብሔር ፀጋ አሳልፋችሁ እየሰጣችኋቸው ነው ። ፀጋው ይደግፋል ።

(ከዙፋን እስከ መስቀል )
..... ወልድን ፍቅር ሳበው ከሰማይ ሀገሩ
ዘማሪ ቴዎድሮስ
የሆነ አንድ ገመድ አለ ። ለዘመናት የኖረ ርዝመት ቢሉት አረዛዘሙ ጥንካሬ ካሉ ጥንካሬ ያለው ፤ይሔ ገመድ ክርስቶስን ከዙፋን እስከ መስቀል ድረስ የጎተተው ገመድ ነው ። ባጭሩ ፍቅር ነው !
ክርስቶስ ከዙፋን እሰከ መስቀል ድረስ የጎተተው ገመድ ፍቅር ነው ። ሌላስ ታዲያ ምን ሊሆን ??
ኢየሱስ እኛ ወደ አለንበት ለመምጣት ተስቧል ተጎትትቷል ራሱን እንካችሁ ሲል አቀብሏል የአባቱን ፈቃድ በመከወን ውስጥ በፍቅር ተጎትቷል ። ከክርስቶስ በላይ ፍቅር ግድ ያለው ማን ነው?? መፀሀፍ ቅዱስ ፍቅር ግድ ይበላችሁ ይለናል በመጀመሪያ ግን ፍቅር ግድ ሲል ያየነው ክርስቶስን ነው እሱም መስቀል ላይ ።
የጥንት አባት የነበሩት አውግስጢን የክርስቶስ መስቀል እግዚአብሔር ፍቅሩን ለአለም የሰበከበት ፑልፒት ነው ይላሉ ። እውነት ነው እንደውም የእግዚአብሔርን ፍቅር የመስቀሉ ስብከት ብለን ብንጠራ የተሻለ የሚገልፀው ይመስለኛል ። መለኮት ፍቅር ለማስረዳት ከመስቀል የተሻለ ስፍራ እንደሌለ አሳይቷል አስገንዝቦናል ።
ኢሳያስ አሉ ከሚባሉ ጉምቱ ቀደምት ነቢያት አንዱ ነው ። በብሉይ ኪዳን ከትንቢት መፀሃፍ መካከል ቀድመን ከምናገኘው መፀሀፍት አንዱ ሲሆን ረጅም ምዕራፍ ያለው መፀሃፍም ነው ። ምናልባት በሶስት ነገስታት ዘመን ሳይኖር አልቀረም። በመጀመሪያ የአገልግሎት ምዕራፎቹ በቁጠኛ መልዕክቱ ይታወቃል አንድ ቀን ግን ባልለመደው መንገድ እና ባልገባው ሁኔታ እግዚአብሔር ተገለጠለት ። (ኢሳያስ 6)
እግዚአብሔርን በረጅም እና ከፍ ባለ ዙፋን አስተዋለ ከማስፈራቱ እና ከግርማው የተነሳ ለራሱ ወዬልኝ ይል ጀመር መላዕክቶች ራሳቸው በዚህ አምላክ ፊት በሁለት ክንፍ ፊታቸውን በሁለት ክንፍ እግራቸው በሁለት ክንፍ ይበራሉ ያመሰግናሉ ። ኢሳያስ ያየው እግዚአብሔር በዙፋኑ እንዳለ አስደመመው አስገረመው አስፈራው ። በዙፋኑ ያየው እግዚአብሔር ውበቱ የሚያስደንቅ ፣ ባለግርማ ሞገስ መላዕክት ሽርጉድ የሚሉለት ፣ ቅድስናው ልብን የሚሰርቅ ባየው ጊዜ ወዮልኝ እያለ ወደራሱ እንዲመለከት ማንነት ልዩ የሆን እግዚአብሔር በዙፋን ላይ ተመለከተ ።
ሆኖም ግን ኢሳያስ ሌላ ከፊተኛው በተቃራኒ የሚያስገርም ነገር ተመለከተ ያ በግርማ በረጅም ዙፋን በከፍታ ያለው መላዕክቱ በፊቱ ሽርጉድ የሚሉለትን እግዚአብሔር ባለተለመደ መልኩ በ53ተኛው ምዕራፍ አየው ፤ የሚያየው አምላክ አሁን ግን የህመም ሰው ደዌን የሚያውቅ በሸላቾቹ ፊት እንደሚታረድ በግ የሚነዳ አይተውት ይወዱት ዘንድ ደምግባት የሌለው ...እንዴት አይነት ነገር ነው ።በዙፋን ያየውን እግዚአብሔር በመስቀል ላይ አየው ። ባለ ዙፋኑ ባለ መስቀል ፣ ባለሞገሱ እግዚአብሔር የህማም ሰው ፣ መላዕክት በፊቱ ሊያዩ ሳይሞክሩ ፊታቸውን የሚሸፍኑለት አይተነው እንወደው ዘንድ ደም ግባት አልባ እንደሆነ ሲታይ፣ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሚባልለት ስቀለው ስቀለው ስለቀው ሲባል እያየ ኢሳያስ ከመደነቅ መበቀር ምን ሊያደርግ ይችላል ? ኢሳያስ ይሔን ሲያይ ፍቅር ብቻ ብሎ የሚዘጋው ይመስለኛል ።
በዙፋን የታየው ኢየሱስ በመስቀል ታየ እነዚህ የማይገናኙ ደረጃዎች ምንስ አገናኛቸው ?ምንስ አጋጣማቸው? ምን አያያዛቸው? 👉 ፍቅር! ብቻ ከዙፋን እስከ መስቀል ኢየሱስሰን የጎተተው ፍቅር ነው ።በትልቅነቱ እና በልግስናው የሚያስደነግጠው መለኮት የሆነው እግዚአብሔር ወልድ ወደ የሰው ልጅ መንደር ንቀት በማያቀው ቅርበቱ ከላይ ወደታች የሰው ህማም ሊካፈል ራሱን ቆረሰ ። ኢየሱስ ክርስቶስ ከዘላለማዊ የእግዚአብሔር ፍቅር ጋር አነካካን ። አለም ሊሸከመው ማይችለውን ፍቅር ኢየሱስ በመስቀል ላይ ገለጠው ።
✍ ፊሊሞን ነጋ

(ከመስቀል እሰከ ዙፋን )
ዩሀንስ ኢየሱስን ሁሉን ትተው ከተከተሉት በእድሜ ወጣቱ ደቀመዝሙር ነበር ። ጌታ ይወደው የነበረ ደቀመዝሙር ተብሎ በወንጌላት ደብዳቤ ላይ ሰፍሯል ። በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን በተለይም ኢየሱስ በነበረበት እና ወደ አባቱ ቀኝ ካረገም በኋላ ዩሀንስ ኢየሱስ እስኪመጣ ድረስ አይሞትም ተብሎ ወሬ ይናፈሳል ምክኒያቱ ደግሞ ዩሀንስ ከሁሉ ሐዋሪያት ይልቅ በእድሜ አርጅቶ እንደሚሞት የተናገረውን ትንቢት በተሳሳተ መልኩ በመተርጎማቸው ነበር ። ሆኖም ዩሀንስ ከሁሉ ሐዋሪያት ወንድሞቹ በኋላ ረጅም ዘመን የቆየ በመጨረሻም ወደ ጌታ የተሰበሰበ ደቀመዝሙር እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ ። በአዲስ ኪዳናን መፅሀፍት መካከል 5 ደብዳቤዎች በመንፈስ ቅዱስ ምሪት አበርክቷል ። እነዚህ ሶስት ደብዳቤ፣ አንድ የወንጌል መፀሀፍት እና የትንቢት ደብዳቤው ፅፏል ። ዩሀንስ ከሐዋሪያት መካከል በተሻለ መልኩ የመስቀሉ ህያው ምስክር ነው ውስጥ ድረስ ገብቶ በጥልቀት ስቅለቱን ሲከታተል በቅርበትም ሲመለከት ነበር ። ኢየሱስም እናቱን ማርያም በአደራ መልክ ሰጥቶታል ። በዩሀንስ ወንጌል ውስጥ በስፋት የተዘገበው የኢየሱስ ሞት እና ትንሳኤ ነው በተለይ ረጅም ምዕራፍ የሚይዘው ከመስቀሉ በፊት ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ እራት በአንድነት በበሉበት ጊዜ ጌታ ያስተማራቸው አስደናቂ ትምህርቶች ናቸው ።ዩሀንስ የኢየሱስ የመስቀል ገድል በእጁጉ የሚማርከው የጌታ ተከታይ እንደሆነ ከመፀሃፍ ቅዱሳችን እንመለከታለን ። እርሱ በነበረበት ዘመን የሮም ቄሳር እንደ አምላክ ይታይ ስለነበር እንደ ዩሀንስ ያሉ ሰዎች ደግሞ ለቄሳር አይመቹም ። በርካታ ስቃይ ከሮሜ ወታደሮች ደርሶበታል በስተ ሽምግልና በዘይት ተቀቅሏል ይሙት ተብሎ ፍጥሞ ደሴት ተጥሏል ። በእዛ አስቸጋሪ ሰአት ውስጥ በደሴት ውስጥ እንዳለ ግን በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርኩ ይላል ።በጌታ ቀን በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያውን ቀን ማለትም እሁድን ክርስቶስ ከሙታን የተነሳበት ቀን እንደሆነ ስለሚታሰብ የጌታ ቀን ተብሎ ይጠራል ። በጌታ ቀን ሲል ትንሳኤውን እያሰበ ነው ፤ በእዛ ቀን ላይ የክርስቶስን ትልቅ ገድል በመንፈስ ሁኖ ያስብ ነበር ። ዩሀንስ ይሔን በሚያስበብበት ጊዜ ኢየሱስ ከሞቱ እና ትንሳኤው በኋላ ወደ ሰማይ ካረገ ወደ 60 አመት ገደማ ይሆናል ። ዩሀንስ ኢየሱስ ካረገ ከ60 አመት በኋላም የክርስቶስ ፍቅር በልቡ ትኩስ እንደሆነ ያሳብቅበታል አሁንም የመስቀሉን ስራ ያሞካሻል ርዕስ አልቀየረም አሁም ለዩሀንስ ጌታ የሰራው ስራ ህያው ነበር ። በተጣለበት የፍጥሞ ደሴት ውስጥ በመንፈስ እንዳለ አንድ አስደናቂ ራዕይ አየ ። ያየው በፊት የተከተለው የነበረው እስከ መስቀል የሚያውቀው የህማም ሰው የነበረውን ኢየሱስ ክርስቶስን በይበልጥ ከሚያውቀው የመስቀል ስቃዩ በተለየ መልኩ ባለ ግርማ ፀጉሩ እንደ በረዶ ፣ አይኖቹ ነበልባል ፣ እግሩ ከጋለ ነሃስ ይልቅ የነገጠረ፣ ደረቱን በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ፣ ከአፉ ስለታም ሰይፍ የሚወጣለትን ኢየሱስ አየ ። በፊት በመስቀል ላይ ደረት እየተደቃ አይዞህ የሚባልለትን አሁን ደግሞ በታየ ጊዜ በእግሩ ስር ግርማው እንደሞተሰው የሚያዘርረውን ተመልክቶ በእግሩ ስር እንደሞተ ሰው ተደፋ ። ከመስቀል ወደ ዙፋን ተመለከተ ።
የነብዩ ኢሳያስ እና የሐዋሪያው ዩሀንስ ወግ ይሔ ነው ኢሳያስ ከዙፋን ወደ መስቀል አየው ፤ ዩሀንስ ከመስቀል ወደ ዙፋን ተመለከተው ። አንድነገር ግን እውነት ነው ኢየሱስ በዙፋኑም እግዚአብሔር ነው ፣ በመስቀሉም እያለ እግዚአብሔር ነው ። መስቀሉ የዙፋን ውበት አልደበቀውም በመስቀል ተንጠልጥሎ ከዙፋኑ አልጎደለም ፣ መንበሩ ከእሱ አልሸሸም ይልቁን በመስቀሉ ውሎ ዙፋን ለሁሉም አስረገጠ የማይነቃነቅ ዙፋን እንዳለው በትንሳኤው አጅቦ ለመስቀሉ ጅግነቱ ምስክርነትን አቆመ ። ከዙፋን እሰከ መስቀል የመጣበት ርቀት ከመስቀልም እሰከ ዙፋን የሄደበት ልብ ስለ ፍቅር፣ ርህራሄው፣ ምህረት፣ በጎነት ፣ ማዳን ፣ ፅድቅ ፣ እውነተኛ ፍቅር ነው ።

ስምህ
@Protestant_song
. ስምህ
°°°°°°°°°°
ዘማሪ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህብረት መዘምራን
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
#Live_Worship
@protestant_songs

(ክርስቶስን በልብ ማኖር)
ሐዋሪያ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች ከፀለየላቸው ፀሎት ውስጥ እንደዚህ የሚል አንድ ሀሳብ አለ "ክርስቶስ በእምነት በልባችሁ እንዲኖር (ኤፌሶን 3:17) " ጳውሎስ ክርስቶስ በልባቸው እንዲኖር በእስር ቤት ሁኖ ይፀልይላቸዋል ። ነገር ግን የሐዋሪያውን ፀሎት በጥንቃቄ ስንረዳው ክርስቶስ በልባቸው እንዲኖር ከመፀለዩ በፊት በምዕራፍ 1 ላይ የፀለየላቸው ሌላ ፀሎት ነበር ።የመጀመሪያው ፀሎት ክርስቲያኖች በክርስቶስ እንዳሉ እንዲረዱ ይፀልያል ።በክርስቶስ ማለት ክርስቶስ ውስጥ ማለት ነው ። አንድ ኢየሱስን እንደግል አዳኝ አርጎ የተቀበለ ሰው በክርስቶስ ውስጥ አለ ።በክርስቶስ ማንነት ውስጥ ተጠቅሏል ማንነቱ በደሙ ጥላ ስር ፣ በትንሳኤው ሃይል ውስጥ ተሸፍኗል ። ክርስቶስ በአብ ቀኝ ተቀምጧል አማኝም በክርስቶስ ውስጥ የተዋጀ ስለሆነ በክርስቶስ ሁኖ በአብ ቀኝ አለ ። በአጭሩ አማኝ በክርስቶስ ልብ ውስጥ አለ ። ክርስቶስ በኤፌሶን ሰዎች ልብ ውስጥ በእምነት እንዲኖር ጳውሎስ ከመፀለዩ በፊት የኤፌሶን ሰዎች በክርስቶስ ልብ ውስጥ እንዳሉ እንዲያውቁ ፀልዪል ። የሚገርም እውነት ለካ በክርስቶስ ልብ ውስጥ አለን ፣ ክርስቶስ እኛን ወርሶናል ፣ ክርስቶስ ለእኛ ትልቅ ቦታ አለው በልቡ አስቦናል ። እኛ በክርስቶስ ልብ ውስጥ አለን ። የጳውሎስ የመጀመሪያው ፀሎት ይሔ ነው አማኝ በክርስቶስ ልብ ውስጥ እንዳሉ እንዲረዱ ሁለተኛው ፀሎት ደግሞ ክርስቶስ በእምነት በልባቸው እንዲኖር ። ዘወትር ኢየሱስ በልባችን በእምነት እንዲኖር የምንፈልግ ከሆንን ይሔን እምነት መለማመድ ከወደድን በመጀመሪያ እኛ በክርስቶስ ልብ ውስጥ ያለንን ስፍራ መረዳት ይኖርብናል።
ክርስቶስ በልቡ አኑሮን በልባችን ሊኖር ወዷል ። ልብን የወደደ የልብ አምላክ !!