"ቤተ ክርስቲያን ቴአትር ቤት፣ እኛም ኮሜዲያን ሆነናል!"
ብዙ አማኝ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣው ለመዝናናት ነው። ሌላውም ሰው ጆክ ሲያምረው፣ መሳቅ ሲፈልግ የእኛን ቪዲዮዎች ነው የሚያየው። በኢየሱስ ስም፣ በልሳን፣ በጸሎት ከት ከት ብሎ ይስቃል። እኛም አብረን እንስቃለን። ምንም ስለማይመስለን ቪዲዮውን እየተቀባበልን እንስቃለን። የእግዚአብሔር ስም መቀለጃ ስለሆነ የሚያየው አይፈራው፣ የሚሰማን አይፈራው። እኛም አላከበድነው በሚገባ አላሳየነው፣ አልገለጥነው፣ አላመጣነው...።
የአብዛኞቻችን አገልጋዮች ዓላማ ራሱ ሰውን ማዝናናት ነው፤ "ምን ብናገር አዝናናዋለሁ ነው።" የብዙ ምዕመናን የቤተ ክርስቲያን፣ የስብከትና የአገልግሎት ምርጫ "የት ብሄድ ያልተካበደ ነገር እሰማለሁ"፣ "መዝናናት አገኛለሁ" የሚል ነው። ቤተ ክርስቲያን ቴአትር ቤት፣ እኛም ኮሜዲያን ሆነናል።
ተዉ እንጂ ብዙም ሩቅ ባልሆኑ ዓመታት፣ የዛሬ ሰልሳ ዓመት ወደ ኃላ "ሪዋይንድ" ብታደርጉ አማኞች የሚፈራ ምገስ ነበራቸው። ሰዎቹ ዛሬም በሕይወት ስላሉ ሄዳችሁ ጠይቋቸው። በቤተ ክርስቲያናቸው ደጃፍ ማለፍ እንኳ ያስፈራ ነበር። ሕይወታቸው ግርማ ነበረው። መልዕክታቸው አስደንጋጭ ነበር። ለማስደንገጥ ብለው ሳይሆን እግዚአብሔር በመካከላቸው ነበር።
እዚያ ለመቀለድ አትሄድም፤ ንሰሐ እንጂ ጆክ ትዝ አይልህም። አጋንንት ይወጣል፣ ሰዎች ይፈወሳሉ። የእግዚአብሔር ቃል፣ የክርስቶስ ወንጌል ይሰበካል። ይኼ ሁሉ የሚሆነው ፐርፌክት [ፍጹማን] ክርስቲያኖች ስለሆኑ አይደለም። ግን የኢየሱስን ስም አስከባሪዎች ነበሩ።
አሁን ቢያንስ ስሙ በሆነ መንገድ ይከበር ዘንድ ብንጸልይስ? ቢያስፈልግ ኮሜዲያኖቹን በጊዜ ቢወስደን፤ ይኼም እኮ አንዱ መንገድ ነው። ወይም ደግሞ ጥግ አስይዞን የሆኑ ሌሎች ሰዎች ቢያመጣ፣ እኛ ዕድሉን አልጠቀም ስላልን ሌላን ትውልድ ቢያስነሳልን፣ ስላላየናቸው እንጂ እግዚአብሔር ስሙን የሚያስከብሩለት ልጆች አሉታ!...
በዚህ ዘመን ወንጌል የምንሰብክበት ብዙ መድረክ አግኝተን፣ ሚዲያ ተመቻችቶልን አልተጠቀምንበትም። በየሰዉ ቤት የጌታን ስም ተሸክመን ለመግባት እንደዚህ ዘመን ዕድል ተሰጥቶን ያውቃል እንዴ? እኛ ግን ጆካችንን ይዘን ገባንበት፤ እግዚአብሔርን መሳለቂያ አደረግነው። ስለዚህ ወገኖቼ በአሕዛብ መካከል የተነቀፈው ማንነቱ የቀለለው ስሙ መልሶ እንዲከብድ በየትኛውም መንገድ ምክንያት ለመሆን መጸለይ አለብን።
ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ

የእግዚአብሔር ልጅ ክፍል አንድ
<unknown>
ይሔ ድንቅ መፀሃፍ ነው በትረካ ብትሰሙት ታተርፋላችሁ ። ኢየሱስን በተመለከተ አስደናቂ ስራ ነው ። የኢየሱስ ማንነት ለፈለገ እጅግ ግሩም መፀሀፍት ነው ።
@cgfsd
@cgfsd
ኢየሱስን መውደድ የአንድ ጊዜ ውሳኔ ወይም ስሜት አይደለም።
ኢየሱስን መውደድ በየቀኑ በየሰዓቱ በየደቂቃው የምመርጠው ምርጫ ነው።
ለኢየሱስ ፍቅሬን ምገልጥለት እና ማሳየው በእያንዳንዱ ቀን እና ጉዳይ ላይ በምወስነው ውሳኔ ነው።
ለምንድንነው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ፍላጎት ብቻ ምታደርገው?
*ኢየሱስን ስለምወደው!!
ለምንድነው የራስህን ፈቃድ እና ፍላጎት ማታደርገው?
*ኢየሱስን ስለምወደው!!
ለምንድነው ለአባትህ ደስታ እና ሳቅ እንደዚህ ምትጨነቀው?
*ኢየሱስን ስለምወደው!!
ለምንድነው ደስ እንዳለህ ማትኖረው?
*ኢየሱስን ስለምወደው!!
ስለምወደው ስለምወደው
ጌታ ኢየሱስን ስለምወደው
ለክርስቲያን ለምን ተብሎ ሲጠየቅ እጅግ ውብ የሆነ ምክንያቱ "የወደደኝን ኢየሱስ ስለምወደው ነው" ነው።
* ኢየሱስን ስለምወደው

Forwarded from HUFELLOW
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ውድ የፌሎአችን ልጆች እንዴት ናቹ?
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
እነሆ አዲስ ነገር ይዘንላችሁ መጥተናል በፌሎአችን ኳየር የተዘጋጀ ስምህ የሚል ርዕስ ያለው የመዝሙር clip በቅርብ ቀን ይዘን እንቀርባለን!!! Stay tuned
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
Excited!! 💯
ስምህ | Hufellow choir new Gospel music video
View - Like - share
@HUfellow
#share_to_others

"ዓለት በቡጢ አይፈርስም፤ ውሃ ምንም ሽቅብ ቢፈስ ሰማይ አይደርስም። ሰው የቱንም ያህል ብርቱ ቢሆን ተራራ በሩጫ አይወጣም። እንዲሁ በሰው አንደበትና አዕምሮ በመስቀል በኩል ስለተገለጠው የክርስቶስ ጸጋ መግለጥ ከባድ ዳገት ነው። የተናገርንለትና የገባን ሁሉ ልኩ አይደለም። እርሱ ከቃላችን ሩቅ ነው። ከመረዳታችንም ብርቱ ነው። ስለ እግዚአብሔር በጣም ከተረዳን የሚገባን እንደማናውቀው ነው። በጥቂቱ ሲበራልን ቃል እስክናጣ እንገረምበታለን።
ኢየሱስ ማንነቱ ራሱ ነፍስን ውጥረት ውስጥ የሚከት ጥያቄ ነው:: የህያዋን ሁሉ ምንጭ ነው ነገር ግን ሞቶ ያውቃል። ሺህ ዘመን የአይን ሽፋሽፍት ከድኖ እንደመክፈት ያጠረለት ጌታ የጌተሰማኔ መንገድ እንደ እልፍ ዘመን የረዘመበት ስቁይ ነው።
እንደ ሰንጴር የደመቀ ደግሞ እንደ ባርያ የተዋረደና በደም የወዛ መልከ ጥፉ ነው። ዙፋን ላይ የሚያምር ጀብደኛ ንጉስ፤ ነገር ግን መስቀል ላይ ደም ግባት የሌለው ደካማ፤ ከተመሰከረበት ወንበዴ ጋር አብ የእኔን በደል በእርሱ የመሰከረበት ወንጀለኛ ነው። እንደ ማንኛውም ወንበዴ የተሰቀለ ከማንኛውም ፃድቅ ይልቅ ግን የፀደቀ ነው። ያ በውርደት ሞቶ በክብር የተነሳ ጌታ የኔ ጌታ ነው።
ኢየሱስ መልስ ለሚያገኙ ሁሉ ህይወት የሚሰጥ ጥያቄ ነው።"
#ከመጽሐፉ የተወሰደ።
በMelkamu Asfaw የተጻፈ "የጸጋው ዙፋን: የትሩፋን ምህረት እና ሕይወት" የተሰኘ፤ በስምንት ምዕራፎች እና ፫፺፶ በሚጠጉ ገጾች የተዘጋጀ አዲስ መጽሐፍ በቅርብ ቀን።

የመስቀሉን ነገረ ድኅነታዊ ፈይዳ መገንዘብ እና መታመን እንጂ በጎልጎታ ተገኝቶ ስቅለቱን በዐይነ ሥጋ መመልከት በራሱ ጥቅም የለውም።
ሔኖክ ኢሳያስ
ሔኖክ ኢሳያስ
ርዕስ:- መስቀል ላይ ነው።
————————
የክርስቶስ ቤዝዎታዊ ሥራ የተፈጸመው መስቀል ላይ ነው። ክርስቶስ ጌታችን የሰውን ዘር የዘመናትን ቀንበር የሰበረው፣ የዕዳን ጽሕፈት የደመሰሰው፣ ከሳሹን ዲያቢሎስ ያዋረደው፣ ሰይጣን የሽንፈትን ካባ ለብሶ የተሰናበተው፣ ለሕዝቡ ነጻነትን ያወጀው መስቀል ላይ ነው። በኢየሩሳሌም መቅደስ ውስጥ አልነበረም። ከምኩራቦች በአንዱ ውስጥም አልነበረም። ከእጁ የበሉት “ከርሱ ጋር አልነበርንም… ከቶም አናውቀውም” ብለው ርቀው በቆሙበት በዚያ ሥፍራ የከበቡት በሸሹበት፣ የቀረቡት በራቁበት፣ የተከተሉት በከዱበት ሥፍራ መስቀል ላይ ነው። ጭብጨባም አድናቆትም ሙገሳም ውዳሴም ባልነበረበት ሰማይ ምድሩ በጨለመበት የብቸኝነት ሥፍራ መስቀል ላይ ነው።
ጌታችንና መድኃኒታችን ክርስቶስ ኢየሱስ ዕውሮችን ሲያበራ፣ የተራቡትን ሲመግብ፣ ለምጻሞችን ሲያነጻ፣ ጎባጣዪቱን ሲያቀና በነበረበት ሥፍራ እንዳይመስለን። ወቅታዊ ጥያቄዎችን በመለሰበት፣ ተከታዮቹ ስሜታቸው በተነካበት፣ ተገልጋዮች ሁሉ በደስታ በፈነጠዙበት ሥፍራ ላይ አልነበረም። ጌታችን በጥብሪያዶስና በገሊላ አካባቢዎች ሲመላለስ ወይም በቅፍርናሆምና በናዝሬት መንደሮች ሲዘዋወር እንዳይመስለን። ዳሩ ግን እርቃኑን በሰማይና በምድር መካከል በተንጠለጠለበት የእሾህ አክሊል በተጎነጎነለት፣ መራራ ጽዋ በጎነጨበት፣ በፈጠራቸው ሰዎች እጅ በምስማር በተወጋበት በዚያ ጎልጎታ በተባለው ሥፍራ በዚያ ኮረብታ በቀራኒዮ መስቀል ላይ ነው።
በቃና ዘገሊላ ሠርግ ቤት የደጋሾችን ገመና በሸፈነበት፣ ውሃቸውን ወይንጠጅ ባደረገበት፣ ተከታዮቹን ባስደመመበት፣ ታዳሚዎችን ባስጨበጨበበት፣አሳዳሪውን ባስገረመበት ሥፍራ አልነበረም ክርስቶስ ለዓለም “ተፈጸመ”ን ያበሰረው። ሺዎችን በመገበበት ከርሳቸውን አጥግቦ ተዓምር ሠራ በተባለበት፣ ርህራኼውን በገለጠበት ሥፍራም አልነበረም። በደብረ ዘይት ተራራ መልኩ በተለወጠበት ክብሩ በታየበት ጴጥሮስ “እዚህ መሆን ምርጫችን ነው” ባለበት በዚያ ሥፍራም አልነበረም። ወደ ምድር የመጣበት ዓላማው ግቡን የመታው ከነዚያ ሥፍራዎች በየትኛውም ሳይሆን ክርስቶስ ጌታችን “ተፈጸመ” ያለው መስቀል ላይ ነው። መስቀል ላይ ነው።
መስቀል አልባውን የቃና ዘገሊላ ክርስትና፣ መስቀል አልባውን የዓሳና የዳቦ ክርስትና፣ መስቀል አልባውን የምቾትና የስኬት ክርስትና መስቀል አልባውን የጭፈራና የዘንባባ ዝንጣፊ ክርስትና ሰይጣን አያሳድደውም። መቼም አይቃወመውም። ከቶም አይጠላውም። ለምን ብሎ? አጃቢው ብዙ ነው። አጨብጫቢው አሸን ነው። ክርስቶስን ከምንም በላይ በዚህኛው ውለታው የምታውቁ ተሰዳጆች ሆይ ደስ ይበላችሁ። የእኛ እምነት መሠረቱ ይኼ ነው የኛ ስብከት መሠረቱ ይኼ ነው። “በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው። እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል።” (ቆላ. 2:14) ቆላስይስን አንብቦ ሲያበቃ ስለ ግንብ ቤት፣ ስለ መርሰዲስ መኪና ስለ ባንክ ቡክ የሚናገር ሰባኪ ክርስትናው የክርስቶስ ይደለም።
በመሆኑም ፊታችሁን አይተን የማንቀይረው መልዕክታችን፣ ለስሜታችሁ መኮርኮር ብለን የማናቀርበው ትምህርታችን የተሰቀለው ክርስቶስ ነው። የቀደሙን የርሱ አገልጋዮች “ምሰሉን” ያሉን ሐዋርያቱ ከክርስቶስ በቀር ሌላ ላለማወቅ የቆረጡቱ ወንድሞቻችን ስብከታቸው ትምህርታቸው ትምክህታቸውም የተሰቀለው ክርስቶስ ብቻ ነበር። “ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።” (ገላ. 6:14) ብለዋል። እኛም ያንን መስመር አጥብቀን ይዘናል። ቁም ነገሩ ያለው መስቀል ላይ ነው። በተሰቀለው ነው። The cross, then the crown!
Workneh