ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሰው ልጅን የሀጢያት እዳ ዋጋ የከፈለው ለማን ነው? ለሰይጣን ወይስ ለእግዚአብሔር ?
Forwarded from My_Damascus#የእኔደማስቆ (Ariel Esther)
የንግሥና ልብስህ በደም የጨቀየ፤ የእሾኽ አክሊል የደፋህ፤ ዙፋንህን መስቀል፤ መናገሻ ከተማህን በጎልጎታ ተራራ ላይ ያደረክ አንተ ንጉሤም፤ ጌታዬም ነህ። ኢየሱስ ክርስቶስ።
ኢየሱስ የእውነተኛዋ ድንኳን አገልጋይ
ዘጸአት 40: 34-38
ደመናውም በላዩ ስለ ነበረ የእግዚአብሔርም ክብር ማደሪያውን ስለ ሞላ ሙሴ ወደ መገናኛው ድንኳን ይገባ ዘንድ አልቻለም።
በሙሴ መሪነት ከግብፅ የወጡ እስራኤላዊያን አርባ አመት በምድረ በዳ በድንኳን ኖሩ። እግዚአብሔርም በሕዝቡ መካከል ያድር ዘንድ እንደሕዝቡ የሚኖርበትን የማደሪያ ድንኳን እንዲሠራለት ሙሴን አዘዘ። በመላዕክት መካከለኛነት የፊተኛውን ኪዳን ማጽኛ ሕጉን ከእግዚአብሔር የተቀበለው ሙሴ ፤ የእውነተኛይቱ ምሳሌ የምትሆነውን የማደሪያውን ድንኳን እግዚአብሔር ባመለከተው መንገድ በጥንቃቄ ሰርቶ በፈፀመ ጊዜ ከደመናው የተነሳ፤ የእግዚአብሔርም ክብር የማደሪያውን ድንኳን ስለሞላው ወደውስጥ ወደ መገናኛው ድንኳን ይገባ ዘንድ አልቻለም። ምክንያቱም እግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል አድሯልና። እግዚአብሔርም ከሕዝቡ ጋር እርቅ እንደሚያወርድ እና ያለ ሕግ መካከለኛነትም ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ክብር እንደሚያይ ያስረዳ ዘንድ መግባትን ተከለከለ። ይሄም በእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ በኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ በመገለጡ ወደ ገሃድ ወጣ።
የዮሐንስ ወንጌል 1: 14
ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።
እግዚአብሔር የመረጣቸው እና ያጸደቃቸው ኃጢአተኞች በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ወደሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ እንደደረሱ እና አሁን ሕግም ሥራውን እንደፈፀመ ያስረዳል። እግዚአብሔር በስጋ በመካከላችን አደረ። እኛም ሁላችን በእርሱ በኩል እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ማየት እንችል ዘንድ ሆነልን። አሁን ሕግ የሚያስፈራ፣ የሚያስደነግጥም ፤ የሚኮንንም አይደለም። ነገር ግን በክርስቶስ ኢየሱስ እንደጸጋ የሚቀበለን ሆነልን።
ሮሜ 10: 4
የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና።
✍ ዳግም

#መስቀል ስር #የታዩ -አስደማሚ -ሰዎች -መካከል አንዱ መንገደኛዉ #ስምዖን ነዉ.😍....ከአንዲት ገጠር ሰከም ሰከም እያለ እየተመለሰ ባለበት መንገድ በዘላለማዊም ዕቅድ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ሀሳብ ዉስጥ ገባ.....እያለፈ #ወልደ እግዚአብሔር እንጨት ተሸክሞ..... ወደ ጎለጎልታ በህማም ሲወጣ አይቶ ሊያልፍ ሲል ጠርተዉ ከመስቀሉ ከመሸከሙ ዉስጥ ሰፉት🖐....... ድንገት በምትባል ቀን.... በአጋጣሚዋ ሰዓት...... የኢየሱስ አጋዥ ሊያዉም መስቀል ተሸካሚ ሆነ.....ሁሉ ሐዋሪያት አንዳች በሌሉበት የዛን ቀን ስምዖን #እድል ወደቀበት #መስቀል ተሸከመ..... መከራዉን ተጋራ ህመሙን test አደረገ....ጥቂት በመሸከም ኢየሱስን አገዘዉ.....የመከራ ወዳጅ የህመሙ ወዳጅ አጋዥ ባለንጀራ ሆነ......እዩማ👀🙆......#እድል ሲቀና....#አጋጣሚ ሲያምር.....#ቀን ሲረዳ....#እጣ ሲወድቅ.....#የጎዱህ መስሏቸዉ #ሲረዱህ ወደ እድልህ ሲያደርሱህ..... ወደ ላቀዉ #ደስታ #ሲገፈትሩህ....ቀንበር የጫኑ መስሏቸዉ ዘዉድህን አክሊል ክብር ሲጭኑብህ🙊 ልክ እንደ አንደዚህ ሰዉ ማለት ነዉ......ለኔ የታደለዉ ሰዉ #ስምዖን ነዉ......እድልስ ማለት እንዳንተ🙌..... #በመስቀል ለኢየሱስ #ወዳጅ.... #በመሸከም እርሱን ማገዝ..... እረዳከዉ....ደሞም በቅርበት አየከዉ.... አዎ #ተካፈልከዉ
👉“አንድ መንገድ አላፊም የአሌክስንድሮስና የሩፎስ አባት ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰው ከገጠር ሲመጣ መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት።”
— ማርቆስ 15፥21.......
✍Ariel Habtewold

አይ ኢየሱስ😭
የህይወት ውሃ የሆነው እሱ ውሃ አጠጪኝ አላት ስትመለከተው በእጁ መቅጃ የለም ውሀንም ከጉድጓድ ለመጎተት አቅም ያለው አይመስልም እንዳውም ልብ ብለው ሲያዩት መልክና ውበት የለውም ይወደድ ዘንድ ደም ግባት አልባ የተናቀ ሰውም ፊቱን የሚሰውርበት ነበር ግን ከማይስበው እሱነቱ😭 ላይ አዳኝ የሕይወት ውሃ ከውስጡ የሚፈልቅ ከነዛም ዓይኖቹ ላይ ርህራሄ የሚንፀባረቅበት ጌታ ነው😭
EFTAH
@cgfsd

(የሰማይ ድባብ )
..........
ሰማይም ስንወጣ ቀራንዬን አንረሳም በጉ እንደ ሆነ እዛም እንደ ታረደ ቁሟል ።
መጋቢ ጋሽ ተስፋ ወርቅነህ(ዶ/ር)
.............
ሰማይ እልል አለ ልኡሉ ድል ነሳ
ማህተም ተፈቶ በበግ አንበሳ
...........
ድባብ የአንድ አካባቢ መገለጫ መስታወት ነው ። ወደ እግር ኳስ ስታዲዮም እና ሲኒማ ወይም ቲያትር ቤት ሲገባ ተመሳሳይ የሆነ ድባብ አይኖርም ። በስታዲየሙ የሚታየው ጩኸት ውካታ በተቃራኒ ደጋፊዎች መካከል ያለው ብሽቅ ፣ የአሸናፊ ቡድን ፎሽታ ፣ የተሸናፊው ቡድን ደካፊ ሀዘን ሁኑ የስቴዲሙ ድባብ ነው ። በሌላ ጉኑ የሲኒማ ቤት የፊልሙን ይዘት ማዕከል ባደረገ መልኩ የሚስቁ፣ የሚያለቅሱ ፣ በጉጉት የፊልሙን ቀጣይ እጣ ፈንታ በንቃት የሚጠባበቁ የተመልካች ሰዎች ድባብ ይኖራል ። የስታዲየሙ ድባብ ደጋፊነት ስሜት ሲሆን የሲኒማ ቤት ድባብ መዝናናት ነው ። የሰማይ ድባብ ደግሞ ከድባቦች ሁሉ ልዩ የሆነ ድባብ አለው እሱም ቤዛነት ይባላል ።በአምልኮ ቤዛነቱን የሰራው ቤዛ ይወደሳል ። ታርደሃል እና ከነገድ ከቋንቋ ዋጅተሃል ይባልታል ። የሰማይ ድባብ የቤዛነቱ ድባብ ነው ። ለዚህም ነው በሰማይ ታርደሃል እና እየተባለ ቅኔ የሚቀኙለት እዛም ሰማይ የቤዛነቱ ጠረን ይሸታል ፣ የቤዛነቱ መአዛ ያውዳል። ቤተክርስቲያንም የክርስቶስ የቤዛነት ድባብ ጉባኤዋን ያጥናል ፣ በመካከሏ የቤዛነቱ ደስታ ያስተጋባል፣ ቤዛነቱ ያንሰፈስፋታል፣ ቤዛነቱ ቀልቧን ይሰርቃል።
@cgfsd
@ownkin

(የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ )
"የህፃናት አይምሮ ነጭ ወረቀት ነው" ሲሉ እሰማለሁ !! ደግሞም ትክክል ናቸው ምንም ያልተፃፈበት ንጣቱ የሚያማልል ወረቀት ነው ። በወረቀቱ ልትፅፉት ያሰባችሁት ፅሁፍ እያለ እንደ ድንገት የእስክርቢቶው (የብዕር ) ቀለም ቢተፋባችሁ ወይም በስህተት ጭረት ቢደረግበት አይለቅም ነጭ ነዋ የመጣውን ነገር ሁሉ አሰፍስፎ ይጠብቃል !!!!
እኔም ታዲያ እንደ ህፃናት በነጭ ወረቀት አይምሮዬ በብዕር ከተከተብብኝ ክስተት አንዱ እንዲህ ነው :-
በማለዳ ማልጄ ነው የተነሳሁት ከተነሳሁ ጀምሮ ደጋግሜ እያሰብኩት ያለው በጥዋቱ ረፋፋድ ላይ ያለው እግር ኳስ ጨዋታ ነዋ ። ጨዋታውን ናፍቂያለሁ !!! ግን አይሆንም ለምን ቢባል በተደጋጋሚ ኳስ ልጫወት ወጥቼ ተሰብሬ ፣ ተካግጭ ፣ ተላልጬ፣ ደምቼ መምጣቴ የተለመደ ስለሆነ ፤ ላልተወሰነ ጊዜ ከኳስ እንድታቀብ ማዕቀብ ወላጆቼ ጥለውብኛል !!! እና በጠዋቱ ሳወጣ ሳወርድ ቆይቼ እንዲፈቀድልኝ መላ ዘይጃለሁ እሱም እናቴ ጠዋት ስራ የማትሄድ ከሆነ የጠዋት ፀሎት ታረጋለች እና የፀሎቷ ጊዜ ተገን አድርጌ እንደተናገርኩ አስመስዬ መውጣት ።
ሀሳቤም ሰመረ እናቴ አራት ባራት የሆነችው ከፍራሽ ቆራርጣ የሰራቻትን መንበርከኪያ ይዛ ለፀሎት ገባች ። እኔ ትንሽ ፀሎት ከጀመርች ከደቂቃዎች በኋላ ገባሁ ። ስትፀልይ አይን አይኗን አያለሁ በመሃል ከፀሎቶቿ አንድ የሚደጋገም ቃል እሰማለሁ !! ቆይታም ፀሎቷን በዚህ ቃል አፍታ ትሰጣለች ፤ መልሳም ወደ ሌላ የፀሎት ርዕስ ልትገባ ስትል ያኑኑ ቃል ትደጋግመዋለች እንዲህ ትላለች
" የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ "
ምን እንደሆነ አይገባኝም ግን ፀሎቷን ሳስብ ይኸ ቃል ያቃጭልብኛል ። ገና ያኔ ብቻ አይደለም አሁንም ሌሊት ስትፀልይ ከምኝታ ቤቴ ጥልቅ ሲል የምሰማው ቃል " የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ " የሚለው ነው ለፀሎት አፌን ስፈታ የጀመርኩትም በዚህ ቃል ነው ።
ከጊዜ በኋላ የገባኝ ነገር ይኸ ፀሎት ተራ የፊደል ስብስብ የሆነ ቃል አይደለም የመለኮት ማንነት እንጂ !!!! ብዙ ሰው ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ከዕለታት አንድ ቀን ይመስለዋል አይሄ ይሄ የሚስኪንነት ጥግ ነው ።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር የሆነው በጊዜው ውስጥ አይደለም ከጊዜም ውጭም አይደለም በመጀመሪያም አይደለም ክርስቶስ መጀመሪያ የለውም እና !!! ከዘላለም በፊት ክርስቶስ ልጅ ነበር አብ ደግሞ አባት ነበር አሁንም ልጅ እና አባት ናቸው ደግሞም ለዘላለም ናቸው ። ክርስቶስ የአብ ልጅ በመሆኑ ከአብ አያንስም አብ የክርስቶስ አባት ስለሆነ ከክርስቶስ አይበልጥም ። ክርስቶስ ልጅ ነው ሲባል አብም የክርስቶስ አባት ነው ሲባል እኩል ናቸው እያልን ማለት ነው ። በጥንት ጊዜ ህዝብ አንድን ሰው ጃንሆይ ካሉ ንጉስ እያሉ እንዳለ ይታወቃል ። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ሲባል አምላክ ነው እየተባለ ነው አብም የክርስቶስ አባት ሲባል አምላክ እንደ ማለት ነው ።
እንጂ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ የተባለው ሰው ሲሆን አልያም ከሙታን ሲነሳም አይደለም ከዘላለም በፊት መጀመሪያ የሌለው ልጅነት ያለው ።
አንድ የምወደው ወዳጄ ጋር ሁሌ የሚያወራኝ እና የምንነጋገርበት አንድ ምሳሌ አለ ። መቼም ዕድሜን ልኩን በሀኪምነት ከቆየ ዶክተር ከአንድ ታማሚው ጋር እኩል ለእኩል በሚባል ደረጃ ስለ በሽታው ስለ መድሃኒቱ እኩል አብራርተው ከህክምና አንፃር ካወሩ ዶክተሩ ማፈር አለበት እንዲሁ በቤተክርስቲያን ያለ የክርስቶስ ተከታይ ነኝ የሚል ክርስቲያን ከውጭ ካለ እራሱን ለክርስቶስ ካልሰጠ ሰው እኩል ለእኩል በሆነ ደረጃ ስለ ክርስቶስ ካብራሩ አማኙ በራሱ ማፈር አለበት !!! ዕድሜ አስቀጥረው ክርስቲያን ነኝ ብለው ስለ ክርስቶስ ሲባል አንጀቴን ፣ወገቤ ተቅለበለበ ፣ምላሴን ወለም አለው የሚል ካለ ከእንደገና ከመሰረቱ ጋር ዕርቅ እንዲፈፅም ጥሪ ይቅረብለት ባይ ነኝ !!!
ለዚህ አይደል ኢየሱስ ሲከተሉት ለነበሩት ደቀመዛሙርቱ ይሄን ጥያቄ ያቀበላቸው ። የሰው ልጅ ማን ይሉታል ????
እነሱም ለቀም አርገው ተሳትፌአቸውን አሳልጠው :
አንዳዶች ኤሊያስ
አንዳንዶች ኤርሚያስ
ሌሎች ከነብያት አንዱ
ይሉሃል እያሉ እያለ ይበቃቸሁል የሚል በሚመስል መልኩ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ ጠየቀ ???
ያኔ የደመቀ የደራ የመሰለው ተሳትፎ ቀዘቀዘ ዝምታ ነገሰ ።
ጴጥሮስ በተራው አንተ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብሎ የታላቅ ታላቁን መልስ መለሰ ። ኢየሱስም መልሶ ጴጥሮስን አንድ ነገር አለው ፤ ይኸን ስጋ እና ደም አልገለጠልህም የሰማዩ አባቴ እንጂ ።
ለካ ይሄ ዕውቀት መገለጥ ይጠይቃል ተሾመ ዳምጠው ለዚህ ነው መሰል ይኸን ዕውቀት መገለጥ የሚጠይቅ ዕውቀት ያሉት ።
ስጋ እና ደም አልገለጠልህም ። ሲለው ስጋ እና ደም በሌላ በአማረኛ ሰው ማለት ነው ። ከሰው በላይ የሆነ ጉዳይ ነው ማለት ነው ። የሰማይ መገለጥ ነው የሰማይ አባት የሚበራው ብርሃን ነው ።
የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ አሜን ካስባለስ ይሔ ነው የሚያስብል
✍ ፊሊሞን ነጋ

ህጉ እና ኢየሱስ
ኢየሱስ የህግ ተቃዋሚ አልነበረም እንደውም ህግ የሚፈፅም ነበር እንጂ ።
ኢየሱስ ህግን ፈፃሚ ህግንም ሰጪ ነው ።
ኢየሱስ ህግ ፈፃሚ ነው ስንል የሚጀምርው ሰው ሁኖ መወለዱ ህግን ለመፈፀም ራሱን እንዳቀረበ እንረዳለን ። የሰው ልጁ ሁሉ ከህግ በታች ለመሆኑ ኢየሱስ ሰው ሲሆን ህግ ሊፈፅም የግድ ይላል ። አገልግሎት ለመጀመር የአይሁድን ስርአት 30 አመት መጠበቅ ነበረበት ። የሰው ልጁ ከህግ በታች ለመላቀቅ ህግ በሙላት ፈፅሞ ከህግ ነፃ የሚያወጣ ነፃ አውጪ ያስፈልግ ነበር ስለዚህም ኢየሱስ ህግ ፈፃሚ ሆነ ።
ኢየሱስ ህግ ሰጪ ነው ስንል ህግ ራሱ የወጣው ከኢየሱስ ነው ። ወንጌል ድንቅ እውነት ከሚያደርገው ነገሮቼ አንዱ ህግን የሰጠው ሰጪ የህግ ባለቤት ህግ ራሱ ፈፀመ በህግ ላይ የበላይ የሆነው በህግ የበታች ሁኖ ራሱን አስገዛ ። ህግ ሰጪ ነው የህግ የበላይ ነው ። ኢየሱስ ህግ ልሽር አልመጣሁም እንደውም ህግ ላጠብቅ ነው ሲል ህግ ሰጪ ነኝ ህግን የምሰው እኔ ነኝ እያለን ነው ። በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 5 ላይ ኢየሱስ ስድስት የብሉይ ኪዳን ህጎች ተናግሮ እነርሱን አጠበቃቸው ። ምሳሌ በፊት የተኛ አመነዘረ ሲባል ኢየሱስ ደግሞ እኔ እላለሁ ያየ የተመኘ አመነዘረ አለ ። ሙሴ ህግ ሲቀበል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል አለ ህጉ ላይ ሰጪ እና የበላይ ስላልሆነ ኢየሱስ ግን እኔ ግን እላለሁ አለ ሙሴ ይላል አለ ኢየሱስ እኔ ግን እላለሁ አለ ። ኢየሱስ ህግ ሰጪ የህግ የበላይ ነው ።
ኢየሱስ ህግ ሰጪም ህግ ፈፃሚ ነበር ። የሰው ልጅ ሊፈፅም ያልቻለውን ህግ ሰው ሁኖ ፈፅሟል ። ከህግ በታች የነበረውን ሰው የህግ የበላይ የሆነው ኢየሱስ ከህግ በታች ሁኖ ሰው ከህግ በላይ አድርጓል ። አሁን ህግ መፈፀም እንችላለን ህግን በፈፀመልን ኢየሱስ አቅም እና ጉልበት ።

(ሰውነት ጨመረ)
ወንጌል እግዚአብሔር ሰው የሆነበት ሚስጥር ነው ።
ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነቱን ሳይቀንስ ሰውነት ጨመረ ፤
አምላክነቱን ሳይቀንስ ሰውነት ጨመረ ። ኢየሱስ አልጎደለም ወይም ከመለኮትነቱ አላነሰም ብዙዎች ኢየሱስ ሰው በመሆኑ የተለወጠ ወይም ስፍራውን የለቀቀ ይመስላቸው ምክኒያቱ ደግሞ አምላክ ሰው መሆን አይመጥነውም እንደ ምሳሌ አንስተው ይሔን ይሞግታሉ ። በአንድ የመፀሃፍ ቅዱስ ጥናታችን ውስጥ አንድ ሰው ኢየሱስ ሰው ሲሆን አምላክነቱ ቀርቷል መለኮት አይደለም ሰው ብቻ ነበር በምድር እያለ የሚል ሀሳብ ያነሳ በሌላ ጎን ያለው ሰው ደግሞ አምላክነት ጃኬት መሰለህ ስትፈልግ የምታወቅ እና የምትጥለው የሚል በሀይለ ቃል የታጀበ መልስ ይመልሳል ። የኢየሱስን ሰው መሆን በተመለከተ የምናንፀባርበው መፀሃፍ ቅዱሳዊ መልስ አልቀነሰም ፣ አልጎደለም ይልቁን ጨመረ እንጂ አምላክ ብቻ ነበር አምላክነት ላይ ሰውነት ጨመረ ።አስቀድሞ አምላክ ብቻ ነበር ነገር ግን አሁን ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ ነው ። መለወጥ በእግዚአብሔር ዘንድ የለም አይለወጥም ማንነቱም ሊቀይር ዘንድ አይቻለው አለመለወጥ በእርሱ ዘንድ አለ ። የማይለወጠው እግዚአብሔር ግን ማንነትን ጨመረ ።
የሰውን ልጅ ስጋ ገንዘቡ አደረገ ። ራሱን የሰው ልጅ ብሎ ያስተዋውቅ ነበር ። ራሱን ከሰው ልጆች እንደ አንዱ ቆጠረ ።
የሰው ወገን ተብሎ ተጠራ ። የሰው ልጅ በሚባል መጠሪያ ተጠራ ። ብዙ ሀይማኖቶች ኢየሱስ ሰው እንዴት ሊሆን ቻለ አምላክ እንዴት ሰው ሆነ ብለው ይተቻሉ መልሱ ግን ፍቅር ነው ። በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመርኩዞ በተሰራ ዘኬዝ ፎር ክራይስት በሚል የፊልም ገፀባህሪ ውስጥ እግዚአብሔር የለም ብሎ የሚያምነው መሪ ተዋናይ ሚስቱ በእግዚአብሔር ስላመነች በንዴት በመነሳሳት ክርስቶስ ተራ እንደሆነ ሞቱን እና ትንሳኤ ወልደቱን ከንቱ ለማረግ በርካታ ጥናቶች ያደርጋል ። የጥናት እውነት ለማረጋገጥ አንድ ቄስ አግኝቶ ያወራል ቄሱን ለምን ይሔ ሁሉ ክርስቶስ ሆነ ምክኒያቱ ምንድን ይለዋል? ቄሱም ቀላል ነው ፍቅር ነዋ አሉት ።
በበረት ተኛ ፣ ህፃን ሆነ ፣ በሰው መንደር አደገ፣ ሰው የሚበላውን በላ ጠጣ፣ እንደ ሰው አዘነ፣ እንደ ሰው ተደሰተ የሰው ልጅ ሲባል አቤት አለ ራሱንም የሰው ልጅ ብሎ ጠራ ።