በክርስቶስ ( in christ)
853 subscribers
99 photos
34 videos
40 files
40 links
Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin
Download Telegram
#የዘላለም ርዕስ #የማያልቅ ምዕራፍ #የማይፈፀም ታሪክ #የማይጨረስ መፀሀፍ #የእሱ መች አልቆብን ሌላ እንጀምራለን #የተሰቀለውን ስንሰብክ እንኖራለን #ዋናው ኢየሱስ ነው  #ዋናው ክርስቶስ ነው #ከሞት ለተቤዥን #በደሙ መፍሰስ #በደሙ መፍሰስ #መቼ አወጅነው እና #የእርሱን ድንቅ ስራ


🎼
@ownkin
@cgfsd
(የነካኝ ምስክርነት)


በክርስቲያን ቤተሰብ በማደጌ ኢየሱስን የማውቀው ልክ  በመስቀል ላይ የተሰቀለ  የሚል ብቻ እውቀት ነበር ። በኋላ ግን ከዛ ያለፈ እንደሆነ አስገራሚ ማንነት እንዳለው ስረዳ አብዝቼ አብዝቼ ኢየሱስ የሚለው ስም አንስቼ ማንነቱ አስቤ አልጠግብ አልኩ ።ስለ ኢየሱስ ሳይሆን ራሱን ኢየሱስ ማወቅ ጀመርኩ ።

ኢየሱስ አስገራሚ ማንነት አለው 😍



@ownkin
@cgfsd
ውዳችን ኢየሱስ ወከባ አያስቆመውም .... ለአየር መተንፈስ በሚከብደው  በግፊያ መሀል ግን ለነካው ይቆማል ።
             
      ምስክር : የደሟ ምንጭ የቆመላት


@ownkin
  @cgfsd
#ኢየሱስ -በምድር በነበረበት ዘመን አለመኖሬ ኢየሱስ እንዲያመልጠኝ አላደረገኝም....በምድር አይኑር እንጂ እሱ ወዳለበት መንፈስ ቅዱስ አድርሶኛል......እርሱ ካልገለጠልን በቀር ኢየሱስን ማወቅም መንካትም አንችልም 😇😘

Ariel

@ownkin
@cgfsd
ኢየሱስ ከክህደት በኋላ የምትሾም አንተ ነህ !! የወደድካቸውን እስከ መጨረሻው የምትወድ ወዳጅ
(የግንዱ ላይ ሰንባች)



  ኢየሱስ ገበሬው አባቴ ነው በማለት ሊሰራ ስላለው ታላቅ ስራ የአንበሳውን ድረሻ የአባቱ  እንደሆነ አስገንዝቦናል ። በእርግጥም እግዚአብሔር ጥንቅቅ ያለ ገበሬ ነው ። ገበሬ ያነገበው አላማውን እስከ መጨረሻው እንጥፍጣፊ ደረጃ ድረስ ሰንቆ የሚተጋ ነው። ሁሉም ነገር የሚታየው ከግቡ የተነሳ ነው ቢጥል ፣ቢያነሳ፣ ቢቆፍር፣ ቢቧጥጥ የሰነቃትን ተልዕኮ ለማሳካት እንጂ እግረ መንገድ የሆነ ራዕይ የለውም ። በጠዋት ማልዶ ሲነሳ ፀሀይ በምስራቅ በኩል መፈንጠቋ ለእሱ ቅንጦት አይደለም ምርቱን በላቀ ሁኔታ ለመጨመር ሌላ እድል አድርጎ ያየዋል ። ዝናብ ደግሞ እንዲሁ አየር ንብረቱ እየሞቀው ስለረበሸው እንደው ቀዝቀዝ ለማለት አይሻውም ይልቁንም የዘራቸው ዘሮቹ እንዲያቆጠቁጡ ተስፋ ይጥልበታል ። ሀብቱም ፣ ንብረቱም ፣ ጉልበቱም  የሚያፈሰው (ኢንቭስት የሚያደርገው ) መሬቱ ላይ ነው ። ምናልባት በለስ ካልቀናችው ደግሞ ኪሳራውም በእጅጉ አስደንጋጭ ነው የሚሆነው ያለውን በሙሉ የሰጠው ለዚሁ ጉዳይ ነውና ።  የእግዚአብሔር ገበሬነት ግን በእጁጉ ይለያል ብሎም ይማርካል ።  ቆይ ግን እግዚአብሔር ምን ገዶት ገበሬ ሆነ 🤔???

    ህብረት ...ህብረት ...ህብረት ብቻ ነው ። እግዚአብሔር የገበሬን ግብር ይዞ የተጠራው እኛን ሆን ብሎ ለማስገረም አይደለም ህብረት ፈልጎ እንጂ ። አምላካች ህብረት የሚወድ ህብረት የሚያረግ አምላክ ነው ። ለዚህም ነው ገበሬ ብሎ የተጠራው !!  የፈለገው ህብረት ደግሞ በግንድ በቅርንጫፍ በኩል የሆነ ህብረት ነው ።  የሚያስገረም ነው ነገር ቢኖር ገበሬው እግዚአብሔር ለዚህ ህብረት ኢንቭስት ያደረገው ዋጋ ነው ። ኢንቭት ለማድረግ ውሃ አልቋጠረም ፣ አፈር አልጫረም ፣አቧራ አላስነሳም አንድ ልጁ ላይ ጨከነበት ። የተጠቀመው ውሃ የልጁን ደም ፣ የተኮኮተው መሬት የልጁን ስጋ ነበር ። ወደር የማይገኝለት ዘላለማዊ ልጁን ስለ ሌሎች ተብሎ ተማገደ ። እግዚአብሔር የመጨረሻ ኢንቭትመንቱን በልጁ ቤዛነት (ምትክነት ) በኩል አደረገው ።ገበሬው አምላካችን በልጁ በኩል አለምን የሚያርስበት ቀን በጉጉት ለቀደሙት አባቶች አመላከተ ። ዘመቻ ቀራኒዮ ...ዘመቻ ጎልጎታ የኢንቭትመንቱ የመጨረሻ ግብ ነበር ። ምንም እንኳን እንደ ገጠሩ አካባቢዎች ለአጨዳ ቀን ሆ ብሎ ሰው በሆታ ሊሰበስብ አልመጣ ይብሱኑ በአንድነት በጩኸት ስቀለው ስቀለው እያሉ አንድያውን አሳልፎ በሰጠው የገበሬውን ልጅ ላይ ለመግፋት ተሰበሰቡ እንጂ ።  ገበሬው በኩራት ይሔው ኢንቭትመንቴ ይሔው ከመስቀሉ ላይ ፣ ይሔው የተሰቀለው እሱ ላይ የሚበቅሉ ቅርጫፎች ውጤቶቼ ናቸው ።ቅርጫፎቹ የሚያፈሩት ፍሬው ደግሞ የሰራውት ታላቅ የኢንቭትመንት ስራ ማሳያዎች ናቸው ።

የልጁ ደም ከልጁ እና ከገበሬው አባቱ ጋር ህብረት ማድረጊያ ነው ።ህብረቱ  ከተሰቀለው ጋር አብሮ መሰቀል ነው ፣ ህብረቱ ከሞተልን ጋር መሞት ነው ፣ ህብረቱ ከተነሳልን ጋር መነሳት ነው ፣ህብረቱ ለግንዱ መኖር፣ ህብረቱን ግንዱ ለመምሰል መኖር ፣  ህብረቱ ገበሬው በቅርጫፉ በኩል የገለጠልን ፍቅር መቋደስ፣ መተንፈስ ፣ ለሌሎች ማካፍል ፣ በፍቅሩ መፈንደቅ ፣ በፍቅሩ መኩራራት ይሔ ህብረቱ ነው ... ገበሬው ... እኛ ለግንዱ ሰጥቷል ... በግንዱ በኩል የማያስፈልገው አኑሮሯል ። ግንዱ ሁል ጊዜ እንዲህ ይለናል በእኔ ኑሩ !! በእኔ ቆዩ ፣ በእኔ ሰንብቱ ፣ በእኔ ክረሙ ፣ በፍቅሬ ኑሩ እያለ ከእርሱ ጋር ወዳለው ቁርኝት እና መጣበቅ ይጠራናል ።

በግንዱ ክርስቶስ ጋር መቆየት ምርጫ የሌለው የህይወት ስርአታችን ነው ። ከእርሱ ጋር እንድንከርም ተጠርተናል ። የገበሬውን የልብ ትርታ ለመረዳት ካሰነበተን ግንድ ጋር መሰንበት ነው ። ግንድ ለቅርጫፎቹ የሚሆኑትን ሚኒራል ፣ ውሃ የሚያስፈልጉት ሁሉ ወደ ቅርጫፎቹ ሳያጓድል ያደርሳል የእኛም ግንድ ክርስቶስ ለእኛ የሚያስፈልገን ለህብረቱ የሚጠቅመን ማንነቶች ሳያዛንፍ ይሰጠናል ።


ከግንዱ ክርስቶስ ጋር ስለተወዳጀን ነው ፤ የገበሬውን ቤተሰብ የተቀላቀል ነው።
በክርስቶስ ( ግንዱ) እና በእኛ (በቅርንጫፎቹ) መካከል ያለው የወዳጅነት መጣበቅ ምክኒያቱ ክርስቶስ ላይ እንድንቆይ የወደደው ገበሬ ነው ።


ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
ክርስቶስ በቅዱሳት መጻሕፍት በኹሉም ስፍራ አለ! ለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስን አብዝቼ የምወድደው!

Diakon abenezer

@cgfsd
@ownkin
ይሔ ንጉስ ማን ነው ?? በፍቅር ያጌጠው #ልብሱ በደም ቀልቶ ሞትን የረገጠው #በጉልበቱ ፅናት የሚረማመደው #አዎን ኢየሱስ ነው አዎን ጌታዬ ነው

🎼

@ownkin
@cgfsd
(ኢየሱስ ያስቀናል )


የፈንሳዩ የጦር አበጋዝ ናፖሊዮ ቦናባርቴ በርከት ያሉ የውጊያ ድሎች አስመዝግቧል፣ ብዙዎች ማርኳል ነገር ግን ስለ ጌታ ኢየሱስ ማራኪነት ተደንቆ ያለ ጠብመንጃ ሚሊየኖች በፍቅር እንደሚከተሉት በአግራሞት ተናግሯል ። የክርስቶስ ማንነት በእጅጉ የሚገዛው በሰባአዊነቱ የሚጠቀሰው ማህተመ ጋንዲ የኢየሱስ ባህሪ ለዕድሜ ዘመኑ እንደጠቀመው ፣ ስብዕናው ውስጡ እንደሚገዛው አትቷል ።አለም በመዝገቧ ከትባ ያስቀመጠቻቸው ታላላቅ ሰዎች በናዝሬቱ ኢየሱስ የተነሳ እየተገረሙ ወቸው ጉድ በማለት እጃቸውን በአፋቸው አጣምረው ጭነዋል ። በአሜሪካን ለሰው ልጆች እኩልነት ወገቡን አስሮ በቀዳሚነት  ዘብ የቆመው ማርቲን ሉተር ኪንግ  እንዲህ ይላል "ኢየሱስ ለፍቅር ፣ ለእውነት ፣ ለመካምነት ፅንፈኛ ነበር "  በማለት ሀሳቡን አጋርቷል ። በዘመነ አብርሆት ለአለም መንቃት አስተፆ የተጫወተው ፈላስፋው ሩሶ ደግሞ በበኩሉ "ሶቅራጥስ እንደ ፈላስፋ ሞተ ኢየሱስ ግን እንደ እግዚአብሔር ሞተ " በማለት እይታውን አስቀምጧል ።

የቀጠናው አስተዳዳሪ ሔሮዶስ እልፍ እየተከተሉት እንደሆነ በተአምራቱ እና በትምህርቱ አካባቢውን አልፎ ዙሪያ ገባውን  የናዝሬቱ ኢየሱስ እንደሞላ ሲሰማ ስለ ስልጣኑ ስጋት ቢኖረው እሱን ሊሰማ ይናፍቅ ነበር ። መሲሁ ኢየሱስ ላይ ጥርስ የነከሱት የካህናት አለቆች ወታደር አሰማርተው ተጠፍንጎ እንዲመጣ ትዕዛዝ ቢሰጡም የተላኩት ወታደሮች ግን በማንነቱ ፣ በትምህርቱ እና በስራው ተመስጠው የተላኩበትን ረስተው  ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ስለ ንፅህናው ሽንጣቸውን ገትረው ተከራክረዋል ። የሸንጎ አባሉ ፈሪሳዊው ኒቆዲሞስ ኢየሱስን ለማወቅ በሌሊት ያለበት ድረስ አነፍንፎ መቷል ። ኢየሱስ ያስቀናል !! እንስማህ፣ እንይህ፣ እንንካህ ፣እንከተልህ ያስብላል ። 

በጨዋታችን መሃል አንድ የምቀርበው ወዳጄ በቤተክርስቲያን መሃል ስለተንሰራፋው ክርስቶስን ስለማይመስለው ልምምዳችን ሲያስብ እንዲህ ይለኛል " እኔ ግን አይገባኝም ክርስቶስን እንዲህ አለውቀውም  ኧረ እኔ ኢየሱስ እንደዚህ አላውቀውም ..ይገርምሃል ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኝ አድርጌ የተቀበልኩት በመፀሀፍ ቅዱስ የዕለት ተለዕለት  ጥናት ወቅት ነበር ። በተለይም ደግሞ የወንጌል መፀሀፍት ማቴዎስ ፣ ማርቆስ ፣ሉቃስ እና ዩሀንስ ወንጌላት ላይ ያነበብኩት ጌታ ባህሪው፣ ትህትናው ፣ ፍቅሩ ፣ አላማው ፣ ታዛዥነቱ ያስቀናኝ ነበር  " በማለት አውግቶኛል ። በትክክል !! በተጨባጭ !!! ለዚህም ነው  የዕውቀት ቀንዲሉ  ሊቁ አልበርታን አንስታይል እንዲህ ያለው " ማንም የኢየሱስን እውነተኛነትን ሳይሰማ ወንጌልን ማንበብ አይችል " ያለው። ይሔው ነው !! የወንጌል መፀሀፍት ስናነብ የኢየሱስ የማንነት ውበት ይወረናል ፣ የባህሪው ማራኪነት ይማርከናል፣ አስደናቂነቱ ቀልባችንን ይገዛዋል ። የህይወት ታሪክ አይደለም አምላክ በስጋ የኖረው ህይወት እንጂ ። በቃ እንዲህ ነው የክርስትና ወጉ ኢየሱስን ከሰማበት ፣ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ መመረቅ ለሌለው ጊዜ ዘወትር በውስጥ እየተቃጠሉ ፣ እጅ እየነሱ መኖር ።

   ኢየሱስ ያስቀናል


ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
እንጀራ ልንበላ አልተከተልህም ሀብት ብልጥግና ወደ አንተ አልጠራንም #ለምድር በረከት ታይቶ ለሚጠፋው #መች ደምህ ፈሰሰ ለሚያልፍ ተስፋ #የዘላለም ህይወት ማግኘታችን ጉዳይ ሁሌ ብርቃችን ነው #ህይወት ያካፈልከን #ኢየሱስ አንተ ነህ #ሌላ አላየንም በነፍሱ የጨከነ ...


🎼 መስኪ

@ownkin
@cgfsd
(ጌታ ኢየሱስ )



የራሴ ድምፅ ብዙ ጊዜ ረበሽኝ ፣ እኔነቴ ያለ ቅጥ  መፈናፋኛ አሳጣኝ ፣ ድካሜ ጉልበቴን ለግሞ ያዘኝ ፣ የምሰማው ነገር አስደነገጥ  በዚህ ሁሉ ግን ስምህ መማፀኛ ግንብ ሆነኝ ። በዙሪያ ካሉት ሁሉ ዘልዮ አመለጥኩበት ። ቃላት አጥቼ ጌታ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ እያለኩ ለማምለጥ ጠራሁት ነገር ግን ማምለጡን ረስቼ የጠራሁት ስምህ ጣፈጠኝ ጌታ ኢየሱስ ብዬ ሳልጨርስ ከእንደገና ስሙን መጥራት ናፈቀኝ ። ጌታ ኢየሱስ ስለው የተወጋው ጎኑ ትውስ ይላል፣ጌታ ኢየሱስ ስለው የፈሰሰው ደሙ እንደ ወንዝ ጅረት በአይነ ህሊናዬ እልፍ ይላል፣ ጌታ ኢየሱስ ስለው በመስቀል እንደ ተንጠለጠ ወድሃለው ሲለኝ ይሰማኛል ፣ ጌታ ኢየሱስ ስለው ልክ በሌለው ጭንቀቴ ውስጥ ልክ የሌለው ሰላሙ ይፈሳል፣ ጌታ ኢየሱስ ስለው ሀዘን ጥላውን ባጠላብኝ ነፍሴ ውስጥ ደስታው እንደ ማለዳ ፀሀይ ይፈነጥቅብኛል ፣ ጌታ ኢየሱስ ስለው በውስጤ ያለው ቅዱሱ መንፈስ ደግሜ እንድጠራው ጉልበት ይሆነኛል ። 

ሰሞኑን ብዙ ተጨነኩ ፣ ብዙ አዘንኩ ፣ብዙ አነባሁ ፣ ብዙ ተልፈሰፈስኩ እና ብዙ ብዙ ልል አስቤ ልፀልይ ተንበረከኩ ጌታ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ ብቻ ብዬ ስጣራ በአንድ ቃል ብዙ ተነፈስኩ ፣ አረፍኩ ፣ እፎይይ አልኩ !!

       ጌታ ኢየሱስ😍

@ownkin
@cgfsd
የተሳለው መልኩ


ከሀምሳ አመታት በላይ አስቆጥሯል አንድ ስመጥር የሀገሪቱ ሹም ወደ ገጠር ከአንድ አማረኛ ከሚችል ፈረንጅ ጋር እግር ጥሎት ይሄዳል ። የስራ ጉዳያቸውን እያጧጧፉ እያለ አንዲት እናት እየሮጠች ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስትል ወደ ፈረንጁ ተጠጋች ። ፈረንጁም አማረኛ ይችል ኖሯል ሳቁን ለቀቀው ያ ሹም ግን ደነገጠ አፈረ ተሸማቀቀ ።
     
(የታሪኩ ምንጭ (መልህቅ በዘነበ ወላ))

    ይሔን ታሪክ ማውጠንጠን ስጀምር የተሳለብን ስዕል እንዴት ነው የሚል ጥያቄ ውስጤ ላይ ፈነጠቀ ።

  ክርስቶስ ሲባል በዘልማድ እንደዛች እናት ፈረንጅ ሁሉ ወይስ በልጅነታችን ለገና እና ለፋሲካ በቴሌቭዥን መስኮት የምንከታተለው ክርስቶስ ሆኖ  ፊልም ላይ የሚተውነው መልከመልካም ሰው ድቅን ይልብን ይሆን???  ደግሞም ይሆናል ብዙዎቻችን ይህን ስናይ ስላደግን ስንፀልይ ወይም ጌታን ስናስብ ያ ክርስቶስ ሁኖ የተወነው ተዋናይ በሀሳባችን መምጣቱ የማይቀር መሆኑን አያከራክረንም !
        በመጀመሪያው ገላቲያ ላይ ተስሎ እንደነበረው የክርስቶስ ኢየሱስ መልክ ዛሬም በዚህ ዘመን ላለን ሁላችን ኢየሱስ እንደተሰቀለ መንፈስ ቅዱስ ሊስልብን እና በደማቁ ሊያደምቅብን ግድ ይላል !!!!
    ትክክለኛው የክርስቶስ ማንነት ነፍሳችን ላይ እንዲሳል መንፈስ ቅዱስ ይርዳን ። 




ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
ተረፈ ማዕዴ ደሙን አፍስሶ
ገበታዬን ሞላው ስጋውን ተቆራርሶ


ስለ ህይወት እንጀራ(ኢየሱስ)!!

@ownkin
@cgfsd
የፍቅር ጉልበት ቀመር ቢሰላ #ይቆጠር ቢባል ከምድር ጅማሬ እስከ በኋላ #የፍጥረት ሁሉ ታሪክ ቢደመር #ጀርባህ ላይ ካሉት ሰንበር አንዷ ጋር እንኳን አይደወዳደር (👉)

  ብወድህ ታዲያ ምን ይገርማል (ኢየሱስ)


🎼
@ownkin
@cgfsd
በእቅፍ ያለው ሁሉን ነገረኝ #የፍቅርህን ልክ እያስተማረኝ #መግባት ሁኖልኝ ስገባ አንተ አለህ #በልጅህ በኩል ትታየኛለህ

እንዴት ታምራለህ ፍቅር ነው ገፅህ #አይቼሃለሁ ልጅህ ሲገልፅህ #እንዴት ታምራለህ ውብ ነህ አባቴ #እድለኛ ነኝ አንተን ማየቴ #ይሔ ሁሉ ፍቅር ያንተ ነው ለካ #አየሁህ ባንድያህ #በልጅህ ትረካ #እግዚአብሔር አብ ያንተ ነው ለካ ።

🎼
@ownkin
@cgfsd
ኪዳኑ(ብሉይ ኪዳን) ያረጀው እግዚአብሔር አረጅቶ አይደለም እግዚአብሔርን መሸከም አቅቶት ነው ።ኪዳኑ አዲስ የሆነው እግዚአብሔር ተለውጦ አይደለም አዲሱን ኪዳን  እግዚአብሔር ተሸክሞት ነው።

@ownkin
@cgfsd
ጌታ ኢየሱስ በአለም ካለ ሁሉ ነገር ይልቅ የደምህ ጠብታ ሚዛን ይደፋል ።

@cgfsd
@ownkin